Friday, June 20, 2014

ማዳበርያ ያልገዙ መሬታቸው ሊነጠቁ ነው!

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

ማዳበርያ ያልገዙ መሬታቸው ሊነጠቁ ነው!
============================
በሑመራ መንግስት በተመነው ዋጋ ማዳበርያ ለመግዛት ፍቃደኛ ያልሆኑ አስራ አንድ ኢንቨስተሮች የተሰጣቸውን መሬት ተነጥቆ ህወሓትን ለሚደግፉ 'ባለሃብቶች' እንዲሰጥ ተወሰነ። እንዲህ ነው ፍትህና እኩልነት። መዳበርያ አለመግዛት መሬትን የሚያስነጥቅ ወንጀል ሆነ። መዳበርያ መግዛት መብት እንጂ ግዴታ አልነበረም። ግን ምን ዋጋ አለው፤ መሬት የመንግስት ሆነ እንጂ የህዝብ ቢሆንማ ኑሮ ኢንቨስተሮቹ በመንግስት አካላት ላይ ክስ መስርተው መሬታቸው ማስመለስ ይችሉ ነበር። መሬት የህዝብ ቢሆን ኑሮ የህወሓት ካድሬዎችም ቢሆኑ የዜጎችን መሬት በጭፍን ባልነጠቁ ነበር። መሬት የመንግስት ሳይሆን የህዝብ ይሁን። መንግስት ህዝብን ማስተዳደር እንጂ የመሬት ባለቤት የመሆን ስልጣን ሊሰጠው አይገባም። ማዳበርያም በፍላጎት ከገበያ የሚሸመት እንጂ በግዳጅ በመንግስት አካላት የሚሰጥ መሆን የለበትም።

No comments:

Post a Comment