Tuesday, June 17, 2014

አልሰደድም! ትግሌንም አላቆምም! ሳሙኤል አወቀ

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

አልሰደድም! ትግሌንም አላቆምም!
ሳሙኤል አወቀ
(ከደብረ ማርቆስ)
ከዚህ ቀደም የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆኔን ካላቆምኩ እስከ ግድያ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድብኝ እና ይህ ከመሆኑ በፊት ከሀገር አንድወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ይህን ባለመቀበሌም ተደጋጋሚ አሳፋሪ የውንጀላ ክሶችን ሳስተናግድ ቆይቻለሁ፡፡ በጥብቅና ሙያየ አገለግሎት አንዳልሰጥ እና ሰርቸ እንዳልበላ ተረጋግቼ በሰላም እንዳልኖር የተከፈተብኝ ዘመቻ ቀላላ የሚባል ባይሆንም ይህንን ተቋቁሜ መስራቴ ያበሳጫቸው የኢህአዴግ ካድሬ ዳኞች ደግሞ በህግ አራዊትነት አስሮ ለማሰቃየትና እንዲሁም ከህዝብ በተሰወረ ሁኔታ ወደ ሌላ ወረዳ ማለትም ባሶ ሊበን ወረዳ /የጁቤ/ ታስሬ እንድቀርብ በፖሊስ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶብኛል፡፡
ምንጮቼ እንዳረጋገጡልኝ የእስራቱ ምክንያት ደምበኛዬ /የወከለችኝ/ ግለሰብ ኪሳራ 2ዐዐ /ሀለት መቶ/ ብር ስላለባት ያለምንም ክስ እና መጥሪያ በመዝገቡ ላይ እንድታሰር እና ከተሰቃየሁ በኋላ በይግባኝ እንድለቀቅ የታቀደ መሆኑን ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ጠበቃ ደምበኛውን ወክሎ የህግ አገልግሎት መስጠት እና ክርክር ማድረግ እንጅ ደምበኛውን ወክሎ ወይም ተተክቶ ሊታሰር የሚችልበትም ሆነ ገንዘብ ሊከፍል የሚችልበት ምንም ዓይነት የህግ አግባብ ካለመኖሩም በላይ የህግ ድርጊት ለመጀመሪያ ጊዜ በእኔ ላይ የተፈፀመ መሆኑን በሃገሬ የፍርድ ቤት ነፃነት እና የዳኞች ገለልተኛነት እንዳሰፍን እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የአፓርታይድን ችሎት በማስታወስ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡
አልሰደድም!
ትግሌንም አላቆምም! ፍትህ! ነፃነት! እኩልነት!
ለአፋኝ የኢህአዴግ ካድሬዎች ሁሉ እንዲረጋገጥ የገበሁትን የትግል ቃልኪዳን እፈፅማለሁ፡፡
LikeLike ·

No comments:

Post a Comment