Monday, June 16, 2014

ስለዚህ የትኛውም ሰላማዊ ታጋይም ይሑን የጫካ ነፃነት ታጋይ ይሕን አስበውበት ፍትሃዊ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪየን አቀርባለው፡፡



ኢትዮጵያ ፍትሃዊ ትግል ትፈልጋለች የትኛውም ታጋይ በየትኛውም ታጋይ መስዋዕትነት መሆን የለበትም የኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያን ነፃነት ማግኘትና ማስገኘት ያለበት ነገር ግን ይሕ ነፃነት መገኘት ያለበት ራሱ በራሱ መስዋዕትነት ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ በወንድሙና ስጋዊ እህቱ ሞት ብቻ አደለም ማልቀስ ሙሾ መደርደር ያለበት ይህ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሞት መሆን አለበት፡፡ የአንዱ ኢትዮጵያዊ ህይወት መጥፋት ነገ የእርሱም እንደሚጠፋ በማሰብ ብቻ መሆን የለበትም መታገልና መውጣት ያለበት…ለምን ማለት ያለበት ለምን ይህ ኢትዮጵያዊ በግፍ ይሞታል ነው፡፡
ህይወት ማጥፋት ፍትሃዊ ሊሆን ይችላል መቼም ኢህአዴግና ከግነቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል የሚመራቸው ድርጅቶች ወይም ከአርበኞች ግንባር ወይም ከትህዴን ወይም ከአማራ ፎርስ እንዲሁም ከኦነግና ለፍትህና እኩልነት ሰራዊት ጋር ጦርነት ገጥመው ሰው ቢሞተ ፍትሃዊ አደለም አንልም ሁለቱም አቅጣጫቸው ፍፁም ተቃራኒ ነውና አንደኛው ነፃነት ናፋቂ ሌላኛው ነፃነት ነፋጊ ናቸውና፡፡
ነገር ግን ልክ እንደ ወያኔ እና ኢህአሰ /ኢህአፓ/ ሰራዊት አርበኞችና ትህዴን ቢፋጁ ግን ይህ ፍትሃዊ አደለም እንዲህ ብሎ የመጣ ሃይልም እንደ ወያኜ ጠብቁኝ መጠሁባችሁ እንደማለት እንጅ መጠሁላችሁ ሊሆን እንደማይችል ጠንቅቀን ማወቅ አያቅተንም፡፡
ስለዚህ የትኛውም ሰላማዊ ታጋይም ይሑን የጫካ ነፃነት ታጋይ ይሕን አስበውበት ፍትሃዊ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪየን አቀርባለው፡፡
አብቢን ነኝ

No comments:

Post a Comment