አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
1 million Iraqi military disintegrated by 10 thousand fundamentalists 1 ሚሊዮን የኢራቅ ጦር በ10ሺ አክራሪዎች እየተፍረከረከ ነው
አገር ሲፈርስ እንዲህ ነው? ኢራቅ ለሶስት እየተሰነጠቀች ነው
1ሺ የአሸባሪ ቡድን ታጣቂዎች 30ሺ የኢራቅ ወታደሮችን አሸነፉ
በ3 ቀናት ውስጥ ትልልቅ ከተሞችን እየወረረ ከዋና ከተማዋ ደጃፍ ደርሷል
አሸባሪው ቡድን በሂሊኮፕተሮች፣ በታንኮች፣ በብረት ለበስ መኪኖች ተንበሻበሸ
ከመንግስት ባንክ 480 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ጥሬ ገንዘብ አግኝተዋል
በአንድ ቀን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሞሱል ከተማ ነዋሪዎች ተሰደዱ

የኢራቅ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ሰሞኑን ለአቡበከር ተንበርክካለች። በነዳጅ ሃብት የሚታወቁ ከተሞችና አካባቢዎችን
ጨምሮ ቲክሪትሪትና ሳማራ፣ የመሳሰሉ ከተሞችም እንዲሁ አቡበከር በሚመራው አሸባሪ ቡድን (አይሲስ) ስር ገብተዋል፡፡
ማክሰኞ እለት በተጀመረው ወረራ ከሶሪያ ድንበር ተነስቶ በሦስት ቀናት ባግዳድ ደጃፍ ደርሷል የአቡበከር አይሲስ፡፡
የአቡበከር ታሪክ ብዙ ባይታወቅም፤ አላማው ግን ድብቅ አይደለም። ሶሪያን፣ ኢራቅንና ሊባኖስን አንድ ላይ
ጨፍልቆ፤ ከቱርክ እና ከኢራን የተወሰነ አካባቢ ቆርሶ፣ ሳውዲ ዓረቢያንና ግብፅን ጭምር በመጠቅለል ሃይማኖታዊ
መንግስት ለመመስረት የተቋቋመ ነው። ሊሆን የማይችልና የማይጨበጥ ከንቱ ቅዠት ይመስላል?
አስፈሪ ቅዠት መሆኑ ባያከራክርም፤ “ሊሆን የማይችል ነገር” አይደለም፡፡ የአይሲስ የሰሞኑ ዘመቻ ለዚህ ምስክር ነው፡፡
አንድ ሺ የሚሆኑ አክራሪው ቡድን ታጣቂዎች፣ በሞሱልና በአካባቢው ላይ በከፈቱት ጥቃት 30ሺ ገደማ የመንግስት ጦር ጨርቄን ማቄን ሳይል ሸሽቶ ሄዷል - አንድ የጦር ካምፕ ውስጥ ተቀምጠው የነበሩ 20 ታንኮችና 2 ሄሊኮፕተሮችን ጨምሮ በርካታ ብረት ለበስ መኪኖችና የጦር መሳሪያዎች በአክራሪው እጅ ገብተዋል። የመኪኖቹ ብዛት ቀላል አይደለም። በመቶ የሚቆጠሩ የጦር መኪኖች ናቸው የተማረኩት። ይህም ብቻ አይደለም። የአይሲስ ተዋጊዎች ሞሱል ከሚገኘው የመንግስት ባንክ ውስጥ 480 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ጥሬ ገንዘብ አፍሰው ወስደዋል።
ከአንድ የጦር ካምፕ ያን ሁሉ የጦር መሳሪያና ንብረት የማረኩ የአይሲስ ታጣቂዎች፤ ከሌሎች የጦር ካምፖች ምን ያህል ምርኮ እንደሰበሰቡ ቆጥሮ ለመጨረስ አስቸጋሪ ነው፡፡ 30ሺ ያህል ወታደሮችን አሰልፈው የነበሩ ሁለት የመንግስት ክፍለ ጦሮች፤ በአንድ ምሽት ብን ብለው ጠፍተዋል፡፡ ካምፖቻቸውን እየጣሉ፣ መሳሪያቸውን እየወረወሩ፣ ወታደራዊ ልብሳቸውን እያወለቁ የሸሹት የመንግስት ወታደሮች በየአቅጣጫው ተበታትነዋል። ማምለጥ አቅቷቸው በአሸባሪው ቡድን የተማረኩ በሺ የሚቆጠሩ ወታደሮች ደግሞ እንደ እንስሳ እየታገዱ ሲገረፉና ሲደበደቡ ታይተዋል፡፡
ድንበር ተሻጋሪ ሃይማኖታዊ መንግስት ለመመስረት ዘመቻ እያካሄደ የሚገኘው አይሲስ፣ ረዥም ታሪክ የለውም። በእርግጥ ተዋጊዎቹና መሪዎቹ አዲስ አይደሉም። በኢራቅ የአልቃይዳ ወኪል በመሆን ለአመታት ሽብር ሲፈጥሩ የነበሩ ናቸው። ከአልቃይዳ ተገንጥለው አይሲስ የተሰኘውን ቡድን የመሰረቱት ግን የዛሬ አመት ገደማ ነው። “አልቃይዳ ለዘብተኛ ነው በሚል ነው” የተገነጠሉት። በሌላ አነጋገር፤ የአይሲስ ተዋጊዎች ከአልቃይዳ የባሱ የሃይማኖት አክራሪዎhttp://j.mp/1n78rC7

No comments:
Post a Comment