Monday, June 16, 2014

በዛሬው የመድረክ ሰልፍ ላይ እጅግ ተስፋ ሰጭና የሚያኮሩ የኢህአዴግ ወያኔን ሴራ መና ያስቀሩ ቁም ነገሮችን ተገንዝቤያለው፡፡ በዚህም ዶ/ር ነጋሶ ኪዳዳ የጀመሩትን እንዳልጨረሱና ከኢትዮጵያን ነፃነት የራሳቸውን ነፃነት በራስወዳድነት ያከናወኑ የራሳቸውን ለራሳቸው ሲሉ ብቻ ያበቁ እንደሆኑ ሳልናገር ማለፍ አልፈልግም፡፡



በዛሬው የመድረክ ሰልፍ ላይ እጅግ ተስፋ ሰጭና የሚያኮሩ የኢህአዴግ ወያኔን ሴራ መና ያስቀሩ ቁም ነገሮችን ተገንዝቤያለው፡፡ በዚህም ዶ/ር ነጋሶ ኪዳዳ የጀመሩትን እንዳልጨረሱና ከኢትዮጵያን ነፃነት የራሳቸውን ነፃነት በራስወዳድነት ያከናወኑ የራሳቸውን ለራሳቸው ሲሉ ብቻ ያበቁ እንደሆኑ ሳልናገር ማለፍ አልፈልግም፡፡
በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ መድረክ ማለት በተለይ ለኦሮሚያ የቆመ ለኦሮረሞ ህዝብ ዘብ የቆመ ድርጅት እንደሆነ ያወሳሉ፡፡ ይሕም ይሁን ግን ጠላትን የሚያኮማትር ሆኖ ያገኘውት ግን ኢህአዴግ አማራውን ከኦሮሞው ክቡር ህዝብ ጋር ለማፋጀት ከቀየሰው መስመርና እቅድ ውስጥ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ አማራዎች የሚሳደዱበትን የሚገደሉበትን ከቀያቸው የሚፈናቀሉበትን ነበር የዘየደው እና ያጠመደው ፈንጅ ይህም በትንሹም ቢሆን ቢሳካለትም በባለፈው ብጣሽ ፅሁፌ ለማብራራት እንደገለፅኩት በጭራሽ አማራውን ከኦሮሞው ማፋጀት እርሱ እንዳሰበው ቁንፅል ሃሳብ ማጋደል እንደማይችል ሁሉ እና የኦሮሞው ማህበረሰብ ይህንን ማውገዝ እንደሚጠበቅበትና ለኢህአዴግ መጠቀሚያ የሆኑ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የተሳሳቱ የኦሮሞው ክቡራን አባላት ኢትዮጵያዊያን ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ የሚል መልዕክት የያዘ ፅሁፍ መሰረት የኦሮሚያ ህዝብ በአማርኛ በኦሮምኛ በእንግሊዝኛና በትግረኛ የአማራው ህዝብ ወንድም እህቶቻችን ናቸው ስለዚህ እነርሱም አማራው ኦሮሞው ትግሬው ሶማሌው ደቡቡ አፋሩ ጉሙዙ ጋንቤላው ያለበት ሁሉ ሃገራቸው ነውና አይፈናቀሉ መፈናቀላቸው ይቁም፡፡ እኛ አንድ ነን፡፡ ኢትዮጵያ በአንድ ህዝብ የተሞላች በደም የተሳሰረች አንዱ ካንዱ ቂም በቀል የሌለውን ህዝብ የያዘች አንት ክቡር አገር ናት፡፡
ህዝባችን በኢህአዴግ ሴራ አይለያይም ኢህአዴግ ካገናኘት አንድ ካደረገን ይልቅ ሊበታትነን የሚሞክርበት መስመር እጅግ በርካታ ነው እባክህን ኢህአዴግ በቃን በቅቶናል ተወን፡፡ አማራ ወንድማችን እንታችን ናቸው፡፡ ትግሬ ሶማሌ አፋር ጉሙዝ ጋምቤላ ሁሉም አንድ ነን የማትርሱትን አትሞክሩት፡፡ በማለት ድምፃቸውን ሲያሰሙ ሳይ ደስ አለኝ፡፡ ይሕ ነው ኢትዮጵያዊነት፡፡ ግን ያልገባኝ ነገር ቢኖር ህዝቡ ስለአንድነት አንድ ስለመሆን ወዘተ…ስለአንዲት ኢትዮጵያ ነው የሚያወራው በየመድረኩ ታዲያ ልምንድን ነው እንዴትም ተቻችለውና ተፋቅረው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድ የማይሆኑት የሚለው ጥያቄ ነው፡፡
ለማንኛውም መድረኮችና ተሳታፊዎች እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እናመሰግናችኋለን!!!
እንዳላችሁትም አዎ የትኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ምድር ላይ ሁሉ የትኛውም ኢትዮጵያዊ ውጭ ይሁን አገር ውስጥ ያገባዋል፡፡ በፈለገው አካባቢ ሄዶ ንብረት የማፍራት ልጆች የመውለድ የመኖር መኖር የመስራት መብት አለው፡፡ ይህንን የማይቀበል ከየትም ይሀን ከየት ጠላታችን ነው የኢትዮጵያ ጠላት ነው፡፡ አዎ መድረኮች ሰፊውን የኦሮሚያ ህዝብ በመወከል ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊያን ጋር ኢትዮጵያዊ እንደመሆናቸው ሁሉ በአደባባይ አንድ ለአንድ መሆናቸውን አረጋግጠውልናል፡፡ እጅግም እናመሰግናለን፡፡ አሁንም ቢሆን ሰፊው አንድነት ናፋቂ ንፁህ ኢትዮጵያዊ የጀግናው ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብና የታሪካቸው ተካፋይ የሆነ የተከበረው የኦሮሞኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ አባልና አካል የሆነ ሁሉ የአኖሌ ሃውልት ለትውልድ ከሚያመጣው በጎ መልዕክት ይልቅ የሚያስተምረው የበቀልና የተሳሳተ አመለካካት ስለሚልቅ በዚህ ላይም አንዴ ሆኦኦኦኦ… ብለን በመነሳት ከአማራ ወንድሞቻችን ጋር ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ድህነትና ኢህአዴግን ለማጥፋት ያለንን አንድነት ናፋቂነት ለማሳየት እንዲሁም ያለንን መተሳሰብ ለማሳየት እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን እንደሆንን ለማሳየት…ከታሪካችን ልንማር እንጅ በታሪካችን ልንጠፋፋ እንደማይገባ ይህንንም ኢህአዴግ ሊያስተምርን ሳይሆን ሊያፋጀን መነሳቱን መቃወማችን ለማሳየትና ከአማራ ወንድሞቻችን ጋር ሊያጋጨን የሚችል ነገር ምንመ አለመኖሩን ለማሳየት የአኖሌ ሃውልት መፍረስ ላይ ድምፃችን ማሰማት አለብን፡፡
የተከበረው ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ኢትዮጵያነት የሚያሳስባቸው የኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪ ወንድምና እህቶቼ ሁሉ እስቲ ኢህአዴግን በቃህ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰራ መጥፎ ታሪክ ቢኖር እንኳን የሰራው የአሁኑ ትውልድ ሳይሆን ከስንት ዓመታት በፊት የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው…እነርሱ በሰሩት ስዕተት ልንማርበት እንጅ ልንፋጅበት ከቶም አይገባም እንበለው እስቲ ኢህአዴግን፡፡ ያኔ ኢህአዴግ ጋር ምንም ቤዛቤስቲ እስደሌለን እናሳያቸዋለን ያኔ ኢህአዴግም አማራጩን ይጠቀማል ያኔ አንድነታችንን በትግባር እናሳያለን፡፡ ይህን በማድረጋችን ምንያህል ለሃገራችን ኢትዮጵያ አባቶቻችን ስላለቁላት ኢትዮጵያ ትልቅ ስራ እንደሰራን ማሳየት እንችለልን፡፡ አማራው ለኦረሞው አንድ ነው አማራው ኢትዮጵያዊ ኦሮሞው ኢትዮጵያዊ ኢህአዴግ ግን ሁለቱን ለማፋጀት የማይቆፍረው የማይፈነቅለው የለም፡፡ ይሕን የጠላታችን የኢህአዴግን ሴራ ማክሸፍ እንችላልን፡፡ የትግራይ ህዝብ ያኔ ወያኔ ትግራይን አስገነጥላለው ሲል እንኳን የአለቆቻቸው ሃሳብ ምን እንደሆነ የማያውቀው የትግራይ ህዝብ ነበር የሚበዛው፡፡ የትግራይ ህዝብ ኢህአዴግ እንዲህ ክፉ እና ግፈኛ እንዲሆን ምንም እጁን እንዳላስገባ የምናረጋግጥባቸው በርካታ ምክያቶች አሉ/ሌላ ጊዜ እንመጣበታለን/ ነገር ግን ይህም ሲባል የትግራይ አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩና እጅግ ዘረኛና ጠባብ የሆኑ እንዳሉም መካድ አይቻልም እነዚህ በጠመዱት የዘረኝነት ፈንጅ ተይዞ ኢህአዴግ ማለት ወያኔ ወያኔ ማለት የትግራይ ህዝብ ወያኔ ከሌለና ሌላ መንግስተ ከመጣ እንደ ጅብ የሚበላቸው በአንድ ቀን ጭጭ እንደሚያደርጋቸው አድርገው የሚወስዱ በዚህ የታወሩ ሞልተዋል፡፡ ይሕ የትግራይ ህዝብ ሃሳብ አልነበረም አሁንም እድሜ ለአረና እያነቃቸው እውነታውን እያወቁት በመሄዳቸው ብዙዎቹ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ተሰልፈው በደመነፍስ መንቀሳቀስን አቁመው እየኖሩ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ለውጥን በነውጥም ቢሆን እየናፈቁ ናቸው፡፡
እንዲህ አይነትን ህዝብ ይገርማችኋል ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ቡድንን እየፈ\ጠሩ ሊያባሉት ሲፈልጉ እንኳን ቅር አይላቸውም፡፡ ታዲያ ይህን ስርዓት ከማስፈንጠር ሌላ ምን አማራጭ አለ፡፡…ሁላችንም አንድ ነን በማለት መፈክር ማሰማቱን መድረክን አንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ወድጄዋለው፡፡ እጅግ አድናቂና ደጋፊያቸው ነኝ፡፡ አስቡት ታዲያ እነዛ ሌላው ራሳቸውን ከኢትዮጵያዊ ለይተው በማየትና ሌላው ከነሱ ጋር እንዳልሆነ ከነርሱ ጋር አንዳችም ነገር የሚያገናኘው እንደሌለ አድርገው የሚቆጥሩት ደካማ ኦሮምኛ ተናጋሪ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ለምን ይህን አይተው አይማሩም ማለት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም መልስ ራሱ እንዲህ የመድረክን ድምፅ አንግቦ አንድ እንደሆንን የሚሰብከው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሰፊውና የተከበረው ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው፡፡ ማንም ከየትም ከኢትዮጵያዊና ከኢትዮጵያዊያን ውጭ መጥቶ የኛኑ የኢህአዴግ ሴራ መሳሪያ የሆኑ ልጆቻችንን እንዲመክርልን እንዲያርምልን ከፈለግን ተሞኝተናል፡፡
አንድ ሳልል የማላልፈው ነገር ቢኖር ይህንን ስርዓት የሌለው ስርዓት ለማውደምና የምንፈልገውን ስርዓት ላማምጣትና ዲሞክራሲያዊ ጥማችንን በዲሞክራሲ ለማርካት ከፈለግን አንዱ አሁን የያዝነው ህዝባዊ ማዕበል መፍጠር ነው፡፡ እስቲ ሁላችሁም የተቃዋሚ ፓርቲዎች እስቲ በአንድ ቀን ተነጋግራችሁ ተባብራችሁ በአንድ ቀን ሁላችሁም በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይህንን መሪያጣ ህዝብ አስተባብራችሁ ሰላማዊ ሰልፍጥሩት ያኔ ነው የባቢሎን ግንብ የሚፈርሰው፡፡ ያኔ ነው የጠላት ክንድ የሚፍረከረከው፡፡ ያኔ ነው አንድነታችን አሁንም ኢትዮጵያ ልጆች እንዳሏት የምናውቀው፡፡ ይህን ለማድረግ እስቲ አንድ የሚያደርጋችሁን ብቻ ይዛችሁ ጥሩን፡፡ አደራ ብያለው፡፡
በነገራችን ላይ ይህ ስርዓት የሌለው ስርዓት አልባ መንግስት ሳናደርገው ምግስታችሁ ነኝ ተኙና ልቀጥቅጣችሁ ተኙና መርቅኑ የሚለን ሃይል ጭንቅላታችን ላይ ወጥቶ ሲያሻው የሚያስረን ሲያሻው አሸባሪ እያለ ፍርድ ቤት ለፍርድቤት ሲያንከራትተን የሚኖር ለዚህ ነው አንድነታችንን የፈረካከሰው መቼም አንድ የምንሆን መስሎ ስላልተሰማው ነው፡፡ ለዚህ ነው የሚገድለን ለዚህ ነው ቃሊቲ ዝዋይ ቂሊንጦና በየክልሉ ያሉ አስር ቤቶች ማጎሪያ ቤቶች እንዲሁም ማሰቃያና የአደራ እስረኛ ጥብቅ እስረኛ ማሰቃያ ቤቶች የሞሉት፡፡ ለዚህ ነው ስዎች!!! ለዚ…ህህህህ ነው!!!
ስለዚህ አሁንም የምደግመው አንድ ትሆኑ ዘንድና የጠላታችን ቅስም እንሰብርና ሁላችንም ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆኑን ለማሳየት ብለን "ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት" በሚል መሪቃል ወይም በተሸለ መሪ ቃል ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተገኙበት እስቲ እንውጣ እስቲ አዲስ አበባና ሁሉንም የክልል ከተሞች ቢያንስ ለአንድ ዙር አንድ ሆነን አንድ ላይ እናድምቃቸው እስቲ እናነቃቃው ህዝባችን…እስቲ ነገውኑ እንጀምረው ይህንን ትልቅ ራዕይና እቅድ…
አዎ አንድና ትልቅ ነበርን አሁንም ወደፊትም አንድና ትልቅም እንሆናለን!! ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው አማራ ትግሬ ጉሙዝ ጋምቤላ ደቡብ ሶማሌ አፋር አዲስ አበባ ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ ሁላችንም በፈለግነው የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ለመኖርና ላለመኖር ሊፈቅድልንም ሊከለክለንም ቢሞክር ውርድ ለራሱ… ብለን እስቲ ራሳችን የራሳችንንን ክብር እንመልስ፡፡
ቸር እንሰንብት
ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክን እናመሰግናለን
የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሰልፉ ተሳታፊዎችንም እጅግ ክልብ እናመሰግናለን፡፡

No comments:

Post a Comment