Monday, June 16, 2014

ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ



ብዙ ዲያስፖራዎች በኢትዮጲያ እድገት
ደስተኛ አደሉም:: ለምን መሰላችሁ??? እነሱ
ከውጭ ወደ አገር ቤት በሚመጡበት ግዜ
ደምቀው መታየት ሀብታም መባል ይፈልጋሉ
አሁን ደሞ ኢትዮጲያ ውስጥ 5የሚሆኑ
ቢሊየነሮች በመቶሺ የሚቆጠሩ ሚሊየነሮች የሚኖሩባት
አገርነች ታዲያ ዛሬ 10 ዶላር
ይዞ መቶ ግርግር ቢፈጥር ማን ያየዋል
እንኯን ሴት ድመት አያየውም:: ሌላው ይቅር
ከአሜሪካ የሚመጡ ዘመዶቻችሁ የሚለብሱትን
ልብስ ተመልከቱ ከዘበኛችሁ እና ከእነሱ ማን
ዘንጧል?? ቀልድ አደለም የእውነት ተመልከቱ! ይሄ ደግም
ትልቅ ኮምፕሌክስ
ውስጥ ይከታቸዋል ለዚህ ነው ሰልፍ ሳንወጣ
ሰልፍወጣችሁ ይሉናል; ሳይርበን አራባችሁ
ይሉናል; በሰላም አገር ጦርነት ላይናችሁ
ይሉናል.. *ዛሬ ኢትዮጲያ በከፍተኛ ፍጥነት
እያደገች ነው . ከአስሩ ምርጥ የአለም ከተሞች አንዷ
ሆናለች ባሀርዳርም ከአፍሪካ
ምርጥ ከተሞች ውስጥ ተመድ ባለች ደስ
አይልም? ታዲያ ምናለ ጥሩ ጥሩውን
ብትመኙልን?
ሰይፉ ቅሌቱ አቦ…የኢትዮጵያን ህዝብ በዛሬው ፖስቱ ላይ ሲሳደብ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልሆነውን ሲል ሳይ ያፈርኩብ ሰይፉ እስቲ ይህን ካለ ከአሁን በፊት ሰይፉ ፌስቡክ ፔጁ ላይ ምን ያህል አዋርዶን ሲሆን ሰውየውም ምንም ስብስብ ያለ ቀልብ እንደሌለው ተረዳሁ…ያም ይሑን እንዴት አይነት ዝፍቅ እንደሆነም ተረድቻለው፡፡ ህፃን ነው የሚመስል የእድሜ ህፃን ሳይሆን የጭንቅላት ህፃን ነገር ነው!!!
ምን ይላል መሰላቹ…ከገረሙኝ ውስጥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስዜናዊን ፎቶ ለጠፈና…ተመልሰው እንደማይመጡ እያወቀ…አይ ሚስ መለስ ኤናዊ አባይን የደፈረ ብቸኛው መሪ…
 ብሎ ለጥፏል
የስዕተቱ ብዛት እናንተየ…
1.      አባይ ዲዛይኑ የተሰራ በመለስ ሳይሖን ገና ጥንት ነው…ሰላም የሰፈነባትን ኢትዮጵያ ያጣው ስርዓት እንኳን በ1976 ዓ.ም የግንባታ ጥሬ እቃዎችን ለማስገባት ጀምሮ ነበር
2.     ቀ/ኃ/ስላሴ ዲዛይኑን በጣሊያን ድርጅቶችና በምርጥ የዘመኑ መሃንዲሶች አሰሩት
3.     ንጉስ ዳዊት ኦቭ ከ15ኛው  ክ/ዘመን በፊት ለግብፆች በፃፉት ደብዳቤ አባይን እንደሚገድቡባቸው ፅፈዋል…ኧረ ስንቱ እነዚህ በቂ ናቸው ላንተ አይነቱ ቅል እራስ…
እኔ ይህን የመለስኩልህ እንደማይገባህ አውቃለው ግን አንተ ደደብ ብትሆንም እኔ እንደንተ መሆን ስለማልፈልግ ነው፡፡ ይህም ይሁን "…እገሌ ናፈቀኝ የሚባል"
እንደሚመጣ ለሚገመት ለጊዜው ለተለዩት ሰው ነው አደል እንዴ ታዲያ ጠቅላዩን ናፈቁኝ ብሎ መናገር ምን ማለት ነው…እያሾፈ መሆኑ ነው!!!! አይ ሰይፉ ኢህአዴግ ይችን ክፍተት ካገኘብሽማ አለቀልሽ ብየ ጨረስኩ…
ለማንኛውም እስቲ ሰይፉን ጓደኛችሁ እንዲሆን አልመክርም አቃጥሎ ነው የጨጓራ በሽተኛ የሚያደርጋችሁ…ግን እስቲ ፌስቡክ ፔጁን ገብታችሁ ዳብሱትና የሰይፉ ጭንቅላት ታዩታላችሁ…
እናንተየ እንዲያው በዚህ ኢቲቪ /የኢትዮጵያ ትቢ በሽታ/ የሚቀርብ ሁሉ ጭንቅላቱ አንድ ቫይረስማ ብግብግ አድርጎ በልቶታል…
ወያኔያዊ ኢህአዴጋዊ ቫይረስና ደደብ ነው የሚሆኑት ወዲያውኑ!!!

ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ
(
ገጣሚ ጌታቸው ይመር )
--------------- -------
እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ.....
ለእልፍ አላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው
ሁለት ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ
መቅረትህ ገዘፈ...
እንደውም እንደውም...
‹‹
በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ዘመን
ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው
እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል
እኔ ምን አውቃለሁ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ...
ግን አንተ ደህና ነህ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ!
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹
ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድትጥልልን....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን
እንደጉድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ?
እኛማ ይሄውልህ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ብትሩን ያውሰን....
እናልህ እግዜር ሆይ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እንዲህ…እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ
አጥተን...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን...
‹‹
የመሄድ ዘመን ነው
ባህር የመሻገር
‹‹
ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ...
ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ....ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ!!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹
ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን!!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው....
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው...
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሾመው ሁሉፀሃይ ነኝእያለ
የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ባቃጠላት እናት ሃገር
ምን ታምር ሊኖርስ ይችላል ፀሃይ ሁኖ
ባንተ እንደመፈጠር....
ኧረ እግዜር በናትህ....
ኧረ እግዜር በናትህ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ
ሙቀት ገደለና!
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ
በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ
ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም
ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነው
ኑሮ ተስማምቶታል....
ሰውን ለማሳሳት
ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ
ሙቀት ገደለና!!

No comments:

Post a Comment