Thursday, July 3, 2014

ዛሬ ለዚህ ድሃ ፍትህ ላጣ ወገናችን የሞቀ ኑሮ፣ ትዳራቸውንና ቤተሰባቸውን ትተው ለህዝብ ነፃነትና እኩልነት ብሎም ይህን አፋኝ፣ ዘረኛና ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ አቋም ያለውን የወንበዴ ቡድን ከወገኖቻቸው ጋር ለመፋለም ታጥቀው...

ውድ ለኢትዮጵያ ነፃነት ለህዝባችን ፍትህና እኩልነት ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳትሉ በመታገል ላይ ያላችሁ ወገኖች በሙሉ 23 መራር እልህ አስጨራሽ የግፍ ዓመታት የሰው ጅቡ ወያኔ የተባለው የባንዳ ጥርቅም አገር ሻጪ የወንበዴ ቡድን በአገራችንና በድሃ ወገኖቻችን ላይ እየፈፀመ ያለው የአገር የወገን ልኧላዊነት አሳልፎ ለባእዳን የሰጠ፣ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገር አሰብን ለኤርትራ ሰጥቶ ያለ ወደብ ያስቀረና ለጅቡቲ በዓመት በርካታ ዶላር በማፍሰስ የወደብ ኪራይ የሚከፍልና ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለበትን የውኃ ችግር ሳይቀርፍ ለጅቡቲ መቶ ኪሎ ሜትር ኢትዮጵያ ውስጥ ገብታ በአካባቢው ያለውን ነዋሪ ደሃ ህዝብ በማፈናቀል ውኃ አውጥታ 30 ዓመት የሚቆይ ውል በነፃ ለመስጠት ሽርጉድ የሚል፣ በአገሪቱ ያሉትን ለም መሬቶች ያገራችንን ድሃ ገበሬ በማፈናቀል ለቻይና፣ ለህንድ፣ ለሳውዲና መሰል አገሮች ሲጋራ ሊገዛ በማይችል ገንዘብ በመቸብቸብ ላይ ያለን፣ እስክሪብቶና ወረቀት ይዘው ስለ እውነትና ፍትህ የፃፉትን ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ድርጅት አባሎችን፣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኰሚቴዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እስር ቤት አጉሮ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መፈፀም የማይገባውን ግፍ እየፈፀመ ይህ አልበቃ ብሎት ድንበር አልፎ ሌላ አገር በመግባት ሊያሳድደን መሞከሩ የመውደቂያው ጊዜ ላይ ለመሆኑ ከሚያደርገው መፍጨርጨር እንረዳለን።
ዛሬ ለዚህ ድሃ ፍትህ ላጣ ወገናችን የሞቀ ኑሮ፣ ትዳራቸውንና ቤተሰባቸውን ትተው ለህዝብ ነፃነትና እኩልነት ብሎም ይህን አፋኝ፣ ዘረኛና ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ አቋም ያለውን የወንበዴ ቡድን ከወገኖቻቸው ጋር ለመፋለም ታጥቀው የተነሱትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ጀግና አንዳርጋቸው ፅጌን በየመን ኤርፖርት በየመን ፀጥታ ኃይሎች ከተያዙ ከሳምንት በላይ ሆኗቸዋል ይህ ሁሉ ደባ የወንበዴው የዘራፊ ቡድን ሴራ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው እናም እያንዳንዳችን ከመቼውም የበለጠ አንድነታችንን አጠናክረን እኝህን ታላቅ የአገር የወገን አለኝታ ጀግናችንን ለመታደግና አንድ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዳልሆኑ ሚሊዮኖች አንዳርጋቸው ፅጌ ከጎናቸው እንዳሉ የምናሳይበት በአገር ቤትም ሆነ በተለይ ውጪ በስደት ዓለም የምንኖር ይህ ወሳኝ ሰዓት ነው እኔን አያገባኝም፣ ፓለቲካ አሎድም የምንልበት ጊዜ አይደለም አገራችን፣ ወገናችን በከፍተኛ የጭንቅ ሰዓት ላይና የኛን ድረሱልኝ ጥሪና ጩኸት እያሰማች ያለበት ወሳኝ ሰዓት ላይ ነው ስለዚህ ሁላችንም የዚህ ወሳኝ ሰዓት የጀግናው አንዳርጋቸምን እወያኔ እጅ እንዳይወድቁ ታላቅ ጥረት የምናደርግበት ወሳኝ ሰዓት ስለሆነ
1ኛ- ለያለንበት አገር የየመን ኤምባሲ ለወያኔ መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጣቸውና በአስቸኳይ እንዲለቃቸው በኢሜል፣ በስልክና ፋክስ ማስጨነቅ፣
2ኛ- አቶ አንዳርጋቸው የእንግሊዝ ዜግነት ስላላቸው የእንግሊዝ መንግስት በአስቸኳይ አቶ አንዳርጋቸውን እንዲለቅ ለየመን መንግስት ተፅእኖ እንዲያደርጉ መገፋፋት፣
3ኛ- ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ለአምስት ኢንተርናሽናል በያለንበት አገር ላሉት ማሳወቅ፣
4ኛ- በያለንበት አገር በቅርብ የምናውቃቸው ወገኖቻችን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከላይ እንደጠቀስኩት እኔ አያገባኝም፣ ፖለቲካ አልወድም ብለው በዳር ሆነው የሚመለከቱበት ጊዜ አይደለም እናም እነዚህን ወገኖቻችንን ይህን ወሳኝ ሰዓት ከጎናችን እንዲሆኑ መገፋፋት፡ አያቶቻችን፣ አባቶቻችን ታግለው ነፃ የሆነች አገር እንዳስረከቡን ዛሬ ይህን እልህ አስጨራሽ ሰዓት አንድ ሆነን አገራችን ከገባችበት ችግር አውጥተንና ይህን ዘረኛ ሥርዓት አንድ ሆነን ጥለን ለረጅም ዘመናት የተደከመለትን፣ የህይወት መስዋዕትነት የተከፈለበትን ህዝብ የመረጠው መንግስት በአገራችን እስኪቋቋም ድረስ መታገል አለብን ለልጆቻችን የተከበረችና ከዘርና ጭቆና ነፃ የሆነች እትዮጵያን ማስረከብ ታሪካዊ ግዴታ አለብን።
ሌላው ወያኔ የኛን አንድነትና ጥንካሬ ለመከፋፈልና ጊዜያችንን በስድብና ጭቅጭቅ እንድናጠፋ ሆዳደር የወያኔ አሽከር ቅጥረኞች በፌስ ቡክ ጓደኛ እየጠየቁን (friend requests) መሃላችን ገብተው የምናደርገውን ትግል ሞራል ለመንካት ስድብና አላስፈላጊ አስተያየት እየሰጡ ያሉ ሆዳሞችን ከጓደኝነት መሰረዝና ጭራሹኑ እኛ ፌስቡክ እንዳይገቡ (un friend & report/block) ማደረግ ወሳኝ ነው እነዚህ ሊማሩ የማይችሉ በጥቅም አይናቸው የታወረ ስለሆነና ከኛ ጋር ሆነው ሊራመዱና የምናደርገውን ትግል ማደናቀፍ የለባቸውም።

ባንዳው ወያኔ ሆይ አንዳርጋቸው ፅጌ ብቻውን ሳይሆን ሚሊዮኖች አንዳርጋቸው ፅጌ ከጎኑ መሆናችንን አትዘንጋ የበለጠ በቁጣ ትግሉን እያፋፋመው ነው!
ሞት ለአገር አጥፊውና ዘራፊው ወያኔና የእርሱ ምርኩዝ አሽከር ሆዳደር ባንዶች!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑር!!!
ተረፈ መኰንን ከኦስትሪያ
Like

No comments:

Post a Comment