Monday, June 16, 2014

‹‹‹‹ዝንጀሮ የራሷን ሳታይ በሰው ቂጥ ትስቃለች›››››

‹‹‹‹ዝንጀሮ የራሷን ሳታይ በሰው ቂጥ ትስቃለች››››› አሉ ኤርሚያስ ለገሰ "የመለስ ትሩፋቶች" በሚለው መፅሃፉ ላይ ፓስተር ባደግ በቀለ በተባለ ከአሜሪካ በመጣ ግለሰብ አየርባየር በተቋቋመ የማሰልጠኛ ተቋም በተሰጠ ሥልጠና የኢህአዴግ ባለሥልጣኖች እንዴት የማስተርስ ዲግሪ ባለቤት እንደሆኑ እንዲህ ይገልፀዋል። "አምስት ኪሎ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጀርባ አንድ በህዝብ የሚተዳደር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር። ይህ የከተማዋ አይን ቦታ ላይ የተቋቋመ ትምህርት ቤት ከ40 አመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ባለቤቱ የአካባቢው ህዝብ ነው። ነዋሪው እንደ ማንኛውም የህዝብ ትምህርት ቤት ከመንግስት ድጋፍ አየተደረገለት ልጆቹን ያስተምርበታል። እናም እነዚህ ካድሬዎች መምህራኑንና ህፃናቱን አባረው ለአንድ ከአሜሪካ ለመጣ ፓስተር ባደግ በቀለ ለሚባል አጭበርባሪ በዜሮ ዋጋ ይሰጡታል። ፓስተሩም ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዮት የሚል ማሰልጠኛ ተቋም ያቋቁማል። እኔን ጨምሮ በረከት፣ ሀይለማርያም፣ ኩማ፣ ሬድዋን፣ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ጁነዲን፣ ደግፌ ቡላ፣ አስቴር ማሞ፣ ጀነራሎቻችን፣ የአማራ፣ ኦሮሚያና ደቡብ፣ ሱማሊያ ካቢኔ አባላት… ኧረ ስንቱ ማስተርሳችንን የሰራነው በዚህ የሌብነት ተምሳሌት በሆነ ለሰርተፍኬት ማስተማር እንኳን ብቁ ባልሆነ የአየር ባየር ተቋም ነው። የተከበረው ፓርላማ ሚኒስትር በሾመ ቁጥር "በተቋማዊ አመራር" አየተባለ የሚቀርበው የትምህርት ደረጃ የፓስተር ባደግ "ኪራይ ሰብሳቢነት" ልዩ ስጦታ ነው።

No comments:

Post a Comment