Thursday, June 19, 2014

የአዲሰ አበባ መጅሊስ አመራሮች የታላቁ አንዋር መስጅድ ኢማምን ይቅርታ ጠየቁ፡፡

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
©BBN ቢቢኤን የናንተው ድምፅ 12/2006
የአዲሰ አበባ መጅሊስ አመራሮች የታላቁ አንዋር መስጅድ ኢማምን ይቅርታ ጠየቁ፡፡
የአዲሰ አበባ መጅሊስ ፕረዝዳንት ዶ/ር አህመድ እና የፅ/ቤት ሃላፊ ሐጂ ክንዱ ካሳው የታላቁ አንዋር መስጅድ ኢማም የሆኑትን ሐጂ ጣሃ ሃሩንን ይቅርታ መጠየቃችው ታወቀ፡፡
የመጅሊሱ አመራሮች ኢማሙን ይቅርታ ለመጠየቅ የስገደዳቸው ከዚህ ቀደም ሼህ ጣሃ ከፌደራል መጅሊስ አመራሮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስለነበራቸው የአዲስ አበባው መጅሊስ አመራሮቹ በድብቅ ሁለት ጊዜ ኢማሙን ከቦታቸው ለማንሳት የደረጉት ሙከራ ስላልተሳካለቸው በዚህም አጋጣሚ ሼህ ጣሃ ከኢማምነታቸው በተጨማሪ በፌደራል መጅሊስ ውስጥ ቁልፍ ባለስልጣኖችን በእጃቸው እንዳደረጉ የአዲስ አበባ የመጅሊሱ አመራሮች በመገንዘባቸው ነው፡፡
ሼህ ጣሃ በበኩላቸው ይቅርታው ተቀባይነት እንዲኖረው እንደ መደራደሪያ ነጥብ ያስቀመጡት በታላቁ አንዋር መስጅድ ውስጥ በአስተዳደርነት በቅርብ ጊዜ የተሾሙትን እና በከፍተኛ ሁኔታ ያስቸገራቸው የሚገኘውን አቶ ሸምሱ አባስ ከስልጣናቸው እንዲያነሱላቸው ጠይቀዋል፡፡
አቶ ሸምሱ ከዚህ ቀደም በመስጅዱ ውስጥ በአስተናጋጅነት(በከዲምነት) ሲያገለግል የነበረ የትምህርት ደረጀው አራተኛ ክፍል፣የሃይማኖት እውቀት ብዙም የሌለው፣ስልጣንን ለማግኝት ሲል ያልተደረገ፣ያላየውን እንዲሁም የማያውቀውን ጉዳይ በመንግስት ስልጠናን በመውሰድ ብርቅዮ በሆኑ የኢስላም ልጆች(ኮሚቴዎቻችን) ላይ የምስክርነት ቃሉን በሃሰት የሰጠ ግለሰብ ነው፡፡
ይህ ግለሰብ የመስጅዱ አስተዳደርም ከተደረገ ቦሃላ የወር ደሞዙ 6ሺ ብር እንደተደረገለት እና የአዲስ አበባ መጅሊስ ከፌደራል መጅሊሱ ጋር ባለው ቅራኔ እንዲሁም ሼህ ጣሃ ከአዲስ አበባው መጅሊስ ጋር ባላቸው አለመስማማት የተናሳ ለግለሰቡ በሚደረግለት የሞራል እና የደሞዝ ድጋፍ ሼህ ጣሃ ላይ በተደጋጋሚ ጫና ሲያድርግባቸው ቆይታል፡፡በአቶ ሸምሱ ጫናም የተነሳ በቅርብ ጊዜ እንካን ኢማሙ በጁመአ ሰላት ወቅት ችግሩን ለህዝብ ሊናገሩ ሲል አምባጋሮ በመፍጠር እንዳይናገሩ መከልከሉ ይታወሳል፡፡ከዚህም በተጨማሪ አቶ ሸምሱ ደም ግፊት አለብኝ በማለት ለህክምና በሚል ምክንያት 30ሺ ብር መቀበላቸውን ምንጮቻችን ጠቅሰወዋል ሆኖም ግን በሚያሳፍር መልኩ አቶ ሸምሱ ብሩ እጃቸው ላይ እንደገባ ወዲያውኑ መዳናቸው ነው፡፡ለምን ህክምና ለኔ መድሓኔቴ ጫት ነው እቅምበታለው ይሻለኛል ማለታቸውንም ምንጮቻችን አክለው ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ ባለስልጣናት የሼህ ጣሃን የመደራደሪያ ነጥብ ተከትለው ለይስሙላ አቶ ሸምሱን የቃል ማስጠንቀቂያ ሰጥተውታል ፡፡እንደ ቅርብ ምንጮቻችን ገለፃ ይህንን ያደረጉት ሼህ ጣሃን ለማባበል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ሼህ ጣሃ ጋር ለይቅርታ ከመጡት መካከል የአዲስ አበባ መጅሊስ ፅ/ቤት ሃላፊ ሐጂ ክንዱ ካሳው ከዚህ ቀደም በኢትዮጰያ እስልምና ጉዳዮች በከፍተኛ ሙስና ወንጀል የተነሳ ከነበሩበት የስራ ዘርፍ በመጅሊሱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር መሃመድ አሊ ተባረው ወደ አወሊያ መግባታቸውን ምንጮቸ ይናገራሉ፡፡ ይህ ግለሰብ ለኦዲት እየተፈለገ ባለበት ሁኔታ የአዲስ አበባው መጅሊስ ዳግም ወደ ስራ መለሳቸዋል፡፡
ሐጂ ክንዱ ከመጅሊሱ የስራ አስፈፃሚ አባላት በላይ ሲሆን ደሞዛቸው ለዶ/ር አህመድም የቅርብ አማካሪ፣ቀኑን ሙሉ ጫት ሲቅሙ የሚውል ግለሰብ መሆኑ ታውቃል፡፡

No comments:

Post a Comment