የግንቦት ሰባት የአመራር አባል የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ደህንነት ሽንጎን ያሳሰበዋል
የግንቦት ሰባት ያመራር አባል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን በኩል ወደ ሌላ ሀገር ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት በሀገሪቱ ባለስልጣናት ከሰኔ 16 ጀምሮ መታሰራቸውን እና እስካሁንም ለማሰፈታ ትየተደረገው ሙከራ ሁሉ እንዳልተሳካ ግንቦት ሰባት ሰኔ 23 ቀን 2006ዓ.ም ካወጣው መግለጫና በኢሳት የመገናኛ ምንጭ ከተዘገበው ተረድተናል።..
በሁለቱም አካሎች የቀረበው መግለጫ የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን
ለህወሀት / ኢህአዴግ ባለስልጣናት አሳልፈው ሊሰጡ እንደሚችሉም አመልክቷል።

አቶ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን መንግስት በመሳሪያ ለማስወገድ
ባሁኑ ሰአት እንደሚታገል በግልጽ አስቀምጦ የሚገኘው የግንቦት ሰባት አመራር
አባል በመሆናቸው ለወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ቢተላለፉ፣ ከፍተኛ ድብደባ ፣
ስቃይ ረጅም እስራት እና ምናልባትም ሞት ሊጠብቃቸው እንደሚችል እንሰጋለን።
ካሁን በፊትም የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች አመራራ አባላት እና ደጋፊወች
በተመሳሳይ ሁኔታ ለህወሀት ኢህአዴግ ተላልፈው ተሰጥተው ከፍተኛ ስቃይ እንደደረሰባቸው እና መዳረሻቸውም እንዳልታወቀ ይታወሳል።
በመሆኑም የየመን መንግስት ከዚህ አይነቱ ተግባር መታቀብ ይገባዋል እንላለን።
ይህ አሳልፎ የመስጠት ጉዳይ ተግባራዊ እንዳይሆንም ኢትዮጵያውያን የፖለቲካና
ሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንዲሁም ፣ የየመን እና አለም አቀፍ ሰብአዊ መብት
ተሟጋቾች አስቸኻይ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን።
በሀገራችን ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር መፍታት የሚቻለው ግለሰቦችን በማገትና
በማሳገት ወይንም ሊያባራ በማይችል የአመጽ አዙሪት ውስጥ በመሽከርከር ሳይሆን
በሆደ ሰፊነት በብሄራዊ መግባባት እና እርቅ ሁሉንም ሀይሎች አሳታፊ የሆነ ስርአት
በመፍጠር ሊሆን እንደሚገባው በተደጋጋሚ የገለጽነውን አቋማችንን ዛሬም ልናሰምርበት እንሻለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
.
http://ethioshengo.org/index.php/u-s/124-2014-07-01-20-41-58

No comments:
Post a Comment