Wednesday, June 18, 2014

የአፍሪካ ህብረት በግብጽ ላይ ጥሎት የነበረውን የአባልነት እገዳ አንስቷል፡፡

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
የአፍሪካ ህብረት በግብጽ ላይ ጥሎት የነበረውን የአባልነት እገዳ አንስቷል፡፡
የህብረቱ የጸጥታው ምክር ቤት በትላንትናው እለት (ሰኔ 10 2206 ዓ.ም) ባካሄደው ስብሰባ ‹‹ በግብጽ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ በመካሄዱ ›› ሀገሪቱ ተጥሎባት የነበረው እገዳ እንዲነሳ መደረጉ ተገልጿል፡፡
የሆስኒ ሙባረክን በህዝብ አመጽ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ የመጀመሪያው በህዝብ የተመረጡ የግብጽ መሪ ለመሆን የቻሉት ሙሀመድ ሙርሲ ፤ በአሁኑ የግብጽ መሪ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አማካኝነት ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት በግብጽ የተካሄደው ‹‹ መፈንቅለ መንግስት ነው ›› በሚል ግብጽን ከህብረቱ አባልነት እንድትታገድ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
ምንም እንኳ የህብረቱ የጸጥታው ምክር ቤት ግብጽ ‹‹ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ አካሂዳለች›› በሚል ምክንያት ወደ አባልነቷ እንድትመለስ ቢፈቅድም አሁን በግብጽ ስልጣኑንን የያዙት አል ሲሲ የአፍካ ህብረት ‹‹መፈንቅለ መንግስት ነው›› ብሎ ያመነበትን ተግባር የፈጸሙ መሆናቸው እና በእሳቸው ለለቋቋመው አዲሱ መንግስት እውቅና መስጠት ‹‹ ለመፈንቅለ መንግስቱ እውቅና እንደመስጠት ነው›› የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡
ግብጽ ወደ አፍሪካ ህብረት አባልነቷ መመለሷን ተከትሎ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስን ጨምሮ ተለያዩ አፍሪካ ዲፕሎማቶች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ለግብጽ ባለስልጣናት እየላኩም ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም ግብጽ በሚቀጥለው ሳምንት በኢኳሪያል ጊኒ - ማላቦ በሚደረገው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ የምትሳተፍ ሲሆን ሀገሪቱ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ የነበራትን ተሰሚነት ዳግም ለማደስ ጥረት እንደሚያደርጉም የግብጽ ባለስልጣናት እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡

No comments:

Post a Comment