Monday, June 30, 2014

ሀበሻ -አቢሲኒያ ፪ አቢሲኒያ ከቀድሞዋ ኢትዮጵያ ከኑቢያ ውጭ ያለው ምድር ሁሉ መጠሪያ እንደነበር ከተረዳን ከዛሬይቱ ኢትዮጵም የሰፋ ክልል መጠሪያ ነበር ማለት ነው፡፡

ሀበሻ -አቢሲኒያ ፪ አቢሲኒያ ከቀድሞዋ ኢትዮጵያ ከኑቢያ ውጭ ያለው ምድር ሁሉ መጠሪያ እንደነበር ከተረዳን ከዛሬይቱ ኢትዮጵም የሰፋ ክልል መጠሪያ ነበር ማለት ነው፡፡
የካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ አቢሲኒያን ከኑቢያ በስተደቡብ ያለው ምድር እንደነበር ይገልጻ፡፡ ይህ ደግሞ በሂየሮግሊፍ ተጽፎ ከተገኘውም ጋር ይጣጣማል፡፡ሃትሽፕሱት(መከሬ) ከዛሬይቱ ላእላይ ግብጽ አካባቢ ተነስታ ደቡቡን ያደረገችው ጉዞ ወደ ፑንት እና ሀበሽቲ የተደረገ ጉዞ እንደነበር በድንጋ ላይ ተቀርጾ በተገኘው ጽሑፏ ይታወቃል፡፡
በየመን ያለውንም ግዛት የሚጨምር እንደነበርም የታወቀ ነው፡፡ ይህን የመከሬን ጉዞ ያጠኑ ምሁራን በቀይ ባህር ግራናቀኝ ያሉ የምስራቅ አፍሪካንና የደቡብ አረብያን ምድሮችን ይጠቁማሉ፡፡ የአረብ ትውፊታዊ የጀግንነት ግጥሞችን ያሳውቁናል፡፡
አቢሲኒያ የሚለው ግዛት እንዲህ ተከልሎ ሲገለጽ እን ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ የኩሽ ተወላጆች (ከኩሽ የወረዱ) በሀገሬው አጋዝ (ነጻ ሰው) ሲባሉ የአቢሲኒያ ህዝብ መሰረቶችም እነርሱ እንደሆኑ ይናገራል፡፡በስተምህራብ ከበርበሮች ወዲህ ከኒጀር ከኮንጎ እና ከዛምቤዚ በመለስ በስተምስራቅ የደቡብ አረቢያን የሚጨምር መጠሪያ ያደርገዋል፡፡
አቢሲኒያ የሚለው ስም በአንድ ወቅት በጀርመን የግሪኩን ከሚለው ጋር በማያያዝ ሊፈቱት ሞክረው ነበር፡፡ ገደል ወይም ገደልማ ማለት ነው አሉት፡፡ ይህን የጠቀሰው ኢንሳይክሎፒዲያ የምሁራን ወግ በማለት ጠርቶ የግድ መጣል ያለበት ነው ይላል፡፡
በጽሑፍ እንደሚገኘው ትውፊታዊው ታሪካችንና እንደስታ ተክወልድ መዝገበ ቃላት አቢሲኒያ የሚለው ቃል አቢስ (አበሲን አበሲኔ) ከሚለው የሰው ስም የተገኘ ነው፡፡ ይህም የኩሽ ልጅ የሳባ ሰባተኛ የናምሩድ ተከታይ ልጅ ነው፡፡ ደስታ ተክለወልድ ሁለተኛ ስሙ ከለው ይባላል ይላሉ፡፡ የሳባ ክፍል ሳባ እንደተባ የአበሲኒ ክፍልም አቢሲኒያ ተባለች፡፡ አቢሲኒያ ማለትም የአቢስ ሀገር ማለት ነው፡፡ አቢስ ከዛፍና ከተክል የወጣ ገነታዊ ስም ነው፡፡ በማለት ደተወ ሲገልጹ ቢሲን፤ቢሲና የሚባል ፍሬው የወይን ፍሬ የሚያክል ጥሩ ተክል አለ፡፡ ህብሩ እጅግ ፍጹም ቁጥር ፤ እጅግም ቀይ ሳይሆ ደበብ ያለ ማህከላዊ ነው፡፡ ጣዕሙና መልኩ ደም ግባቱም ከማዓዛው ጋር ደስ ያሰኛል፡፡
አያይዘውም አቢሲን ማለትም እን ቢሲን ፍሬ የሚያምር የቢሲና ፍሬ የሚመስል ማህከላዊ ቀለም ያለው ጥሩ ደመግቡ ማለት ነው ይላሉ፡፡ በመጨረሻም ተከታዩን ጥሩ ጥቆማ ያስቀምጣሉ፡፡
ሲኒጋል የሚባለው የሱዳን ቁራጭ እንደሆነ መደገዝካርም (ማዳጋስካር) የአቢሲኒያ ቁራጭ ነው ይባላል፡፡ ይኸውም በቅርጹና በመልክአ ገጹ ይታወቃል፡፡ ይህንን ከግሪክ ታሪክ እንዳገኙት በቅንፍ ይጠቁማሉ፡፡
እንግዲህ አቢሲኒያ ማለተ የጠያይሞች ሀገር የድብልቅ ህዝብ ሀገር ማለት ነው፡፡ አቢሲኒያ የምትባለውም የኢትዮጵያ ምድሮችንም የሚያካትት እንደነበር እንገነዘባለን፡፡ ሀበሻም ማለት ይኸው ነው፡፡
ሰለሞን_አበበ_ቸኮል‬

No comments:

Post a Comment