Wednesday, August 13, 2014

ሳይጣንም ቢሆን ሳይጣን እንደሆነ እያወቅነው ለጉልበቱ ቢያግዘን ሊከፋን ከቻለ ተሳስተናል ግን ሰይጣኑ መልአክ ይሆናል ብለን ካሰብን ትልቅ ስዕተተ ነው

ሳይጣንም ቢሆን ሳይጣን እንደሆነ እያወቅነው ለጉልበቱ ቢያግዘን ሊከፋን ከቻለ ተሳስተናል ግን ሰይጣኑ መልአክ ይሆናል ብለን ካሰብን ትልቅ ስዕተተ ነው
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------

ምን ሆናችሁብኝ ወገኖቼ ዛሬ እግር ጥሎኝ አንድ ርዕስ ሳነበ ደነገጥኩ! እውነት ለመናገር በጣም ደነገጥኩ!
እንዴ ይህንን ያህልስ ለተራ ጉዳዮች ራሱን ቢዚ የሚያደርግ እና ትንሽ ጉዳዮች ትልቅ ትልቅ ጉዳዮች ትንሽ የሚሆኑበት ህዝብ ነው እንዴ ይህችን ሃገር የሞላት አልኩ!
ለምን በሉ
ሚኒሊክ ሳልሳዊ የተባለ ግለሰብ ማንስ ሆነ ማን ምን አስጨነቀን! ማለቴ ይህ ሰው ይሚሰጠንና ይሚያቀርብልን መረጃና ማስረጃ ህዝባችንን እኛን ኢትዮፕያን እንዲሁም ኢትዮፕያዊነታችንን የሚያጎለብትልን የሚያሰፋልን ከሆነ??
እኔ የማስበው ይህንን ነው ምክንያቱም ይህ ሰው በምንም በሉት በምንም መረጃዎችን በማስረጃም ጭምር እየመገበን እያነቃንና እየነቃንበት ነው ያለው ኢቭን ለመሸወድ አስቦ ቢሆን እንኳን አይችልም እርሱ ነው የተሸወደው ምክንያቱም ምናልባት ከእርሱ ጋ "ጭውውት ያበዙና የማገጡ" ምናልባት እንዳላችሁት ከሆነ ብየ ነው ይህንን ቃል የተጠቀምኩት ካላችሁ ብቻ ነው እንጅ የተሸወዳቸሁት እርሱ ግን እንደምትሉት እንደዛ አይነት ሰው ሆኖ ከሃዲና ፖለቲካዊ ብልግና በተከበረው ኢትዮፕያዊና ሃገራችን እንዲሁም ኢትዮፕያወነታችን ላይ ፈፅሞ ከሆነ እርሱ ነው የተሸወደው እኛ አደለንም
እኛማ እንዲሁም በእኔ መመዘኛ እስካሁን እርሱም ቢሆን ምርጥ የመረጃ ሰው ነው ብንጠራጥረው እና እንደተባለው አይነት ሰው ቢሆን እንኳን እውነታዎች እውነት እስኪሆኑ ድረስ የሚያቀርብልንን እየበላን የምንተፋውን እየተፋን ትግላችን መቀጠል እንችላለን ማድረግ ያለብንም ይህንን ብቻ ነው
ምናልባት ከእርሱ ጋ እውነታዎች እውነት እስኪሆኑ ድረስ መረጃ አለመለዋወጥ ሊቻል መልዕክት አለመፃፃፍ ሊቻል ይችላል እንጅ ይህንን ያህል ቢግ ኢሹ ሊሆንብን አይገባም እውነት ቢሆን እንኳን ይህንን ሰው በጣም ልናመሰግነውና እስካሁን ላደረገልን መስመሩ ውስጥ ለማስገባት ሲጥር እኛ ጉያ ስር ሆኖ ትግላችንን ስላፋጥነልን ልናመሰግነውና ልናደንቀው ይገባል ከዚያ በህዋላ የየራሳችንን እርምጃ መውሰድ እንችላለን
ይህ ሰው ማን ነው?
ለምትሉ ደሞ ማንም ይሁን ብቻ የትግላችን ደጋፊ ይትግላችን ወይ ማገር ወይ ምሰሶ ሆኖ እስከቀትለና ተጨማሪ ጉልበት እሴከፈጠረልን ድረስ ልናወግዘው ሳይሆን አመስግነን ከዚህ በሁዋላ ትግላችንን ልታግዘን ሳይሆን ልታዳክምብን ስለሆነ አንሰማህም ማለት እንችላለን እኮ ማንም ጀሮና አይናችንን አያስገድድም ዝምምም ብሎ ግን የተሻሉ ሆኖ ሳይገኙ ማብጠልጠል ተገቢም ትክክልም አደለም
በነገራችን ላይ በረከት ወይም ደብረፂወን ወይም ጌታቸው አሰፋ ወይም ረዳ በስማቸውም ሆነ እኛ በማናውቀውም ሆነ በምናውቀው ድብቅ ሚሴጥራዊ ስም ይሚኒሊክን ያህል መረጃን በማስረጃም ይሁን ትግላቻንን አንድ እርምጃ ወደፊት ማስኬድ በሚችል አቅም ቢቀጥሉ በእኔ በኩል እቀበላቸዋለው
ግን ግን ብሏል ሃበሽ
ግን ይህ ሰው ወደራሱ መስመር ሊያስገባ ይሚጠመዘዝባቸውን ማዕዘኖች ሁሉ ከማፈራረስ ወደሁዋላ አልልም ምክንያቱም ይህ ትግል ነው ግን የምለያቸው እንዲህ ስም በማጥፋትና የመንደር ወሬ በሚመስል መልክ ሳይሆን አደጋ መቀያየም በማይፈጥርበት መልክ ነው ይህ በመኮራረፍና በመቆጣጣት የሚፈታ ሳይሆን በመጠናናት የሚሆን ብቻ ነው
በቃ ከፈለገ ሳይጣን ሰይጣንነቱን እያወቅነው ከቻለ እንደመላክ አድርጌ ሳልቀበል መላዕክታን የፈጣሪ መልዕክተኖች ናቸው ቢለኝ እስካልተሳሳተ ድረስ እቀበለዋለው መሳሳት ሲጀምር ግን እክደዋለው
አለበለዚያ ማን ወንፊት ማንስ ተነፊ ልንሆን ነውና እንዲህ አንዳችን ተንጓላይ ሌሎቻችን አንጓላይ ልንሆን የምንችለው? ይህ ትግል ነው
ሻቢያ ነው ወያኔን ለዚህ ያበቃው አሁን እንዲህ ጠላት ሊሆኑ
አንድነትና መኢአድም ሊዋሃዱ ሲሉም ትህአዴግ አዎ መዋሃድ አለባቸው ብለው ባሰረጓቸው ባንዳዎቻቸው ያስጎተጎቱት መዋሃዳቸውን ፈልገውት ሳይሆን ቀጣዩን በሌላ መንገድ ቢሄዱ ሊሳካላቸው ይማይችሉትን ሴራ ስላሴሩ እንጅ ወያኔ መሰሪ ድርጅት ነውና አዎ መዋሃድ አለባቸው አለና ወዲያውኑ በእጁ ይነበረውን መርዝ ጨመረ ይህም መርዝ ሁለቱ ሲዋሃዱ ግን በሰላማዊ ምርጫ አንድ ፕሬዘዳንት መመረጥ አለበት አለና በታተናቸው ሁለት ጥቅም አንድም ሲዋሃዱ እንዲዋሃድ ይማይፈልጉና ግዙፍና ብቸኛው አኔጋፋ ባለብዙ አባላት ፓርቲው መኢአድ በቀጣፊውና በሰርጎገቦች አንድነት ሊዋጥ ነው ምናምን የሚሉት እንዲገነጠሉ አደረጉ ሌለው ጥቅም በሁለቱ ፓርቲ ተወካይ ተወዳዳሪ እጩ ፕሬዘዳንቶች ምርጫ ፉክክር ወቅት መቃቃርና መለያየት እንደሚመጣ እርግጠኞች ነበሩ ይዛን ጭላንጭልም የምናየው ነው ምን ቀረን
ልላችሁ የፈለኩት መንቃት ያለብን ይተሳሳተን ወይም የነቃንበትን ማጥፋትና መክሰም ብቻ ላይ ሳይሆን እነዚህን ስዎችስ እንዴት ካሰብነውና ከደረሰን መረጃ እውነታ በተለይ መልኩ ልንጠቀምባቸው እንችላለን እንዴትስ ትግላቸውን በትግላቸው ልንውጥና ትክክለኛውን ትግል ልናሳያቸውና ልንመዝናቸው ልናርማቸው እንችላለን? እንዴትስ አድርገን የጥፋት ሴራቸውን ልናከስምባቸው እንችላለን? ሰይጣንነታቸውን እያወቅንም ቢሆን እንዴት ልናስተናጋቸው እንችላለን? ይሚሉት ላይ ማተኮር ይሚሻል ይመስለኛል
ይህ ትግል ነው
ሰይጣን መልእክ ነን ብል ቢመጣም ትግላችንን እስካገዘንና እስከረዳን ድረስ በየደረጃው ልንቀበለው ይገባል መልእክ ነን እና እኔ አማልዳችሁዋለው ካለን ግን ያኔ ወራጅ አለ ብለን መውረድ ሳይሆን ና በል ውረድ ልንለው እንችላለን ግንም እኔ መላክ ነን ላማልዳችሁ ነው ይመጣሁ ለዚህም ከፈለጋችሁ ይሄው ላድናችሁ ብሎ እስካዳነ ድረስ አሁንም እንቀበለዋለን ማዳኑን ቀድሞ ሰይጣን ሃይል እንዳለው እስከተነገረን ድረስ ማለትም ቀድሞ ነገር ትግላቻንን አንድ እርምጃ እንደሚያፈጥንልን እስካወቅን ድረስ
ምንም ሆነ ምን ግን ሚኒሊክ እስካሁን የሚሰራቸውና የሚያወጣቸው መረጃዎች ሁሉ ለኔ ይስማሙኛል ፖለቲካዊ ያልታየኝ ጥቅም ከሌለው በስተቀር
የዚህ ሰው ብቻ ሳይሆን የበርካቶች ልክ እኔ ለበርካቶች ኮንፊውዚንግ እንደሆንኩት ሁሉ ማንነታቸውና እስከጫፍ ይመሄዳቸው ጉዳይ ያሳስበኛል ነገር ግን አሁን በሚያደርጉት ትግል ቀን ከሌት ቤታቸው መሄድ ሳያስፈልግ እዚሁ ይፌስቡክ መደራጀት ላይ መከታተልና መቆጣጠር ይቻላል እንጅ ዝም ብሎ አንድ ሰው ስላለ ብቻ ይተባለውን ይዞ ማንፀባረቅ አግባብ አደለም
በዋናነት እነዚህ ስዎቸ አሁን ይብዛም ይነስ ለህዝባችን ምን አይነት መረጃ ነው እያቀረቡ ያሉት የሚለውን ማየትም አግባብ ይመስለኛል
ኦኬ ሌላው ይቅር ዋት ኢፍ ይህንን ማለትም ሚኒሊክ ሳልሳዊ የወያኔ ተላላኪ ነው ያለው ሰው ቢሆንስ ሊያስበላን የሚሯሯጠው ይህንንስ አስባችሁታል? ያሰብናቸው ሳይሆኑ ያላሰብናቸው ቢሆኑስ ሊይስቆረጥሙን ሊያሳስሩን ሊያስገድሉን እና በወያኔ ወጥመድ ውስጥ ሊያስገቡን ይሚሯሯጠት?
ለማንኛውም ጥንቃቄ ጥሩ ነው ግን አግባብ ይኑረው
ሳይጣንም ቢሆን ሳይጣን እንደሆነ እያወቅነው ለጉልበቱ ቢያግዘን ሊከፋን ከቻለ ተሳስተናል ግን ሰይጣኑ መልአክ ይሆናል ብለን ካሰብን ትልቅ ስዕተተ ነው የሚሆነው
ሚኒሊክ እስካሁን ባለው ድረስ የራሱ ይሆኑ ድክመቶች ሊኖሩበት እና ትንሽ የአምባገነንነት ባህሪ ቢኖርበትም በሚኖረው የውስጥ መፃፃፍ ጊዜ የእርሱ ባንዳነትና ለወያኔ መስራት አይታይኝም ይህንን ብንልም ራሳችንን ከእርሱ በቻ ሳይሆን ከሌሎች ቢሆንም መጥበቃችንን መርሳት አያስፈልግም
ይቀጥላል...

አብቢን ህሊና አንዳርገቸው ነኝ

No comments:

Post a Comment