Thursday, July 3, 2014

በተለይም «የዐማራ ክልል» ብለው በሠየሙትና አብዛኞቹ የዐማራ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ይህንን ዘመቻ በበላይነት የመራው ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ነው።

ፋሽስቶቹ የትግሬ-ናዚ-ወያኔዎች እና የአማራ ካባ የለበሰው ቅጥረኛው ትግሬ ናዚ-ብአዴን እስከዛሬ በዐማራው ላይ ምን አደረጉ?
ፋሽስቶቹ የትግሬ-ናዚ-ወያኔዎች ገና ክጥንስሣቸው ጀምሮ ለዐማራ ሕዝብ ያላቸውን ጥላቻ እና ያንንም የመረረ ጥላቻቸውን እስከ ዘር ማጥፋት በሚደርስ እርምጃ ከመግለፅ የቦዘኑበት ወቅት የለም። ይህ ያልተገለፀለት ሰው ቢኖር ከገሃዱ ዓለም ወጥቶ በተምኔታዊ የቅዠት ኅዋ ውስጥ ራሱን የደበቀ ብቻ ነው። የትግሬ-ወያኔዎች በዐማራ ሕዝብ ላይ ከፈፀሟቸው አያሌ ከሆኑት ናዚያዊ ተግባሮቻቸው መካከል ዋና ዋናዎቹን አለፍ አለፍ እያሉ መጥቀስ ለማስታወስም ያህል ይረዳል።
ገና ሲሽፍቱ በትግራይ ውስጥ ብቻ በሚነቀሣቀሱበት የመጀመሪያዎቹ ሦሥት ዓመታት እነርሱ ቀዳሚ የዘር ማፅዳት ሠለባ ያደረጓቸው እዚያው ትግራይ ውስጥ በሥራም ሆነ በሌላ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች ነበር። እንዲያውም ከእነዚያ ዐማሮች መካከል አንዳንዶቹ ከትግሬዎች የተጋቡ እና የተዋለዱ ነበሩ። ለትግሬ-ወያኔዎች ግን እኒያ ሰዎች ዐማሮች ሰለሆኑ መወገድ ነበረባቸው። ስለዚህ አንድ በአንድ በወረንጦ እየለቀሙ ጨፈጨፏቸው።
ከ1971 ዓ.ም. ጀምሮ ወያኔ ከትግራይ ወደ ጎንደር የመስፋፋት ጦርነት አድማሱን ሲያሠፋ የመጀመሪያ እርምጃው በወልቃይት እና ጠገዴ የሚኖሩ የጎንደር ዐማሮችን በጅምላ መፍጀት ነበር። እስከዛሬ ምን ያህል የወልቃይት እና የጠገዴ ዐማሮችን እንደጨፈጨፉ በአሃዝ ለይቶ ለማስቀመጥ ቢከብድም በ20 ሺህዎች የሚቆጠሩትን ከምድረ ገፅ እንዳጠፉ፣ ከ70 ሺህ የማያንሱትን ደግሞ ከጥንት አባቶቻቸው ርስት አፈናቅለው ስደተኛ እንዳደረጓቸው ይታወቃል። ወያኔዎች የጎንደር ግዛት የሆነውን የወልቃይት ፣ የጠገዴ እና የፀለምት አካባቢዎችን «የትግራይ ክልል» ብለው ነጥቀዋል። በአካባቢውም ከተለያዩ የትግራይ አውራጃዎች ያመጧቸውን የራሣቸውን ዘር አሥፍረውበታል።
ሥልጣን ከያዙበት ከግንቦት 1983 ዓም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ ዐማሮችን፦ «ነፍጠኞች፣ ትምክህተኞች፣ አድሃሪዎች፣ ጨቋኞች፣ የትግራይ ሕዝብ ደም መጣጮች፣ ወዘተርፈ» እያሉ ከአገራቸው አፈናቅለዋል፣ ጨፍጭፈዋል። በተለይም ከግብር አጋሮቻቸው ከሻቢያ ፣ ከኦነግ እና ከኦብነግ ጋር በመሆን በሐረርጌ (በበደኖ፣ በሐብሩ፣ እና ሌሎች ሥፍራዎች)፣ በአርሲ (በአርባ ጉጉ እና ጢቾ)፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በኢሉባቦር፣ በባሌ፣ በሲዳማ፣ በጌድኦ፣ በወላይታ፣ በከፋ፣ በጉራፈርዳ፣ በመተከል፣ በአሶሳ እና በሌሎችም አካባቢዎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን በአሠቃቂ ሁኔታ ፈጅተዋል።
ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ «ብረት ማስፈታት» በሚሉት ዘመቻ ዐማራው ሙሉ በሙሉ ትጥቁን እንዲፈታ ተደርጓል። በተለይም «የዐማራ ክልል» ብለው በሠየሙትና አብዛኞቹ የዐማራ ተወላጆች በሚኖሩበት አካባቢ ይህንን ዘመቻ በበላይነት የመራው ኤርትራዊው በረከት ስምዖን ነው። ዛሬ ዛሬ የዐማራ ተወላጅ እንኳን የጦር መሣሪያ ይቅርና የብረት ጅንፎ ያለው ዱላ መያዝ ጦር መሣሪያ እንደመታጠቅ ተቆጥሮበት ራሱን ከትንሽ አውሬ የሚከላከልበት ዱላ እንኳን መያዝ አይችልም።
ከ1985 እስከ 1987 ዓ.ም. ባካሄዱት «ሽፍታ ምንጠራ» ብለው በሠየሙት ዘመቻ ከዐማራው መካከል ንቃተ-ኅሊናቸው ከፍ ያሉትን እና «ለትግሬ-ናዚያዊ አገዛዝ አይንበረከኩም» ብለው የሚያስቧቸውን ዐማራዎች እየለቀሙ አሥረዋል፣ ደብዛቸውን አጥፍተዋል፣ ገድለዋል።
ከ1986 እስከ 1987 ዓ.ም. ዐማራውን በሦሥት መደቦች ከፋፍለው፦ የወያኔ ኮር አባል፣ ተራ ዜጋ እንዲሁም ቢሮክራት እና ፊውዳል ብለው መድበው መሬት አከፋፍለዋል። የመሬት ድልድል ሲያደርጉ በገጠሩ የዐማራ ማኅበረሰብ መካከል የመደብ ልዩነት በመፍጠር ዐማራው እርስ በእርሱ እንዲፋጅ ሲያደርጉ፣ በተለይም ደግሞ አብዛኛውን ዐማራ የኢኮኖሚ ዐቅሙ የተዳከመ እና ፍፁም በድነህት የሚማቅቅ ምስኪን አድርገውታል።
ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በምሥራቅ ወለጋ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች «የጦር መሣሪያ ታጥቃችኋል፣ የኦሮሚያን መሬት ለግላችሁ አድርጋችኋል፣ የኦሮሚያ የቦታ ሥሞችን የዐማራ ስም አውጥታችሁላቸዋል፣ የከብት ዝርፊያ ትፈፅማላችሁ፣ ደን ትመነጥራላችሁ» እና የመሣሠሉትን ሠበቦች በመደርደር ከ12 ሺህ የማያንሱትን አፈናቅለዋቸዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩትን ዐማሮች ደግሞ የአካባቢው የወያኔ ሎሌ የሆኑት የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ታጣቂዎች ፆታ እና ዕድሜ ሣይለዩ በአሠቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፈዋቸዋል። የተፈናቀሉት ዐማሮች ከነበሩበት ሥፍራ ተባርረው ጎጃም ክፍለሀገር አገው ምድር አውራጃ ውስጥ ጃዊ የሚባል እጅግ ሞቃታማ እና በወባ ወረርሽኝ በሚጠቃ ወረዳ እንዲሠፍሩ ተደርገው አብዛኞቹ በወባ ወረርሽኝ እንዲያልቁ ተደርገዋል።
ከሚያዝያ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. ወዲህ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች “የግንቦት 7 ንቅናቄ አባሎች ናችሁ” ተብለው ከታሠሩት ከ37 በላይ የሲቪል ፣ የደህንነት ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የወታደር እስረኞች መካከል አብዛኞቹ ዐማሮች ናቸው። በእኒህ እሥረኞች ላይ የወያኔ መርማሪ ፖሊሶች ካደረሱባቸው ዘግናኝ ግርፋት ዓይነቶች መካከል፦ የወንድ የዘር ብልት ማኮላሸት፣ በኤሌክትሪክ መጥበስ፣ ጥፍር መንቀል፣ ከባድ ድብደባ፣ በአስጨናቂ ሁኔታ በካቴና ጠፍሮ ማሠር እና ከጣሪያ ላይ ማንጠልጠል፤ እንቅልፍ መከልከል፣ በርሃብ እና በውኃ ጥም ማሠቃዬት፣ ጫካ ውስጥ ወስዶ ግድያ እንደሚፈፀምበትና ሬሣው ለአውሬ እንደሚጣል ማስፈራራት ይገኙባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በአካል የተሠቃዩት ሣያንስ እጅግ ቅስም-ሠባሪ ዘለፋ ለመስማትም ተገድደዋል፦ ከወያኔዎቹ አረመኔ ገራፊዎች ከሚወጡት ቃላት ውስጥ፦ “ትምክህተኛ ዐማራ፣ ግም ዐማራ ፣ ብስብስ ዐማራ፣ ሽንታም ዐማራ፣ ፈሪ ዐማራ፣ በኤድስ ቫይረስ የተበከለ ደም እንወጋሃለን፣ ከሃምሣ ጋይንት አንድ አጋንንት ይሻላል አንተ ሆዳም ጋይንቴ፣ ዘር-ማንዘርህን ቀሚስ አልብሰን የወጥ-ቤት ሠራተኛ አድርገን እንገዛዋለን፣ አንተ ደም መጣጭ ጎጃሜ እናቃጥልሃለን፣ ዘረ-ቆሻሻ ዐማራ፣ ወዘተርፈ” የሚሉ ይገኝባቸዋል። እኒህ እሥረኞች በወያኔው የጨረባ ፍርድ ቤት እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
እነዚህ ሁሉ የትግሬ-ወያኔዎች የዐማራ ጭፍጨፋ ድርጊቶች ከራሣቸው አንደበት እና ዘገባ ማረጋገጥ የተቻሉ ናቸው። በተለይም በ1999 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔዎች ባካሄዱት የሕዝብ ቆጠራ «አረጋግጠናል» ብለው ለሕዝብ ይፋ ባደረጉት መረጃ መሠረት ከ1989 እስከ በ1999 ዓ.ም. በነበሩት 10 ዓመታት ብቻ 2 ሚሊዮን 500 ሺህ ዐማሮች የደረሱበት አልታወቀም ብለዋል። በእርግጥ ይህ የአሃዝ አገላለፅ ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በራሣቸው በወያኔዎች የታመነውን ጉዳይ ከማስተባበል ይልቅ ከጨፈጨፏቸው የዐማራ ነገድ ተወላጆች መካከል ከዚህ ቁጥር ውስጥ ያልተካተቱት ምን ያህል እንደሆኑ ማጣራቱ ይበልጥ ትርጉም ይኖረዋል።

No comments:

Post a Comment