Sunday, June 29, 2014

እንዴት ዴሊት አድርገን የጠፉ ፋይሎችን መመለስ እንችላለን?

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
እንዴት ዴሊት አድርገን የጠፉ ፋይሎችን መመለስ እንችላለን?
ከኮምፒውተሩ ዴስክ ቶፕ፣ ማይ ኮምፒውተር፣ ማይ ዶክመንት ወዘተ የኮምፒውተሩ ክፍል ላይ በስህተት ወይም ፈልገን ዶክመንቶችን ሲጠፋብን ፋይሎቹን መመለስ እንችላለን፡፡
የጠፉ ፋይሎችን ለመመለስ የምንከተለው ሂደት(ስቴፕ)
1. ከኮምፒውተሩ ላይ የሚጠፉ ፋይሎች የሚቀመጡት ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ሲጫን በተዘጋጀው ሪሳክልቢን (Recycle Bin) አይከን ውስጥ ሲሆን አይከኑን በዴስክቶፕ ላይ እናገኘዋለን በቀላሉ አይከኑን በመክፈት የምንመልሰው ፋይል ላይ right-click በማድረግ Restore. በማለት መመለስ

2. ፋይሉ ከመጥፋቱ በፊት ባክአፕ እንዲሆነን በሌላ የኮምፒውተሩ ሃርድ ዲስክ ክፍል ላይ አስቀምጠን ከሆነ እንዲሁም በሲዲ፣ በዲቪዲ፣ በኤክስተርናል ሃርድዲስክ ፋይሉን አስቀምጠን ከሆነ በቀላሉ ፋይሉን ኮፒ አድርገን በማምጣት ወደነበረበት መመለስ እንችላለን
3. ፋይሉን ባክአፕ ሳንወስድ እንዲሁም ከሪሳክል ቢን ውስጥ አጥፍተነው ከሆነ፣ ሽፍት + ዴሊትን ተጠቅመን አጥፍተን ከሆነ፣ የጠፉ ፋይሎችን ሪከቨር አድርጎ የሚመልስ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም የጠፉ ፋይሎችን መመለስ እንችላለን የተለያዮ ሪከቨር ማድረጊያ ሶፍትዌሮች ያሉ ሲሆን እኔ ግን እንድትጠቀሙ የምነግራችሁ Recuva Portable ሶፍትዌርን ሲሆን ሶፍትዌሩ ለመጠቀም ቀላል ሲሆን ከዚህ በፊት ዴሊት ተደርገው ከኮምፒውተር ላይ የጠፉ ፋይሎችን፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮ ሪከቨር በማድረግ ይመልሳል ሶፍትዌሩን ከጎጉል ላይ በቀላሉ በመፈለግ ዳውንሎድ አድርገን መጫን እንችላለን ምንም አይነት ክፍያም ሆነ የተወሰነ ግዜ ብቻ ለማስጠቀም ሳይሆን የሚሰራው በነፃ ነው፡፡
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
ላይክ ሸር ያድርጉ
Share your knowledge free for millions

No comments:

Post a Comment