የህይወት እሩጫ የሚያቃትተው ወጣት፡፡
ሰው ችግር ብቻ ሳይሆን ስራ ፍለጋ የሚሩዋሩዋጠው፤ እድገትም ፍልጋ መሆኑን እያየን ነው፡፤ በአንድ ሞሰብ መብላት ቀርቶ፤ ሁሉም የተቆረጠ እንጀራውን ይዞ መሮጥ ከሆነ ወዲሕ፤ ለአስር ሰው አንድ ሰው አስር ሰሀን መግዛቱ ከወሰነ ወዲህ ኑሮ አልቀለለችም፡፡ ስልጣኔ ምቾት ናት ግን ችግርን አብዢም ናት፡፡ ለአንድ ልጅ አንድ መኝታ ቤት ማሰብ፤ እና ግራውንድ ፕላስ ቤት መመኘት አልያም ቪላ ፤ እድገት በእደገት ከሆነ ወዲህ የሰው ልጅ እግርአውጭኝ፤ ብር ስጭኝ ሆኖአል፡፡ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን መቼም ፤ታችአምናም በአገራችን አንድ ሰው ከአንድ ቤት ጠንካራ አይጠፋም እና፤ ብዙ ሰው ይዞ ለመብላት ግድ የለዋል፡፡ የተባረከ ቢጣልም እንደዮሴፍ አንድ አልጠፋም በኢትዮጲያ፡፡ ስራ መፍጠር በየአገሩ ወጣቱ ተያይዞታል፡፡ የመጣበት የስራ ማጣት ሁኔታ እራሱን ስራ ፈጣሪ እንዲያደረገው መርጦአል፡፤ ለምሳሌ ከደቡብ አሜሪካ ወደታላቂቱ ሰሜን አሜሪካ በድብቅ ድራግን እየወሰዱ የሚሸጥ፤ መነገድእና ቁጥጥሩ ከባድ እና አስጊ እየሆነበት የመጣው ወጣት ነጋዴ፤ ዛሬ ብዙው ከፖሊስ ጋር ምን አታገለኝ እያለ የስራ ዘርፍ ለመቀየር ተገዶአል፡፡ ሕጻናቶችን በድብቅ ባልተፈቀደ መንገድ ወደሀብታሚቱ አሜሪካ ለማሻገር ደቡብ አማሪካዊ የሆነ ገንዘብ ከፋይ አልጠፋም፡፡ ይህም ወንጀል ቢሆንም እንደድራጉ ትልቅ ሪስክ ገና ስለሌለው፡፡ ስራ ፈጠራ ይሉሃል እንዲህ ሆኖአል፡፡ የሚያዋጣ ቢዝነስ፤ ከደሃ አገር ወደሃብታም አገር ሰው ማሻገር፡፡ የአንዳንድ አገር ፖሊሶች የሚሰሩት አላጡም፡፡ ከአንዱ የስራ ዘርፍ ወደሌላው የሚሩዋሩዋጠው ወጣት ስራ መፍጠር እንዲሕ ቀላል መሆኑን ያሳያናል፡፡ ለነገሩ ኢዮሮፕም የፈለገችውን ጥረት ብታደርግም እና ወሰኑዋን ማንም እንዳይገባባት ብታጠናክርም፤ ከወሬ ሊያልፍ ያልቻለው፤ ወጣት ስደተኛ እንደጎርፍ ይገባ ይዞአል፡፡ አስተዳደሩ እንዴትም እንደሚገቡ ማወቅ የተቻለው አይመስልመ፡፡ ስራ ፈጣሪዎች አሉእና ስራን እንዲሕ ይፈጥሩታል፡፡ ሁሉም በድብቅ በብልጠት የሚሰራበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፤ የሰው ልጅ መከራ ሲበዛበት ማን ነው ያብዳል ብቻ የሚለው፡ አይምሮውም ይፈጥራል እንጂ፡፡ ሰው የሚባለው ፍጡር ከእንሰሳ የሚለየው ሕይወቱን ለማዳን የሚወስደው የእርምጃ ጥበብ ነው፡፡ አይዞን፤ አንዱ ቢጠፋም፣ እጽዋቶች በተበላሸው አየር ሊጠፋ ቢዳዳቸውም፣ ደግሞም መሬት ብትንሸራተትም ፣ በረሃው ቢሰፋ ፣ አውሎ ንፋስ የቀላቀለው ንፋስ ቢያስቸግርም፣ አለምን እንጠብቃት ልትጠፋ ነውእና እያለ ተቆርቁዋሪ ቢለፍፍም፤ አይዞን ሰው ያጠፋል እንጂ አይጠፋም፡፡ ጥበበኛ ነኝ የሚለው የሰው ልጅ ነፍሱን ላመትረፍ ይጥራል፤ ዘዴ ይዘይዳል፣ ይገላል ይሰርቃል፣ ይማራል ይመራመራል፡፡ በሬሳም ላይ ተረማምዶ ቢሆን፤ እኔ ግን እኖራለሁ እተርፋለሁ ብሎ አፍጥጦ እና ደፍጦ እያየነው ነው፡፡ እራስ ወዳድነቱን የሚያሳየው የሰው ልጅ፤ እንሰሳትን በልቶ፤ እጽዋትንም ጨፍጭፎ፤ ጌሾንም ተጎንጭቶ ቢሆን አዎን የተርፋል ይኖራል፡፡
በዚህም የተነሳ ከወደአገሬ ኢትዮጲያም ወሰንን በመሻገር ጥበብ ያካበተው አገሩን ትቶ ወደኢሮፕም መጉረፍ ይዞአል፡፡ ግን ከእንግዲህ የኢይሮፕም ኑሮ ቀለል ብሎ አለመታየቱን እንየው፡፡ ለምን መጣህ ብቻ አይደለም ጥያቄው እንዴት ገባህም ቀላል አይሆንም፡፡ በየቀኑ ዘዴውን የሚቀያይረው አገባብ፤ ፈተናው ብቻ ሳይሆን ግቡንም ሳይመታ እየቀረ አላማውን ግብ ማድረስ ያቃተው ወጣት ሆድ እያስባሰው ይገኛል፡፡ የቅዠት ህይወት መጡብኝ፣ አዩኝ እና አላዩኝም የሚለው የእብደት ዳር ዳሩ ጭንቀት እየወረሰው የመጣውንም ስደተኛ ቁጥሩን መናገር ይከብዳል፡፡ አገባቡ ላይ እንጂ አኑዋኑዋሩ ላይ እጅግም ኢንቬስት ያላደረገው ወጣት፤ ወይኔ ገንዘቤን አውጥቼ ብሎ የሚቆጭም አልጠፋም፡፡ እንግዲህ ከአገር ከወጡ መውጣት ቀላል አልሆነም፡፡ ማን ያንን ይፈልጋል? እንዴት ልመለስ የሚያሰኘው ብቻ ፍርሃት ሳይሆን፤ ያወጣሁትን እንኩዋን ሳልተካ፣ የተበደርኩትን ሳልመልስ የሚለው እራስ ምታት ሆኖአል፡፡ ቁዋቅ የሚያሰኘው ምን ይዠ ልግባ እና ገብቸስ ምን ልሰራ አሞራ ይብላኝ ያለ ይመስላል፡፤ በዚህም ጉዳይ ላይ ማንም የሚነጋጋር የሚጫወት የለም፡፡ መቆዘም ሆኖአል፡፡ ብር መሰብሰብ አልተቻለም ግን አገር ላለመመለስ ዘዴ መዘየድ ብቻ ሆኖአል፡፡ ይህ መፍተሄ ሳያገኝ፤ በየቀኑ አዲስ የሚገባ በሽ ሆኖአል፡፡ በጀርመን ብዙም ያልተለመደው ዲፖርቲሽንም ወይም ተገዶ ወደኢትዮጲያ መመለስ ምንአልባትም እውን ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ ሳይከሰት አይቀርም፡፡ ይህን የሚያደርገው የፖለቲካው ምክናያትህ ነው፡፡ በብዛት የሚሰጡት የፖለቲካ ምክናያት አጥጋቢ አይደለም፡፡ ብዙው የሚለው ማደግ እፈልጋለሁ፣ መማር እፈልጋለሁ፣ ሰርቼ መኖር እፈልጋለሁ ነው የሚለው፡፡ ወዳጄ እዚህም መማር የሚፈልገው የተጨናነቀበት አገር ሆኖአል፤፤ ደግሞም ስራ ያጣውም ብዝቶአል፡፡ ማደግም የሚፈልገውም ቢኖር ያደገውም እያሽቆለቆለ የሚሄድበት ክስተት እየደረሰ ነው፡፡ አንድ አገር ስለሌላው አገር ስራ ማጣት ምንአገባው? እራሱም ስራ አጥ አለው እና ይልሃል፡፡ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ነውእና፡፡ ሁሉም እራሱን ለማዳን በሚፍጨረጨርበት በዚህ ክፉ ዘመን፤ የመኖር እና የኪስ ዋስትናንም ለመጠበቅ ሲባል አንድ ሴት ባሉዋን በሌላዋ እንደምትነጠቅ ነው፡፡ እነዚህ አጋጣሚዎችም እየተያዩ በመሆናቸው፤ ፈረንጅ ባል ያላት ሴት፤ ሴት ጉዋደኛ ይዛ ለማስጠጋት ለመተባበር እየከበዳት ሄዶአል፡፡ ብቻ የፈለገው ይሁን አገሬ አልመለስም የሚለው መንገድ ለኢይሮፕ ቀሎ የሚታይ ጊዜ አልሆነም፡፡ እዚህ ድረስ መጥተህ ለፍተሕ እና ከስረህ ወይ ከማበድ፣ ከመሞት አልያም ዲፖርት ከመደረግህ በፊት ማሰብ ደንብ ነው፡፡ እውን ዛሬ የትም ሮጦ ማደግ ይቻላል ወይ? የሚያሳድግህስ እውቀት ይዘሃል ወይ? ከአገር የሚያሰድድስ የፖለቲካህ ሁኔታ እውነትነት አለው ወይ? አይምሮሕስ የሚችለው ግፍ ምን ያህል ነው? መከራን ለማለፍ ተዘጋጅተሃል ወይ? እንግዲህ አገርህን ከመልቀቅህ በፊት እራስህን መዘን፡፡ ኢይሮፕ ስደተኛ እየበዛባት በመሆኑ እያንጉዋለለው እንደታምራት የሚዘፈንበት ትንቢት መሰል የዛር ዘፈን እውን መንጉዋለል እንዳይሆን ልብ በል፡፡ ሰሞኑን አንድ ሁለት ኢትዮጲያዊ ሴቶች ዲፖርት ልንደረግ ነው በማለት በፍርሃት፣ በእንቅልፍ ማጣት እና በመረበሽ አገኘሁዋቸው፡፡ የሚበሉት አላጡም አራባቸውም እንጂ አይምሮአቸውን ግን ለማጣት ጫፍ ላይ ደርሰዋል እና፡፡ አጥጋቢእና የታወቀ የፖለቲካ ኬዝ የለለው፤ መንገድ አይጀምር፡፡ ስደት በፖለቲካ እንጂ የኢኮኖሚ ስደት አሳሳቢ ቢሆንም እዚህ ለመኖር በቂ ምክናያት አይሆንልህም፡፡ „ማር ሲበዛም ይመራል“ እንዲሉ፤ አንድ አገር ምን ያህል ህዝብ ይችላል የሚለው ጥያቄም ኑዋሪውን እያሳሰበው እና እያስቀየመው እየሄደ ነው፡፡ ሰው እራሱ ካልደላው፤ ስለሌላው የሚያስብ መለአክ አይደለም እና፡፡ በቸር ባዩሽ

No comments:
Post a Comment