Sunday, June 29, 2014

አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ የቀረበባቸውን ክስ ክደው ተከራከሩ

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ የቀረበባቸውን ክስ ክደው ተከራከሩ
‹‹ልንመሰገንበት በሚገባ ሥራ ወንጀለኛ መባላችን ያሳዝናል›› አቶ መላኩ ፈንታ
‹‹እንኳን 16 ቤት አንዲት ደሳሳ ጐጆ የለኝም›› አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ
‪#‎Ethiopia‬ addisadmassnews.com ‪#‎EPRDF‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)‪#‎finotenetsanet‬ #Ethiopia ‪#‎EthioMuslims‬ #EPRDF ‪#‎FreedomofReligion‬ ‪#‎BBN‬ #‪#‎ሳምቮድሶን‬ ‪#‎አብቢን‬ ‪#‎Minilik‬ Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ‪#‎gezahegnabebe‬ ‪#‎netsanetyibetal‬ ‪#‎TPDM‬ ‪#‎EPPF‬ ‪#‎G7PF‬ ‪#‎EthioBilalTube‬ ‪#‎ZubayrPeace‬ ‪#‎zhabesha‬ #BBN ‪#‎reporter‬
በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣
የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከር ድርጊቱን አለመፈጸማቸውንና ጥፋተኛም እንዳልሆኑ ለፍርድ ቤት ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. አስረዱ፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሦስት የክስ መዝገቦች ክስ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ አንደኛውን የክስ መዝገብ እንዲያሻሽል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ያዘዘው ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ ላይ ይግባኝ በማለቱና በማሳገዱ ተጠርጣሪዎቹ በሁለቱ የክስ መዝገቦች ላይ ብቻ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡
በመሆኑም ሰኔ 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ሁሉም ተጠርጣሪዎች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ‹‹ድርጊቱን አልፈጸምንም፣ ጥፋተኞችም አይደለንም›› በማለት ቃል ሲሰጡ፣ አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ ግን ከጠበቆቻቸው ጋር መመካከር የሚገባቸው ጉዳይ መኖሩን ጠቅሰው፣ በተለዋጭ ቀጠሮ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ በጠየቁት መሠረት ተፈቅዶላቸው ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰጥተዋል፡፡
አቶ መላኩና አቶ ገብረዋህድ የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡት በቀረበባቸው ክስ ‹‹ድርጊቱን አልፈጸምኩም፣ ጥፋተኛም አይደለሁም›› በማለት ብቻ አይደለም፡፡ በመሀል ዳኛ ሸምሱ ሲርጋጋ፣ በቀኝ ዳኛ በሪሁ ተወልደብርሃንና በግራ ዳኛ ግዛቸው ምትኩ የተሰየሙበት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት፣ ተጠርጣሪዎቹ የተመሠረተባቸው እያንዳንዱ ክስ ተነግሯቸውና ‹‹ክሱ ግልጽ ሆኖላችኋል?›› በማለት ተጠይቀው ‹‹ክሱ ግልጽ ነው›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
‹‹ድርጊቱን ፈጽመዋል አልፈጸሙም?›› የሚል ጥያቄ ለአቶ መላኩ ሲቀርብላቸው፣ ‹‹ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ አልፈጸምኩም ከማለቴ በፊት…›› ብለው፣ በክሱ ከታክስና ገቢ ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን የሚመረምር ኮሚቴ እያለ ሕገወጥ የቴክኒክ ኮሚቴ በማቋቋምና መመርያ በማውጣት ሕገወጥ ኮሚቴው እንዲያየውና ታክስ እንዳይሰበሰብ በማድረግ በመንግሥት ጥቅም ላይ ጉዳት ማድረሳቸው በተገለጸው ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አቶ መላኩ እንዳብራሩት፣ ሲጀመር የወንጀል ሕግ 411 ሊጠቀስባቸው አይገባም፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ፣ የመንግሥት ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት ወንጀል አለመሆኑ ነው፡፡ የተጠረጠሩበት ወንጀል እውነት ቢሆን እንኳን ሊወድቅ የሚችለው በወንጀል ሕግ 351 (በመንግሥት የገቢ ምንጮች ላይ ጉዳት ማድረስ) በሚለው ላይ እንደነበር የግብር ቅሬታ የሚያቀርብን ሁሉ እሳቸው ማስተናገድ ስለማይችሉ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማስተላለፋቸውን ገልጸዋል፡፡
‹‹የኔ ሥራ ሥርዓት መዘርጋት ነው፤›› ያሉት አቶ መላኩ፣ ግብር አትሰብስቡ አለማለታቸውንና የመንግሥትን ጥቅም ማስከበራቸውን እንጂ ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሳቸውን በማውሳት ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ያማቶ ኢትዮጵያ የተባለ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ አብዱላሂ የተጨማሪ እሴት ታክስና የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ኦዲት ተደርጐ ከ48.4 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፍሉ ሲወሰንባቸው፣ ለአቤቱታ አጣሪ ኮሚቴ ቅሬታ አቅርበው ካጣሩ በኋላም እንዲከፍሉ ሲወሰንባቸው፣ የተወሰነባቸውን የገንዘብ መጠን 50 በመቶ ለግብር ይግባኝ ጉባዔ ማቅረብ ሲገባቸው፣ በቀጥታ ለአቶ መላኩ ሲያቀርቡ ተቀብለዋቸው እንደገና በኮሚቴ እንዲታይ በማድረጋቸው፣ ግብር እንዳይሰበሰብ ማድረጋቸውን በመግለጽ በቀረበባቸው ክስ ላይም አቶ መላኩ አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡
ክሱ የያዘው ፍሬ ነገር ሐሰት መሆኑን ገልጸው፣ ሥራውን የሠሩት ሕግ በሚፈቅደው ሥርዓት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የድርጅቱ ባለቤት የእሳቸው ባልሆነ ማስረጃ ግብር ክፈሉ መባላቸውንና አቤት ማለታቸውን ጠቁመው፣ መንግሥት በሐሰተኛ ሰነድ ገቢ ስለማይሰበስብ ‹‹ይረጋገጥ›› ብለው ማዘዛቸውን ገልጸው በድርጊቱ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኦቨርሲስ ቴክኖሎጂ ሊሚትድ የተባለ ድርጅት መክፈል የነበረበትን ግብር ከ34.386 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፍል ሲወሰን አቶ ገብረዋህድና አቶ ጥሩነህ በርታ (በባለሥልጣኑ የመረጃ ቡድን መሪ የነበሩ 13ኛ ተከሳሽ ናቸው) የጠቋሚ ክፍያ ከገቢው ላይ ተቀንሶ ለግለሰቦች ያላግባብ እንዲከፈል ሰዎችን በማዘጋጀት፣ ቃለ ጉባዔ በማዘጋጀትና ጠቋሚ ያልሆኑ ሰዎች በጠቋሚነት እንዲመዘገቡ ማድረጋቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ የወሮታው ክፍያ ጥያቄ በማስነሳቱ በማኔጅመንት ኮሚቴና በኦዲት ተጣርቶ ድርጊቱ አግባብነት እንደሌለው ሪፖርት ሲቀርብላቸው፣ አቶ መላኩ ማድረግ የነበረባቸው አቶ ገብረዋህድና አቶ ጥሩነህን በሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ ማድረግ የነበረ ቢሆንም፣ በዲሲፕሊን ብቻ እንዲጠየቁ ማድረጋቸው በሥልጣን ያላግባብ መገልገል መሆኑን በሚመለከትም ለቀረበባቸው ክስ አቶ መላኩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ተከፈለ የተባለው የግብር ገቢ አለመከፈሉን አስረድተው፣ በሕዝብና በመንግሥት ላይ ባልደረሰ ጉዳት በመከሰሳቸው ጥፋተኛም፣ ወንጀለኛም አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ መላኩ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ከ3.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ንብረትና ገንዘብ አፍርተዋል በሚል ለቀረበባቸው ክስ፣ እንደማንኛውም ሰው 175 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ቤት መሥራታቸውን ገልጸው፣ ይህ ደግሞ ለእሳቸው ብቻ ተነጥሎ ወንጀል ሊሆን እንደማይችል አስረድተዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ የቤቱን ግምት አሳስቶ ማቅረቡንም ጠቁመዋል፡፡ ቤቱን ያሠሩት ከባንክ ተበድረው መሆኑንና የባንክ ብድራቸውንም መክፈላቸውን በማስረዳት የቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ሊያስብላቸው እንደማይችል ገልጸዋል፡፡
በሌላ ሰው መብት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ አቶ ደምሴ ዓለማየሁ የተባሉ ግለሰብን ሚስት ወ/ሮ መቅደስ ለማን አፋተው ባለቤታቸው እንዳደረጉ በመግለጽ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን ክስ፣ የክሱ ፍሬ ነገር የእሳቸውን ሰብዕናና ስም ለማጥፋት ሆን ተብሎ የቀረበ በመሆኑ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን በሐዘን ስሜት አስረድተዋል፡፡
አቶ ከተማ ከበደ አራጣ በማበደር ወንጀል ተጠርጥረው ማስረጃ ተጠናቅሮ ለአቶ መላኩ ሲቀርብላቸው አጣርተው ለሕግ ማቅረብ ሲገባቸው ከአቶ ከተማ ጋር በፈጠሩት ስውር የጥቅም ግንኙነት ሌሎች ሲከሰሱ እሳቸው እንዳይቀርቡ በማድረጋቸው፣ መንግሥትንና ሕዝብን በሚጎዳ ሁኔታ የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን መርተዋል ለሚለው ክስም አቶ መላኩ አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡
አቶ መላኩ ለአጭር ጊዜ ውክልና ተሰጥቶት (መሥሪያ ቤቱ) አጥጋቢና ለሕዝብም ትምህርት የሚሰጥ ሥራ መሥራታቸውን አስረድተው፣ ‹‹ተመሳጥሬ ክስ እንዳይመሠረት አላደረግኩም›› ካሉ በኋላ ጥፋተኛም ወንጀለኛም አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በርካታ ሆቴሎች ከቀረጥ ነፃ የገቡ የሆቴል ዕቃዎችን ከታለመለት ዓላማ ውጪ እየተገለገሉበት መሆኑ መረጃ የደረሳቸው አቶ መላኩ፣ ጄኤች ሲሜክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል) ማስረጃዎች የቀረቡበት ቢሆንም፣ ከአቶ ስማቸው ከበደ ጋር ባላቸው ስውር የጥቅም ግንኙነት፣ ክስ እንዳይመሠረትባቸውና እንዳይቀርቡ ስለማድረጋቸው በቀረበባቸው ክስም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከቀረጥ ነፃ የገቡ የሆቴል ዕቃዎችን በሚመለከት፣ ‹‹ይኼ ይፈጸም ይኼኛው አይፈጸም›› ያሉት ነገር እንደሌለ ገልጸው፣ ድርጊቱን አጣርተው የመንግሥት ጥቅም እንዲከበር ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሁሉም ሆቴሎች ለመንግሥት መክፈል የሚገባቸውን እንዲከፍሉ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ ማንንም ለይተው ወይም ተመሳጥረው ያደረጉት ነገር እንደሌለ ገልጸው ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ክስ ማንሳታቸውን በሚመለከት ምላሽ የሰጡት አቶ መላኩ፣ ‹‹ክስ አንስተናል፣ ንብረቱን ወርሰናል፡፡ ይኼ የተደረገው ደግሞ ሰውዬው (ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ) የበለጠ ጥቅም ይሰጣሉ በሚል ከሚመለከተው ሚኒስቴር ስለታዘዝን ነው፤›› ካሉ በኋላ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም የሥራ ሒደት መሪ የነበሩት አቶ አስመላሽ ወልደ ማርያም፣ ለቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ከውጭ ከቀረጥ ነፃ የገባ ሲሚንቶ ለሦስተኛ ወገን ሲሸጥ ዝም ማለታቸውንና ከሥራ በማገድ እንዲከሰሱ ማድረግ ሲገባቸው፣ የዲሲፕሊን ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው በማድረግና አቶ አስመላሽ መልቀቂያ እንዲያስገቡ ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸውን በሚመለከት ምላሽ የሰጡት አቶ መላኩ፣ ለሕግ መቅረብ የነበረበት ሠራተኛ ለሕግ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ያጓጓዙ ትራንስፖርተሮች ለሕግ እንዲቀርቡ አላደረግንም፡፡ መከሰስ ያለባቸው ግን ተከሰው የመንግሥትን ጥቅም አስከብረናል፡፡ ልንመሰገንበት በሚገባ ሥራ ወንጀለኛ መባላችን ግን ያሳዝናል፤›› ብለው፣ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን አስመዝግበዋል፡፡ ከማንም ጋር ምንም ዓይነት ስውር ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸው፣ ‹‹በፍጹም በፍጹም ሙሰኛም ጥፋተኛም አይደለሁም፤›› በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተው አጠናቀዋል፡፡
አብዛኛው የተከሰሱበትና የተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል ከአቶ መላኩ ጋር የሚመሳሰለው አቶ ገብረዋህድ፣ የቀረቡባቸውን በርካታ ክሶች ክደው ተከራክረዋል፡፡ የአራጣ ተጠርጣሪዎችን በሚመለከት፣ ከቀረጥ ነፃ ከውጭ ስለገቡ የሆቴል ዕቃዎች፣ ክስ ስለማንሳትና ሌሎች የተጠረጠሩባቸው ክሶች እሳቸውን እንደማይመለከቱ፣ መንግሥት የሾማቸው ከእሳቸው ሥልጣን ጋር እኩል ሥልጣን ያላቸው ብዙ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች መኖራቸውንና የተጠቀሱባቸው ክሶች አብዛኞቹ እነኛን የሚመለከቱ በመሆናቸው፣ ምናልባት በስመ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በስህተት የእሳቸው ስም ሳይጠቀስ እንዳልቀረ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢንዱስትሪ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ አንድ የውጭ ባለሀብት ተከሰው ክሳቸው እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን ያመኑት አቶ ገብረዋህድ፣ በወቅቱ የውጭ ኤምባሲዎችና ዲፕሎማቶች ግለሰቡ መከሰስና መታሰር እንደሌለባቸው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ተከትሎ ሕጋዊ የመንግሥት አሠራርን ተከትለው የውሳኔ ሐሳብ በማቅረብ፣ ክሳቸው እንዲዘጋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ መንግሥትም በኢንዱስትሪና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩትን ባለሀብቶች ተንከባከቡ ይል ስለነበር፣ በወቅቱ ያደረጉት ጥፋተኛም ወንጀለኛም ሊያስደርጋቸው እንደማይችል አስረድተዋል፡፡ በስብሰባ ላይ የተናገሩት ሊያስጠይቅም ሆነ ሊያስከስሳቸው እንደማይገባ የተናገሩት አቶ ገብረዋህድ፣ አንዳንድ ቅሬታ ያቀረቡ ሰዎችን በሚመለከት በስብሰባ ላይ ‹‹ይታይላቸው›› ማለታቸውን ገልጸዋል፡፡
መወረስ የሚገባውን መኪና እንዳይወረስ ማድረጋቸውን በሚመለከት የተናገሩት አቶ ገብረዋህድ፣ ከብዙ ተሽከርካሪዎች ቀረጥ እንዲቀርጡ በማድረግ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገኘታቸውን ጠቁመው፣ የሚፈለግባቸውን ገቢ ካስገቡ በኋላ መለቀቃቸውን አምነዋል፡፡ ግዴታቸውን በመወጣታቸው መሸለም እንጂ ጥፋተኛም ሆነ ወንጀለኛ ሊባሉ እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡ ከጠቋሚ ጋር በሚገናኝ የቀረበባቸውን ክስ የፈጠራና የውሸት መሆኑን፣ ክስን ማንሳት በሚመለከትም ክስ የሚነሳው ለፍርድ ቤት በተጻፈ ሕጋዊ ደብዳቤ እንጂ በእሳቸው ትዕዛዝ አለመሆኑን በመግለጽ፣ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ሰብስበዋል በሚል ስለቀረበባቸው ጉዳይ ሲያስረዱ፣ ‹‹በእኔና ቤተሰቤ ተገኘ የተባለው ሀብት ስህተት አለበት፡፡ ኮምፒዩተሮችና ላፕቶፖች የክስ መሠረት ሆነዋል፡፡ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት የለኝም፣ በስህተት የተጨመረ ነው፡፡ ሁሉንም ያላቸውን ሀብት በሀብት ማስመዝገብ አዋጅ መሠረት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መያዝ በሚለው ክስ እኔና ባለቤቴ በታሪክ የመጀመሪያ እንሆናለን፡፡ ባለቤቴ ከመከላከያ አባልነት ስትለይ ኒሻን ተሸልማ በክብር የወጣች ነች፤›› በማለት፣ የቀረበባቸው ክስ ሁሉ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ክሱም ሕጋዊ አለመሆኑን አክለዋል፡፡
በቤታቸው መሣሪያ መገኘቱን በሚመለከት ‹‹ሁለታችንም ታጋዮች ነን፡፡ መሣሪያ መገኘቱ ወንጀል አይደለም፤›› በማለት፣ ወንጀል ቢሆን እንኳን የመክሰስ ሥልጣኑ የኮሚሽኑ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡
አቶ መሐመድ የሱፍን (የኦፊስ ቴክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤት) ጉቦ ጠይቀዋል ስለተባለው አቶ ገብረዋህድ፣ ‹‹ይኼ አሉባልታ ነው፡፡ ሰውዬውን በፍጹም አላውቀውም፤ ደላላም አላውቅም፤ ሰውዬው የታክስ አጭበርባሪ ሆኖ በመገኘቱ ታስሮ የተወሰነበት ነው፤›› ብለዋል፡፡
አቶ ፍጹም ገብረ መድኅን የተባሉ ተጠርጣሪን በመጠየቅ አሥር ሺሕ ብር የሚገመት የቤት ዲዛይን ስለማሠራታቸው አቶ ገብረዋህድ እንዳብራሩት፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 16 ቤት አለው ተብሎ በካሜራ ተቀርፆ መነገሩ የሚያሳዝን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹እኔ በአዲስ አበባ ውስጥ አንዲት ጐጆ የለኝም፡፡ ቢኖረኝ ኖሮ ልጆቼ መጠለያ አያጡም ነበር፤›› ብለው፣ መሬት ግን መቀበላቸውን አልሸሸጉም፡፡ ቤት ለመሥራት አቅም ስለሌላቸውም እንዳልሠሩበት ገልጸዋል፡፡ ‹‹እንደ ከሳሾቼ 100,000 የማከራየው ቤት የለኝም፤›› ብለዋል፡፡ በአቶ ገብረዋህድ የመጨረሻ ንግግር ያልተደሰተው ፍርድ ቤቱ፣ የሌሎች ሰዎችን ሥራና ክብር መንካቱ ተገቢ ሆኖ እንዳላገኘውና እሳቸውም ለወደፊት እንዲታረሙ አስጠንቅቋል፡፡ በመጨረሻ ሁለት ተጠርጣሪዎች ንብረታቸው እንደታገደባቸውና ጠበቃ ማቆም እንደማይችሉ በመግለጻቸው፣ ቃለ መሀላ ፈጽመው መንግሥት እንዲያቆምላቸው ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡
የኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ፣ በተከታታይ ቀጠሮዎች ፍርድ ቤት ባለመቅረባቸውና ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል መተኛታቸው በመገለጹ፣ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የግለሰቡ ሕመም ፍርድ ቤት የሚያስቀርባቸው ወይም የማይችሉ ስለመሆኑ ሆስፒታሉን ጠይቆ ማስረጃ እንዲያቀርብ ታዞ፣ ሆስፒታሉ በሰጠው ምላሽ አቶ ከተማ አጭር ጊዜ ለሚቆይ ችሎት ከሆነ ፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚችሉ ምላሽ መስጠቱን ሰኔ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የቀረበባቸውን ክሶች ክደው የተከራከሩ በመሆናቸው፣ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮቹን ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ አቅርቦ እንዲያሰማ ታዟል፡፡

No comments:

Post a Comment