Monday, June 16, 2014

OMG god has turned his face away from us



ሴቶቻችን በሴቶች ቀን ወደ እስር ቤት ይገርማል የሃገራችን ነፃነትና ቦለቲካ ስዎች!!! እጅግኮርተንባቸዋል፡፡እጅግ ያስቀናሉ፡፡ እንዲህም አለ እንዴ ይህን ፕሮግራመና ድፍረት ከማሰብ እስከ ማስፈፀም ድረስ አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ ሁሉ ትልቅ ምስጋና ከሃገራችን ኢትዮጵያና ከውዱ እና ከተከበረው ህዝባችን ትልቅ ምስጋና ይገባችኋል፡፡
እኔ የገረመኝ ግን እሽ ለመብታችሁና መብታቸው እንዲሁም ለሃገራችን ብሄራዊ ጥቅም ያልወጣው ምን ሊባል ነው
ሴት እንዳንለው ሴቶቻችን ጀግኖች ናቸው፡፡ ምን ትባሉ ኧረ ኧረ ምን እንበላችሁ ሴቶቻችን እንዲህ ከማንም በላይ ወጥተው ለመብቶቻቸው ሲታገሉ…ለመብቶቻቸቸው ብቻ ሳይሆን ለመብቶቻችሁም ነው የሚታሰሩት የሚሞቱት የሚቆስሉት እስር ቤት ውስጥ የሚደፈሩት…ታዲያ ምን ትባሉ ወንድ እንዳትሆኑ አደላችሁም…በአሁኑ ሰዓት ወንዱ ለመብቱ ብቻ ሳይሆን ለመብታችንና ለመብቶቻቸው ብሎ ወደ ትግል መስመር ካልገባ ና ለሃገራችንና ለህዝባችን ካልደረሰ…ይህ የሞት ሞት ነውና ወንድም ሴትም አደለም፡፡ አቦ ተነሷ፡፡
ይህን ስል አገብጋቢያንና በልቶ ካጆች እንዲሁም ባንዳ ወያኔያዊያን አንተ ሴትና ወንድን ደግሞ በፆተው መጣህ ሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት እያደረስክ ነው ትላላችሁ፡፡ ግን ጉዳያችሁ ነው እነዚህ የነፃነት ታጋዮጭ ማለት የፈለጉትንና ነገም ዛሬም መቸም ማለት የምንፈልገውን ጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ለማንኛውም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መጋቢት 28 2005 ዓ.ም ሴቶቻቸን በቀናቸው ታሪክ ሰሩ፡፡ ቀናቸው ይህ ብቻ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አደረጉት ትልቅ ክብርና ሞገስ ይገባችኀኋል፡፡
ይህን ዝግጅት ወደ ተግባር የቀየረውንም አካል ለታሪካችን ዝክር ሁሌም ከህሊነ ልባችን አይጠፋም፡፡ ለማንኛውም ክብር ሞገስ ምስጋናና ፍስሃን ከናንተ ጋር ይሑን፡፡ ዊ ታንክ ዩ!!!

ቆይ ግን የማሌዥያው አውሮፕላን ወደ ህዋ መፅቆ ቢሆንስ ወይም ዩፎዎች ወስደውት ቢሆንስ በነገራችን ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ በቅርቡ በህልሙ የት እንዳለ ሊያይ ይጭላል ተባለ!!
በመሰረቱ አውሮፕላኑ
1.      በብዙ ሽህ ማይል ወደ ህዋ ከመጠቀ እዛው ተንሳፍፈው ቀርተው ሊሆን ቢችልስ
2.     እንደ አሜሪካ ያሉ ሃላን ሃገራት ጠልፈው ድራሹ እንዲተፋ አድርገዋል
3.     ፓይሬትስ ጠልፈውታል
4.     የኢትዮጵያ መንግስት ትዊተርና ጠቅላይ ሚኒስቴሩን የጠለፉ ፀረ ልማቶች ጠልፈውታልም የሚል ጭምጭምታ አለ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከጠለፋው እነዚህ አካላት እጃቸው ሊኖርበት እንደሚችል ማብራሪያ ለአልገጀራ ሰጥቷል፡፡

ፕሮፌሰር አስራትና የ ኢህአፓ ሞት አንድ ነው ለኢትዮጵያ ህዝብ!! ሁለቱም የኢትዮጵያን ህዝብ ቅስም ስብር ስብርብር አድርገው የሄዱ ናቸው!!! ይህ የተሰበረን ልባችንን የሚጠግንልን እንፈልጋልን እያልን ኢትዮጵያዊያን እንጠይቃለን!! ሁላችንም በያለንበት ለዚህ እንታገል!!


ባህርዳር ላይ እንዴት ነው ይህ የመላው አገር አቀፍ ስፖርቶች ፌስቲቫል ነው ፈስትኋን የሚባል ገና ስቴዲየም ውስጥ ሳያልቅ ልክ ብርቅ እንደሆነበትና ሳያጥብ ሳልቫጁን እንደሚለብስ ህፃን ለመዝለል በየቦታው በቢሊዮን ብር አበልም ሙስናም ምናምንም እያለ ለማባከን እንዲመቸው ሲዘል እያንዳንዱ የባህርዳር ህዝ ግን በተለያዩ ችግሮች ይሰቃያል፡፡
ይህንንስ ለምደውታል እንዲያው ኔትወርካቸውን ቢለቅቁላቸው ምናለበት!! ገና እስኪያልቅ ለቀናት ያለኔትወርክ!!ኧረረረረረረረረረረረረረረረረረረረረረ…አሁንስ ደሜ ቀጥ አለ!!
ሁለቱንም ኢህአዴግ እንደገደላቸው ማንም ያውቃል!! ኢህአፓ አሁን ልጆቹን እየተካ ሲሆን ፕሮፌሰርን ግን ገና…አላቆጠቆጡም ማን ይተካቸው

ዘመዶቼ መረጃ ማቀበል ሃገርን መካድ አደለም፡፡ ይህ መረጃ ነው፡፡ ማንን ሊፈልግ ነው የሚሄድ ይህ ሰራዊት
መልሱልኝ ግብፅን ነው እንዴ
እንዲህ ወንድሙን ከወንድሙ ለማፋጀትና ለማጨራረስ አሰሳ ወይም ምናምን ብሎ ብሄራዊ ኪሳራ ከመክሰር ይልቅ በአንድ ቀን 70 እና ከዚያ በላይ ንፁህ ኢትዮጵያዊያንን ኢትዮ ሱዳን ድንበር ላይ የሱዳን ወታደሮች እና ታጣቂዎች ገብተው ሲረሽኗቸው ዝም ማለቱን ትቶ ሌላው ቢቀር ጥያቄውን እንኳን ማንሳት አልፈለገም፡፡ ስዎች ጭንቅላትማ ይኑራችሁ እንጅ ግብፅን ሊፈልግ ነው እንዴት የሚሄድ ምናልባት ቢሄድ ከቻለ ያውም የሚያገኘው እኮ አርበኞች ግንባርን ደምሂትን ግ7ን ፍትህና እኩልነትን ኦነግን አማራ ፎርስንና ሌሎችንም ነው፡፡ መቻል አለመቻሉን ሲሄድ ያዋል፡፡ ይህ ህዝብን ለማወናበድ ሆን ተብሎ የተቀየሰ ነው፡፡ ይገርማችኋል እነዚህ ሃይሎች ለአንዲት ኢትዮጵያ የቆሙ፡፡ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ለምን ብለው ሄደው ለመጠበቅ የሞከሩ በራሱ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚወጉ ምርጥ ዜጎች ናቸው፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን በግብፅ የሚረዱ የኢትዮጵያ አማፅንን ብለው ዜናው እንዲቀርብ ያደረጉትም ለዚህ ነው፡፡ ህዝቡ ለግብፅ ያለውን አመለካከት በመገመት፡፡ እኛም ያሉትን በቀጥታ ነው ያቀረብነው፡፡ እባካችሁ ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ፡፡ በክህደት መሞላት ትርፉ ኪሳራ ና ትዝብት ነው፡፡

…ይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ ባለም
ኢትዮጵያ እድሜ ላንች ያላየሁት የለም
አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና
ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና
ማማ ካረግንልሽ በላይ የምታረጊልን
መጠሪያ እናታችን አንችው ኑሪልን
እማማማማማማማማ…

ይህን የዘፈነው ማን ነው?
 ለምንስ ዘፈነው?
ጥላሁን ገሰሰ ነው!!

እስቲ ኤዲት ተደርጎ እስኪያልቅና ጠቅላላ ይዘቱ እስኪጠናቀቅ ይህችን ቀምሳችሁ ቆዩ ምንም አይነት ችግር ቢኖርበት ለዚህ ሁሉ ተጠያቂወ ራሴ ኢትዮጵያን ፖለቲክስ እንደሆንኩ ወይም ሐቴርሳታ ነህምያ እንደሆንኩ እንድታውቁት እፈልጋለው!!!
መልካም ንባብ

የደህንነት ሰዎቻችን ዛሬስ ጥሩ ጥያቄ አነሱስ ስዎች? በመሰረቱ ጥያቄያቸው ዕነርሱ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ባለስልጣናትም ጥያቄ ቢሆን ጥሩ ነበር በርግጥ አደለም ማለት እና መደምደም አይቻልም ምክንያቱም ባለፈው ወ/ሮ አና ጎሜዝ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እያለ"…ሁሉም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተነጋግሬያለው እናም ሁሉም ለውጥ ያውም ስር ነቀል ለውጥ ቢመጣላቸው ደስተኞች እንደሆኑ የነገሯቸውን በአደባባይ መናገራቸውን እናስታውሳለን…" ስለዚህም ይህ በአጋጣሚም ሆነ በተሰላ መንገድ ደህንነቶች ያነሱት ጥያቄ የበርካታ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች እንዲሁም የመንግስት ደጋፊዎችና አባላት ፍላጎት እንደሆነ በየሄድንበት ሁሉ የምንሰማው የዕለት እለት ወሬ ነው፡፡
ለማንኛውም በርቱልን ተበራቱልን እንላለን፡፡ በመሰረቱ ይህ መንግስት ስሩ ድራሹ የጠፋ ዛፍ ማለት ነው፡፡ ድራሹ በምስጠ ድባ የጠፋ ዛፍ ታውቃላችሁ አንድ ቀን እንደ ደራሽ ጎርፍ ሳይታሰብ ዘው ብሎ ነው የሚወድቀው፡፡ የሚገፋው ከተገነ ደግሞ ያው ነው…እንደ ዞምቤ ደፋ ሲል ምናልባትም ያሳዝነን ይሆናል…
የደህንነት ሃይሎቹ ያነሱት ጥያቄ እጅግ መሰረታዊ ከመሆኑም በላይ ይህ ጉዳይ ሌሎቹንም የመንግስት ሃይሎች ተመሳሳይ ጥያቄ ለማንሳት ሙሉ ኮነንፊደንስ በራስ መተማመን እንዲኖራቸው  የሚያደርግ ሲሆን በዋናነትም ይህ ጥያቄ ለህዝቡ ቀጥተኛ የሆነ ምላሽ የሰጠ ሆኖ አልፏል፡፡
ህዝቡ በተለያየ ሰዓትና ወቅት በርካታ የፍትህ የእኩልነት የአንድነት እንዲሁም የመብትና የብሄራዊ ጥያቄዎችን በተለያየ ደረጃ ከመተየቅ ተቆጥቦ አያርፍም፡፡ ሁሌም ይጠይቃል አሁን ያለው ሁናቴ እንዲያውም ከጥያቄም አልፎ ወደ ተጋባራዊ ትግል በመግባት ይህንን በጠመንጃ የመጣ ሃይል በጠመንጃ ብቻ እንደሆነ ግብዓ ከመሬቱን የምንፈፅመው በማለት በረሃ የወረዱ ጫካ የሚገቡት ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እየሆነ ነው፡፡ ምንም እንኳን በረሃ የወረዱት ሃይሎች ብዛትና የልዩነት ግልፅ አለመሆን እንዲሁም ከህብረተሰቡ መሃል ገብቶ መመልመል አለመቻል ትልቅ ድክመታቸው ቢሆንም ቅሉ፡፡
እነዚህ ሀይሎች በክፍለጦር ደረጃ ተደራጅተው መንግስትን እየወጉና በበርካታ አስር ሽህዎች ሃይላቸውን በትጥቅና ስልጠና ደረጃም ቢሆን በረሃን የቀመሱና የጠገቡ የወጣላቸው ወጣቶችን በመሰብሰብ ብሶት ልጅን ወልዶ ልጅ ትግልን ፈጥሮ በፍቅር ተሳስሮና ዓላማን አንግቦ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁርና ብርድ ሳይበግራቸው ትግላቸውን እጅግ በደመቀና በአማረ መልክ እያካሄዱ መሆናቸው ዓለምን ከማስደመመሙም በላይ እነዚህ ሃይሎች ብሶት ወለዳቸው እና ፍትህ እጦት ያንገበገባቸው መሆኑ ለድላቸው ምናልባት ትልቅ መሰረት እንደሚሆናቸው ምንም የሚያወላዳ ጉዳይ አይሆንም፡፡
ሆኖም እነዚህ ሃይሎች ትጥቅ ትግልን ዓላማየ ብለው የተነሱበት ጉዳይ በመሆኑ አንዳች ሃይል ጀንጅኗቸው አንዳች ሃይል አስገድዷቸው ያላደረጉት ሆኖ ምናልባት ለድላቸውና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ስለመሳባቸው ምንም ጥርጥር ባይኖርም ሁሉም የታጠቁ ሃይሎች አንድ ሆነው፤ ለአንድ ዓላማ፤ ለአንዲት ሃገር ከሁሉም በላይ ስላስተሳሰረን ስለአንድነታችንና የክብራችን መገለጫ ስለሆነው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቃችን ሲሉ ተመሳስለውና ተዋህደው ከታሪክ ተምረው ካለፉት ስዕተቶቻቸው አንዳች ለትውልድም የስኬት ትምህርትን ታሪክን ምን ላይ ለምን ማስታወስና መድገም እንዳለብ ከታሪክ ስእተቶች ምን ምኖችን ማስተካከል አለብን ብለው አንድነታችን በአንድነታቸው ካላሳዩን መፃኢ የሃገራችን እጣ ፋንታ እጅግ መቸም በዘመነ መሳፍንት ያላየነው ውጥንቅጥ ውስጥ ሊያስገቡን እንደሚችሉ መገመት ለቀባሪ የማርዳት ያህል ከባድ አይሆንም፡፡
ዋናው ጉዳይ ይህን ሃሳብ ተመስርቶ የፅሁፌን ጭብጥ ለማስጨበጥ ነው እንጅ ስለነእርሱ እነርሱ ብቻ ይመለከታቸዋል ማለት ራስህ ሃገር ከምንላት ሃገር ኢትዮጵያችን እጃችንን ታጥበን የመውጣት ያህል ብቻ ቀላል አይሆንም፡፡ ማንኛውም ሃገራችን ውስጥ የሚፈፀም በጎ ተግባር የሁላችን ኩራትና መመኪያ እንደሆነው ሁሉ ርካሽ ስራዎችና አንዳች አፍራሽ /የኢህአዴግን አፍራሽ ቃል አደለም ሀሃሃሃሃሃ… እዚህ ላይ የተጠቀምኩት ነገር ግን ይህች አፍራሽ የምትል ቃል ማንኛውንም በመንግስትም ይሁን በዜጋው ማንኛውም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ክብር ለሚነኩ ጉዳዮችና ስዕተቶች ነው የተጠቀምኩት/ ተልዕኮ በሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ የሚፈፅም ውርደትን እንዳከናነበን ሁሉም ዜጋ የሚረሳውና የሚዘነጋው ሆኖ የሚያልፍ አደልም፡፡ ምናልባት ግን እስከ ጊዜው ምናልባት ሊዘገይ ይችላል፡፡
ታሪካችን ለብቀላና ለመጨቃጨቅ ከዳረገን ማለቴ ካዋልነው ቆሻሻውን ታሪክ ከፈፀመው አካል በላይ እኛ የከፋውን እንደፈፀምነው ማመንና ሃገራችን ላይ እጅግ አደገኛ መርዝን እየረጨን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ሃገር በታሪክ የምታድግ በታሪክ የምትወድቅ ቢሆን ኖሮ እንደእኛ ማን ነበር፡፡ የት በደረስን እንደእኛ ተላልጦ ተጋግፎ ተመላልጦ ካለበት እድሜ /ዕድገት አላልኩም እድገትን ለውጥን አላየንም ገና ምናልባት ግን እናያለን ሃሃሃሃሃሃሃሃ…እርሱ ሲፈቅድ/  የደረሰ የለም፡፡
 እኛ ግን ኖረናታል፡፡ መላላጣችን መላላጥ ብቻ አልነበረም፡፡ ሁላችንም ታሪካችን ዞር ብለን ማሰብ እንችላለን፡፡ ለማንኛውም እዚህኛው ተመልጦም ተጋግፎም መኖር መዳን የሌለበት ዘምን ላይ ደርሰናል አሁን ላይ ከመመላለጥና ከመጋጋፍ ከመቆሳሰል ምናልባት ሞት ሳይሻል ይቀራል ብላችሁ ነው፡፡ አሁን ምንም አይነት መላላጥና መጋጋፍ ላይ ባንደርስ ይሻል ነበር፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን ሃገራችን እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ እነድትገባ የሚያደርጋትም የማያደርጋትም ይሄው መንግስትና መንግሰት ብቻ ነው፡፡ መንገስት ካላላጠንና ካጋጋፈን እንደዛው እንሆናለን መንግስት ውረድ ስንለው የሚወርድ ቆይ ትንሽ እባክህን ምራን ካልነውም ከመራን ሌላ መልካም ነገር ግን …ምናባህ በምርጫ አደለም ያሸነፍኩ አንተም ያኛውን መስመር ተከተል ካለን ግን ያው መላላጥና መጋጋፍ መጣላችሁ…ያኔ ፍሩ ግን ሆኗል ሌላ ቀጠሮ አያስፈልግም ሆኗል፡፡ዞሮ ዞሮ አሁን የሚሆነውን እስቲ እናያለን፡፡
ለማንኛውም መንገስት የሚያደርገውን የማያውቀው ለምንድን ነው? ምንድን ነው ምክንያቱ ስልጣን ምን ይሰራለታል? ይህ ምስኪን ህዝብ ሚፈልገውን ነገር ቢፈፅም ምን ይሆናል? በቃ አልፈልግህም ካለው ምን አገገመው? ኦኬ ምናልባት የጀመርኳቸው ስራዎች አሉ ብሎ አስቦ ከሆነ የጀመረው ሁሉ ጊዜው ሲሰላ እኮ ከአርባና ሃምሳ ዓመት በላይ ይቆያል? አቦ ሽል በሉልና ምነው ሌላ ፊት እንይ እንጅ!!
እንዴ ደግሞ ከዛ በኋላ ሌላ ስራ መጀመር እና ሌላ ሃምሳ ዓመት እስቲ ወይ ቁርጣችሁን አሳውቁን እና አርፈን እንቀመጥ፡፡ ከዛም እኛም ወይ የራሳችን መንግስት እንመስርትና ራሳችን በራሳችን እውቅና ሰጥተን እንኑር፡፡
ምንድን ነው?!!! አቦ በቃና!!
በርካታ ጋዜጠኞች ነፃነት ነፃ ነት እያሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚጮሁ የሚፅፉና የሚናገሩ ሁሉ አሁን አንድም ስደት፤ አለያም እስር ቤትና ሲከፋም የሞት ሞትን ፅዋ ተጎንጭተዋት አልፈዋል እስር ቤትና ስደት ላይ የሚገኙትም ኣረ እንዲያው ያው የማይቀረው ሞቴ ይሻለኝ ነበር እያሉ ቀን ከሌሊት በጨለማ ክፍልና የአዕምሮ በሽተኞች ካሉበት ክፍል እየተከተተቱ አይጥ እባብና ከእባብ ያልተናነሱ የመንግስት ስውር ሰላይ እስረኞች ክፍል ውስጥ እየታጎሩ ያለምግብ ለበርካታ ቀናት መቀመጣቸው ሳያንስ ቶርች እየተገረፉ የሰው ልጅ አንጀት በሌላቸው የወያኔ አገብጋቢዎች እየተነረቱ፤ ወንዶች ሳይቀር እየተደፈሩ አንድም ባህላችን እምነታችንና የሰውነት ዘር በሙሉ እርኩሰት እንደሆነ የጠላውን ግብረሰዶም ሲያስፋፉብን በሌላ መልኩ ደግሞ አስገድዶ ያውም ወንድን ልጅ ወንድ ልጅ እየደፈረው ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
እኔ ግን ማይገባኝ መንግስት ያን ሁሉ ተፈጥሮ የሰጠችንን እንደ እጅ እንደእግራችን አቅም እንደ ኦክስጅን ተዝቆ እንኳን የማያልቀውን ነፃነታችን ምን አደረሱት ለማን ሊያወርሱት ፈለጉ????
በርግጥ ለዚህ ሁሉ የልብ ልብ የሰጠነው እኛው እራሳችን ነን፡፡ ምንም አይነት ዋጋ ተከፍሎ ያገኙት ስልጣንና ወንበር እንደመሆኑ ዝም ብለን ማየታችን ከደሙበት ከቆሰሉበት ከሞቱለት ወንበር ያላጥቃቸውና እንደሚያደርጉት 50 60 ዓመት እንዲገዙን ከማድረግ ውጭ ምንም ተፅዕኖ አይኖረውም፡፡
ስለዚህ ዝምታ ልባቸውን አሳብጦ ደረታቸውን አስገልብጦ በፊታችን አያንጎራዳቸው ባንልም እንኳን ቅሉ አናታችን ላይ ወጥተው የበላንን ቅማል እንኳን ሳልፈቅድልህ አታነሳውም እንደሚሉን እንደጀመሩት ሁሉ ምናለ በሉኝ፡፡ አንድ ወቅት አልበርት አንስታይን “…ዓለም ክፉ በሰሩትና በሚሰሩት አደልም የምትጠፋው እነዚህ ክፉ ሰሪዎች ክፉ ሲሰሩ ዝም ብለው ባዩት የክፉ ክፉዎች እንጅ…“ ለማለት እንዲህ ብሏል፡፡
“The world will not be destroyed by those who do evil, but by those who watch them with out doing any thing”
እንዴት አንጄት የሚያርስ አባባል ነው!!!
ታዲያ እኛስ ዝም ብለን የምናይ እርሱስ ነፃነታችን አባቶቻችን ያላስለመዱንን ታስሮና ተቀፍድዶ መኖር ምን ሊደርገን ለማን ሊሰጥብን ፈልጎ ነው ምን ወደ ውጭ ብሄራዊ ባንክ ላይ አጥሮ ያስጨነቀውን የውጭ ምንዛሬና መዘዙን ለማሟላት ኤክስፖርት ሊያደርገው ፈለገ እንዴ ነፃ ነታችን አቦ!!!
ላማንኛውም ዝምታው ይብቃና ሁላችንም እንደየአቅማችን ታሪካችን እናስመዝግብ እኔም አንድ ካልኩ በርከት ያሉ ሳምንታትን አስቆጠርኩ፡፡ በቃ ጀምሩ በቃ ተነሷ!!!!
አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ጉዳይ ቢኖር ከዛሬዋ ዕለት በፊት ማለትም ይህ እውነተኛ መረጃ ማለትም የደህንነቶች ስብሰባ ጥያቄያቸውና ሁለንተናዊ ሁነቱ  ከመውጣቱ በፊት አንድ ፀጥታ ሃይል በተለይ ደግሞ የደህንነት ሃይል በህዝቡ አይን እንደምን ይታይ እንደነበር ማስታወስ ብቻ በቂ ነው፡፡ ደህንነት ሲባል ፖሊስ ሲባል መከላከጣ በተለይ ወታደር ሲባል ህዝባችን እንደእሾህ እንደ አውሬ ከሰው ልጅ እንዳልተፈተረ አድርጎ ሚያይበትን የአይን ብሌን ማስቀየር ብሎም ከናካቴው ተሻለ አመለካከት መፍጠር የሚያስችል ነው፡፡
ከአሁን በፊት እነዚህ አካላት ለምን ይፈራሉ ያልን እንደሆነ መንግስታት ማለትም ስልጣን ላይ የሚቀመጡ ሃይሎች በባህሪያቸው አግባብ በሆነ መንገድ ወንበሩን የያዙ ባለመሆናቸውና አንዱ ቡድን አንዱን እዋጠው፤ አንዱ አንዱን እቆረጠመው፤ አንዱ አንዱን እቀሰፈ፤ አንዱ በአንዱ ደምና አጥንት ላይ እየተረማመደ፤ ለህዝብ መብትና ሁለንተናዊ ደህንነት ሳይሆን ለስልጣንና አንድን ቡድን የተሸለ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ በሚደረግ ትንቅንቅ ዋሻ ውስጥ ያለፉ በመሆናቸው ይህን ሃይል ይህን የሚፈልጉትን ሃይል ለመምታት እና ቀጥቅጦ ለመግዛት ብቻ እንጅ ለምንም አይፈልጉትም፡፡
በዚህ ረገድ ከወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ይልቅ ቀደምቶቹ ተሸለ አድርገው እንደተጠቀሙበት በሙሉ ልብ መናገር ይቻላል፡፡ አነዚህ መንግስታት ውስጣዊ መናኮራቸው ህዝቡንም ሃገሪቱንም ራሳቸውንም አፈር ዱሜ እንዲበሉ ቢያደርጋቸውም ቅሉ በዋናነት ግን ብሄራዊ ማንነትና ሉዓላዊን ላይ ያላደገመ እርምጃ በመውሰድ እጅግ የዜሮና የየትሌሌ ያህል ልዩነት አላቸው፡፡
የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት እንዲሁ ከታሪኩም ከአመጣጡም ቢሆን ሲታይ አላማው የወደቀና የረከሰ ስረርዓት እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን፡፡ ይህ ያለምክንያት ተባለ አደለም፡፡ በማስረጃም በመረጃም መቅረብ የሚችል ሃቅ እንጅ፡፡ ለምሳሌ ከአላማው ብነነሳ እንኳን የወያኔ አላማ ነበረው አማራውንና የኦርቶዶክስ እምነትን ወደ መቃብር መክተትና ድጋሚም ብቅ እንዳይል ማድረግ ነው፡፡
ስልጣን ላይ ለመውጣት ትልቅና ፅናት ሚጠይቅ ቢሆንም ቅሉ ይህን አላማ ብሎ ወንድማማቾች እንዲፋጁ ማድረግን ያህል ቅሌት ይህን ያህል ብሄራዊ ድፍረት ግን አላም ላይ የለም ቢኖርም እንኳን ከአሸባሪነት በላይ ታሪካዊ ስዕተት ነው፡፡ ሰው ልጅ ሁሉንም ጉዳይ ሊረሳ ይችላል በይቅርታም በምንም መልኩ ታሪክና ፈጣሪ ግን አይረሱም፡፡ ፈጣሪ ምናልባት በይቅርታና በንስሃ ሊረሳው ሳይሆን ሊምረን ይችላል፡፡ ታሪክ ግን ምንም ምህረት ምንመ አይነት ይቅርታ የለውም ታሪክ ህሊና ነው፡፡ ህሊና ደግሞ ዝመ ካላለ አይረሳም ዝም ሲልም ረስቶ ሳይሆን ትቶት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ታሪክ ማይረሳውን ዝም ቢልም የሚረረሳው ኩነት አደለም፡፡
እስቲ እንቀጥል ኢሕአፓ ልምን ከምድረ ገፅ ጠፋ
ይህን ጥያቄ የጠየቅን እንደሆነ፡፡ ይህ ከምድረገፅ ተፍቶ በለስላይ የስንት ሽህ ኢትዮጵያን አንድነት በመናፈቅ ህይወታቸው የተሰውት ውድና ልሂቃን ወንድሞቻችን በዚሁ በወያኔ የመገነጣጠል ሴራ ነው፡፡ አስቡት የኢህአፓ ሰራዊት ክተት አዋጅ ምታ ከበሮ ብሎ ሲነሳ ከተማ ገጠር ሳይል ኢትዮጵያን ከገኝጣዮች ማዳን አንዱ ኣላማቸው ነበር፡፡ ለዛም ወያኔና ሻብያ ይህንን የማይፈልጉት ጥሪ ላይ የጠሰባሰበ ሃይል ስለነበረ ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ በደምና ረሃብ ያጨቀያቸው ጀመር፡፡
ሰውናቸውና ሲተኩሱና ሲገድሏቸው መሞት አይቀርም የሚሞተው ሲሞት ያልሞቱትም በየስፍራው አውሬና አሞራ ራት ሆነው ቀርተዋል፡፡ ያኔ ተገደሉት ኢሕአፓዎች አልነበሩም ግን ሃገራችን ኢትዮጵያ ህልውናና መፃኢ ዕጣፋንታ ነው አብሮ አሞራ የበላው፡፡
ግን ኢትዮጵያ ህልውና ግን እንደሞቱት እና አፈርም አሞራም አውሬም እንደበላቸው ኢህአፓዎች ሳይሆን አሞራውና አውሬው መሬቱም ሲለማ እንደሚገነው ወርቅ ነው፡፡ ሁሉም ሲጠፉ እንደገና ያለመልማል፡፡
አስቡት እንዲያው ታሪክ አስታውሶኝ ይህን ያህል የልጅ ወሬ እንደልጅነቴ ዘበዘብኩ አንጅ ዋናው አላማየ ግን ይህ ሳይሆን ወያኔ ማሌሊትን አላማ መናገር ነው፡፡ ኦኬ እንቀጥላ፡-
ስለዚህ ኢህአፓዎችን ከናካቴው ዘራቸው ጠፍቶ ልክ አማራውና እምነቱ እንደታቀደለት አሁን ይህን ያህል ተፅዕኖ መፍጠር በማይችሉበት ደረጃ ላይ ስለመሆናቸው ምንም ለማለት መረጃ የሚያንሰኝ ቢሆንም ቅሉ ወጣት ክንፉ ዕየተንቀሳቀሰ እንዳለ ያለውን ትተን ለዚህ በተለይ አሁን ላለው በ20ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ላለነው ጀኔሬሽን መድረስ አልቻለም፡፡
በመሰረቱ ይህን ያህል ወያኔ በኢህአፓ ላይ የሰራውን ደባ እና የአንድ ጀኔሬሽን ዘር ማጥፋት ብናወራም ቅሉ አንዳንድ ፀሃፍት እንደሚሉት ግን ኢህአፓ የራሱ ሆነ ክፍተትና ጉድለት የነበረበት ስለመሆኑ ምንም መረጃ ማጣቀስ አያስፈልግም፡፡ ኤኒወይስ ይን የ ጊዜ ሰው ይበለንና እንመለስበታለን፡፡
ለማንኛውም በ1983 ዓ.ም እና በፊት እየኮረመመ እየኮረመመ በሚባል ደረጃ ሳይሆን እጅግ በሚዘገንንና ትውልድ ሊረሳው በማይችል ሁናቴ ኢትዮጵያን ለዚህ ዳርጓታል፡፡ ሃገራችን ላይ ያኔ ሁለቱም ማለትም ደርግም ወያኔም ምንም አይነት ስዕተት ባይሰሩ ኖሮ ሃገራችን አሁን ላለችበት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊ ባህላዊና የዜጎቿ ስነልቦናዊ ቀውስ አትዳረግም ነበር፡፡
ሆኖም ያን ያህል ሰራዊት አለቀ፡፡ ያን ያህል የተማረ ሃይል አፈር በላው በሜዳ ተበትኖ ቀረ፡፡ ያን ያህል ኢትዮጵያዊ የአሞራና የአውሬ ሲሳይ ሆኖ ቀረ፡፡ አይ ሰይድ ኢትዮጵያዊ ትክክለኛና ምርጥ ኢትዮጵያዊ ንፁህ ኢትዮጵያዊያን አለቁ፤ ተረሸኑ፤ በመኪና እየተጎተቱ ስጋቸው አቧራ ጋር በኖ ጭቃ ጋር ተላጥቆ፤ ስርንቻና ድንጋይ ጉራንጉሩ ስር እንደ ቡትቶ ለቃሚ አጥቶ ቀባሪ አጥቶ ተበተነ፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ በወንድሞቻቸው አሁን ስልጣን ላይ ሆነው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለውን ቀሪውን ለመጨረስ ታጥቀው ከተነሱ ይሄው 40 አመታትን መሳሪያ አንግተው በመሳሪያ ካልሆነ አንለቅቅም ብለው ሰፍተውናል፡፡
አሁንም ድጋሚ ሌላ በሽግግር መንግስቱና ከዛ በፊትም በነበራቸው አላማና አቋም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ የጮኁ ልሳናትን እስከወዲያኛው እየዘጉ ኤርትራን በነፃነት እና በወደፊት ድብቅ ህልም ስም አስገነጠሉ ሳይሆን ገነጠሉ፡፡ ከዚያም ብግለሰቦች ጦርነት አንዴ የአሰብ ጦርነት ዋር ኦቭ አሳብ ሌላ ጊዜ ዋር ኦቭ ባድሜ ልላ ጊዜ ዘመቻ እብሪተኘኛውን ቅልበሳና ድምሰሳ ዘመቻ ፀሃይ ግባት ገለመሌ እየተባለ አሁንም ሌላ የወንድማማቾች እልቂት፡፡ በሁለቱም ወገን ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ያላነሰ ወጥትና አምራች ሃይል በበረሃ ቀረ፡፡
በነገራችን ላይ ይህን የኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ሁለት አንደኛው በእንጀራ እናት ሌላኛው ደግሞ በእንጀራ እናት የሚሰቃዩ ወንድማማቾች ጦርነት አድርጌ ነው የማየው፡፡ ሁለቱም ወንድማማቾች ናቸው ነገር ግን አባትና እናቶቻቸው በመለያታቸው ምክንያት ሁለቱም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በደሉ የማንም ቢሆን ተገዳደሉ፡፡ ተመሳሳይ ነው፡፡
አሁንም የኤርትራና ኢትዮጵያ ጦርነት ታሪክ አንድ ቀን የሚመለከታቸውን አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን ሁለቱን "ሃገራት" ባለስልጣናት የሚፋረዳቸው መሆኑንና የሁለቱም "ሃገራት" ህዝቦች ከአንድነት በፊት በኋላም ይሁን በአንድነት ሰዓት የሚፋረዷቸው ስለመሆኑ አንድም ጥርጣሬ የለኝም፡፡
አሁን ኢትዮጵያም ኢትዮጵያ አደለችም፡፡ አርትራም ኤርትራ አደለችም ሁለቱም "ሃገራት"  አደሉም፡፡ ሁለቱም በመጠን የማይገናኙ የታላቋ ኢትዮጵያ አካላት ናቸው፡፡ በእውን አንድ ሰው ሰውን ሰው የሚያሰኙት ነገሮች ውስጥ አንዱ እንኳን ቢጎድለው የጎደለው የለምን? ሰውየው ሰው ነው ግን ሙሉ ለመሆን የጎደለው ሰው፡፡ ይህን አባባል እኮ ኢህአጌግየ ለጥቅሟ ልታውለው ትችላለች እና ወገኖቼ ቀለል አድርጋችሁ ተረዱልኝ፡፡ ሰው አደለም አደለም ያልኩኝ ግን ከሌሎች ስዎች ይልቅ አንድ የሚጎድለው ነገር በመኖሩ አንድም በስነልቦና ሁለትም በአካላዊ ባለቤትነት እንደጎደለው መረዳቱን ማም ገማች አያስፈልግም ለመናገር፡፡
ያም ሆነ ይህ በሃገር ደረጃ ስንመጣ ግን ሃገር ህሊና የላትም ሃገር እንደሰው አታሸትም ሃገር እንደሰው አትዳስስም ሃገር እንደሰው አትለፈልፍም ሃገር እንደሰው ጎደለኝ አትልም ሃገር የሰው ምስል የሰው ማንነት መገላጫ ራሱ ሰው ለከለላ ለመኖሪያ የሚሰማት የሚረዳት የሚያውቃት የሚኖርላት የሚሞትላት የሚሞትላት እድለኛ ከሆነ በአጠቃላይ ሃገር ስሜትና "ነፍስ" ናት፡፡ ነፍስ ሰል ከተሜዎች የእድሜ እኩዮቼ እንደሚሉት "ነፍስ ነገር" የሚለው ሳይሆን በእንግሊዝኛው "soul" የሚለውን ቃል የሚተካውን ነው፡፡ አንድ ሰው ነፍስና ስጋህ ሊለይ ነው ቢባል ፤ምንድን ነውየሚያስበው በቀጥታ ልትሞት ነው የሚለውን ነው፡፡
በትክክልም ትክክል ነው ይህ ሰው፡፡ ነፍስና ስጋ ከተለያየ ሞተ ነው፡፡ ሰውነታችን ያለሃገር ደግሞ ሞት ነው፡፡ ለነፍስ ስጋችን ዋጋ እንደሌለው ሁሉ፡፡ ነፍስ ሽርፍራፊ ላትም ሃገርም ሽርፍራፊ ላትም፡፡ ነፍስ ተሸረፈች ካልን ምናልባት ቢሆን እንኳን ስጋችን ሞተ ለማለት ብቻ ነው /ሃሃ…ሰውየው አሽሟጣጭ ካልሆነ በስተቀር/ ማለቴ ነው፡፡ ሃገርም ተሸርፎ ሃገር የለም፡፡ እነ አሜሪካዊው ዴቪድ ሽን እንቅበጥ ብላችሁ ይህ አውት ዴትድ ነው ካላችሁ ጉዳየ አደለም፡፡ ዴቪድ ሽን ኢትዮጵያ ባድመን ትስጥ አሰብ ጉዳይም የሞተና የበሰበሰ አስተሳሰብ ነው ጊዜው ያለፈበት ጥያቄ ነው፡፡ ብለዋል አሉ፡፡
እርሳቸው ያሉ ከአሜሪካ ጥቅም አንግል ነው ወዳጄ፡፡ ለዛም አደል አሜሪካ አሁን ኤርትራ ጋር ምን ልትሰራ እንደሆን በትክክል  ዳብል ኤጅንትነቷን ባናውቅም እተመላለሰች ማዕቀብ ተደርጎባታል ሲባል እርሷ እርዳታ በእርዳታ የምታዠጎደጉድ፡፡ ምናልባት አረቡ አለም ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን አሸባሪነነትን ከኢትዮጵያ ይልቅ ኤርትራ ላይ ሆና መቆጣጥር እንደምትችል ስታውቅ ሃሃሃሃ…እኛን ለኤዥያዎቹ አይጠበሎች ቅርምት ትታን ሽል አለች፡፡
ስዎች ታድያ ይሀን የወንድማማቾች ጦርነት አካሄድን ብየ ዝም አልልም፡፡  ምክንያቱም ለምን ተካሄደ በትክክል ጦርነቱ ባድመን ልውሰድ አትወስድም ልቀቅ አልለቅቅም ወይስ አሰብን ስጠኝ አልሰጥም፡፡ ወይስ ናቅፋን ለምን አትመሽ ብሬን ባንክሽ ቀርቅረሽ ኔን ሃገር ጥሬ ሃብት ለቃቀምሽ? ምንድን ነው ታዲያ ያን ያህል ስንት የስራ እድል መፍጠር የሚችል ሃብትና ንብረት፤ ስንት ፋብሪካዎችን ማስገንባት የሚችል፤ ስንት መሰረተልማት ማሰራትና የሀገሪቱን ህልውናና ዜጎቿን ኑሮ ማሻሻል ደህንነት ማስተበቕ በቂ የሆነ ከልመና ማስወጣት ሚያሰችል ሃብት መውደሙ?
ምናልባት እንደ ወትሮው ዘመን ጦራችን እስቲ እንሞክረው እስቲ እናጋጥምና ይለይላቸው ብለው ወታደርና ጠባቂ እያደለቡ ህዝባቸውን በቅኝ ግዛት ብቻ ሳይሆን ባሪያ አድርገው እንደሚገዙት ጋጠወጥ መሪዎችና የጦር ምርጦች መሆኑ ነው፡፡ ዱሮ ግላዲያተር የሚሏቸውን ወታደሮቻቸውን ማለትም ባሪያወቻቸውን እያደለቡ እና ጦረኛ እያደረጉ እንዲሁም እስኪመላለጡ ስራ እያሰሩ ንጉሶቹ ጦርነት ብቻ ሲያውጁ ከየት ሃገር ጦር ጋር ሄጄ ልግጠም ይሆን እኮ እስከማለት የሚስቡበት ዘምን ነበር እንዲህ አይነት ችግር ነበረበት፡፡ ይህም የጦር ፈተና መሆኑ ነው፡፡
ምናልባት ታዲያ እንደዛ እና ለዛ ነው ካልተባለ እኮ የኢትዮጵያነ ኤርትራ ጦርነት ለምን እንደተካሄደ ታሪክ ካልመለሰው በስተቀር ማንም ሊመልሰው አይችልም፡፡
ሆነም ቀረ ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ ያለምንም ምክንያት ጦርነቱ በአንዱ አሸናፊነት ተከናወነ፡፡ አለቀ ካልን ብየ ነው፡፡ ከዚያም እንደዴሞክራሲ ምናምን ይሞክረን እስቲ ምን ምን ነው የሚል ብለው ሊቀምሱት አሰቡና ነው መሰለኝ የ1993 አካባቢ ላይ የተነሳወን ትርምስና የጠጎዱ ቤተሰቦችን እረስተወው 1997 ላይ ተሞከረ፡፡
እኔ ያን ጊዜ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ነበርኩኝ እና ሰላማዊ ሰልፋችን ሁሉ አመፅ ነበር የምንለውና እስቲ አመፅ እያልኩ ልጥራውና ቅንጅት ቅንጅት ቅንጅት ማናምን እያልን በስሜትም በምንም ለውጥ ሳይሆን ቅያሪ በማሰብም ፖስቴ እስቲ እንምታ ኑሮ ትንሽ እንኳን ፈቀቅ ቢልልን ብለን ብንሞክረው እንኳን ፈቀቅ ሊልልን የኑሮ ጎርፍ ይዞን ጭልጥ አለ፡፡
አንዳንዴ ሳስበው እንዲያው ባልነካካነው ኑሮን እላለው፡፡ ያኔ አንድ ኩንታል ጠየፍ አስታሳለው 90 ብር ነጭ ጠየፍ ተመርጦ ነው መገዛት የሚችለው የነበር፡፡ 1000 ብር የሚያገኙ በወር የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝተኞች እጅግ ናጠጡ ሃብታም ነበሩ፡፡ ምክንይቱም ሁሉም ከዚያ በታች ስለሆነ በጠየፍ እንኳን ብናስበው 7 ኩንታል ነጭ ጤፍ በአጭሩና ዘመናዊ ሆነ ሶፋ ወዲያውኑ…ቴሌቪዥን ማናምን ብለው ምነ አደከማችሁ በሶስት ወር ምን መሰለ ቤትም ሳይሰ ይቀራሉ፡፡ ላማንኛውም በ1997 ምርጫ ባንነካው ጥሩ ነበር ነካክተን ዲሞክራሲን እንቀምሳለን ብለን የእንዶድ ቅጠል ሆኖብን ዲሞክራሲ ጠቅላላ ውጥንቅጣችን አውጥቶን እስካሁን ሳናገግም አለን፡፡ ምናለፋሁ 1997 ምርጫ ኤች አይ ቪ ሆኖብ አለ፡፡ በሽታውስ ማስታገሻ አለው ይህማ ዋናው አመንምን አደል እንዴ፡፡
ታዲያ የኔ ነገር ብቻየን ማወራ መስሎኝ አንዱን ይዠ አንዱን ሆነ እንጅ ይህን የ1997ቱን ምርጫ ያስታወሰኝ እንዲያው ለምን እንደሆነ አይገባኝም እኛም ጅሎች ነን፡፡ ያኔ ተወዳዳሪ ፓርቲዎቻችንም ምን ነበሩ ልበል እንደዛ ሊሆን አንደሚችል ያልነገሩን ቀድመው፡፡ ነገሩ እኔን የተጫወተብኝን ስለማውቀው ተውት አስሸውዶኛል አስሸውዶኛል፡፡ ግን ራሳቸው ትልልቆች ናቸው፡፡ ወጣት አንኳን ያው ከንቱ ብቻ ነበር መሰለኝ እና እንዴት ለዲሞክራሲ ምንምን ይላል ቅምሻ ብቻ እንደነበረ እንዴት እንዳላወቁ አይገባኝም፡፡ ለነገሩ እነርሱም እኮ ገና ቀመሳ ላይ ነበሩ፡፡ ለማንኛውም ምስኪኑ ህዝብ ኑሮን ቀመሳት ያልቀመሰ የለም ብቻ፡፡
ኤኒወይስ ሁላችንም ቀመስን ከቀማሾች መካከል ግን መንግስት ሽህ ጊዜ አቅምሶን ሳይገባን እሱ ግን አንድ ጊዜ ቀምሶ ዲሞክራሲና የዲሞክራሲን ቅምሻ ወዲያውኑ ወንድ ነው እንኳን በዚህ አጋም ላጋም ሸንተረር ለሸንተረርም ሽል ማለት የማይጠፋው መንግስት ወዲያውኑ አስቀይሶን ሙዱን ይዞ ሽብልል አለና ስንሯሯጥ እያየን በሳቅ ፍርስ እያለ ከቤቱ ቀድሞ ገዛውን እየነፋ ቁጭ፡፡
እና ከ1997ስ ምርጫ ምን ተጠቀምን ምንግሰት እጥፍ ማለቱን፡፡ ለምን ነበር ምርጫው የተካሄደው፡፡ ቀጠለ እንግዲህ በነገራችን ላይ ይህ የማወራላችሁ ሁሉ ከፃፍኳቸው ታሪኮች በእያንዳንዱ መሃል ጎን ለጎን ራስ ለራስ ግርጌ ለግርጌ /ሃሃሃሃሃ…/ በርካታ ታሪኮች በርካታ ያለውጤት የተጠናቀቁ ጨዋታዎችና መዘዛቸው፤ ያለምክንያት ምንግስተ ሰማያትን ተቀላቀሉ ነፍሶች፤ ያለምክንያት ተካሄዱ የታሪክ ጠባሳዎች ያለጠመንጃ የተደረጉ ጦርነቶች፤ ያለምንኩስና የተሄደባቸው ባዶ እግሮች፤ ግፍ፤ ስቃይ፤ ሞት፤ ሽልማት፤ እንልት፤ ግርፋት ቶርች፤ ብቻ ያለ ምክንያትና ውጤት የተፈፀሙ ኩነቶች ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡
ኣረ የትም ሳትሄዱ ሳይነገርላቸወው ሞቱት ሳይነገርላቸው የታሰሩት ሳይዘፈንላቸው የተረገጡት ሳይባልላቸው አንገታቸውን የሰጡት ስንቶች ናቸው፡፡ ወዳጆቼ ይህች 27 አመቴ ስንቱን አሳችኝ፡፡ አሁንስ በገላገለኝ፡፡ የዘረፈና የሰረቀ፤ የገደላ ያሰረ፤ ያረደና የባረከ ብቻ፤ ያለው ብቻ ሚኖርባት ሃገር ሆናለች በኢኮኖሚ ሳይንስ እኮ ሰውች ያላቸው ብቻ ሲኖሩና መኖር ሲችሉ እኮ አደለም አንዲት ሃገር የምትኖረውና አድጋለች የምትባለው፡፡ የሌለውም መኖር ሲችል ነው፡፡ ሃብት ላይኖረው ይችላል፡፡ መኖር ግን መብት ነው፡፡ መኖር ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ሃሃሃሃሃ…እሱማ ሃብትም ነበር እንዲያው እንተውላቸው ብለን ነው እንጅ፡፡
በአጠቃላይ ያለምንም ነገር አንድን ብሄራዊ ጉዳይ ማከናወን ከታሪክ ተወቃሽነት ብቻ ሳይሆን በታሪክ ፍርድን ከማግኘት አያስጥልም፡፡
ሲቀጥልም ያልንም ውጤት ሁለተኛው ምርጫ የማሟያ ምርጫ ምናምን እተባለ ቀጠለ…እያለ ደግሞ የሶማሊያ ጉዳይ ያገባናል ብለን እርፍ አልንና ዘለን ገና ለገና ከአሜሪካ የሚመጣው እርዳታና ብድር ይቀራን ብለን እርዳታውም መጥቶ ብድሩም መጥቶ እኮ ምንም ከእርዳታው ቢበልጥም ለህዝቡ ሚደርሰው በሆነ ግን እዛው ተበትኖ ለሚቀረው አልሸባብ ያኔ ሰማሁት ቃል ስለሆነ ጅሃድ አወጀብን ምናምን ተብሎ ወንድሞቻችን ብቻ ሳይሆኑ እህት አባትና እናቶቻችን ሄደው በባዕድ ሃገር አለቁ፡፡ያው እንዳያችሁት የኛው ወገን ወታደሮች ምንም በማያገባቸው ገብተው ዘላለም አልሸበብን ተላትነትም ሶማሊያ ህዝብ ጠላትነትንም አትርፈን መችም አደልም እኛ አሜሪካዊያን ማጥፋት ላይችሉ ቢሞክሩም በግዙፍ ኢኮኖሚያቸው ብቻ ላያጠፉት ሊታገሉት እንደሚችሉ እያወቀ መንግስት አስቸረሳቸው፡፡ አስከሬናቸው በባዕድ ሃገር ቀባሪ አጥቶ ልጅሽን አሞራ እንጅ አይቀብረውም ዘመድ…ስለተባለ እነዳይሉን አሞራም አልበላቸው አስከሬናቸውን ጎዳና ላይ ምንም እንዳያነሳቸው ተብሎ በፀሃይ ቀልጠው እንደ ሰም ሲፈሱ እንደ ዘይት መሬቱን ሲያበላሹት ብቻ ነው ወደ ቆሻሻ መጣያ ተጣሉ እንደ ሙዝ ልጣጭ፡፡
ለምን ለምን ለምን ለምን…ውጤቱስ ምን ሊሆን ምን ጥቅም አገነች ኢትዮጵያ ምን ጥቅም? ኣረ ምን ጥቅም? ኣረ ምን?
ለማንኛውም አስቡት፡፡ አልሸባብን እንደፎከርነው አሸነፍነው? አጠፋነው? አልሸባቦች አሁን የሉም? ከሌሉ ጥሩ ግን እንዲያውም ሙሉ የሶማሊያ ህዝብ ሆ ብሎ ሊነሳ አንድ እስኪሆን እስኪደራጅ ብቻ እንደሚጠብቀን ተስፋ እናድርግ፡፡ አልሸባብ እንደሆነ ሙሉ የሶማሊያ ህዝብ ነው፡፡ መች ነው የሶማሊያ ህዝብ ኢትዮጵያ ጋር ልባዊ ግንኙነት ፈጥሮ የሚያውቀው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራችን ደግሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አሚሶንን መቀላቀሉን አብስረውናል መበሰር ከሆነ ለሌላ ሞት እርሳቸውም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አልሸባብን ዲባቅ መትተን ድጋሚ እንዳይነሳ ለማድረግና ባይደዋ ላይ ሴክተር ሶስት የተባለውን በዛው በገባበት ቀን መቆጣተሩን ነገሩን እኛም ይሁና ወንድምና እህቶቻችንም አስጨርሱ እኛስ ዝም አልንም አላልን ምላሹ ትርፍ ካለው ውብ ብለናል ግን ውጠየቱ ትርፉና ኪሳራውን እንድታስረዱን ስንል እንማፀናለን፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ሊንክ ጎብኙ
https://www.facebook.com/hashtag/ethiopian?source=feed_text  #‎Ethiopian troops join #‎AMISOM in #‎Somalia and took control of Sector 3 in Baidoa earlier today. This will create better opportunity to flush out #‎AlShebab . Somalia deserves peace & development & #‎Ethiopia is ready to help in any way possible
እሽ ብለን እንቀጥላ ግን አልሸባብ የማያልቅ የዘር ፍሬ እንዳለው በትክክልም መናገር ይቻላልና ብንጠነቀቅና ራሳችን ብቻ ብንከላከል በቂ ይመስለኛል፡፡
ኦኬ እስካሁን ያየናቸው ሁሉ ያለምንም ተጠናቀቁ፡፡ ከዛስ…
ከዚያም የ2005 ምርጫ በጣም የሚገርማችሁ እኔ ባለሁበት አካባቢ አንድነት ሙሉ በሙሉ እንዳሸነፈ አባቴ ታዛቢ ስለነበረ በትክክል ነግሮኛል ያውም በስንት ውጣወረድ እና ማጭበርበር፡፡ አስቡት አሁን ህዝቡ አማራጭ አጥቶ እንጅ አንድነት ያኔ ቢያሸንፍ ፓርላማ ወንበሩን ይዞ መንግስት ሆኖ ምንግስትን ማለቴ ወንበር ላይ ያለውን መገዳደር ይችል ነበርን ነገር ግን ህዝቡ ስላጣን ላይ ባለው መንግስት በመማረሩ ብቻ ሁሉም የሚመጣውን ባለማስተዋል መረጠ፡፡ ተሸነፈ መንግስት አሸናፊ አንድነት፡፡ ስለዚህ ልምን ምርጫው ተካሄደ? አንድነቶችስ ምንድን ነው ሚፈልጉት? ትእገግስት አለ እንዴ ፖለቲካዊ ጉዳትና ብሄራዊ ጥቅም ላይና የማንነት ህልውና ላይ? ሆሆሆ…እያለ እያለ
ብረካታ ተጓዳኝ ኩነቶችና እውነታዎች ተከሰቱ፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ ያለጥቅም ብሄራዊ አንድነታችን ብሄራዊ ጥቅማችን ብሄራዊ ሉአላዊነታችን ብሄራዊ ክብራችን ብሄራዊ ዜግነታችን ከፋፈልን አጣን በዜሮ ተሸኘን፡፡ በአጣቃላይ ብሄራዊ ኢትዮጵያዊነታችን ተነጠቅን እስካሁንም አላስመለስንም፡፡
አስቲ ማን ይሙት ኢትዮጵያ ወደብ ኖራትም አልኖራትም ልዩነት ለውም እንዲያውም ደረቅ ወደብቷ በለጠ ጥቕም አለው ሴኪውርድ ያደርጋታል ተብሎ ንግግር ምንድን ነው?!!!
ነው ወይስ እኔና መሰሎቼ ደደቦች ነን?!!!
እንዴ ታዲያ ለምንድን ነው በአመት ከመቶ ሃያ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለወደብ ክፍያ የምናወጣው? ያውም ያንን በመከራ ስንትና ስንት ጊዜ እየተዛተብን፡፡ እንደአንደኛ አመት ተማሪ አሁን አባረሩኝ አሁን ጫሩኝ እያለ እንደሚቸናነቅና በመጨናነቁ ብቻ በራሱ ጊዜ እንደሚታመምና እንደሚጫር ተማሪ፡፡ እንዴ እስቲ አንድ ጉዳይ ልንገራችሁ፡
በነገራችን ላይ በአንድ ወቅት ኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር …ኢትዮጵያ እራስዋ እምቢ አለች እንጅ የአሰብ ወደብን መጠቀም ህጋዊ መብት አላት ብለው ተናግረዋል፡፡
እስቲ ይህንን ሊንክ ተጭናችሁ አረጋግጡ በራሳችን ቋንቋ ስለተናገሩት እኔም እናንተም አናጭበረብርም

ታዲያ እምቢታው ምንድን ነው፡፡ ምነው አብስትራክት አደረጉት እኮ ማትሪክስ ሆነ እኮ ታዲያ ለምንድን ነው ያኔ መጠቀም ያልፈለግነው፡፡ አንዳንዴ መምህር ሚከብደው ፖርሽን ላይ ሲደርስ ወይም የሚከብደው ምዕራፍ ሲገጥመው፡፡ ለተማሪዎቹ እንዲህ ብሎ ነው የሚጀምረው
"…እንግዲህ ቀጣዩና ዛሬ ምንጀምረው ቻፕተር ብጣም ከባድ ስለሆነ ይህን አስተማሪ ምን ልጠይቀው ብላችሁ ካሰባችሁ ላለፉት 17 ሰኮንዶች ማለትም ከአጠቃላይ 20 ፐርሰንት ኦቭ የአጠቃላይ ፔሬዱን አላዳመጣችሁኝም ተብሎ ስለሚታሰብ ምንም ሳትሰሩ በፅሞና ተከታተሉኝ፡፡ ይህን አስተማሪ ምን ብየ ልጠይቀው ሳትሉ ምን ብቻ መስማት እንዳለባችሁ አውቃችሁ ተከታተሉ፡፡ ለዚያ ውጤት ላይ ዋጋችሁን ታገኛላችሁ…"
ብሎ ነው የሚጀምረው፡፡ ያኔ ተማሪዎች ትምህርቱ ከባድ ነው ስለተባሉ ስለትመምህርቱ መክበድና ሊመጣ ስለሚችለው የውጤት መበላሸት እንጅ ስለትምህርቱም መምህሩ ስለፈራው ውጤትም አደለም፡፡ በዚህም አስተማሪው ስነልቦናቸውን ቀድሞ ስለጎዳውና ምንም ለምንም ዝግጁ እነዳይሆኑ አድርጎ በክብደቱ ስለነገራቸው ከከባድ ጥያቄዎች ሲያመልጥ ምስኪን ተማሪዎቹ ጠይቀው የሚገባቸውን ከማጣታቸው በላይ አዳምጠው የሚረዱትን ሳይረዱ በመቅረታቸው ይወድቃሉ፡፡ አስቡ ተማሪዎቹ መምህሩ ከነሱ የተሻለ እንደሆነ ስለሚያውቁ የሚላቸውን ሰሙ፡፡
ታዲያ አሰብ አያስፈልገንም ያለው አካል እነደመምህሩ ህዝቡን ደግሞ እንደ ምስኪን ተማሪዎቹ አድርጋችሁ ውሰዱ፡፡ ተማሪዎቹ መምህራቸው ያላቸውን እንደሰሙ ሁሉ እኛ ምስኪን ኢትዮጵያዊያንም መምህራችን የምንሰማውን ሰማን፡፡ እናም አሰብ ላይ አታስቡ ስንባል የተሸለ አለ እንዴ ብለን ሰማን፡፡
እኔ ግን ጅሎች ነን፡፡ አሃ…አሃሃሃሃሃሃሃ…አለ አቶ ሜቶ ኦባንግ… ለካ እነርሱ እንደልባቸው የሚያዙትን ወታደር መዓት ተማምነው ነው፡፡ እንዴ!! ኤርትራና ሶማሌን ትተህ ይሄ ሲቪል ወታደሩ አልችል ስላለ ማለትም ፖሊስና ልዩ ሃይል አልችል ስላለ ጦርነቱን ትተህ ህዝብህን ውጋ ቢሉት ከመጨረስ ወደኋለ ስለማይል ያንን ተማምነው ነው ለካስ፡፡
ለማንኛውም አሜሪካ ስለእኛ አንድም አታውቅም አውቃም አታውቅም፡፡ እንክት ያለው ይህ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን በቂ ነን ማንም አያስፈልገንም፡፡ ዴቪድ ሽን በአንድ ወቅት ሌላ እንዳላሉ አሁን ደግሞ ሰማችሁትን በአለም ያውም በማይነጥፍ ብዕር ስለእኛና ስለአካላችን ቁራጭ ዘብዝበዋል፡፡
ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው አለ ያገሬ ሰው፡፡ ለማንኛውም የኢህአዴግ ህወአት ወያኔ ማሌሊት አላማና ለምንነት አይገባኝም፡፡ አሁንስ አንዲገባኝም አልፈልግ አቦ!!
ኤኖወይስ በርካታ ግፎች ተፈፅመውብናል ይህ በመሆኑም ሌሎች ወንድሞቻችን ነፃነታችን በሃይል እናስመልሳለን ብለን ጫካ በግተናል ግማሾቻችንም ተስፋ ባለመቁረጥ "በሰላማዊ" መንገድ እየታገልን እንዳለን እናውቃለን ግን ትግላችን ገና እንኳን መታገል መች ተፀነሰና!!!
.
.
.ይቀጥላል፡፡




ዛሬ ባህርዳር አሳቀችኝ አቦ!! አንድ ሚኒስቴር ከየት እንደሆነ ይመጣል ተብሎ ታሰበና መንገዶች ላይ ያሉ ዝንቦችና ወፎች ንቦቹም ሁሉ ከአስፋልቱ ዞር እንዲሉ ታዘው ሁሉም መግቢያና መውጫ አጥተው ቆዩ ከ9፡00 ጀምሮ እኔም አንዷ ካፌ ስር ጠጋ ብየ በሌለ ቤቴ አንደ ሻየን አስሬ አያመላለስኩ ድራማውንና ምን ስለሚመጣ ነው ይህ ሁሉ ንፋስ እንኳን እንዳይነፍስ የተደረገ ብየ እየቋመጥኩ ስጠብቅ ቆየሁኝና አይደርስ የለም ሰዓቱ ደርሶ ወደ አስር ሰዓት አካባቢሁለት ሞተር ባይክ የያዙ ትራፊክ ናቸው የሚል ኮፍያ ያደረጉ ሰማያዊ ለባሽ ፖሊሶች ሞተራቸውን ዕያስጎሩ በአስፋልቱ ላይ ብቻቸውን ሽው ብለው አለፉ፡፡
ከዚያም ከአጠገቤ ኩፍ ካሉት ህፃናት መካከል ያው እንደኔ የሚመጣውን አካል ለማየት ብለን ነው ሰው ይሁን ሰይጣን ወይም መላክ ግን አላወቅንም፡፡ ለማንኛውም ብቻ ግን ህፃናቶቹ
አሁን መጡ ሞተሮቹ አለፉ መጡ እየው መጡ…
ሲባባሉ
ግን ማነው የሚመጣው ብየ ጠየቅኩኝና
ቀስ ብለው በጀሮ ፖሊሱ እንዳይሰማቸው ሆነው
የአፍሪካ ህብረት ነው አሉ
አሉኝ፡፡
ኣሃ…!!
ብየ እኔም ነው እንዴ አልኩና ወንበሬን ንጥቅ አድርጌ ልሄድ ብየ ለምን መቸረሻውን አልከታተልም ብየ ድጋሚ ሻይ አዘዝኩ፡፡ እና ሻይ ጠጭ ሳይሆን እንደሻይ ማሽን እየተንተከተክኩ… የሚሆነውን እከታተላለው፡፡
ሲቪል ለባሽ ደህንነትና ህዝብ አሸባሪዎችም ከዚም ከዛም ይላሉ፡፡ ምናለፋችሁ ለህዝቡ እንዳይነቀሳቀስ ሲታገድና ዝም ብሎ እንዲቆም ሲደረግ አሁን አባቶቻችንና እናቶቻችን ለወደቁለት ለአንድነት ምልክቷ ሰንደቃችን እንዲህ ህዝቡ እንዲቆምና ብሄራዊ መዝሙራችን ይህ ሳይሆን ዋናው ብሄራዊ መዝሙራችን ተዘምሮ እስኪያልቅ ሰንደቃችን ወደ ክብር ቦታው አስኪወጣ እንድቆም ቢያስገድዱን አይሻልም ነበር ብየ አሰብኩና ምንም ላላመጣ ብየ ተውኩት፡፡
ፖሊሶቹ በራዲዮን ያውካካሉ ሃምሳ አርባ 15 ምናምን ይባባላሉ፡፡ አቤት አቤት አለው፡፡ 50 አለው፡፡ ምናምን ይባባላሉ፡፡
አሁን ማንም ዝር እንዳይል ሁሉን ከእግረኛ ምንገድ አስወጡት፡፡ አንድም ሰው ምንገድ ላይ እንዳይንቀሳቀስ፡፡ መንግስት ሰራተኞች ወደ መንገድ እንዳይወጡ ምናምን…
ይላል ከወዲያኛው የስልክ ራዲዮ መገናኛ የሚያዝዘው፡፡
ወዲያውኑም ሁሉም ባለበት ወደ ኋላ እንዲሸሽ ታዘዘ ሁሉም ሰው ወደ ኋላ ተመለሰ፡፡ መንገዷ ፀጥ ረጭ አለች ወፍም ዝንብም ፖሊስ የሚያበሽቅ ነፋስም አልነፍስ አለ፡፡ በርካታዎቹ ሲቪል ለባሾች መገናኛቸውን ወጣ ገባ እያደረጉ በጎን በኋላና በፊታችን በተለይ በየሽንጉሪቱ ይንሻፈፋሉ፡፡ ኮተት ቀስ እያሉ የማይታዩ እየመሰላቸው እንደሆነ አላውቅም ጠጋ ብለው አንዱ ጥግ ላይ ስልክ ያወራሉ፡፡
360 ድግሪ አንገታቸውን እያሽከረከሩ ያማትራሉ፡፡ ይመለከታሉ፡፡
አይ ይህ ሰው የሚበላው ሲያጣ አሁን አንድ አፍሪካዊ መሪ ይገድላል ብለው ነው የሚፈሩ ይህን ምስኪን ህዝብ የሚያንገላቱት!! እኔ ይገርመኛል፡፡ ለማንኛውም ድራማው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከፊት ለፊት በርካታ ፖሊሶች ክላሻቸውን ወድረው በፊታቸው ያለው ህንፃ ጋር ተፋጥጠዋል፡፡ ምን እንደሚያዩ ምን እንደሚጠብቁም ምንም የሚያውቁ አይመስሉም፡፡
እኔም ግራ ገባኝና
ፊት ለለፊቴ በጎኔ በሁሉም አቅጣጫ ያለውን ህንጻ መቃኘት ገባሁ፡፡ ምን ትዝ ብሎኝ መሰላችሁ ፕሬዘዳንት ኬኔዲን የገደላቸው ሰው በኮንስፓይሬሲ ቲወሪስቶች ሲተነተን ከየት ሆኖ በጀርባቸው እንደበሳቸውና ሾፌሩንም እርሳቸውንም በአንድ ጥይት እንደገደላቸው ትዝ ብሎኝ፡፡ ምናልባት ብሬን ወደረ ይመጣሉ የተባሉትን ስዎች ሊገድል የተዘጋጄ ይኖር ይሆን እስቲ ቢያጋጥመኝ ብየ መነፅሬን ግጥም አድርጌ እፈልግ ጀመር፡፡ ወይ ኩቲ ጠላታችሁ ይሙትና ምንም ዝር የሚል የለም፡፡
እንዴ አልኩኝ
ለራሴ፡፡ እንዴ የአሜሪካን ፊልም አምጥቼ እዚህ ሸለምኳቸው አይይይይይይ… ብየ ዝም አልኩና የሚሆነውን እንደገና ወደፖሊሶች ዞር ዞር ብየ አየሁ፡፡ ግን በርካታ ፖሊሶች አይናቸውን ወደ እኔ ሲወረውሩ እንደመፍራት እንደመፍራት አልኩኝ መለስ ሲሉ ደስ ይለኝና እንደገና ሲያዩኝ እፈራለው አሸባሪ ነው ብለው ቢያስሩኝስ ቢደበድቡኝስ ኣረረረረረ… በቃ አርፌ ወደ ቤቴ ለምን አልሄድም ስል እንደገና ተሟሟቀና ፖሊሶቹ በተጠንቀቅ ቆሙ፡፡
ከርቀት የአምቡላንስ ድምፅ ሰማሁ፡፡ መጡ ስል እነዛ እየበረሩ ሄዱት የትራፊክ ፖሊስ ይሁኑ ቦለቲካ ቦሊሶች ሲከንፉ መጡ በእውነቱ የሁለቱ ቦሊሶች አነዳድ ያስደምማል፡፡ ጎበዝ ሞተር ጋላቢዎች ናቸው እየተወዳደሩ ያሉ ነው የሚመስሉት፡፡ እኔ እቀድም እኔ እቀድም ያበሩታል፡፡
ሲቀጥልም ሁለት ፒክ አፕ ጂፖች ተከተሉ ከዚያም አንድ ስትራይፕ ያለው ላንድ ክሩዘር ተከተለ፡፡ ቀስ ብየ አጮልቄ ሳይ ላንድ ክሩዘሩ ውሰጥ አንድ ሱፉን ግጥም አድርጎ የለበሰ ሰው አለ፡፡ መኪኖች ከኋላ ዕየተከተሉት ከነፉ፡፡
ከዚያም ፖሊሶች ሁሉም መንቀሳቀስ እንዲጀምር መመሪያ ሰጡ፡፡ ከዚያም ምንድን ነው ያለፈው ብየ ስጠይቅ አንድ ሚኒስቴር ነው ብለውኝ እርፍ፡፡
እኔም አይ ኢትዮጵያ ሃገሬ ብየ አዘንኩ እባካችሁ አስተዛዝኑኝ!!



እኔ የሚገርመኝ ለምንድን ነው አይናችሁንም ሸፍኑ አላየሁም በሉ ብለው የሚያስገድዱን ጌትነት አልማው ተብየ የሃገሩ ምንነት የማይቆጨው ሃገሩ ምን እየሆነች እንዳለ ሳይሰማው መንግስት ምንም አይነት መሬት ለሱዳን አልሰጠም በማለት በሚከተለው መልክ ፅሁፌ ነው ያለውን ባልገባው መልክ አስቀምቷል፡፡
እግዚያብሄር ያሳያችሁ ባጋጣሚ ይህ ጉዳይ ሲፈፀም እኔ ሁመራ አካባቢ ሰንብቻለው ለራሴ ጉዳይ ማስረጃ የምለውን ማለትም ከዛ እንደነበርኩኝና ሁሉንም ጉዳይ ማሳየት ብችል ደስ ባለኝ ነገር ግን አስፈላጊ ሲሆን እና አደጋ በሌለው መልክ ልለጥፈው እንደምችል ተስፋ አደርጋለው፡፡
ለማንኛውም ጉዳዩ ሆኗል አሁን መንግስት ባለፈው ፅሁፌ ላይ እንዳሰፈርኩት ሱዳንም ትንሽ ወደ ኋላ ማለቷ ሲጀምርና የቆየ ክህደቷን ማጉረምረም ስትጀምር መንግስት ከሁለት አንድ ያጣው መሆን አልፈልግም ብሎ በማሰብ የመሬቱ ጉዳይ በቀጥታ ወደ ዲማርከኬሽን ከምገባ ይዋል ይደር ብሎ እንደያዘው እዛው አካባቢ ባሉና ስልጣን ላይ በሚገኙ ምንጮቻችን የሚረዋወጥ ጉዳይ ነው፡፡
ይህን ያየና የሰማ ማመንም አለማመንም ይችላል እኛ ግን አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት ከራሳችን ብቻ መረጃውን የምናወጣ ይሖናል፡፡ ለማንኛውም እባካችሁን ይህ የባንዳነት ታሪካችሁን ተውና ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ ባይ ነን፡፡
ይህን ማስተባበያ ከየትም ማዥጎድጎዳችሁ ምናልባት ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማደናቀፍ አስባችሁና እንደለመዳችሁት ቦይኮት ለማድረግ መሆን ስላልጠፋን አርፋችሁ ተቀመጡ፡፡ ዳር ድንበርን አስከብሮ መኖር ለጎነደር ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ጉዳይ አደልም፡፡
አቶ አያሌው ጎበዜ ሰጡት የተባለው ምላሽና የህዝብን ጥያቄ ከማድበስበስ አልፎም የህዝቡን ክብር የሚነካው ፅሁፍ እርሳቸው ለመናገራቸው ምንም ማስረጃም መረጃም የላችሁም እየቆራረጣችሁ የምታመጡት ነገር ለሁላችንም ህዝብን ማደናገር ስለማይጠቅም ብታስቡበት ይሻላል፡፡ አቶ አያሌው ምንም ይበል ምንም ግን ይህ ዳር ድንበራችን መነካት የለበትም ነው፡፡ እንዴ አልሰማህም እንዴ ራሱ ደህንነቶችን በስብሰባ ሲመራ የነበረው ባለስልጣንና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ እኮ …ይህ መሬት የእኛ ስላልሆነ እና የኛ ስዎች ማለትም ገበሬዎች ከመቶ ዓመት በላይ ይዘውት ስለቆዩ የእነርሱ መሰሏቸው እንጅ መሬቱ የእኛ አደለም…ነው ያለው፡፡ታዲያ ይሕ ምን ማለት ነው ላንተ እባክህ፡፡
ለማንኛውም ማንም ምንመ አለ ምን ጉዳያችን አደለም ዋናው ጉዳይ ይህ ጉዳይ መቆም ካልቻለ ችግር ይፈጠራል ነው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለው፡፡ ወዳጄ ስንቱን እንታገል ስንቱን እንጣል ኣረ ተው ይህ ቀን ያልፍና የፍርድ ቀን ሲመጣ እናንተ ተበቃዮች ብላችሁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስም ማውጣት እንዳትጀምሩ፡፡
ቆይ ግን ሃገር ለእናንተና ለመሰሎቻችሁ ምን ማለት ናት፡፡ እስቲ በእናታችሁ መልሱልኝ ምን ማለት ናት፡፡
ይሄውልህ ወዳጄ ከእኩይ ተግባርህና የኢትዮጵያን ህዝብን ማጭበርበር ምንም አይጠቅመንም፡፡ ይህች ሃገር ያንተም መሰለችን፡፡ ገና ለገና የምለው በሚያምኑኝ ይታመን ብለህ የምትፅፈው ምናልባትም አደጋ ስለሚኖረው ቢቀርብህ የተሸለ ነው የሚሆነው፡፡
የባንዳ ሃገራችን ውስጥ መኖርም ምንም አዲስ ጉድ አደለም የኖረ የቆ ነው፡፡ ከስንዴ መሃል እንክርዳድ አይታጣምና ያንተ ምንም ማለት አያስከፋንም ግን ሃገራችን ኢትዮጵያን አስከፍተሃል ህዝባችን ደፍረሃል፡፡ ኢትዮጵያ ስንቱን ጉድ ይዘዋለች ስዎች፡፡ ለማንኛውም በቀጣይ ላንተ ብቻ መልሴ እንገናኝ፡፡
እስቲ የጌትነት አልማውን ማደናገሪያ ፅሁፍ ምላሽ ስጡበት እንደሚከተለው ይላል ተቆራርጦ ከቀረበው ማስረጃም መረጃም መሆን የማይችል ማጣቀሻ ጋር፡፡ የጌትነት አልማው ግለሰባዊ ማነነት የምትፈልጉ ሁሉ ፎቶው ግርጌ ላይ የምታዩት ሰው ነው፡፡ ወደ ታች በእንግሊዝኛ ተፅፈው የምታዩዋቸው ደግሞ የተደናገሩና ትክክለኛ ምላሽ የሆኑ ኮሜንቶቹ ናቸው፡፡



? ኢህአዴጋዊያን በክህደት ዓለም አቶ አያሌው ጎበዜ ምን ነካቸው ለተራ ፖለቲካዊ ጥቅማጥቅም አድር ባይነታቸውን አረጋገጡልን አቦ በእውን ከመንገስት ጋር ላለመጋጨት ሲባልና ፖለቲካዊ መደብተኝነትን ለመጠበቅ ሲባል የህዝብን ጥያቄና ህጋዊ ማንነት ምላሽ በተዛባ መልኩ መመለስና መካድ ምን ይሉታል፡፡
አቶ አያሌው የአማራ ክልል ህዝብ ለትግራይ ኦን ላይን የሰጡት ቃለምልልስ ሁሉንም ሰምተነዋል፡፡ ቆይ ግን እኛ አማራዎች አደለንም እንዴ ስለእኛ እያወሩ እኛን የሚዋሹን፤ ኣረ ተው የህዝብ የማይነጥፈው ፍቅርና መውደድ ክብር ያሻለወታል፡፡ እህ እኔ እኮ የሚገርመኝ አቶ ታምራት ላይኔም ተመሳሳይ ክህደት ፈፅመዋል፡፡ እባክዎትን የህዝብ ፍቅር ይሻለወታል አሁንም ጊዜ አለዎት!!!
ምነው አቶ አያሌው የደህንነት ባለስልጣኑ ምን እንዳለ አልሰሙም እንዴ ልድገምላቸዋ…ያ ቦታ የሱዳን መሬት ሆኖ እያለ ከ100 ዓመታት በፊት የኛ ገበሬዎች ሰፍረውበት የቆዩ በመሆኑ እና ይህ መቆየታቸውም ቦታው የራሳቸው እንደሆነ አድርገው እንዲወስዱ አድርጓቸዋል፡፡ ችግሩ ይህ ነው!!! እንጅ መሬቱ የእነርሱ ነው ብሏል እኮ ስዎች ምነው!! አምታቱንስ፡፡
በርግጥ ይገባናል በርግጥ ካሉት ሁሉ አንድ የገባንና በትክክልም አውነቱን የተናገሩት ምኑ ላይ ነው መሰላችሁ …ጉዳዩ አንኳን ተፈፅሟል ብንል የአማራው ክልል በዚህ ጉዳይ አይመለከተውም ይህን የሚመለከተው የፌደራሉ መንግስት ነው…ነገር ግን ይህ ጉዳይ ላይ ማንም ጥያቄ አንስቶ አያውቅም ማንም ለመወያያም ለመከራከርም አንስቶት አያውቅም፡፡ ይህን ጥያቄ ለመመለስ አጋጣሚውን ማግኜቴ ደስ ይለኛል…አሁን የኔን ከአማራ ክልልነት መነሳት…በአመራሩ መካከል መከፋፈል ስላለ ነው የተባለው ትክክል አደለም…አንዳንዶችም ከሱዳኑ ጥያቄ ጋር ያገናኙታል…የአማራው ክልል ያገባው ይመስል…የፌደራል ጉዳይ እንዳልሆነ ሁሉ…የኢትዮጵያን መሬት አሳልፎ ለመስጠት አንድም ሃሳብ ተነስቶ አያውቅም…የተሰጠ መሬት የለም ቢኖር እንኳን ቋራና መተማን የምናውቀው ጉዳይ ነው…ካቢኔን መከፋፈል ነውር ነው…ይህንን የሚያስተጋቡት ህ/ሰቡ ቆጭቶት ሊነሳ ይጭላል፡፡ የብአዴንን አካላት ለመከፋፈል የተነሳ ፀረሰላም ሃይል ነው፡፡…ህዝቡ ግን ትግስተኛ ነው፡፡ መሬት አሳልፎ የሰጠ የለም…አልሰጥም ብሎ ተከራክሮ ሳይስማማ የተለየ አካልም የለም፡፡…
ብለዋል የወትሮው የአማራ ክልል ፕሬዘዳንቱ
እስቲ ያሏቸውን ቃላት አውጥተን እንተንትናቸው፡፡
መጀመሪያ እንህ ሰው የሚታወቁበት ባህሪያቸው ቢኖር በአንድ ቃል ሁለቴ ሁለት መልዕክት መናገር ችሎታቸውን አስመስክረዋል፡፡ ዋናው ግን ይህ መሬት መስጠት ውስጥ ሁለት የሚጋጩ ቃላትን በሚስጥራዊ አገላለፅ ተናግረዋል፡፡ እስቲ ምን አሉ፡፡ እንይ፡፡
መጀመሪያ ሲናገሩ ቆይተው ምን አሉ…
ይህን ጥያቄ ለመመለስ አጋጣመውን ማግኘቴ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡ አሉ
ይህ በትክክልም መቼም ቢሆን በላይኛው ክፍል ላይ ቁጭታቸውን ለመግለፅ የፈለጉ ይመስላሉ፡፡ ምክንያም ከአሁን በፊት በርካታ ኢንተርቪዎችን አድርገዋል፡፡ ለምን በዚህ ሰዓት እጅግ ደስተኛ ሆኑ? ለምን ከአሁን በፊት በርካታ ሚዲያዎች ለመጠየቅ ሲደውሉላቸው ምላሽ ለመስጠት አልጣሩም ለምን ይህንን ጉዳይ ለመመለስ እንደሚቸገሩ ሲናገሩ ቆዩ? 
ከዚያም የሚቀጥለውን ንግግራቸውን እንስማ
…ይህን የድንበር ማካለል ዙሪያ እንደ ሃሳብ ለክርክርም ለውይይትም በመካከላችን ተነስቶ አያውቅም…አንድም ቀን በመካከላችን አለመስማማትን ፈጥሮ አያውቅም…አንደኛው ተስማምቶ ሌላኛው ሳይስማማ በልዩነት ተለያይተን አናውቅም…ይህ ጉዳይ አልሆነም፡፡ ሆኗል ብንል እንኳን ይህ ጉዳይ የሚመለከተው የፌደራሉ መንግስት እንጅ የአማራ ክልል አደለም፡፡
ይህን ሲሉ ምን ማለት ነው ሃላፊነታቸውን መሸሻቸው አይመስልም ወይ? ምክንያቱም በአንድ በኩል ከመንገስት የሚደርስባቸውን መዋከብና የሚከተለውን ሲያስቡት ቅድሚያ ጉዳዩ እንዳልተፈፀ መ በመናገር ራሳቸውን ነፃ ማስመሰል ቢሞክሩም እና ቢሆኑም እንኳን ቅሉ እርሳቸው ግን ይህ ጉዳይ ቢፈፀም እንኳን ይህ ፌደራል መንግስቱ እንዳደረገው የአማራው ክልል ምንም እንደማይመለከተው መግለፃቸው ነው፡፡
መቼም ይህ አነጋገር ለአማርኛ ተናጋሪው ብቻ ሳይሖን ለየትኛውም አማርኛን መስማት የሚችል ሰው ምንም የሚከብደው ፈሊጥ አደለም፡፡ ከዚያም ይቀጥሉና ይሕ ጉዳይ ማለትም ድንበር ማካለሉ በፌደራል መንገስት ብቻ ነው የሚታየው አሉና ይህ ጉዳይ ተፈፀመ ብንል እንኳን የአማራ ክልል አይመለከተውም፡፡ አሉ ታዲያ ይሕ ጉዳዩ ተፈፅሟል ግን እኔ የለውበትም ማለታቸው አደለም ወይ ስዎች፡፡
አንድ ነገር አንሸወድ ለስንት ዘመን ሚዲያዎች ላይ የሚወጡ ብሄራዊ ጉዳዮች ውሸት ናቸው ይህ የፀረ-ሰላም ሃይሎች ሴራ ነው ምናምን የአፍራሽ ሃይላት አንድ የትግል አጀንዳ ነው፡፡ የተቃራኒ ርዕዮት ተከታዮች ተንኮል ነው፡፡ ይህ አሸባሪዎች ተልዕኮ ነው ምናምን እየተባልን ስንቴ ተዋሸን ራሱ ውሸታም ራሱ ውሸታም ባይ ራሱ አሸባሪ ሆኖ እያለ እኛን አሸባሪ ራሱ ፀረ ሰላምና ፀረ ሃገራዊ አጀንዳና ተልዕኮ ይዞ እያለ ራሱ ፀረ አንድነትና ብሄራዊነት አቋም ይዞ እያለ ሁሌም ተመሳሳይ ብሄራዊ ጥያቄዎች በሚነሱበት ሰዓት ይህን ተለጣፊ ታርጋ ዕየሸለመ ሲያሸማቅቀን መቆየቱ አሁንም አቶ አያሌው ላይ ደርሶ ሲቀላቅሉ አየናቸው እንጅ ምንም አዲስ ነገር አደለም፡፡
ክህደት ከወያኔ ኢህአዴግ እንኳን ለእኛ ለራሳቸው አፈር በጥብጠው አንድ ባሩድ አሽተውና ታጥነው በአንድ ማዕድ ቀርበው በአንድ መደብ ተኝተው አንድ ጫማና ቁምጣ አድርገው ለታገሉት ጓዶቻቸውምም አይሰጎድ፡፡
ለማነኛውም አቶ አያሌው በምንም መንገድ ቢሆን አሁንም ግልፅ መረጃ አስቀምጠዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ከሆነ እንኳን ፌደራል መንግስትን ነው የሚመለከተው ብለዋል፡፡ ሲቀጥሉም ደግሞ …አንድም የብአዴን አመራር ይህ ጉዳይ አንደ ሃሳብ እንደ መወያያ አጀንዳ እንደ መከራከሪያም ተይዞ ሳይስማሙ የተለያዩበት ጊዜ የለም ብለዋል፡፡
እንዴ ይሕ ታዲያ ምን ማለት ነው?
ሳንስማማ ተለያይተን አናውቅም ማለት አንድም ኢህአዴግ ወያኔ በሚፈለገው መልክ ሲተረጎም አንስተነው ጉዳዩን እንኳን አናውቅም ማለት ሲሆን በትክክለኛውና በሆነው መንገድ ደግሞ መሬቱን ለመስጠት ማለትም ለሱዳን ለመስጠት ሃሳቡ እንደ አጀንዳ እንደ መወያያ እንደ መከራከሪያ ተይዞ ሳንስማማ ቀርተን አናውቅም ተለያየተንም አናውቅም፡፡
ነው ያሉት እንግዲህ ይህ ሁለተኛውን ማለትም ሁላችንም በአንድ ድምፅ ተስማምተን ተግባብተን የወሰንነው ነው የሚለው አንድም ፌደራል መንግስቱ ነው እንጅ እኛ አይመለከተንም ከሚለው ጋር የሚጋጭ ሲሆን በአጠቃላይ ግን መሬቱን ለመስጠት በርካታ ጊዜ ተነስቶ ሁሉንም በመስማማት እንደተለያዩ ነው የሚናገሩት፡፡ በፊት ደግሞ ፌደራል መንግስቱ እንጅ የክልል መንግስቱ አያገባውም ሲሉ የሚጋጭ ሃሳብ ያቀርባሉ ይሕም አንድም የአነጋገር ብስለታቸውንና አሁንም እውነታን መሸሸግ እንዳልፈለጉ ነገር ግን ለግላዊ ህይወታቸው ማለትም ከመንግስት ሊመጣባቸው የሚችለውን በመፍራት ብቻ የጠናገሩት ግን ለፈሊጥ ፈላጩ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን መሬቱን ለመስጠት ያልነዳች ችግር ተስማምተን ወስነናል፡፡ ውይይትና ክርክራችን ጨርሰናል ማለት ነው፡፡
ከዚያ በተረፈ ይህ ድንበር ማካለል ሲሉ ያቀለሉት የመሬት ሽያጭ ወይም ድንበር ቆረሳ እና ዝርፊያ ለሱዳን መንግስት ለየትኛው ተግባሩ ሽልማትም ይሁን መሰጠቱን ያለው የሚዲያ ማስረጃዎች በቂ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የመንግስት ስዎች እንዳሉት ሳይሆን
1.      ሱዳን ትሪቢየን ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ለበርካታ ጊዜ ምላሽ ያላገኘው የመሬት ይገባኛል ጥያቄያችን ለበርካታ ዘመናት ሳይፈፀም ቢቆይም በህወሃት ወያኔ ተፈፀመ ገበሬዎቻችንም ደቡብ ምስራቃዊ ለም መሬታቸውን እጃቸው አስገቡ ሲሉ
2.     ከዚያም ይህን ቦታ በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች ለመጠበቅ ሲጥሩ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችና ገበሬዎች ከባድ ምላሽ እንደተሰጣቸው ገበሬውም ትንሽ እንዳስቸገራቸው የድንበር መካለሉም ስራ በቅርቡ እንደሚፈፀም ዘግበዋል ከአንድም ሁለት ሶስቴ
3.     በርካታ ሚዲያዎችም ከባለስልጣናት ድብቅና ሚስጥራዊ ምንጮቻቸውን በመጥቀስ ይህ ሱዳን መሬቱን እንዳገኘች መሬቱም 1600 ኪ.ሜትር ርዝማኔ ከ35-45 ኪ.ሜትር ወደ መሃል ሃገር እንደሚገባ ይህም ሸኸዲንም ወይም ግንደወይንንም እንደሚጨምር ገለፁ፡፡
4.     በርካታ ተቃዋሚ ሃይሎች አገር ውስጥም ያሉ ውጭ በየሚዲያዎቻቸው ይህን ሚስጥር አወጡ፡፡
5.     ኢሳትም መረጃውን ሲያወጣ ቆየ
6.     በመጨረሻም ራሱ የደህንነት ባለስልጣኑና የጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማካሪ ይሕ በስህተት ከ100 ዓመት በፊት ይዘንባቸው የቆየነው መሬት እንደሆነና በነገ ነገ ጊዜው እየተራዘመ የዘገየ ስራ እንደሆነና ሱዳኖችም ማግኘታቸው እንደማይቀር ገለፁ፤
ታዲያ ቢያንስ የተለያየ ጉዳይ በተለያዩ ስዎች በመዘባረቅ ተቃዋሚዎች ወይስ መንገሰስትና ስዎቹ የዋሹት? ኦኬ መንግስት ከዋሼ መሬቱ ተሰጥቷል ወይስ አልተሰጠም፡፡ ምናልባት ድጋሚ ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ባሳየችው ቸልተኝነት ምክንያት መንግስት በመበሳጨትና ሶስቱም ሱዳን ግብፅና ኢትዮጵያ ሳይስማሙ ካርቱም ላይ መለያየታቸው ለኢትዮጵያ ራስ ምታት ስለሆነባት ሱዳን ደግሞ የግብፅ ጉዳይ ስጋን ቢያሙ ይገሙ ሆኖባት የመጣ መቃቃር ይሆን ይህን ያህል የሰጡትን መሬት መልሶ ለመቀማት አልሰጠንም አይናችን በጨው የሚሉት?
ወይስ ሰማያዊ ፓርቲ ጎንደር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ለጊዜውም ቢሆን ተረባርበን ሰው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይሄድ እናድርገውና ከዚያ በኋላ የምናደርገውን እናውቃል ለማለት፡፡ ለእኔ ግን ሁሉም ጅልነቶች ናቸው፡፡ ውድ የኢትዮጵያ መንገስት የታጠቁ የኢትዮጵያ ሃይሎች በሱዳን ድርሽ እንዳይሉ ብለህ ዳር ድንበራች እስካባቶቻችን ደረቅ ደምና አፅም ድረስ ከምትሰጥብን ሁሉም ጥንቅር ይበልብን እኛ ጋር ተስማምተህ የምንፈልገውን አድርገህ መብታችን አክብረህ መሬታችን አክብረህ አንድነታችን አክብረህ ብሄራዊ ጥቅማችን አስጠብቀህ ኢትዮጵያችንን አንድ አድርግልንና እኛ ድርሽ አናደርጋቸውም ነገር ግን ይህን ባታደርግ እድሜ ለህዝባችን እድሜ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ እነርሱስ ለሃገራችን ሁለንተናዊ አንድነትና ብሄራዊ ጥቅም ስለብሄራዊ ሉዓላዊነታችን እስከቆሙ ድረስ እንንከባከባቸዋለን፡፡
የሱዳን መንገስት ምንም ሊያደርግላቸው አይችልም፡፡ በነገራችን ላይ እኔ የዚህ ፀሃፊ ሐቴርሳታ ነህምያ እባላለው ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ፅሁፎች ሳወጣ ቅርብ ጊዜየ ነው፡፡ ደጋፊያችሁ እንኳን ሆኜ አላውቅም ይልቅ እናንተን በመርሳት ስትራቴጅ ተቃዋሚዎችን ደግሞ አንድነትና ውህደት ፈጥረው መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ለጎሪጥ ሳይ ቆይቼ ሌላ እናነተ የተወለዳችሁበት መስመር ሳያዋጣ አይቀርም ብየ የምቀጥል በስራችሁ ሁሉ ቸጓራየ ደህና ቢሆንም በእግዚያብሄር ቸርነት ትክን ብየ የኖርኩ ልጃችሁና የአንድ ያለፐርፐዝ ተማሪዎችን ከሚያስተምረው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አስተማሪ ነኝ፡፡
ለማንኛውም ከአሁን በኋለ ይህን አይነትና ማንኛውም ፖለቲካዊ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ባህላዊ ታሪካዊ እና መደባዊ ብሄራዊ ሉዓላዊነትን ጥቅምን የሚነኩ ጉዳዮች ላይ ምላሽ ስሰጥ ብቻ ነው የምታገኙኝ
ቻው
ጉዳሞች


…ዛሬ አንድ ጉዳይ ላይ እንፋጠጣለን፡፡ መጀመሪያ እኔ የሙያው ሰው ባለመሆኔ ምን ልትሉ እንደምትችሉ ምንም ግንዛቤ የለኝም ሆኖም ግን እነደ ግለሰብ እንደ አላዋቂም እንደ ፈዳላም እንደ ስራ አጥም እንደ ተቃዋሚም እንደ ሰላማዊ ታጋይም እንደ ታጠቀ ሃይልም እንደ ካቢኔም እንድምንም ማየት ትችላላችሁ ይህች ሃገር ሁላችንም እትብታችን ከመቀበር አልፎ ህይወታችን እስከ ዘር ማንዝራችን ድረስ የተነሳና የወደቀባት፡፡
አጥንትና ደማቸው የተበተነባት፤ ስለአንድነት ስለ አብሮ መኖር፤ ስለ መቻቻል በልዩነታችን ፍቅርና መተሳሰባችን አድምቆን ማንም ሳይመራን ማንም ሳያሳየን ራሳችን ሆነን የኖርን፤ አንገታችን ሳንደፋ ሳናፍር ሳንሸማቀቅ ኖርንባት ምድር፤ ታሪክ ባህላችን እምነት ከሃይማኖቶቻችን እንደየራሳችን አንዳንዴም ብቻ ሳይሆን በርካታ ጊዜና ብርቅ በማይሆን ደረጃ አንድ ላይ አምነነን ተጋብተን ወልደን ተዋልደን ተጋብተን ዘፍነን አልቅሰን የኖርንባት፡፡
ልዩነታችን አንድም ቀን ሳናስታውስ አንድም ቀን ጥቁር አሻራውን ሳይቀባን ሳያሳርፍብን በኛ ጥኝካሬ ብቻ ሳይሖን በፈጣሪ ተዓምር በእምነቶቻችን አስተምህሮቶች አንድም ቀን የከፋ ጉዳት ሳይደርስብን ብቻ ሳይሖን አብሮነታችን ላይ አደጋ አምጥቶ ሳይለያየን ስንኖር ይሄው በርካታ መቶ ቸመታትን አሳለፍን፡፡
ነገር ግን ይህ ሲባል ማን ምን አደረገ ማንም መልካም ሰራ ማን ምን መጥፎ ታሪክ ቁርሾና ጣላቻን አፈራ በመካከላችን ለሚለው እድሜ ለሚዲያው ቴክኖሎጅ መራቀቅ እንጅ ነጋ ጠባ በየሰኮንዱ ማረጋገጥ እንችላልን እውነታውን መረዳት መገንዘብ ማብላላትና መተርጎም አስችሎናል፡፡ ይህ ሁሉ የሚዲያ ጠቀሜታ ግን አንዳንዴ በከንቱ ቡን ብሎ ሲቀር ድካማችሁና ልፋታችሁ ከንቱ ሲሆን ይሰማኛል፡፡
አንድ አባባል መሳይ ተረት አለ ኢትዮጵያ ውስጥ
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
አንድ አዝማሪ ነው አሉ ረዘም ያለ መንገድ ለመሄድ አስቦ ማለድ ብሎ ሌሊቱ የአህያ ሆድ ሲመስል ይነሳና ደሮ ደጋግሞ ሲጮህ የነቃው አዝማሪ መሰንቆውን ይዞ ካሰበበት ቦታ ቀድሞ ለመድረስ እያንሰላሰለ ጉዞውን ይጀምራል፡፡ ይህ አዝማሪ ጉዞ አዲሱ ባይሆንምና በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በሰዓታት በመጓዝ ስራውን የሚሰራ ቢሆንም ማታ ላይ ትንሽ ደከም ብሎት በማረፉ፡፡ ድካም ድካም ከማለቱም በላይ ጉልበቱ ፍርክክ ፍርክክ ብሎበታል፡፤
ለማንኛውም ጉዞውን ጀመረና ከሰዓታት ጉዞ በኋላ አንድ ዛፍ ስር አረፍ ብሎ ስንቁን ሲበላላ ቆይቶ እንደገና ጉዞውን ሲጀምር አንድ ትልቅ ወንዝ ይደርሳል ሰማዩ ዳምኗል፡፡ በዚያ ላይ ጀሮ ከራስ የሚነጥቅ ነፋስ ይነፍሳል፡፡ ኩንንቡን እስከ አይኑ አጨልሞ ብርዱን ለመካላከል ይሞክራል ማሲንቆውን አንቆ ይዟል፡፡
ዳመናው እየጠቆረ በመምጣቱ ወንዙን ቀድሞ መሻገር እንዳለበት ስለሚያውቅ ቸኮል ቸኮል እያለ ይሄዳል በድንገት ግን አንድ ሰው ከርቀት አይቶት የነበረ ሰው እርሱ ወደ ሚሄድበት አቅጣጫ ሲመጣ ያየው አሁን በምን ያህል ፍጥነት እንደደረሰበት ባያውቅም አጠገቡ ደረሰና
…ጌታው እንደምን አረፈድህ…
ሲል ይጠይቀዋል እርሱም
…እግዚያብሄር ይመስገን ደህና ነኝ…፤አንተው መንገድ ቀንቶሃልስ እንዴት ደረስክብኝ…
ሲል ጠየቀው ያኛውም
…እኔ የምሄደው ዳስ ልጥል ነው…አንተ ግን ለዝላይ ነው፡፡
ይለዋል፡፡
…እንዴ ኣረ ዝላዩንስ ባለቤትህ ትዝለለው እነዲያው እኔስ ለስራ ነው…
ብሎ በነገር ሲሸነቁጠው አዝማሪ ሆየም የዋዛ አደለችምና እርሷም ሸንቆጥ አደረገችው፡፡
…ኣረረረረረ!!! ሊቀመኳስ እርስዎ ነዎት እንዴ…እርስዎስ ያደርጋሉ…
ይለዋል፡፡ አዝማሪም
አዎ እኔው ነኝ አሁን መዝለል ትቼ ማዘለል ሆኗል ስራየ…
አለ አዝማሪው፡፡
ኣረ መልካም ነው፡፡ አለ ያኛው
ከዚያም ሁለቱም እየተሸነቋቆጡ ጉዟቸውን ሲቀጥሉ በጨዋታ መሃል ሆነና የጠቋቆረው ዝናብ ከበድ እያለ ከወደ ግራቸው በስሜን በኩል እየከበደ ሲመጣ እና ከየትም ያለው እየከበደ እየጠቆረ እየጠቆረ ሲሄድ ልብ ያሉት አይመስሉም ሁለቱም በወሬ ድምቅ ብለው ከወሬ ቅሚያ ወደ ምርቃና ገብተዋል፡፡
ለማንኛውም ወንዙ ላይ ደረሱ፡፡ ወነወዙ ትንሽ ሃይለኛ ቢጤ ነው፡፡ ምንጩ ከተራራ ስለነበር በደራሽ ጎርፍ የታወቀና እጅግ ፈጣን በመሆኑ በርካታ ነፍሳትን ቁርጥም አድርጎ በላና የሚበላ ነው፡፡ አዝማሪም
እባክህን ይህ ዝናብ ሽቅብ እየሄደ ነው ትንሽ አረፍ እንበል ይሄው ፀሃይ ገለጠልን እኮ
ይሄ የፀሃይ ካፊያ ነው፡፡
አለ እጁን ከጋቢው ወጣ አድርጎ ካፊያውን በማስመታት፡፡ ስለዚህ ትንሽ እዝች ጋ አረፍ እንበል፡፡ አለ ደግሞ፡፡
ያኛውም ቀና ብሎ ሲያይ ዳመናው ምንም እንኳን ጥቁር ብሎ ቢከብድም ትንሽ የፀሃይ ብልጭታ በማየቱ አመነና
እሽ በቃ እንዳልክ
አለ፡፡
ሁለቱም አርፈው ቁልቁል የሚፈሰውን ወንዝ ገንቡ ላይ ሆነው ይተክዙበታል፤ ያወሩበታል ይሳሳቃሉ፤ ይጫወታሉ ለአንድ ሰዓት ይህል በእረፍት ስም ፈታ ዘና ብለው ከተቀመጡ በኋላ
…ኣረረ ይህ ወንዝ አረፋ መጣበትስ…አንተ ቶ እንሻገር ይህ ወንዝ ሊሞላ ነው፡፡ ኣረ ባክህ አደርን ከሞላ አይጎድልም፡፡ አንተ እየሞላ ነወው፡፡
አለ ያኛው ሰው፡፡
…አዝማሪም ባክህ አደለም፡፡ በምኑ ነው የሚሞላ፡፡ ሽንትህን ሸናህ እንዴ!! ምናልባት ከሸናህ ግን ሊሞላ ይችላል!! ሲል ተሳለቀ፡፡ አዝማሪው፡፡
ኣረ ተው አትቀልድ ይህ ወንዝ እየሞላ ነው፡፡ ይሄው ስብርባሪ እንጨቶችና አይጦች መምጣት ጀምረዋል፡፡ ባክህን ተነስ እንሂድ ብሎ ቢጎትተው ምን ቢል ማሲንቆውን አውጥቶ ይባስ ብሎ ለወንዙ ያቀነቅን ገባ፡፡
ወዲያውኑም የወንዙ ቀለም ቀይ እየሆነ አቧራማ እየሆነ እየደፈረሰ እየደፈረሰ መጣና ከየት መጣ ሳይባል ያኝ የሚያህል ወንዝ እፍ እስከ ገደፉ ሊም ብሎ ሞላ፡፡
ይሄውልሃ አንተ ሊቀሞኳስ ገደልከኝ እኔ አልነጋልኝ ብሎ ያደርኩ ሰው አሁን እዚሁ ታሳድረኝ አይ አንተ ተጫወትክብኝ ሲል
አይ አንተ ታዲያ የሞላ ሁሉ ይጎድል አደል…እንዲያውም እስቲ ትንሽ ላጫውተው አለና ማሲንቆውን አውጥቶ እንዲህ ሲል ገጠመ፡፡
መንገድ መንገድ ለው መንገድ  ያለው እግሬ
ማልዶ ቀደም ብሎ ተነሳና ዛሬ
ለዝላይ ለጭሆት ሲያሰኘው ሃገሬ
ሲኳትን ሲባዝን ወገቤን አስሬ
ደረስኩ ስል አልደርስ
ውሃው ሲያጉረመርም ወንዙ ሲደፈርስ
ይጠራል ጠብቀው እሱን ያልኩት እኔ
ወንዝ ተቆልቋዩን አይ እኔ ማመኔ
ማሲንቆ ወጥሬ  ልዝፈንለት ትንሽ
ወንዙ ተሸቆልቋዩ እንዲያው ወደ መሬት ጥቂት ብትል ግሽሽ
እያለ ብርካታ ግጥሞችን እየደረደረ ቢዘፍን ቢዘልል ቢያንጎራጉርም ሰሚ ጀሮ የሌለው ወንዝም እያጉረመረመ ቁልቁል መወርወሩን አላቆም አለና፡፡ ቅንቀናውን ትቶ
አንተየ እንዲያው ምንድን ነው ክኔው ይህን ያህል እየዘፈንኩለት ልምን ትንሽ እንኳን ጎደል አያውቅም
አለ አዝማሪው፡፡
የማሲንቆው ዜማ አንዴ ሰመመን ውስጥና ሃሳብ ውስጥ ሲገባና ሲወጣ የቆየው መንገደኛ ድንገት ብድግ አለና
አንተ እብድ ነህ እንዴ እንዴት ለወራጅ ውሃ ትዘፍናለህ ቢለው
ተውማ ወንዝ  ወራጅ ቢሆንም ይሰማል፡፡ ሲል መለሰ
እንዴ ይህኛው ቢሰማህ የሰማህ ይሄድና ያልሰማው ይመጣል ታዲያ እንዴት ነው ይህን የምታስታርቀው ይህ ይሰማሃል እንበል ከዚያም እንደሰማህ ይሄዳል ያልሰማው ደግሞ ይመጣል፡፡ እንዲህ እያለ ይቀጥላል አለው ይባላል፡፡
የሚዲያተቋ ማትም እንዲሁ ናቸው፡፡ አንድ ዜና ያመጣሉ፡፡ ያን ዜና እንዳስተላለፉ በዚያ ሰዓት የነበረ ይሰማዋል ወይም ያነበዋል ምናልባትም ማንም ሳያየው የሚያልፍ ዜና ወይመ አዲስ መረጃ ይኖራል ስለዚህ ማንም ሳይሰማው ያልፋል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሚዲያ ተቋማት ይህን ችግር  መፍታት አለባቸው፡፡ መፍትሄ የሚሉትንም ተደራሽ የሚሆኑበትን መንገድ መዘየድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አንድ ዜና በተቻለ መጠን ጫፉ ሳይታወቅ ድራሹ መጥፋት የለበትም…
ይቀጥላል…



How can we live in our country how can we work in our country in my mother land?

This is my question I am just crying when I have been writing this piece. How can we live? Okay let me leave your question but how can I live not allowed to work what I need what God has given me as a talent.
Let me tell you one story friends. It may sadden you or may make you smile if you got me kid!!
The story started before 7 years I were 3rd year economics senior student in one of the universities of Ethiopia which has been used to be called the University of Peace unlike today since you all know as what is happening now.
Anyways, I had good background from lower and other lever classes in my education time. I have good background I used to score higher rank and I grow up from the child care center from Around Gondar then joining the university in 2005. It was time of election of course I had no know how as from which ethnic group I may belong I had been knowing as I only have been an ETHIOPIAN only an Ethiopian.
The only thing that I know were about politics was that while we have been preparatory school student we were lined up before we enter in to the class at the morning and in the afternoon when to back to home and our director always out to the front stage and ORDER the students to sing the AMHARA national ANTHEM.
At that time most of the students if I am not mistaken about 85% of the students refused to sing it and the rest some kept silent including me and others about 5% of the students on that shift sing the AMHARA region anthem.
Whether you believe it or not I didn’t know why some kept quite from singing and why others kept silent; but now I do and some talked as why they refused to talk and our class representative whose name I have forgotten told me one thing. Depending up on the next question of the students. That their next question was as they don’t need to sing the AMHARA region ANTHEM but if the management allow them they can sing the ETHIOPIAN NATIONAL ANTHEM.
WOW HOW genius they have been!!
Then everybody including me knowingly or unknowingly sang the national anthem of ETHIOPIA refusing the regional anthem. But the management were very Angry at us and soon they called the police and those police of the town came and torched us.
And I remember that time even there were some who were shot down. But fortunately we my friends and me escaped and…
Then we became grade 12 and same manner the school management obliged us to sing the regional anthem and we voluntarily or involuntarily we keep singing but most used to keep silent. Nonetheless the continuation of the singing the students have not stopped asking the management and have not stopped fighting with the management. And for the second time it was me from the representatives who were elected to serve as the reflector of the interest of the students to the management. But we be imprisoned. Then else without getting solution we joined universities but those who have not lucky to join failed to get the solution. Even if we too.
Then I be student of one of the universities as I mentioned before. I know nothing about being Amhara, tigre, oromo, somale, hadere, gurage, gumuz, gambela, debub, afar or others what I only know was as we all belong from Ethiopia. Soon thanks to the 2005 election even if it has snatched the life of manys; it created the ground for us to let us know much about politics.
It was at that time that I knew as there are different ethnic groups and as Ethiopia have born lot of children like Amhara, ORomia, afar, tigrie, addis ababa, Somalia, SSNP, gambela, Benshangul gumuz...so now we all got it as this is result and consequence of FEDERALISM…then the 2005 election came in to near and one of my friend who is now university teacher and have gone abroad came to my dormitory and told me as I shall elect KINIJIT and helped me in awaring listening the song of Tedy Afro lambadina, dahlak lay, and others we always send our ear to media specially to VOA and voice of doutche Amharic services and sometimes BBC any ways our ears and eyes toil to find the media which tells about ETHIOPIA/kinijit.
We successfully got the knowhow and we get too near to the election may 7 and we gave our voices to whom we need and 100% voice was given to KINIJIT even those who have been gossiped with to be members and supporters of the government gave their voice to KINIJIT.
Soon by the reason we don’t know the result was told as it is fraud by the government and told as the winner is the government.  The fake victory said to be for the government and all bads continue to happen.
We all were fighting the government and the students killed one inspector by the slice of mirror and guns start to explode and fired to us but I have not seen somebody who died except have heard as there are many students who are raped, who are taken to unknown place and who are killed.
The clash between the students and the government police from ordinary police to the federal, the soldiers from the ordinary to the COMMANDOS, and the Agazzi Special Forces all surround us escalated worsened but the students with WONCHIF and with their hands continued fighting with the firing soldiers sometimes we control the buildings and other time they control for three days we fought.
We stopped learning but heard as we have last two weeks when we started learning while we have not. It was at that time the worsened clash started buildings burnt mirrored windows smashed and broken in to pieces the police entered with special forces commandos and others the torched us.
This was the worst female students were beaten to death I have seen this with my naked eye. Manies were made blind wounded and killed. Same was happening to all universities and towns soon the worst happened in the town the town’s population out and start fighting hand to hand with forces and manies lost their life and were beaten to death.
Nevertheless we lost that opportunity, most of us start to go to the neighboring countries expecting that they will kill us and torch us but time lapsed and we start to calm down and start back learning since we were told to leave the university. We have not eaten for most of the days. but has not hindered us from revolting.
WE LOST IT!!
Okay now let me come to my point which let me to burst in tears.
While I have been studing for my mid exam of microeconomics I got one reference which is titled by the financial economics a book written by one Indian man. In this book I got one fascinating point which is the story of Muhammad YEnus who is well known professor and who is from Bangladesh.
This man now has the international bank called Grameen bank which mainly gives priority to woman. Let me leave the history to you.
Then I took that idea and was highly inspired to implement that idea in to project after graduation and I pick up a pen and wrote it on my daily note book. Saying
                “…this is the business that I need to do in my country in Ethiopia… and the project has to be called ABROSCA first…”
Planning short term and long term dreams and plans.
The time of graduation reached and we did graduate but the idea was always talking to me; I used to read read and read about the issue and developed it in to local idea and  making it completely local I designed its microplan having about 43 different projects and 11 main projects.
From the projects the following were among
1.       IROSCA New Nation Project which will launch a life saving empowerment programme in the in ethiopia
2.       ECX and A”CX, TCX, OCX, as the start up
3.       Feasible local house building which no more than 10000 birr costing
4.       Mobile banking and Shop banking and other 23 different types of sub projects
5.       The short and efficient, least cost way of collecting taxes
6.       JCPG job creating projects for graduates
7.        Crop banking and exchange
8.       SSOE Solution seeking organization establishment project all over Ethiopia
9.       Iqub based projects which mainly concentrates on organizing of Ethiopian poor who are unable to handle day to day expenses
10.   DBCTP data base based and code reading writing translating projects with Different Interlocking projects on different problems of the country about 10
11.   Safety net projects which are about 10 again

Then  I provided to all to the national bank of Ethiopia ministry of trade . Then they told me this is not the project on which they have no power to give license. Then I asked them as who will give me the license above their power. But they insist on not to give me the licence. Mind here guys this beureau if found at ministrial level and all inside are the top experts of the country.
At that time the governor of the NBE was deputed by ato leolseged who latter was accused of bribery and the main governor was also involved in making decision as whether to give the license or not. They tried many ways not to give the licence but they were unable to be successful in stopping us from asking about.
Latter on anyways the gave me a temporary licence by which we can open in a different way and not to work saving matter while the rest gaps are open. Then we started and then we come back home and employed 40 workers then we started our task and unbelievably we got about 3000 potential customers. And from which we have got about 75,000 birr as net profit and we fulfilling office materials. Then escalating our positive success we worked for three years and we soon opened about for branches and asked for upgrading of our project to BANK systems with completely different operational and system of service provisions and with completely different programmes that are not started in our country and in the world too.
But they soon sent from the federal minister offices and came to me where I work and detained me for ten days with not taken to court…
Let me leave this and let me talk about the rest.
Then they took or loot all my office materials computers copy machins, printers money in cash and tthey blocked my bank Account.
The main reason which instigates me to write about is that one project with the same system is started all over Africa and it is Ethiopia which has started the system accepting the branch of that foreign company with completely same system and operational techniiqes.
And what has annoyed me is that all Ethiopian who are on power do not believe by the ablity of ETHIOPIANS than trusting by our ablity and excellence they better need to trust foreign companies. But there are people who assist me for its success.
Thank you!!
ወይደሮ ሚሚ/ሚጡ ስብሃቱ ምነው የኢሳሳሳሳትትትትት ነገር የእግር እሳት ሆነብዎት ቅናት ነው እንዴ!! እስክሰማው ቸኩየ ነበር ከሰማሁሽ በኋላ አፈርኩ ያንች አይነት ብሽቅ የኢትዮጵያን ህዝብ ጀሮ ስታበሰብሽ!!! አረ ጉድ እኮ ነው ቀድሞ ነገር አንድ ሚዲያ ስለሌላው ሚዲያ ማውራቱ ስምማጥፋት ያውም ያሳፍራል እያሉ ማውራት የራስን ክፍትነት ብርግድነት ያሳያል፡፡

አንዳንድ ስዎች የሚናገሩት ስለተባለ ብቻ ነው እንዴ ወይደሮ ሚጡ ስብሃቱ ስለኢሳት ምን አንገበገባቸው ብየ ስለፃፍኩ አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል የምትለዋን ሃረግ ጭምር አደረገና ይህን የምትቃወም ማን ስለሆንክ ነው አንተ አይነት አስተያየት ይፅፋል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ እናንተ የላፕቶፕ ጀግሞች ይሉናል፡፡
ለምን ይሆን የናንተን ያህል ደደብ እንድንሆን የምትጠይቁን ነው የኔ መልስ ደግሞ፡፡ ለኔ ሰውን እንደኔ ካላልክ በኔ መስመር ካልመጣህ ክላሽ መትረየስ እንደኔ ይዘህ ካልመጣህብኝ ጀግና አልልህም የሚል ሁሉ ደደብ ነው፡፡ አኔ እውነቱን የምናገረው ግን አሁን ባለንበት የሃገራችን የትኛውም ሴክት ነባራዊ ሁናቴ ማንም ሰው የትኛውንም አማራጭ ተጠቅሞ ይሕንን ታይራንት ገፊ መንግስት የሚታገል ሁሉ ከአንድ እውር ድንብሱን ከሚደግፍና አቁማዳው ሲሞላ ከሚደግፈው አንድ ምጎጎ ጭንቅላት ካድሬ ወይም ደጋፊ ይበልጣል፡፡
እኔ የሚያሳዝኑኝ ሳያውቁ የሚደግፉት ናቸው፡፡ ኢህአዴግ እና ልጆቹ እንዲሁም እንደ ኦህዴድና ብአዴን አይነት ተለጣፊ የእንጀራ ልጆች አይነት ዓለም እስካሁን ካሳለፈችው የፖለቲካ ህይወትና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ስውር አምባገነኖች ማንም የለም፡፡
ይህ ብልጠት ወይም ትክክለኛ ፍልስፍናና ህፀፅ የሌለው ርዮት መስሎ ስለሚሰማቸው ብቻ ሳይሆን ሆን ብለውም የህዝቡን አሞት በመቅመሳቸው ብቻ የሚሰሩት ሁሉ ዋጋና ፍዳቸውን ለማስከፈል የመጀመሪያው እርምጃችን በመሆኑ የትኛውንም አማራጭ መከተላችን ትክክል እንጅ ስህተት አደለም፡፡
አንዳንድ ደጋፊና ገንፎ ላፎች ግን የበሰለ እየበሉ ጥግብ ብለዋል ደግሞ በምን መታገል እንዳለብንም መስመር ሊያስይዙን ይፈልጋሉ፡፡ ጅሎች፡፡ እኔማ ለናንተ አይነቱ የምመልሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ግብረገብ ህዝብ የሚዘርፍ የሚበዘብዝ የሚገድልና የሚያስር ማፊያ ቡድን ለማውረድ ብቻ ሳይሆን ለማውደም የትኛውም አማራጭ ትክክል ነው እላለው፡፡
አሁን በነገራችን ላይ ያልሰማችሁትን ልንገራችኋ ውድ የኢህአዴግ ደጋፊዎች አባላትና አቀንቃኞች እኔና መሰሎቼ የትግል አጋሮቼ የምንፈልገው አሁን ይገርማችኋል ይህንን ማፊያ ሃይል አፈር ዱሜ ማብላት ነው እንጅ ቅድሚያ የሰጠነው ሌላ ምንም ነገር የለም፡፡ እመነኝ በትክክልም ልቦናህ ያውቀዋል ልብሱን እያወለቀ ያለና በሚስጥር ቁምጣው ብቻ የሚንቀሳቀስ እጅ እግር የሌለው አንጎሉ ወልቆ የወደቀና ያበቃለት ገዥ መደብ ደጋፊ እንደሆናችሁ አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው እንደሆነ፡፡
ለማንኛውም ከፈለግን እኛ ሁላችንም ራሳችንን አዲስ የኢህአዴግ አባላት አድርገን ውስጣችሁ ገብተን በህይወታችሁ መጥምጠን በልተን እንድናጠፋችሁ ልንመርጥ እንችላለን ይህንንንም እያደረግን ነው፡፡ እኛ የምንፈልገው ይህ ሰወበላ እና ወሮ በላ መንግስታችሁ ከወንበሩ ወርዶ ይህን ህዝብ መምራት የሚችል አሁን ባለው ሰዓት ኢትዮጵያ ሃገራችን መድረስ ከሚገባት ቦታ ማድረስ የሚችል ህዝብ የመረጠው ሃይል እስኪወጣ መታገላችን በየትኛውም መንገድ አይቀርም፡፡
ወደዳችሁም ጠላችሁ የአሁኑ የእኔና መሰሎቼ የትግል አቅጣጫ ሁለገብ ነው፡፡ እኔ በግሌ ይህንን ገሎ ቅበር መንግስት ባንዳ ቡድን ግብዓ ከመሬት የሚያፋጥን ሳይጣንም ቢሆን እንቀበለዋለን የኢትዮጵያችንም ማንነትና ታሪካዊ ዘውግ ግን አናስነካም እንደናንተ ደደቦች አደለንም፡፡
ጨርሻለው!!!

No comments:

Post a Comment