Monday, June 30, 2014

"ያ እብሪተኛው፣ ህፃናትን የጨፈጨፈ ወራሪ ኃይል የገባበት ገብቼ እደመስስና ወዳንተ እመለሳለሁ" (ሻዕብያ ደምሲሰ መልሰይ ናባኻ እየ)

Abraha Desta
2 mins ·
"በርሀ ሻዕብያ" In My Mind
==================
በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ነው። ሻዕብያ ኢትዮጵያን ለመወረር ዝግጅቱ ማጠናቀቁ እየታወቀ፣ ራሳችንን ለመከላከል መዘጋጀት እንዳለብን እየተነገረ ዝምታ መረጥን። አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ (በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር) የሻዕብያን ዝግጅት ለኢትዮጵያ መንግስት ያስተላልፍ ነበር። ገብሩ አስራት፣ ስየ አብርሃና ሌሎች ለመለስ ዜናዊ ይነግሩት ነበር። መለስ ግን ዝምታ መረጠ። ሳንዘጋጅ ተወረርን። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፈርሶ ስለነበር ምልሻዎች፣ ፖሊሶችና የቀድሞ ታጋዮች ሙሉ ዝግጅት ሳያደርጉ ወደ ጦር ግንባር ተላኩ። ሻዕብያ ጨረሳቸው። ባጭር ግዜ ብዙ የኢትዮጵያ ወጣቶች ዳር ድንበራቸው ለማስከበር ቆርጠው ተነሱና የሻዕብያን ኃይል ደመሰሱ። መሬታችንን በደማቸው አስመለሱ። ለሀገራቸው መስውእት ከፈሉ። ክብር ይገባቸዋል።
ሻዕብያን ከደመሰሰ በኋላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዓሰብን መቆጣጠር ይችል ነበር። ዓሰብን እንዳይቆጣጠር ተብሎ እዛ አከባቢ የነበረ መከላከያ ሰራዊታችን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንዲመለስ ተደረገ። በተመሳሳይ ግዜ 'በርሀ ሻዕብያ" በሚል ስም የሚታወቅ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መኮነን 23ኛ ክፍለጦር ይዞ የሻዕብያን ወታደሮችን ደምስሶ የኢሳያስን መንግስት ለመደምሰስ አስመራ ለመግባት ጥቂት ኪሎሜትሮች ሲቀሩት "ተመለስ፣ የሌላ ሀገር መሬት አንወርም!" የሚል ትእዛዝ ተቀበለ።
በርሀ ሻዕብያ "አልመለስም" አለ። "ያ እብሪተኛው፣ ህፃናትን የጨፈጨፈ ወራሪ ኃይል የገባበት ገብቼ እደመስስና ወዳንተ እመለሳለሁ" (ሻዕብያ ደምሲሰ መልሰይ ናባኻ እየ) አለ። ወደ አሥመራ ሲገሰግስ የነበረ የበርሀ ሻዕብያ ክፍለጦር ፈተና እንዲገጥመው ተደረገ። ሆን ተብሎ በመለስ የተደረገ መሆኑ ነው። የበርሀ ክፍለጦር ሲመለስ ወታደሮቹ ጥቃት ተፈፀመባቸው። አለቁ። (ከነዚህ ሲመለሱ ካለቁ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት አጎቴ ይገኝባቸዋል)።
ይህን ሁሉ መስዋእት ከተከፈለ በኋላ የኢትዮጵያ ሰራዊት አሥመራን እንዳይገባ መከልከሉ ክፉኛ አዘነ። ተስፋ ቆረጠ። በርሀ ሻዕብያም ተመለሰ። ዓሰብም የሻዕብያ ወታደሮች በድጋሜ ተቆጣጠሩት። ብዙ ደም ከፈሰሰ በኋላ፣ ብዙ መስዋእት ከተከፈለ በኋላ ወደ ድርድር ተገባና መስዋእት የተከፈለበትን መሬት ለኤርትራ እንዲወሰን ተደረገ። ከጦርነት በኋላ ድርድር ብሎ ነገር አለንዴ?
ነገሮች ሁሉ ተገላበጡና በርሀ ሻዕብያም ተመለሰ። በርሀ ሻዕብያ ላደርገው አስተዋፅዖ ሽልማት ሲገባው የመለስ ዒላማ ሆነ። ከነ ሚስቱ ተገድሎ ተገኘ። ከዛ 'ሚስቱ ከደለችው" አሉን። ይህን ሁሉ እንደሚፈፀም የሚያውቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዴት ነፃ ይሁኑ?
በርሀ ሻዕብያን አደንቃለሁ። ለሀገር መስዋእት የሚሆኑ ይገደላሉ። ሀገር የሚሸጡ ደግሞ ይሸለማሉ፤ ፎቶአቸውን በየመስርያቤቱ ይለጠፋል። ጀግኖች ተሰዉ፤ ሌቦች ሀገር መሩ፣ ሀገር አጠፉ። እውነተኛው ታሪክ የሚጋለጥበት ግዜ ሩቅ አይሆንም።
ክብር ለሀገርና ህዝብ ደህንነት ለተሰዉ ጀግኖች!
It is so!!!

No comments:

Post a Comment