አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
***** ይድረስ ለዲሞክራሲ ሐይሎች ******
=============================
Ermias Legesse
(የቀድሞው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚ/ር ሚኒስትር ደኤታ)
በቅርብ ቀን ከአሜሪካ ድምጵ ሬዲዬ ጋር ያደረኩትን ቃለመጠይቅ https://soundcloud.com/voa-amharic/14-2014-3 እና እውር ድንበሩ የወጣበትን የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ሰምታችኋል ። ለኢትዮጵያ ህዝብ የቀረበበት አግባብ ፍትሐዊነት የጐደለውና የሚዲያ ስነምግባር ያልተከተለ ነበር። በዚህም ምክንያት ለተወዳጁ ጋዜጠኛ አዲሱ በስልክ ቅሬታዬን አቅርቤያለሁ ። ለጣቢያው አመራሮች ደግሞ ፎርማል ደብዳቤ እያዘጋጀሁ ነው። እውነቱን ማወቅ መብቱ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ምላሽ እንደሚሰጡ ተስፉ አደርጋለሁ ። ይህን ካላደረጉ ግን " የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ የሆኑ" ሚዲያዎች ምሥጋና ይግባቸውና ጊዜ ሳንሰጥ እውነቱን አውጥተን የለመዱትን የሀፍረት ማቅ ይለብሳሉ። ጉዳዩ የኩሸት ጥርቅም የሆነውን ኢሕአዴግ ማጋለጥ ብቻ ሳይሆን VOA ያጋጠመውን መስቀለኛ መንገድ ማሳየትም ጭምር ይሆናል። ሂደቱ ያመላከተኝ ነገር ቢኖር የሃገራችን አምባገነኖች ከኢትዮጵያ ተሻግረው VOA ላይ ለመጨፈር እየተዘጋጁ መሆናቸውን ነው። ይህ ተራ ሐሜት እንዳይሆን በደብዳቤዬ ላይ ከተካተቱት የተወሰኑትን ላካፍላችሁ።
1• ጋዜጠኛ አዲሱ ቃለመጠይቅ ሊያደርግልኝ እንደሚፈልግ ሲጠይቀኝ በመጀመሪያ የገለጵኩለት የበላይ ሀላፊያችሁ Peter በሆነበት ሁኔታ ፍቃደኛ አይደለሁም የሚል ነበር። Peter የፈፀመው ነውረኛ ተግባር ያውቀዋልና የእኔ ወደ VOA መቅረብ እንደሚያስበረግገው አውቃለሁ። ከተወሰነ መከራከር በኋላ ለጋዜጠኛ አዲሱ ካለኝ ክብር በመነሳት ፍቃደኛ ሆኛለሁ። ይህም ሆኖ Peter ኢትዮጵያ በነበረ ሰአት የፈፀመውን ነውር የተናገርኩ ቢሆንም ተቆርጦ እንዲወጣ ተደርጓል ። ይህ መረጃ ቢወጣ የግለሰቡ ነውር ብቻ ሳይሆን የቪኦኤ አማርኛ ክፍል ያጋጠመው አደገኛ ሁኔታም ውስን ክፍል ይጋለጥ ነበር። ራሴን ወደ ኢትዮጵያ ህዝብ ያወጣሁት ዋነኛ ምክንያት ለእውነተኛ መረጃ ነውና በቅርብ ይፉ አደርጋለሁ ።
2• ሁለተኛው ስህተት የኢህአዴግ ባለሥልጣናት እኔ የሰጠሁት ቃለ መጠይቅ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከመቅረቡ በፊት እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በጣም የሚያሳዝነው ከአንዴም ለሁለተኛ ዙር መደረጉ ነው። ይህ እንደሚሆን አስቀድሞ ቢነገረኝ ኖሮ ለቃለ መጠይቁ ፍቃደኛ አልሆንም ነበር። ከሚዲያ ሥነምግባር አንፃር ትክክል አይመስለኝም ።
መሆን የሚገባው፣
ሀ) ሁለታችንንም ፊትለፊት አጋጥሞ ማከራከር ነበር። በእርግጥ ይህ እንደማይሆን አውቅ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ " ሐገር ወዳዱ ኢህአዴግ! " ሌሎችን " በሐገር መክዳት" እና " ሽብርተኛ " ከፈረጀ ፊትለፊት በመግባት ምላሽ አይሰጥም ። ይህን ቪኦኤ በደንብ የሚያውቁት ነው ።
ለ) የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብረው እንዲያውቁት ተደርጐ ቃል በቃል ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ ነበር። በዚህም ቢሆን ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አይሆኑም።
ስለዚህ ለአምባገነኖች በሚፈልጉት መልኩ ተደረገላቸው ። ለዚህም ቢሆን ምላሽ ወደ መስጠት ያስገባችው ጉዳይ አንድና አንድ ብቻ ነው። እኔ ባቀረብኩት 5% የማይሞላ መረጃ የኢህአዴግ አባላት የህዋስና መሰረታዊ ድርጅት ( በተለይም በአዲሳአባ) ለሁለት ተከፍለው መጨቃጨቅ መጀመራቸው ነው። በቅርቡ የአዲሳአባ ኢሕአዴግ ቢሮ ውስጠ ድርጅት ሰነድ እንደሚያዘጋጅና የማጨድ ስራ እንደሚሰራ ሰምቻለሁ ።
ሌላው አስቂኝ ነገር ምላሽ እንዲሰጥ የተመረጠው ለሆዱ ያደረ ግለሰብ የሰጣቸው መልሶች ገሃድ የወጡ ውሸቶችን መሸከሙ ነው። እነ በረከት ዛሬም ከራሳቸው ስም ውጪ ሌላውን በከርሱና የሚያቀርቡለት የጫት መጠን( ሬድዋን፣ሽመልስ፣ገነነው ፣ሚሊዬን፣ ሚሚ፣ዛዲግ…) መመዘን አጠናክረው መቀጠላቸውን ነው።
ለእኔ ምላሽ የተመደበው ሆድአደሩ ጌታቸው በአካል ለአንዲት ቀን ተያይተን አናውቅም ። ሊያውቀኝ ይችል ይሆናል እንጂ አላውቀውም ።በየትኛውም ደረጃ(ከፍተኛ፣መካከለኛ፣ዝቅተኛ) ካድሬ ስላልነበረ አላውቀውም ። ፊትለፊት ብንገናኝ የምጠይቀው የመጀመሪያ ጥያቄ ይህ ነበር።
ከሁሉም በላይ እነ በረከት ሰውየውን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ያዋረዱት ሽርፍራፊ መረጃ ሳይሠጡት ማጋፈጣቸው ነበር። ሆድአደሩ ጌቾ ሳያቅማማ እንዲህ በማለት ተናገረ፣
" … ሚስቴን እጠይቃለሁ ብሎ አሜሪካን ሄዶ በዛው ኮብልሎ ቀረ!!"
እኔ ጌቾን ብሆን የዚህን ምላሽ ስሰማ ወይ መልቀቂያ አስገባለሁ፣ አሊያም የአሜሪካን ቪዛዬ ካልተቃጠለ ኢህአዴግን ከድቼ ከሐገር እኮበልላለሁ። ምክንያቱም ከእንግዲህ የምናገረውን ማንም ስለማያምነኝ !!! ጌቾ ወዳጆቼ በውስጥ በኩል ገብተው ይቅርታ እንድትጠይቅ እንደመከሩህ ነግረውኛል። እኔም ቢሆን ይህን ካደረክ " የኢትዮጵያን ህዝብ" ይቅርታ እንደጠየክ እቆጥረዋለሁ ። ትግሌ ላኪዎችህን በዚህ ማእቀፍ ማስገባት ስለሆነ ምንም ከማታውቀው ጋር ፀብ የለኝም። በሌሎቹም ጉዳዬች ላይ ተራ በተራ እመጣበታለሁ። ቪኦኤን በጠየኩት መሰረት ፊትለፊት ለመገናኘት ጫት አቅራቢ አለቆችህ ከፈቀዱልህ ሂሳባችንን እዛው እናወራርዳለን። የዛ ሰው ይበለን።
( ለወዳጆቼ የደረስኩበትን በየጊዜው አሳውቃለሁ።)

No comments:
Post a Comment