Thursday, July 3, 2014

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን በጸጥታ ሀይሎች መታገትን በመቃወም በኖርዌ ኦስሎ ሰለማዊ ሰልፍ ተደረገ::

 
 
 
 
 
 
 
 
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን በጸጥታ ሀይሎች መታገትን በመቃወም በኖርዌ ኦስሎ ሰለማዊ ሰልፍ ተደረገ::
የየመን መንግስት በግንቦት7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ በሆኑት በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የወሰደውን የአፈና እርምጃ በመቃወም በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት በኖርዌ ኦስሎ ታላቅ ሰለማዊ ሰልፍ ተደረገ :: በዛሬዉ ቀን ሃሙስ ጁላይ 3/2014 ከቀኑ 14፥00 ሰዓት ጀምሮ በኖርዌ ኦስሎና በተለያዪ ከተማ የሚኖሩ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ኢትዮጵያኖች በአንድ ላይ በመሰባሰብ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝና በማሰማት የተቃዉሞ ድምጻቸዉን በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሲያሰሙ ዉለዋል ::
ሰልፈኞቹ በሰልፉ ላይ ሲያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል አቶ አንዳርጋቸው የነጻነት ታጋይ እንጅ ወንጀለኛ አይደለም የየመን መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኮይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ልትፈታቸው ይገባል ፣ አንዳርጋቸው የነጻነት ታጋያችን ነዉ ፣ የእንግሊዝ መንግስት የዜጎዋን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት አለባት እና የመሳሰሉትና ሃገራዊ መፈክሮች ጎልተው ተስተጋብተዋል። ሰልፉን ሲመሩት የነበሩት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ ሲሆኑ በአቶ ዳዊት መኮንን የግብረ ሃይሉ ተወካይ አማካኝነት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን በጸጥታ ሀይሎች መታገትን በተመለከተ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የአቆም መግለጫ ለሰልፈኛዉ በንባብ ካሰሙ በኋላ ለእንግሊዝ ኢምባሲ በኖርዌይ ለአምባሰደሩ ተወካይ አስረክበዋል የአባሰደሩም ተወካይ ደብዳቤውን ከአቶ ዳዊት እጅ ከተቀበሉ በኋላ ባደረጉት አጠር ያለ ንግግር ጉዳዩን የእንግሊዝ መንግስት በአንክሮ እየተከታተለ ነው እኛም ከየመን መንግስት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን ለማከናወን ጥረት ላይ ነን” በማለት ተናግረዋል። በመቀጠልም አቶ ዳንሄል አበበ የግብረ ሀይሉ ተወካይ በሰለማዊ ሰልፋ ላይ የተገኘዉን ህዝብ በማመስገን የሰልፉን አላማ ለሰልፈኛዉ በማስረዳት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስኪፈቱ ድረስ ትግላችንን አናቆምም በማለት የተናገሩ ሲሆን በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዮሀንስ አለሙ በእልህ የተሟላ ንግግር አድርገዋል አቶ ዮሀንስ አንዳርጋቸው እራሱን መሰዋት ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ የነጻነት ታጋይ እንደሆነና ይሄ የነጻነት ታጋያችን እስኪፈታልን ድረስ ማንኛዉንም መሰዋት በመክፈል ትግላችንን እንቀጥላለን ብለዋል :: በመጨረሻም ሰለማዊ ሰልፉ በተያዘለት ሰአት በቀኑ 15 ፡ 00 ላይ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

No comments:

Post a Comment