ዜግነታችን
መቼ ነው ማረጋገጥ የምንችለው? መሰረታዊ ጥያቄው ይህ ነው። የዜግነታችን ጌታ አንድ ሽፍታ ወንበዴ ብቻ መሆኑ
የማይበሳጭ እንደ ሰው ለማዬት ይቸግራል። ጸጥታ – ዝምታ – እርጭታ እስከ መቼ? ከውጪ ወጥተን ደግሞ ለመንቀሳቀስ
ከወያኔ ፈቃድ መጠይቅ አለብን ወይ? ይህ የኢትዮጵያዊነት ሃሞታችን አያበሳጨውም – አያራውጠውምን? entoto times
እስከ ምን ድረስ ይሆን አረሙ ወያኔ እኛን መግዛትና ማስተዳደር የሚችለው?
እንደ እኔ – ይህንን ጎርበጥባጣ ገጠመኝ ልጎ መልክ ማስያዝ የሚያስችለው ከመጠን ያለፈው ግፍና በደሉ መንፈስን መበጥበጥ፤ አላስቆም አላስቀምጥ ብሎ መነሰት ሲችል ብቻ ይሆናል። የወያኔ የግዛት ዳር ደንብር ልኩን አውቆ የጠነሰሰው መርዝ አበጥሮና አንተርትሮ ብስጭትን ወልዶ የወያኔን ምንጠራ አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ ያስፈልጋል።
መደፈርን (ጠብቆ ይነበብልኝ ፍቹ አሉታዊ ነው) መቀበል አቅመ ቢስነት ነው። ጥቃትን መቀበል የደምን አደራ እንደ መርገጥ ነው። መሸነፍን መቀበል የምልዕትን ዕንባ መጠቅጠቅ ነው። የወያኔን የበቀል እርምጃ በገለልተኝነት ማዬት የሰውነት ደረጃን ቁልቁል ያወርደዋል – ዘቅዝቆም ይሰቅለዋል፤ የቋሳን ሂደት ተከትለው የሚደርሱትን በደሎች ሁሉ አሜን ብሎ መቀበል ፈሪነት ነው። ያሳፍራልም።
የኢትዮጵያዊነት – ደም መወራጨት አለበት። የኢትዮጵያዊነት ደም መንተክትክ አለበት። ዬኢትዮጵያዊነት ደም መፍላት አለበት። ምክንያቱም ፍቹ ያለው ከደማችን ውስጥ ነውና። እንዲህ በአለም ዐቀፍ ደራጃ ያለን ሙሉዑ የሰብዕ መብታችን በተገኘንበት ቦታ በግልና በተናጠል እዬተነጠለ የምንቀጠቀጥበት ምክንያት አምክንዮ ኢትዮጵያ ሀገራችን እና የተከበረው ህዝባችን በሽፍታ ወንበዴ በጠላት በወያኔ የሚመራ በመሆኑ ነው። የሴራው ምንጭ ይህ ነው።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ወይ ተወልጅበሽ ወይንም ተጎራብቸብሽ የምትባል ታላቅ ሀገር ልጆች ተከብረው፤ ተፈርተው የሚኖርበትን ዘመን ፍቆ እንዲህ ማንነታችነን በማናለብኝነት ለሚረግጥ ሽፍታዊ አስተዳደር አልፎ ተርፎ ለባእድ አሳልፎ ለሚሰጥ ወራሪ መፍትሄው አንድና አንድ ነው። በጫካ ተመክሮ የመደፈራችን ፍሬ ነገር እንዲቆጠቁጠን – እንዲያጎሳቁለን ስንፈቅድለት በህሊናችን የሚስረከረከውን ብክል የኢጎ ጠቀራ ጠራርጎ ወደ ወረሰንው አርበኝነት ምርጥ ዘርንት ይመልሰናል። ወኔ!
ዛሬ በአንድ የሀገራችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛውን ሚና በሚጫወቱት፤ የወያኔን ሆድ እቃ አበጥረውና አንተርትረው በሚያውቁት የግንቦት 7 ከፍተኛ መሪ አካል በተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተደረገው የማስተጓጉል እኩይ ተግባር ለመላ ኢትዮጵያ ህዝብ አጀንደው ሊሆን ይገባል። ዜግነት ማለት ይህንን ማንበብ ሲችል ብቻ ነው።
ዛሬ ይህ ኢትዮጵያዊነት የምንለው ሚስጥር እስክምን ዘልቆ እንደፈተሸን ፊት ለፊት ተገናኝተን አኃታዊነታችን የታተመበት፤ ወይንም የተጋለጥንበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ወቅቱ – ሁላችንም ከክብሩ ማንነታችን ጋር ስለመሆናችን እራሳችን የፈተሽንበት ወቅት ነው።
ልብ ላለው፤ ህሊና ላለው፤ መንፈሱ ለተሰተካካል ፍጡር ጉዳዩ የግንቦት 7 አይደለም። በፍጹም። የሁላችንም ነው። በሀገራችን መኖርን ተነፍገን፤ ተሰደን ደግሞ ጎብጠን እንደንኖሮ የተሸረበ ጥልቅ የበቀል ድርና ማግ ነው። ይህን ማሸነፍ ሰውነትን ይጠይቃል። የትናንቱን የሉዕላዊነትን የደም ሰንደቅ አደራ በጥልቀት ብህብር ማገናዘብን ይጠይቃል። በስተቀር ኢትዮጵያዊነታችን የምናጠወልገው እኛው እራሳችን ስለመሆናችን እርምጃችን ወይንም ዝንባሌያችን ይለካዋል። ወይንም ይመትረዋል። ኢትዮጵያ ሀገሬ ለሚል አንድ ብቁ ዜጋ አንድ ትልቅ የፖለቲካ መሪ በጠላት እጅ ሲወድቅ በገልልተኝነት፤ በባይተዋርንት፤ እለሰማሁም አላዬሁም ብሎ ካሊሙን ተሸፋፍኖ መተኛት ውርዴት ነው ለትውልዱ – ኪሳራ። መራራም።
ደግሞስ ከጠላት ጋር ወገን በምን ማንዘርዘሪያ፤ በምን ማንተርተሪያ፤ በምን ወንፊት ይለይ?! ልዑላዊነትን ያወረደ ተግባር የትም ቦታ ሲከወን ከጫፍ እሰከ ጫፍ ሁሉም ቀፎው ተንክቷልና እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ መነሳት ይኖርበታል። ፈቃዱ የደም ጉዳይ ነው። ደምን ሌላ ባዕድ ሀገር ሲጨፍርበት – ሲሳለቅበት – ሲስቅበት – ሲያሾፍበት እንዳሻው ማለት በእርግጥም የወያኔ የጫካ ተምክሮ ሁለመናቸን ሰልቦታል ማለት ነው – ማነስ። ይህ ደግሞ በቁም መቀበር ነው።
ለእኔ ኢትዮጵያዊነት ማለት እራሱን አሸንፎ ማደር ማለት ነው። ዛሬ ሙሉ ቀን ጠብኩኝ ከሸንጎ በስተቀር አንድም ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ወይንም የሲብል ድርጅት አቋሙን – አመለካከቱን – ዝንባሌውን በወልዮሽ አለመግለጹ የትውልዱን የሃላፊነትን ደረጃ ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። ሃፍረት።
እጅግ የምናፍቃችሁና የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች – ማናቸውም ነገር ከኢትዮጵዊነት በታች እንጂ በላይ የሚሆን ከቶ አንዳችም ነገር አይኖርም። እርግጥ ነው ሀገር ውስጥ ያሉት የግንባር ሥጋዎች ምንም አይጠበቅባቸውም። እነሱም በፍል እዬተቀቀሉ ነው። የተወሰደው እርምጃም ዬእነሱን አቅል ለመበተን፤ ጥንካሬያቸውን ለመስለብ። ለማስፈራራትም ነው። ወያኔ አቅዶ ነው በደል የሚፈጽመው። በታሪክ ቋሳ ታቅዶ ሲከወን ያዬነው በወያኔ ዘመን ነው።
ወደ መሰረታዊ ጉዳዬ ስመለስ ለመሆኑ ውጪ ያለነው ግን ምን አስፈራን? ይህ እኮ የሉዕላዊነት፤ የሰብዕዊነት ጉዳይ ነው። ይህን መመለስ ያልቻለ ግልሰብ ይሁን ድርጅት ለእኔ ለ80 ሚሊዮን ህዝብ መብት ክበር ነገ ይቆማል ለማለት ፈጽሞ አልችልም። በጠራ ቋንቋ እራዕዩ እራቃኑን መለመላውን ቁሞ በደመነፍስ ይታዬኛል።
በምንም ሁኔታ፤ በዬትም ቦታ፤ አንድን ሰው መታደግ ስንችል፤ በአንድ ሰው መከራ እኩል መታዳም ስንፈቅድ ስለ ሚሊዮን አስባለሁ – እቆረቆራለሁ ማለቱ ያስኬዳል። ቁጥር ከአንድ ፍጥረትም ከእንቁላል ይጀምራል። ሰውነትም በፈተና ይነጥራል። አብሶ እንደ እኔ ላላ ተራ ባተሌ ዓለምና ፍላጎቶቿ ዝክንትል መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅም የዝክንትሏ ተሸካሚ ባሬያ ለመሆኑ መፍቀዱ ትዝብ ሳይሆን ሳልወለድ ቀርቼ ብሆን አብዝቼ እንድመርጥ እገደዳለሁ። ….
ይቋጭ። የኔዎቹ – ማንነቴን ለውጭ ሀገር ስሸልመው እራሴን ለባርነት እያዬሁ መሸጥ መለወጤን ይገልጸዋል። ኢትዮጵያውያን ማንነታችን ተበድረን ወይንም ተውሰነው ያልኖርንበት ተፈጥሯችን ዛሬን በቸልታ ከተመለከትነው በእርግጥም ፍላጎታችን – ራዕያችን – ተስፋችን እራሳችን አክስለነዋል ማለት ነው። ይህንን የወቅቱን ፈተና እግራችን ዘርግተን እምናስተናግድ ከሆነ „ኢትዮጵያዊነታችን ላይ ሞት ፈርድንበታል። ሰንድቅዓላማችን ጠቅጥቀነዋል ማለት ነው“
ይህ ስሜት፣ ይህ ቋያ፣ ይህ ነበልባል ዛሬን በድል ሊሞሽር – በአንድነት ሊብብ ሲገባ ነገር እዬሰነጠቁ ዳር ቆሞ ማዬት ወይንም መቆዘም – ማላገጥ ነው ለእኔ – ለሥርጉተ። ሁሉም እንደ አንድ ስክነትን ሰንቆ ማስተዋልን ምራኝ ብሎ በታቀደና በተደረጃ እንቅስቃሴ ለመጓዝ በተጠንቀቅ መጠብቅ አለበት። ለዚህ ቀስቃሽም ፕሮፖጋንዲስትም አያስፈልገውም። ሊስቡ ወ ይንንም በትርኪ ምርኪ ሊጎትቱ የሚፈለጉት እያራጋፉ አቅማችን ገንብተን ጥቃትን ማንጫጨት የወቅቱ መሪያችንና አጀንዳችን ሊሆን ይገባል እላላሁ እንደ ዘመኑ ታዳሚነቴ። ለነበርን ጊዜ ቁርጠኝነትን በፍቅር አቅልሜ ጋብዤ ልሰናበት። ቸር ወሬ ያሰማን። አሜን!
ጀግኖቻችን አምላካችን ይጠብቅልን!
እንበሳጭ!

No comments:
Post a Comment