Thursday, July 3, 2014

ለምን እንደያዝነው አናውቅም…. ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ በተመለከተ የመን ታይምስ እናየመን ቱደይ(አልዮም) ጋዜጦች ዘገቡ በግሩም ተ/ሀይማኖት via አብቢን


ለምን እንደያዝነው አናውቅም….
ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ በተመለከተ የመን ታይምስ እናየመን ቱደይ(አልዮም) ጋዜጦች ዘገቡ
በግሩም ተ/ሀይማኖት
የአቶ አንዳርጌ ጽጌ ጉዳይ አነጋጋሪ ከሆነ ሰንበት አለ፡፡ ወደ ኤርትራ እየተጓዘ ሳለ ለትራንዚት የመን ኤርፖርት ሲደርስ በኤርፖርቱ ደህንነት ሀላፊ ትዕዛዝ መያዙን ዛሬ የመን ውስጥ ለህትመት የበቁት ጋዜጦች ዘገቡ፡፡ የመን ቱደይ(የመን አሊየም) የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ሰኞ ማታ ወደ ኤርትራ በመጓዝ ላይ እያለ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ከሚባሉት ውስጥ የትጥቅ ትግል የሚካሂደው ግንቦት 7 ፓርቲ ሁለተኛ ሰው ስለሆነ የተያዘውም በዚሁ ነው ሲሉ የመን ታይምስ እና የመን ቱደይ ጽፈዋል፡፡
ተቃዋሚዎች ከየመን ባለስልጣናት ጋር ለመደራደር እና ለመጻጻፍ የሞከሩ ቢሆንም…ይላል የየመን አሊየም ዘገባ፡፡ ኢንፈሸል…በማለት አለመሳካቱንም ግልጾልናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የየመን መንግስትም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ‹‹..ዝምታ ነው መልሴ…›› ሲሉ እያቀነቀኑ ነው፡፡ የጋዜጣው ዘገባ እንደገለጸው ከሆነ ደግሞ ያዦቹ ለምን እና በምን ምክንያት እንደያዙት ሲየቁ ለምን እንደያዙት እንደማያውቁ መናገራቸውን ገልጾዋል፡፡ ለምን እንደያዙት ካለማወቃቸው ጋር ምስጢራዊ ሊያደርጉ የፈለጉበት ጉዳይ ደግሞ ግልጽና ግልጽ ነው፡፡ ለመረካከብ ድርድር ላይ እንደሚሆኑ መገመት አያቅተንም፡፡ ቢሆንም እንዳይሳካ ድምጻችንን እናሰማ…minilike salisawi ‹‹ግንቦት ሰባት እያለ ራሱን የሰየመውን ድርጅት መቃወም ማለት የአንዳርጋቸው ጽጌን የዘመናት ጀግንነት መካድ ማለት እንዳልሆነ እያንዳንዱ ስሜታዊ ፖለቲከኛ ሊረዳው የሚገባ ጉዳይ ነው።…እንዳለው እኛ የግንቦት ሰባት ደጋፊ ያልሆነውም ቢሆን ድምጻችንን ስለ አንዳርጌ ልናሰማ ግድ ይለናል፡፡ አንዳርጋቸው የሚታገለው ለእኛም ነጻነት ነው፡፡ አንዳርጋቸውን ፍለጋ በየመን ለሚለው እሳቤዬ ከረዳኝ ብዬ ..በኤርፖርት ሴኩሪቲ ሀላፊ ትዕዛዝ መያዙን በመስማቴ መደዛው ሄጄ ሳጠያይቅ ወደ ሌላ የደህንነት ቢሮ ማስረከባቸውን ነግረውኛል፡፡ የተባለው ቦታ ግን እንኳን እኔ ወፊቱም ያለፍቀዋድ ብትደርስ አሳሯ የምታይበት ነውና ወደዛ ለመሄድ አልሞከርኩም፡፡
እዚህ ጋር ግልጽ በግልጽ በሆነ ቋንቋ እናውራ ብንል ማንም ሊያውቀው የሚገባ እውነታ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ አለበት፡፡ ያለበለዚያ ሊያዝ የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ የመን ያለው ፖለቲካ ከአለም ለየት ያለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የቀድሞው ፕሬዘዳንት አሊ አብደላ ሳላ አል-ሀመር እያሉ መንግስት ላይ ጦር ያወጀው የየመን ከመላከያ ባለስልጣን ጄኔራል አሊማ ሁሴን አል-ሀመር እዚሁ ከተማ ውስጥ ተንደላቀው ተቀምጠው ነው ጦርነት የከፈቱት፡፡ በኤርፖርት ተጠቅመው ሳዑዲያ ኩዌት….እየሄዱ እየመጡ ነው ያዋጉት፡፡ አሁን ከዋና ከተማ ሰነዓ ከ50 ኪሎ ሜትር የማይበልጥ ርቀት ላይ ጦርነት እየገጠመ እና መንግስትን እያስለቀቀ ያለው ‹‹ሁቲ›› መሪ እዚሁ ሰነዓ ከተማ አለ፡፡ ሌሎችም ታጋዮች አሉ፡፡ ይህን ሁሉ የምገልጸው እነሱ ለራሳቸው ስልጣን የሚያሰጋቸውን ተቃዋሚ ተዋጊ ጦር መሪ በዋና ከተማቸው አስቀምጠው ምንም የማይነካቸው አንዳርጋቸውን የሚያስሩበት ምክንያት የለም፡፡ ይህ ቶሎ ድንብር የሚለው ኢህአዴግ ስራ ነው፡፡


Leading Ethiopian opposition figure detained in Yemen
Published on 3 July 2014 in News
Bassam Al-Khameri (author)
Tsegie’s Ginbot-7 is classed as a ‘terrorist group’ by Ethiopia’s government.


Tsegie’s Ginbot-7 is classed as a ‘terrorist group’ by Ethiopia’s government.
SANA’A, July 2–The Ginbot-7 Movement for Justice, Freedom and Democracy, an outlawed political organization in Ethiopia, claimed on Monday that the movement’s secretary general Andargachew Tsegie has been detained in Yemen since June 23.
According to the organization’s website, Tsegie was arrested at Sana’a International Airport while in transit from Ethiopia to London. Tsegie is an Ethiopian with British citizenship.
The circumstances of his arrest remain unclear.
In a press release published on the official Ginbot-7 website on June 30, the movement said that it had tried for a week to release Tsegie, adding that it had asked the Yemeni government not to hand him over to the Ethiopian government. “We will retaliate in any way and at any place for any harm done to the body, spirit and life of Andargachew Tsegie,” the movement warned.
Khalid Sheikh, the director of Sana’a International Airport, denied any knowledge of Tsegie’s alleged detention.
The Yemen Times contacted the Ethiopian Embassy in Sana’a, which claims to have no information on Tsegie’s alleged arrest so far. The British Embassy could not be reached.
Ethiopian news website Awramba Times cited a senior Ethiopian official as saying “Yemeni authorities will definitely issue an extradition warrant and he will face justice based on the Ethio-Yemeni Security Pact (EYSP), which was signed in 1999 between the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi and Yemeni’s former President Ali Abdallah Saleh.”
The website’s article did not give any further details of the arrest.
Ginbot-7 is a political movement that was founded by Dr. Berhanu Nega and that, according to its mission statement, aims to establish a national political system in which political authority is gained through peaceful and democratic means.
The Ethiopian government listed Ginbot-7 as a “terrorist group” in June 2011. Tsegie allegedly survived an attempted assassination in November 2013 in Asmara that Ginbot-7 holds the Ethiopian regime responsible for.

No comments:

Post a Comment