#EthioMuslims #EndureTheStrugle #JumaDemostration
ነገ በመላ ሃገሪቱ ግዙፍ ህዝባዊ ንቅናቄ በማድረግ የቀጣዩን ትግላችንን መንገድ እጠርጋለን!
ሐሙስ ሰኔ 26/2006
ህገ መንግስታዊ መብቱን ለማስከበር ቆርጦ የተነሳው ኢትዮጵያዊው ሙስሊም በነገው እለትም ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ለማካሄድ የሚያደርገውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሙስሊሙ ከምንጊዜውም በበለጠ ለመንፈሳዊ ተሃድሶ በሚተጋበት በዚህ የተቀደሰ የረመዳን ወር ከእስትንፋስ የላቀውን ዲናዊ መብታችንን በማስከበሩ ትግል ውስጥ አንድ ተጨማሪ ጠጠር ለመጣል መቶ ሺዎች በጉጉት እየጠበቁ ነው፡፡ ለታላቁ ተቃውሞ እእምሮአዊና አካላዊ ዝግጅት ከማድረግ ባለፈም ሁሉም በየፊናው መፈክሮችን እየዘጋጀ ይገኛል፡፡ እንደእስከዛሬው ሁሉ የነገዋም ጁሙዓ ህዝበ ሙስሊሙ የተዋሃደ ድምጹን የሚያሳይባት ድንቅ ጁሙዓ እንደምትሆን አይጠረጠርም!

የነገው ሃገር ዓቀፍ የጁመዓ ተቃውሞ ከወትሮው የሚለይባቸው በርካታ ነጥቦች አሉ፡፡ ላለፉት አመታት በነበሩን ዋና
ዋና ተቃውሞዎች ስናስተጋባቸውና ከየቤታችን አዘጋጅተን ስናመጣቸው የነበሩ መፈክሮችን ዳግም ይዘን እንመጣለን፡፡
በዚህም ሰላማዊ ትግላችን ጥያቄዎቹን ጥሎ በእስር እና እንግልት አጀንዳ እንደማይዋጥ ለሁሉም አካል እናሳያለን፡፡
ይዘን እንድንመጣ የተመረጡት መፈክሮች፣ ማለትም ‹‹ለሀይማኖታዊ መብታችን በፅናት እንቆማለን!!››፣ ‹‹ፍትህ ይስፈን - የታሰሩት ይፈቱ!!››፣ ‹‹መጅሊስ ለህዝበ ሙስሊሙ ይመለስ!!››፣ ‹‹የእምነት ነፃነታችን ይከበር!!››፣ ‹‹አፈና፣ ግፍ እና ማስገደዱ ይቁም!!››፣ ‹‹የእምነት ቤቶቻችን ክብር ይጠበቅ!›› የሚሉት በሙሉ የትግላችን ዋና ማጠንጠኛ የሆነውን የሃይማኖት መብታችንን ለማስከበር እና እሱን ለማምጣት ባደረግነው ጉዞ የደረሱብንን ወሳኝ የሰብዓዊ መብት እጦቶች የሚያመላክቱ ትልቅ ትርጉም ያላቸው ናቸው፡፡ በድምፅ የምናስተጋባቸው መፈክሮችም፣ ማለትም የፅናት ተምሳሌት የሆነው ‹‹አሃዱን አሃድ!›› እና የቀጣዩ ትግላችን አስኳል የሆነው ‹‹መብታችን ይከበር!›› የሚሉት መፈክሮቻችን የጉዟችንን ሁለንተናዊነት ገና በመጀመሪያው ጁመዓ የምናመላክትባቸው የወኔ መገለጫዎች ናቸው፡፡
ነገ በመላ ሃገሪቱ ግዙፍ ህዝባዊ ንቅናቄ በማድረግ የቀጣዩን ትግላችንን መንገድ እጠርጋለን!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment