Wednesday, June 18, 2014

የመሪዎቻችን ችሎት ዛሬም ቀጥሏል! የጀግናው ኮሚቴ አባል የነበሩት ሐጂ ዩሱፍ ሙዘሚል ምስክርነታቸውን አሰምተዋል! ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

#‎EthioMuslimPrisoners‬ ‪#‎EthioMuslimCommitteeTrial‬
የመሪዎቻችን ችሎት ዛሬም ቀጥሏል!
የጀግናው ኮሚቴ አባል የነበሩት ሐጂ ዩሱፍ ሙዘሚል ምስክርነታቸውን አሰምተዋል!
ረቡእ ሰኔ 11/2006
የጀግኖች ታሳሪዎቻችን ችሎት ትናንትና እና ዛሬ ቀጥሎ ውሏል፡፡ ትናንት በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ብቻ በተሰየመው ችሎት የኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ዑመር አብዱረዛቅ ቀሪውን ምስክርነታቸውን በሌሎች ጭብጦች ላይ አቅርበዋል፡፡ በተለይም ‹‹ኮሚቴው አክራሪ ሚዲያ አቋቁሟል›› በሚል የቀረበውን ክስ አስመልክተው በስፋት ማስተባበያ የሰጡ ሲሆን ኮሚቴው አንዳችም ያቋቋመው ሚዲያ ስላለመኖሩ፣ የተጠቀሱት ሚዲያዎችም በህጋዊ መንገድ የተቋቋሙ መሆናቸውንና አሁን በእስር ከሚገኙት ጋዜጠኞችም ሆነ ከሌሎች ሙስሊም ጋዜጠኞች ጋር ኮሚቴው የነበረው ግንኙነት እንደማንኛውም የሚዲያ ተቋም ግንኙነት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም መንግስት ኮሚቴውን በህገ ወጥነት ከመፈረጅ አንስቶ የተለያዩ ህገወጥ የጥቃት እርምጃዎችን መውሰዱን በማንሳት ኮሚቴው በዚህ ሁሉ ወቅት ህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ከማድረግ የዘለለ አንዳችም አጥፊ ሚና ያልነበረው መሆኑን መስክረዋል፡፡
ዛሬ ጠዋትና ከሰዓት በዋለው ችሎት ደግሞ ምስክርነታቸውን ያሰሙት የጀግናው ኮሚቴ አባልና የሸኽ ሆጀሌ መስጊድ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሐጂ ዩሱፍ ሙዘሚል ሲሆኑ እሳቸውም ምስክርነታቸውን በጥሩ ሁኔታ አሰምተዋል፡፡ በተለይም ኮሚቴው ህጋዊ ውክልና ያገኘበትን ህዝባዊ ሂደት በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ከተመረጡት 20 ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በተለያዩ ምክንያቶች መሳተፍ ባለመቻላቸው በሁለተኛው ዙር ጥሩ ማህበራዊ ስብጥር ያለው ኮሚቴ ተመርጦ በህዝብ መጽደቁን አብራርተዋል፡፡ በመጀመሪያዎቹ ወቅቶችም ይኸው ኮሚቴ ከተለያዩ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት የህዝቡን ፍላጎት ለማሳወቅ ጥረት ማድረጉን አውስተዋል፡፡ ‹‹መንግስት በግልጽ ሁኔታ በሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል›› ያሉት ሐጂ ዩሱፍ በወቅቱ ሲስተዋሉ የነበሩትን የመንግስት አይን ያወጡ የጣልቃ ገብነት ድርጊቶች በስፋት በመዘርዘር አቋማቸውን በበርካታ ማስረጃዎች አስደግፈው አቅርበዋል፡፡ በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ላይ በጥሩ ሁኔታ ምስክርነታቸውን አስደምጠዋል፡፡
ችሎቱ በነገው እለት ከተከሳሽ ጀግኖቻችን መካከል አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ አቡበከር ዓለሙ የህክምና ቀጠሮ ያለው በመሆኑ የምስክር መስማቱን ሂደት ለመቀጠል ለአርብ ሰኔ 13 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል፡፡
የሐሰት ከስ አይገዛንም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!

No comments:

Post a Comment