አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
የሀገራችን አንዱ ችግር ትክክለኛው ሰው በትክክለኛው ቦታ አለመቀመጡ ነው::
#Ethiopia #EPRDF #UDJ #AEUP #Blueparty addisadmassnews.com
ዛሬ፤ በዕውቀት ብርሃን የተጋ ዜጋ ያስፈልገናል፡፡
አገኘን የምንለውን ድል በአግባቡ ካልተጠቀምንበትና በዚያ ተኩራርተን ትርፍ መንገድ እንሂድ ካልን የጥፋተኝነታችንን ያህል ኪሣራውን መክፈል ግዴታችን ይሆናል፡፡የጋራ አገር እንዳለን እንዲሰማን ያስፈልጋል፡፡ በጋራ እንደግ ብሎ ልብን መክፈት ያስፈልጋል፡፡ አገር ጥቂቶች የሚለፉባት ሌሎች የሚያፌዙባት እንዳልሆነች መገንዘብ ይገባል፡፡ ሀገራችንን በጋራ ዐይን እንያት፡፡ የእኔ መከራ ያንተ መከራ አይደለምን? እንባባል፡፡ የሀገርን አንድነት፣ የሀገርን ኢኮኖሚ፣ የሀገርን ባህል፤ ተጠንቅቆ ጠብቆ በቅጥ በቅጡ ለማቆየት፤ በፍቅርና በመተሳሰብ እንጂ “የራቀውን በመድፍ፣ የቀረበውን በሰይፍ” የምንልበት የምንበቃቀልበት፣ የምንጠፋፋበት ዓይነቱ ዘዴ፤ ቢያንስ ዘመናዊ አይደለም፡፡ “ጀግናን ዘገንኩና አፈር ብዬ ተውኩት”፣ እንዳለች ዕድሜዋን ትገፋለች አሉ የጐበዝ አገር እናት፡፡ ዛሬ፤ በዕውቀት ብርሃን የተጋ ዜጋ ያስፈልገናል፡፡
ያለሙያ መግባት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ አገኘን የምንለውን ድል በአግባቡ ካልተጠቀምንበትና በዚያ ተኩራርተን ትርፍ መንገድ እንሂድ ካልን የጥፋተኝነታችንን ያህል ኪሣራውን መክፈል ግዴታችን ይሆናል፡፡ ፖለቲከኛው ባለሙያው ሥራ ውስጥ ተሸብልቆ ከገባ፣ ባለሙያ ባንድ ጀንበር ፖለቲከኛ ነኝ ብሎ ከተፈጠመ፤ ጉዟችን የእውር የድንብር ነው የሚሆነው፡፡ በእጃችን ያለውን ሙያ ትተን የማያገባን ሥር ውስጥ ገብተን መቧቸር ከሁለት ያጣ ያደርገናል። የሰለጠንበት ሙያ ሌላ፤ የምንሠራው ሥራ ሌላ ከሆነ፤ ከሁለት ያጣ እንሆናለን፡፡
የራሳችንንም ሥራ አልሠራን፤ ሌሎችም ሥራ እንዳይሠሩ አደረግን፡፡ የሀገራችን አንዱ ችግር ትክክለኛው ሰው በትክክለኛው ቦታ አለመቀመጡ ነው ወይ በዘመድ፣ ወይ በታሪክ አጋጣሚ፣ አሊያም በዕድል ያለሙያችን የተቀመጥንበት ቦታ ከልማቱ ጥፋቱ ይበዛል፡፡ ሁሉ በጄ፣ ሁሉ በደጄ ማለታችን አይቀርምና ከእኛ በላይ የሚያውቅን ሰው አላግባብ ማጐሳቆላችን፣ “እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ፣ እኔ ያልኩትን ብቻ ፈጽሙ” ወደሚል ግትርነት ማዘንበላችን አይቀሬ ነው፡፡ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የአተካሮና የውሃ ወቀጣ ባህልን ዘሎ ማሰብ የሚችል አዕምሮ ብቻ ነው የመፍጠር ክህሎትን የሚቀዳጅ፡፡ ነፃ አዕምሮ ነፃ አስተያየትን ይወልዳል፡፡ ራሳችንን መጠየቅ ያባት ነው፡፡ በተግባር የማንፈጽመውን አዋጅ ማወጅ፣ የማንከውነውን መመሪያ ማውጣት፣ በዕውቀት ላይ ያልተመሠረተ ፖለቲካ ማውራት፣ የሩቁን ትተን የዕለት የዕለቱን ብቻ እያወራን በአየር ላይ መኖር፤ መሠረት ያለው፣ ዕውቀትን የተንተራሰ ከወሬ ያለፈ ህብረተሰብ ለመገንባት ጥረት እናድርግ፡፡

No comments:
Post a Comment