Friday, June 20, 2014

" አሁንም አልረፈደም "

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
ጋዜጠኛ ሰርካለም ፍሲል " አሁንም አልረፈደም "
ጋዜጤኛ አበበ ገላው -- አቃቤ ህግ ቴድሮስ ባህሩ ሳሁኑ ግዜ በአሜሪካ ይገኛል...ይሄ ግለሰብ ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላ የፓለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ የተለያዩ አክትቨስቶችን የድጋፍ ደብዳቤ እንዲሰጡት ጥያቄ አቅርቦ ነበር... በዛ ምክንያት ነው በተለይ ቀልባችንን የሳበው ...አሁን ግለሰቡን ለማነጋገር ቃለ ምልልስም እንዲሰጥ እንዲሁም ደግሞ ህሊናውን እንዲፀዳ እንደውም ያጠፋው ጥፋት ካለ በግልጽ እና ባደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ እድል ሰተነው ነበር...በተደጋጋሚ ጠይቀነው ለመቅረብ ፈቃደኛ አልሆነው ...እንደውም ያለው ምንድነው ባጭሩ "ቤተሰቦቼ አደጋላይ ሰለሚወድቁ አላደርገውም " ብሎ መልስ የደጠበት ሁኔታ ነው ያለው ...ይሄንን ምላሽ አንቺ እንዴት ታይዋለሽ ? አንቺ የአቶ እስክንድር ነጋ ባለቤት ከመሆንሽ አንጻር እና 18 ዓመት የተቆለፈበት ውድ የሆነ የኢትዮጵያ ልጅ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን እና አንቺ በዚህ ጉዳይ ምን አስተያየት አለሽ ?
ጋዜጤኛ ሰርካለም ፋሲል -- እኔ እውነት ቴድሮስ ብርሃኑ .... ቤተሰቦቼን አደጋ ላይ እጥላለሁ ካለ በጣም አዝናለሁ:: በጣምም ያሳፍራል በጣምም እንደ ኢትዮጵያዊነቴ እሽማቀቃለሁ :: እሱ የሰንቱን ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ነው ያፈረሰው ? የስንቱን ኑሮ ነው ያፈረሰው :: የስንቱን ልጆች ነው አባት ያሳጣው :: እሱ ቤተሰብ ካለው ... እራስህ ላይ እንዲደርስ የማትፈልገውን ነገር ሰው ላይ አታድርግ :: እንዴት አሱ የራሱን ቤተሰቦች አደጋ ላይ እንዳይጥል ሲፈልግ የሌሎቹን ቤተሰብ አደጋ ላይ ለመጣል እንዴት ህሊናው ፈቀደለት ? ሌላው ኢትዮጵያዊ አይደለም ? ሌላው ወፍ ዘራሽ ነው ? ሌላው ዜጋ አይደለም ? የሱ ቤተሰብ አደጋ ላይ መውደቅ ካሳዘነው .....የስንቱን ቤተሰብ ነው የሱ በሃሰት ክስ ውንጀላ ቃልቲ የተቆለፈባቸው ሰንት ውድ ልጆች ለኢትዮጵያ ብዙ ነገር የሚሰሩ ልጆች ቃልቲ ውስጥ ታጉረው እሱ ለቤተሰቡ ደህንነት መሰጋቱ በጣም የሚያሳዝን በጣምም ያሳፍራል :: አሁንም እኔ የምለው ለአቶ ቴድሮስ ባህሩ እውነት ህሊና ካለው እውነት የሚቆጭ ህሊና ካለው አደባባይ ወቶ ይቅርታ ይጠይቅ :: የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ ያደርግለታል እኔን ጨምሮ:: ሃጥያቱን ይናዘዝ ሃጥያት ልበለው .....ሃጥያቱን ይናዘዝ የነበረውን ነገር ይፋ ያውጣ :: ይቅር እንባባል :: ከዚህ ባለፈ ግን እሱ ሰላማዊ ኑሮ ሊኖር....የሌሎቹን ህይወት አናግቶ የሌሎቹን ቤተሰብ በትኖ የቤተሰቡ መስጋት ..ለቤተሰቡ የሚያስብ ከሆነ ይሄ ከአንድ ኢትይዮጵያዊ ወይም ከአንድ ህሊና ካለው ወይም ከአንድ ተምሬያለሁ ከሚል አካል የሚጠበቅ በፍጹም አይደለም :: ያንን ቢፈራ እማ መጀመርያ የሂደቱ ተሳታፊ ባልሆነ :: በነ እስክንድር ጉዳይ ብቻ አይደለም በነ ርዮትም በነ አቡበከርም በሁሉም ጉዳይ ውስጥ ዋና ዋና በሚባሉ የፕለቲካ ክሶች ሂደቶች ላይ ዋና ተዋንያን ነበረ:: የሰንቱን ቤተሰብ እንዳፈረሰ እያወቀው ዛሬ እሱ ለራሱ ቤተሰብ እና ለራሱ ደህንነት መስጋቱ በጣም አዝናለሁ ከሚገባው በላይ ...ቢችል ከመጀመርያው ሂደት ውስጥ መውጣት ነበረበት :: ህሊና ቢኖረው ..ቤተሰብ የሚያሰጋው እሱ እውነት የቤተሰብ ሃላፊ ከሆነ የቤተሰብ ህይወት ቢያሰጋው ኖሮ ያኔ ህሊናው ያላመነበትን ነገር ህሊናዬ አላመነበትም ብሎ ከጨዋታው ውጭ መሆን ይሽል ነበር አሁንም ቢሆን አልረፈደም ::
...አሁንም ደግሞ አልረፈደም
ምስጋና ለጋዜጠኛ አበበ ገላውhttps://www.facebook.com/photo.php?fbid=596938197090755&set=a.105688126215767.7190.100003237401892&type=1

No comments:

Post a Comment