Friday, June 20, 2014

የጥላቻ ፖለቲካ! ===========

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

የጥላቻ ፖለቲካ!
===========
የኦሮሞ ተወላጆችን የበደሉ ያለፉ (ያሁኑ) ስርዓታት እንደሆኑ ከማስረዳት አማራ እንዲህ አደረገህ እያልን ከሰበክን፣ የአማራ ተወላጆችን የበደለ ህወሓት/ኢህአዴግ ነው ከማለት ይልቅ የትግራይን ህዝብ ጨቆነህ እያልን ካስተማርን፣ የትግራይ ተወላጆችን የበደለ የደርግ ስርዓት ነው ከማለት የአማራን ህዝብ እንዲህ በደለህ እያለን ካጭበረበርን የኦሮሞ ልጅ አማራን ለማጥፋት፣ የአማራ ልጅ የትግራዩን ለመግደል፣ የትግራይ ደግሞ የአማራን ሰው ለመበቀል ጥረት እንደማያደርግ ምን ዋስተና አለን???
ለፖለቲካ ስንል የምናስተምረው ጥላቻ ለወደፊት አንድነታችን ስጋት እንደሚሆን መገንዘብ እንዴት ያቅተናል? ፖለቲከኞች የህዝብን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ የብሄር ካርድ ይጠቀማሉ። ህወሓት የትግራይን ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ደርግና አማራ አንድ አድርጎ አቀረበልን። አንዳንድ የኦሮሞ ኤሊቶች የሚኒሊክ ስርዓት የአማራ አድርገው ያቀርባሉ፣ ኦሮሞዎችን ለመቀስቀስና ድጋፍ ለማሰባሰብ። አንዳንድ የአማራ ሊሂቃንም ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ አንድርገው እየሰበኩ ነው። ይሄንን የብሄር ካርድ ድጋፍ ለማሰባሰብ ይርዳ እንጂ አደጋ አለው።
የሚገርመው ግን የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ተደርጎ ሲወሰድ ህወሓቶችም ደስተኞች መሆናቸው ነው። ምክንያቱም የትግራይን ህዝብ የሚጠሉ ኃይሎች ሲመጡ የትግራይ ህዝብ ሳይወድ ህወሓትን መደገፉ አይቀርምና ነው። ባጠቃላይ ግን ህዝብ ዒላማ ማድረግ (አንድ) የፖለቲካ ኪሳራ ያመጣል፣ (ሁለት) በመርህ ደረጃም ስህተት ነው። ምክንያቱም አንድ ስልጣን ለመያዝ የሚታገል ፖለቲከኛ ህዝብን ለማገለገል ማቀድ ሲገባው ህዝብን የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ካለመ የፖለቲካ ብቃቱ አነስተኛ መሆኑ ያሳያል።
በገጠር መንደር በግብርና ተሰማርቶ ህይወት ለመግፋት ላይና ታች የሚል ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግራዋይ ወዘተ የፖለቲከኞችን የጥላቻ ፖለቲካ ምንሙ አይደለም። ጥላቻ ከምታስተምሩት ፍቅርን፣ አብሮነትን፣ አንድነትን አስተምሩት፤ ሰላም ስጡት።

No comments:

Post a Comment