Wednesday, July 2, 2014

የደሞዝ ጭማሪዉን ግሽበት በነጋዴዉ ማላከክ ይቁም!!!

የደሞዝ ጭማሪዉን ግሽበት በነጋዴዉ ማላከክ ይቁም!!!
የዋጋ ንረት ደሞዝ ስለተጨመረ የሚከሰት ሳይሆን ሀገሬቱ በሚፈጠርባት የገንዘብ ግሽበት ሳቤያና ገቢያዉ ዉስጥ በሚረጨዉ ገንዝብ ምክኔያት ያላት የምንዛሪ አቅም ጭማሪዉን መቆጣጠር የሚያስችል ባለመሆኑ ነዉ፡፡
ኢትዮጲያ በዚህ ዓመት 10.5, 11 በመቶ ወዘተ አደገች እሰየዉ ነዉ ዕድገቱ እዉነት ከሆነ ጥያቄዉ ግን ከዕድገቱ ህዝቡ ምን ያህል ተጠቃሚ ሆነ የሚለዉ ዋነኛዉ ጥያቄ ነዉ ዕድገቱን ተከትሎ ከሀፍት ክፍፍሉ ተጠቃሚ የሆኑት እጂግ ጥቂት ተሰሚነት ያላቸዉ ግለሰቦች ናቸዉ በዚህም የተነሳ ከፍተኛና የሆነ ሀፍት እንዳፈሩ ይታወቃል ነገር ግን በዝቅተኛ ደረጃ ገቢ ያላቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች በዚህ ዕድገት ምንም ጥቅም አላፈሩም ይባስ ብሎ ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ የኑሮ ዉድነቱ ከሚሸከሙት በላይ እየሆነባቸዉ አበሳቸዉን እያሳየ ይግኛል ዝቅተኛ ገቢ ከሚያገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ዉስጥ የምንግስት ሠራተኞች ( ሲቪል ሰርቫንት) ከፍተኛ የሆነ ጫና የሚያርፍባቸዉ እነሱ ላይ ነዉ ለኢኮነሚ እድገቱ የአንበሳዉን ድርሻ እነሱ ቢወስዱም ከተገኘዉ ዕድገት እና ከሀፍት ክፍፍሉ የምንግስት ሰራተኞች ምንም ተጠቃሚ አልሆኑም ይባስ የኑሮ ጫና እየበረታባቸዉ ይገኛል ትላንት ራዲዮ ፋና ዜና መፅሔት ላይ መንግስት ለሲቪል ሰርቫንቶች ከሀምሌ ወር ጀምሮ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደርግና ይህን ተከትሎ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት መንግስት ከወዲዉ ቅድመ ዝግጂት እያደረገ እነደሚገኝ ዜናዉ አስታወቀ በጣም የሚገርም ዘገባ ነዉ ገና ላተጨመር ደሞዝ የዋጋ ንረት ሊከሰት ይችላል ብሎ መተንበዩ ምን አስፈለገ ወይስ ነጋዴዎች ከወዲዉ እንዲጨምሩ ቅስቀሳ ነዉ አልገባኝም ? ወይስ የተጨመረዉ ደሞዝ በእጂ አዙር በነጋዴ ሰበብ ሊቀበል? የሚል ጥያቄ ይፈጥራል፣ ማንም ነጋዴ ( አከፋፋይ) በስመ ደሞዝ ጭማሪ ሰበብ ህዝቡ ላይ ጫና ማሳደር የለባቸዉም ማሰብም አያስፈልግም አይችሉምም ምክኒያቱም መንግስት ያለበት ሀገር ስለሆነ እንደምሳሌ ካየን ከምግብ ነክ ከሆኑ ነገሮች እስከ ቅንጦት ዕቃዎች ድረስ ከጥቂቶች በስተቀር 3% የማይሞላ በመንግስት ተፈትሾ ቀረጥ ተቆርጦ ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገባ ዕቃ ነዉ ይህ ሆነ ማለት ደግሞ መንግስት በንግድ ሥራቱ ዉስጥ ከፍተኛ ቁጥጥር አለዉ ማለት ነዉ ስለዚህ ማንኛዉም ቸርቻሪ ከመሬት ተነስቶ ህዝቡ ላይ ዋጋ ጨምራለዉ ቢል ሐገሪቱ ከሚፈጠርባት የአቅም ዉስኑነት ካልሆነ በስተቀር አይታሰበም ምክኒያቱም አብዛኛዉ ነጋዴ በንግድ ፎክክር ዉስጥ ያለ በመሆኑ፡፡ ከዚህቀደም በቀድሞ ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ለመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ተደርጎ በጥቂት ቀናቶች ዉስጥ በኢትዮጲያ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ 86 ፐርሰንት አርሶ አደር በሆነባት ሀገር ምግብ ነክ በሆኑ ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ አሳየ መንግስት ለ10 ቀን በማይሞላ ጊዜ ነጋዴዎችን አስረ ሆይ ሆይ ተባለ ከዛን ጉዳዩ አበቃ መንግስትም ችላ አለ ደሞዙን አስታኮ የተነሳዉ የዋጋ ንረት ቀን ከቀን እየጨመረ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ እስካሁን ድረስ አበሳ እያሳያቸዉ ይገኛል በጣም የሚያሳዝኑኝ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸዉ የምንግስት ሠራተኞች ናቸዉ. ለመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ሲደረግ በሚያገኙት የደሞዝ ስኬል መሠረት ነዉ ለምሳሌ መንግስት 30% የደሞዝ ጭማሪ ቢያደርግ አንድ የሦስት መቶ ብር(300 ብር) ዝቅተኛ ደሞዝተኛ የሚያገኘዉ ጭማሪ 90 ብር ብቻ ይሆናል የ ሁለት ሺህ ብር ደሞዝተኛ(2000ብር) የሚያገኘዉ ጭማሪ 600 ብር ይሆናል ልብ በሉ የዋጋ ንረቱ ሲከስት ለሁለቱም ግለሰቦች እኩል ነዉ ይበልጥ የሚጎዳዉ ግን የ300 ብር ደሞዝተኛዉ ን ነዉ ምክኒያቱም የዋጋ ንረቱ ለሁለቱም ግለሰቦች እኩል ነዉና የሚደረሰዉ እንደምሳሌ አንድ ፈረሱላ ጤፍ በ 250 በር ሁለቱም ቢገዙ የ300በር ደሞዝተኛዉ = 300+90=390-250=140ብር ይቀረዋል የ2000ሺህ ብር ደሞዝተኛዉ ፡2000+600=2600-250=2350 ብር ይቀረዋል በዚህ ስሌት መሰረት ከፍተኛ ጫና የሚያርፍበት ዝቅተኛ ደሞዝ የሚያገኘዉ ግለስብ ላይ ነዉ ስለዚህ ሚዲያዎች እና መንግስት በተለይ ሚዲያዎች ገና ለገና ደሞዝ ይጨመራል በሚል ምክኒያት ህብረተሰቡ ላይ በተለይ የመንግስት ሠራተኛዉ ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ጫና እያሳደራቹ ነዉ በተለይ ለነጋዴዎች ዋጋ እንዲያንሩ በሩን እየከፈታቹ እነደሆነ ልትረዱት ይገባል በዜና ዘገባቹ ላይ ለመንግስት ሥረተኞች እንደ ስርፕራይዝ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ነዉ ብላቹ ማብሰር ሲገባቹ የምንግስት ሠራተኛዉን ገና ደሞዙ ሳይጨመር ጭንቅ ዉስጥ እየከተታችሁት ትገኛላቹ እባካቹ ዘገባችዉን ብታስተካክሉ. ሀገር ያለ ሠዉ ምንም ነዉ ስለዚህ ከሁሉም ነገር በፊት ሠዉ ይቅደም

No comments:

Post a Comment