Tuesday, July 1, 2014

" ,,,, , . እስኪ`` እንባ ´´ አውሱኝ ......

" ,,,, , . እስኪ`` እንባ ´´ አው" ,,,, , . እስኪ`` እንባ ´´ አውሱኝ ......ሱኝ ......
ሆዴን ሆድ ብሶታል ቅርም ተሰኝቶ እንባ ግን ደርቆታል
እንባ አውሱኝና ላልቅስ ልንሰቅሰቀው ውስጤ እንባን ይሻል
ደስም ቅርም ብሎኝ እንባ ግን እሻለው
ስጠፋ ስበራም መጮህ መጮህ መጮህ እናፍቃለር
ለምን አትሉኝም ??
ያየኝ የለም እንጂ ያላየውት የለም በተሰጠኝ እድሜ
ወንድነት ተንቆ ሴትነት እረክሶ አሳየኝ በቁሜ
እንዴት በምን መልኩ ወንድነት ተናቀ
እንዴትስ ተደርጎ ሴትነት እረክሶ ሴትነት ወደቀ ??
እሾኩ አግጥጦ ሴትነት እረግፏል
ስሩም ተቦርቡሮ ወንድነት ተንዷል
እንደፊት ባህሉ ከቤት መዋል ቀርቶ
ሴትነት ውጪ ነው አጉል ምሽግ ሰርቶ
እንደ ጥንቱ ቢሆን እንዳባቶቻችን
ወንድነት ማገር ነው ከለላ ዋሳችን
ግና ምን ሊረባ የዛሬ ወንድነት
ምናባዊ ተስፋ ምናባዊ ውበት
ላልቅስ ልንሰቅሰቀው እንባ አውሱኝና
ወንድም ሴትን የለ ጠፍቷል ለናሙና
እሪ በል ለራስህ መንገድህን ግታው
ተነሺ እህቴም ውበትሽ ስምሽ ነው
አይርከስ አካልሽ ደምሽ ይወቅስሻል
አይግዛሽ በገንዘብ ገላሽ ወርቅ ያስንቃል
አትውደቂ የትም ክብርት ነሽና
አይጥፋ ውበትሽ ይቅር ለናሙና
ተመከር አንተ ሰው ቤትህ አዘንብሏል
ወኔህንም ት'ከል ወኔህም ያቀናል
ወንድነትን ወልደህ ወንድነትን አምጣው
ቤትህም ቤት ይሁን ለቤትህ ዋስ ሁነው
እንደ ቴውድሮስ ተኩስ በወንድነት እረፍ
ታሪክን ድገመው አንድ ታሪክም ፃፍ
ብልሀትን ውረሽ ከጣይቱ ማጀት
ሴትነት ፅድቅ ነው የህይወት መሰረት
ከናሪ@

No comments:

Post a Comment