Sunday, June 29, 2014

ዛሬ በነበረው የአራዳ ምድብ ችሎት ቆይታችን

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

ዛሬ በነበረው የአራዳ ምድብ ችሎት ቆይታችን
1. ኛና ዋናው የነ በፍቄ መዝገብ ለ5ኛ ግዜ 14 ቀን ተቀጥሯል::
2ኛ. እነ በፍቄ ወደችሎት ሲገቡ ፎቶ ልታነሳ የነበረች ልጅ እዛው ከመካከላችን ፓሊሶች ወስደዋታል:: ማዋከቡ እንዳለ ነው:: አብሯት ዮናታን ተስፋዬ አለ::
ቀጥሎ ከፌደራል ፓሊሶቹ ጋር ውጡ አንወጣም ክርክር ከኛ መሃከል 'ምን ችግር አለው ፎቶ ማንሳት?' ቢለው ፌደራሉ 'እንኯን እስረኛ የቆምክበትን መሬት ለማንሳት አትችልም!' ብሎት እርፍ
እና ከዚህ በኃላ ' የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን ለችሎት የሚመጡ ጏደኞቻችን ፎቶ ማንሳት ፈልገናልና ፓሊስ የተለመደውን ትብብር አይንፈገን ልንል ነው ማለት ነው
በመጨረሻም ከችሎት በኃላ ውጡ ስንባል አንወጣም በሚለው ጭቅጭቅ (ችሎት መከታተል በህግ የተሠጠ መብት ነው ልብ በሉ) ከዛ ፌደራሉ ምን ቢለን ጥሩ ነው "በህግ አምላክ ውጡ" ሃሃ
ከዚህ ሁሉ በኃላ ግን ከግቢ ከወጣን በኃላ ከሰፈሩም ሊያባሩን ቢሉም ሁሉም ረግቶ በመቆሙ የግቢውን በር ዘግተው በየት እንዳሶጧቸውም አላወቅንም::
እኛም ከግማሽ ሰዓት በላይ ጠብቀን ተበትነናል:: አሁን ጩኸቴን ቀሙኝ አይነት ሆኖ ነው እንጂ ማነው 'በህግ አምላክ' ማለት ያለበት?!

No comments:

Post a Comment