አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
ሰማያዊ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ አስታወቀ
June 17/2014
አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ ሰኔ 8/2006 ዓ.ም ባደረገው የብሄራዊ ምክር ቤት ሁለተኛ አመት ልዩና አስቸኳይ ሁለተኛ ስብሰባ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የምክር ቤት ተጠባባቂ አባላት፣ ኦዲትና ኢንስፔክሽን እንዲሁም ስራ አስፈጻሚውን ጨምሮ ውይይት በተደረገበት ወቅት ፓርቲው መጭውን 2007 ምርጫ አስመልክቶ ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ እንዲኖር፣ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲደረግና ፓርቲዎች እርስ በእርሳቸው እንዳይወዳደሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ከአቻ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት እና ውስጣዊ አደረጃጀቱን በማጠናከር የአገሪቱ አማራጭ የፖለቲካ ኃይል ሆኖ ለመቅረብ የስምምነት ሀሳብ ላይ መድረሱን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

‹‹ወቅታዊ በተለይም የውህደት፣ ትብብርና ቅንጅት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ፓርቲው የሚያራምደው አቋም ላይ ውይይት
በማድረግ የተደረሰበት የውሳኔ ሀሳብ ፓርቲውን ወደፊት አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ በአጠቃላይ የአገሪቱን ህዝብም
ለማስተባበርና በትግሉ ለማሳተፍ ጠንክሮ የፓርቲው አደረጃጀት ላይ መስራት እንደ ዋና አማራጭ ተወስዷል›› ያሉት
ኃላፊው ‹‹ከዚህ ጋር ተያይዞ በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ እየጠበበ የሚመጣውን
የፖለቲካ ምህዳር ለማስከፈትና ፍትሃዊ እንዲሆን ለማስገደድ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ፓርቲዎች ጋር
ተባብሮ ለመስራትና መልካም ግንኙነት ለመፍጠር በርካታ ስራዎችን በጋራ እንሰራለን፡፡›› ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ‹‹ያለፈው የአገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውህደት፣ ቅንጅት፣ ግንባር ባልተጠና እና ውስጣዊ አቅም ሳይፈጠር የሚፈጸም በመሆኑ ውድቀትንና ተስፋ መቁረጥን ሲያስከትል እዚህ ደርሰናል›› ያሉት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ይህን በማገናዘብ ፓርቲያቸው የተለየ አማራጭና አካሄድ ይዞ እንደመጣ ገልጸዋል፡፡

No comments:
Post a Comment