Monday, June 16, 2014

ድል ለሰፊው አንድነት እና አንድ ኢትዮጵያን ናፋቂ ህዝብ



አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን፡፡ ቀጣይነት ያለው ትግል ውስጥ አስገቡንና እኛም እንታገል…!!! አለያ ሁሌም ሰበር ዜና እየተባለ አንዱ ሰበር ሲሄድ ሌላኛው ሰበር የሚቀጥል ከሆነ መቸም የድል ቀናችን ልንቀርበው አንችልም አደለም መያዝ!!
ሰላም ቀን ሌሊት
ድል ለሰፊው አንድነት እና አንድ ኢትዮጵያን ናፋቂ ህዝብ
እኔ የምቃወመው የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተነውን እንገነጠላለን አባዜ እና ሞኝነት እንዲሁም የኦሮሞ ፈርስት ጥያቄ ኦቭ አንዳንድ የኦሮሚያ ልጆችን ሃሳብ እንጅ ይህ የነፃነት ጥያቄ ኦቭ የኦሮሞ ልጆችን ሰላማዊ ሰልፍና የሰለጠነ አካሄድ ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ ድረስ እደግፈዋለው፡፡

አሁንም ልብ እንበል ኢህአዴግና የኢትዮጵያን አንድነት ለመበታተን የተነሱ አካላት አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ያልበሰለ አዕምሮ ባለመያዝም ይሁን በሌላ ሴራ ሊሆን ይችላል ወይም በሌላ በምን ምክንያት ብቻ ለወያኔ በሚመች መልኩ
ሰሞኑን የሚደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ሚኒሊክን የሚነቅፍ የሚያዋርድ መፈክሮች ተብለዋል ገለመሌ ሃሮማያ ላይ በተጣለ ቦንብ የተጎዱት አማራዎች ናቸው ይህንንም ያደረጉት ኦሮሞዎች ናቸው
እያሉ መርዛቸውን መርጨት ጀምረዋል እነ እንትና…ስለዚህ አማራ ሆይ ይህን ጉዳይ በትዕግስትና ከአሁን በፊት ከነበረህ ትዕግስት በላይ አስተዋይነት በላይ አድርገህ የወያኜ ማወናበጃና የራሱን ጥፋት ንፁህ ኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ላይ ለማላከክ ያደረገው ሴራ ስለሆነ በጥንቃቄ ማየት ይገባል፡፡
በቃ በቃ ይሁና እኛ ለሃገራችን አንድነት እንጅ ለሃበራችንና ህዝባችን ነፃነት እንጅ ለጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ተናቁረን ለእናንተ ለጋራ ጠላቶቻችን በር አንከፍትም በሏቸው እነዚህን ሴረኛ ወያኔዎች እና ደጋፊ አባላቶቻቸው፡፡
ይህ ሴራቸው ነው ይህ ሴራቸው ነው ይህ ሴራቸው ነው!!!
ስማኝ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊያን ናቸው ኦሮሞ ብሄር አካል ሆነ ሰው እንኳን ፈንጁን ጥሎት ቢሆን ይሁን የራሳችን አማራ እንደጨረሳቸው ፈንጁን አማራ እንደወረወረው አድርገንም ልንወስድ እንችላለን ያንን ህግ ይጨርሰዋል እንጅ አማራ ብሄር አይጨርሰውም የልጆቹ መሞት መቁሰል መጎዳት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሞትና መቁሰል ያሳምመዋል ስርዓቱ ክፍተትና የገዥው መንግስታችን ሳናደርገው መንግሰስት ነኝ የሚለን አካል ያበሳጨዋል ስርዓት አልበኝነቱና ለዜጎች ምን ያህል እንደማጨነቅ ለስዎች ህይወት ከፖለቲካው በላይ እንደማያይ ይሰማዋል ያቃጥለዋል እንጅ ሌሎች ወንድሞቹ ላይ ጣቱን አይቀስርም ይህ ባህሪውንም ለበርካታ መቶ አመታት ይዞት ቆይቷል እንደሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ፡፡
በመሰረቱ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ተግባር እንዲሰሩለት ተቃዋሚ የሆኑና ብሄርን ከብሄር ሊያጫርሱ የሚችሉ አስፀያፊ ተግባራትን ግድያዎችን እንዲፈፅሙለትና የእገሌ ብሄር አባላት ናቸው ይህን የፈፀሙብህ ለማለት እንዲመቸው ያሰማራቸው የሁሉም ብሄር አባላት ሴረኛና ሳይጣናዊ ፍጡራን ኢትዮጵያዊ የማይመስሉ ስዎችን አሰማርቷል፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ትግላችን በብስለት ማስኬድ አለብን፡፡ ትግላችን በዚህ መልክና እንዲህ አይነት ሴራዎችን መደምሰስ በሚያስችል መልክ ብቻ መጓዝ አለባቸው፡፡ ካልሆነ ግን ይህን ስርዓት ስልጣኑን ከማማሟቅ ውጭ ምንም ጥቅም የለውም፡፡
ይህን ፈንጅ የየትኛውም ብሄር አካል ይወርውረው ወንድሞቻችን ሟቾቹ ከየትኛውም ብሄር ይሁኑ እነርሱ ሞተዋል ልክ እንደ አምቦ ሟቾች ወንድም እህቶቻችን አምቦ ላይ ባህርዳር ላይ ጎንደር ላይ ሃሮማያ ላይ ወለጋ ላይ አዴት ላይ ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ላይ በርካታ ወንድም እህቶቻችን እየሞቱ እየቆሰሉ ነው፡፡ እናም የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ሟችና ቁስለኛ ወንድምና እህቶቻችን የእኛ ናቸው የገደሏቸውም ከእኛ የወጡ ናቸው ኢትዮጵያዊ ገዳዮች ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ገደሉ አቆሰሉ…ይህን ድርጊት ከልብ እናወግዛለን…እንቃወማለን እንታገለዋለን፡፡
ግን መንግስት ያሴረው ሴራ እንደሆነ አናጣውም፡፡ በመሆኑም ጥያቄያችን ስርዓቱ ራሱን ከስልጣን ማውረድ አለበት እንጅ ራሱን ያስተካክል ብለን ለሌላ የስቃይ ዘመናት ራሳችን አሳልፈን አንሰጥም፡፡ ልቀቁንንንንንን….
 በቃ የየትኛውም ሆነ የየትኛው ብሄር ፈንጁን ይወርውረው ስዎቹ ንፁሀን ተማሪዎቹ ሞተዋል ቆስለዋል ይህ ሊወገዝ የሚገባው የሚያሳዝን ክስተት ነው፡፡ ሆኖም ግን አንድ ደነዝ የየትኛውም ብሄር አባል ይህን አደረገ ብለን አንድ ብሄር የአማራ ህዝብ ሄዶ ሚገጥምበት ጦርነት የሚከፍትበት እውነት በአማራ ህዝብ ታሪክ የለም፡፡ አንድነት አንዲት ሃገር አንድ የሆነ ህዝብ የሚሻ ኩሩ ህዝብ ነውና አማራ፡፡
ይህ ሲባል ግን አማራ ህዝብ ራሱን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድምና እህቶቹ ጋር በመሆን ስርዓቱን በአፍ ጢሙ ለመድፋት አይታጠቅም አይዘጋጅም አይነሰም ማለት አደለም፡፡
ነገር ግን ሸም ኦን በአማራ ላይ ለሚያሴርና ለማጥፋት የሚነሳ ስዕተት መሆኑ ያልገባው ዜጋ እንጅ አማራማ ትግሉና ጦርነቱ ገዥው ስርዓት ጋር እንጅ ከወንድም እህቶቹ ጋር አደለም፡፡ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከሶማሌ፣ ከጋምቤላ፣ ከትግራይ፣ ከጉሙዝና ከደቡብ ወንድምና እህቶቹ ጋር ጦርነት ግባ ሊጨርሱህ ነው ገለመሌ የሚል ሁሉ…ወደ ተሳሳተ መስመር እየመሩት እንደሆነ የአማራ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃልና ማንም መሪ ማንም አስታዋሽ ኣያስፈልገውም፡፡
አሁን አማራ የሚፈልገው አንድ ኢትዮጵያና አንድ ህዝብን በአንዲት እናት ሃገር ስር  ለመፍጠርና ልትበታተን ምንም ያልቀራትን ኢትዮጵያ የሚደግፍና የሚያነሳላት ጠላቶቿን ከፋፋዮቿን የሚያጠፋለት ሃይል የሚተባበር ሃይል እንጅ ማንንም ከፋፋይና ልዩነት ፈጣሪ አካል አይሻም፡፡

እባካችሁን ከስዕተታችሁ ተማሩ ይህን ሴራ ያሴራችሁ አካላት
ድል ለሰፊው ህዝብ
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ሞት ለከፋፋዮችና ለበታታኞች

No comments:

Post a Comment