አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
ይድረስ ሀገርክን ለዘነጋኸው የዘመኑ መምህር
ከኢመማ ተጋድሎ ምን እንማራለን?
ዘመን በመቁጠር ሂደት የወርና የሁኔታ ግጥምጥሞሽ ይከሰታል፡፡ በሰነድ የተያዘ ማስረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 14 ቀን 1941 ዓ.ም ‹‹የመምህራን ህብረት›› በዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት በአዲስ አበባ ተቋቋመ፡፡ የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበርም አቶ ሚሊዮን ነቅንቅ ነበሩ፡፡ ይህ የመምህራን ህብረት ስያሜውን እንደያዘ እስከ 1954 ዓ.ም ድረስ ቀጥሏል፡፡ ኅብረቱ ከየትኛውም አካል መንግስትን ጨምሮ አደናቃፊ ኃይል ሣይገጥመው እንዲያውም ድጋፍ እየተደረገለት ነበር እዚህ ወቅት ድረስ የቆየው፡፡ ምዝገባ፣ በህግ የመታወቅና ያለመታወቅ ጥያቄም አልተነሳም ነበር፡፡ ኅብረቱ በ1953 የእውቅና የምዝገባ ጥያቄ ተነስቶ በዚያውም አፈናና የመንግስት ጣልቃገብነት ተጨምሮበት ጉዞው አስቸጋሪ ሆነ፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ሁኔታ እንዳለ ሆኖ 12ኛው በፈረንሳይ አገር ተደርጎ የነበረው የዓለም መምህራን ማህበር ጉባኤ 13ኛው ጉባኤ በአፍሪካ ውስጥ እንዲደረግ ወስኖ ስለነበር በወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸውና ቀደም ብሎም በመምህራን ማህበር አመራር ላይ የነበሩት አቶ መኮንን ዶሪ ትምህርት ሚኒስትርን በመወከል 13ኛው የዓለም መምህራን ጉባኤ 1957 ዓ.ም በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ጋበዙ፡፡ ነገር ግን ማህበሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ባለመቋቋሙ ሕጋዊ ሰውነት የሌለው መሆኑ አወዛጋቢ ሆነ፡፡ወዲያውኑ ለአፄ ኃይለስላሴ ቀርቦና ፈቅደው የመምህራን ህብረት ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ አቅርቦት የነበረው የምዝገባና ሕጋዊነት ጥያቄ በመጋቢት 14 ቀን 1957 ዓ.ም ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ‹‹ኢመማ›› በሚል ስያሜ ተመዘገበ፡፡ አፄ ኃይለስላሴ ይህን ድርጊት የፈፀሙት የዓለም አቀፍ ዝና ለማግኘት ሲሉና የዓለም መምህራን ማህበርም የአሜሪካን መንግሥት ድጋፍ ስለነበረው መጋፋቱን ባለመፈለግ እንደሆነ ቢነገርም የኢትዮጵያ መምህራን በአፄው ዘመን ከደርግም ሆነ ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የተሻለ ነፃነትና ክብር እንደነበራቸው የሚያሳይ መሰለኝ፡፡ ከተሳሳትኩ እታረማለሁ፡፡ ለነገሩ ደመወዛቸውሳይቀር ከወረዳ እና አውራጃ አስተዳዳሪዎች እኩል (በለጠ) ነበር፤ የዛሬን አያድርገውና ወሰዳት አስተማሪም ተብሎ ተዘፍኖም ነበር፡፡
ግራም ነፈሠ ቀኝ በየጠቅላይ ግዛቶቹ የማህበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተቋቁመው ወኪሎቻቸውን መላክ በመቻላቸው 35 አባላት ነሐሴ ወር 1957 ዓ.ም በአፍሪካ አዳራሽ በተካሄደው 13ኛው የዓለም መምህራን ማህበር ጉባኤ ላይ ተሳተፉ፡፡ ይህ የመምህራን የትግልና የመስእዋትነት ውጤት መሆኑን ሲያመለክት ከ1953-1957 በነበረው ጊዜ በአገር ውስጥና በውጭ የኢመማ ግንኙነት ተዳክሞ የመታየቱ ሰበብ በ1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግስት ማህበሩ ድጋፍ ሰጥቷል የሚል እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በ1958 ዓ.ም ላይ የወጣው የመምህራን የደመወዝ ደረጃ በመምህራን በኩል ተቀባይነት በማጣቱ በ1960 ዓ.ም በአቶ ከበደ ደስታ ይመራ የነበረው የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር መምህራንን አስተባብሮ መንግስት ያልጠበቀው የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ሌላ የመንግስት ጣልቃገብነት፣ የአፈናና እንደ አሁኑ የከፋ ባይሆንም የመከፋፈል እርምጃ መከሰቱ አልቀረም፡፡ (በነገራችን ላይ አቶ ከበደ በዘመነ ህወሓት በአንጋፋው ኢመማ የአባት መምህራን ተወካይ ሆነው ሲያገለግሉ የእስር ገፈት ቀማሽ እንደነበሩ አስታውሳለኹ)
ቀደም ሲል በመምህራን ያቀረቡት የደመወዝ ‹‹እስኬል›› ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ የትምህርት ዘርፍ ክለሳ (Education Sector Review) ወጥቶ ይፋ ሆነ፡፡ ይህም የትምህርት ዘርፍ ክለሣ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ የተመሠረቱ ተቃውሞ ነበረው፡፡
የሴክተር ሪቪው ተግባራዊነትና ውጤቱ ለመምህራን ሳይገለፅ በሚስጢር መያዙ፣ መምህራን፣ ወላጆችና ተማሪዎች ተሳትፈው አስተያየት ያልሰጡበት መሆኑ፣ በሙከራ ሳይታይ በአገሪቱ በሙሉ በሥራ ለመዋል መሞከሩ፣ ለከፍተኛ ትምህርት ገንዘብ እንዲከፈልበት መጠየቁ፣ ለመምህራን የታሰበው መነሻ ደመወዝ ብር 153 መሆኑ፣ በገጠር የመሬት ይዞታ ለውጥ ሳይደረግበት የገበሬውን ኑሮ ያሻሽላል መባሉና ሌሎችም ነበሩ፡፡
በዚህም መሰረት በ1966 ዓ.ም ከታህሳስ 12 እስከ 15 የዘለቀ ልዩ ጠቅላላ የማህበሩ ጉባኤ ተጠርቶ የሴክተር
ሪቪውና የመምህራን ደመወዝ እስኬል መጠን ወስኖ ከሌሎች ተዛማጅ ጥያቄቆች ጋር መልስ እንዲሰጣቸው ተስማምቶ ተነሳ፡፡ እስከ የካቲት 11 ቀን 1966 ዓ.ም ድረስ ለጥያቄዎቹ መልስ ሳይሰጥና የመምህራን ድምፅ በወኪሎቻቸው አማካኝነት ቀርቦ ሳይሰማ ቢቀር ማህበሩ ሁኔታው እንዲቃና የተቻውን ሁሉ ስለፈፀመ የመሰላቸውን እርምጃ ቢወስዱ በኃላፊነትም እንደማይጠየቅም አሳወቀ፡፡ የመምህራን ጥያቄ መሠረታዊና ስር የሰደደ መሆኑን ያልተገነዘበው ትምህርት ሚኒስቴር ግን በራሱ አካሄድ የወሰነውን ፕሮግራሙን ተግባራዊ ማድረግ ስለጀመረ አፈፃፀሙ ማህበሩንም ሆነ መምህራንን ይበልጡኑ ለተቃውሞ አስነሳ፡፡ ዘግይቶም ቢሆን ትምህርት ሚኒስቴር የሠራተኛ ማስተዳደሪያ ኮሚሽንና የኢመማ መሪዎች በአንድነት ለድርድር በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ስብሰባ ቢያደርጉም ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡ ጉዳዩን ለተመለከተው የዘውዱ ሥርዓት ባለሥልጣናት በውይይትና በመደራደር ረገድ ከደርግና ከህወሓት/ኢህአዴግ ተሻሚዎች በተሻለ ደረጃ መሆናቸውን ነው፡፡ ከላይ ለማስታወስ እንደሞከርኩት የማህበሩ የታሕሳስ 1966 ዓ.ም ልዩ ጠቅላለ ጉባኤ ባሳወቀውና በማስጠንቀቂያው መሠረት የካቲት 11 ቀን 1966 ዓ.ም ሥራ በማቆም ከመምህራን ጎን ቆሙ፣ ሥራ ባላቆሙት ታክሲ ነጂዎች ላይም እርምጃ ወሰዱ፤ የሠራተኛ ማህበራት አባላትም ሥራ ለማቆም ማቀዳቸውን ታወቀ፡፡ ይህ ሥርዓት ለውጥ አምጭ የኢትዮጵያ አብዮት ዋዜማ መሆኑ ለኢመማ የሕዝብ አለኝታነት አሌ የማይባል ነው፡፡ መምህራን ሥራ ማቆማቸውን ሲሠሙ አፄው፡- አስፈላጊ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ሴክተር ሪቪው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ፤የደመወዝ ጉዳይ ተጠንቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ስለሚደረግ መምህራን ይህን አውቀው ሥራ እንዲጀምሩ የካቲት 16 ቀን 1966 ዓ.ም አስታወቁ፡፡ በዚህም በዚያ የጥያቄው ዓይነትና ብዛት አገር አቀፍና ህዝባዊ ይዘት ተላብሶ ሕዝባዊ አመፅ (አብዮት) አስነስቶ የዘውዱን ሥርዓት አስ
ወገደ፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጥያቄዎች ከነበሩት ጥቂቶቹና ጎላ ብለው ይታዩ የነበሩት የሚከተሉት ናቸው ‹‹መሬት ላራሹ››፣ ‹‹የድሃ ልጅ ይማር››፣ ‹‹ዴሞክራሲዊ መብቶች ያለገደብ ይከበሩ››፣‹‹የመምህራን የደመወዝ እስኬል ይሻሻል››፣ ‹‹በጋዝ ላይ የተደረገው ጭማሪ ይነሳ››፣‹‹የሃይማኖት እኩልነት ይከበር››፣ ‹‹ህዝባዊ መንግስት ይቋቋም››፣ ‹‹የሴቶች ድርብ ጭቆና ይወገድ››፣ ‹‹የሴቶች የእኩልነት መብት ይከበር›› ‹‹ፊውዳሊዝም ይውደም››፣ ‹‹ኢምፔሪያሊዝምይውደም››፣ ‹‹የሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 8 ሰዓት ይሁን››፣ ‹‹የብሔረሰቦች የእኩልነት መብት ይከበር››...ወዘተ የሚሉ ነበሩ፡፡ እውን ከላይ የተጠቀሱት የሕዝብ ጥያቄዎች ዛሬ በዚህ ዘመን ተመልሠው ይሆን? ኢመማ በአብዮቱ ወቅት የተጫወተው ሚና በዋዛ
የሚታይ አልነበረም፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ እንዳልካቸመኮንን ውጥረቱን ለማስታገስ የኢመማ አመራር አባላትን ጠቅላይ ፖስታ ቤት ቢሮአቸው አጠርተው መምህራንን እንዲያስታግሡላቸው ትብብር ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል፡፡ የጦር ሀይሎች፣ የፖሊስ ሠራዊትና የብሔራዊ ጦር ሰኔ 21 ቀን 1966 ዓ.ም እንደቋቋመ አንድ ቡድን ኢመማ ጽ/ቤት መጥቶ አነጋግሯል፡፡
የትብብር ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ሐምሌ 3 ቀን 1966 ዓ.ም ኮሚቴ ለኢመማ በፃፈው ደብዳቤ መነሻነት ከሐምሌ 3-5 ቀን 1966 ዓ.ም የተሰበሰበው የኢመማ ሥራ አስያጅ ኮሚቴ በሰጠው መልስ ላይ ‹‹ኮሚቴ›› የሚለውን
‹‹ደርግ›› በሚል ስለተካው ወራደራዊ ኮሚቴው ከኢመማ በወሰደው ‹‹ደርግ›› ብሎ እራሱን እንደሰየመ ይታወሳል፡፡ ኢመማና ደርግ ዓይንና አፍንጫ ነበሩ፡፡ በተለይ ጳጉሜ 1967 ዓ.ም በጅማ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥርዓተ ትምህርት፣ ዝግጅትና ከዚሁ ጋር አስታኮ የወታደራዊውን መንግስት አካሄድ በመቃወም የኢኮኖሚና የመብት ጥያቄዎችን አቅርቦ መልስ የማይሰጥ ከሆነ ሕዳር 7 ቀን 1968 ዓ.ም መምህራን የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ወስኖ ተበተነ፡፡ አድማውም አልተሳካም፣ ስብሰባም
አልተቻለም፡፡ ምክንያቱም ደርግ ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት በመወያየትና በመደራደር ፈንታ የኃይል እርምጃና አፈናን በመምራጡ ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢመማ መሪያዎች ታደኑ ታሰሩ፣ ተገደሉ፣ ተሰወሩ፣ ለስደት ተዳረጉ፡፡ እስከ 1971 ዓ.ም ድረስ ዋናው ማህበር ሥራ
በማቋረጡ የኢመማ ጽ/ቤት ሠራተኞች እንኳ ደመወዝ የሚከፍላቸው አጥተው በብድር ስም የወሎ መምህራን ማህበር እየከፈላቸው እንደቆየ የማህበሩ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ከዚያ በኋላ አፋኙ ደርግ አንድ ጊዜ በኢማሌድ፣
አንዴ በኢሠፓአኮ፣ በሌላ ጊዜ በኢሠፓ አመራር ስር እያለ
ማህበሩ ምርኮኛ አባላቱን ጥገት አድርጎ እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ ባተ፡፡
በ1983 ዓ.ም በውስጥ ቦርቧሪዎች፣ ቅጥረኝነትና በታሪካዊ ጠላቶቻችን ስውር ድጋፍ በኢትዮጵያ ገበሬዎች ተጋድሎ ህወሓት/ኢህአዴግ የአገሪቱን ጦር አተራምሶ፣ ደርግና አገሪቱ ያፈራቻቸውን እውቅ የጦር ጄኔራሎች
በማጥፋት አገሪቱን በመላ ከተቆጣጠረ በኋላ የህዝባዊ ማህበራትን እያፈረሱ ንብረታቸውን እየወሰነ ጽ/ቤቶቻቸውን ሲዘጋ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በኢመማ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ አልወሰደም፡፡ ይሁን እንጂ የማህበሩን አመራር ይዘው የቆዩት መሪዎች አዲሱ ክስተት ውስጥ በነፃነት መሥራት የማይችሉ መሆናቸው ስለገባቸውና የማህበሩ ቆይታም በኢሠፓ ቅኝት የታጠረ ስለነበር ከመምህራንም ተቃውሞ ስለገጠማቸው ሌላ ምርጫ
ተካሂዶ ለአዲስ መሪዎች አስረክበው ለመውጣት በመንግስት ስም የተቀመጠውን ቡድን ጠይቀው በተፈቀደላቸው ወቅቱ ዝብርቅርቅ ሁኔታ የተፈጠሩበት ስለነበር በመላው ኢትዮጵያ ምርጫ እንዲካሄድ የሚያደርግ
አካል ባለመሆኑ በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ማህበሩን እንደገና የሚያደራጅና ጉባኤ ጠርቶ ምርጫ የሚያካሂድ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ሁኔታዎች ተመቻችተው ሰኔ 21 ቀን 1984 ዓ.ም ልዩ የምክር ቤት ስብሰባ ኮሚቴው ተመረጠ፡፡ መምህራን በተወካዮቻቸው በኩል ለተቋቋመው የአስተባባሪ ኮሚቴው የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ በርካታ ጥያቄዎችን ልከው ኮሚቴው ከተላኩት ሁሉ ጨምቆ 20 ጥያቄዎችን ለሽግግር መንግሥቱ አቀረበ፡፡ ‹‹ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ›› እንዲሉ ነውና አገዛዙ በጡጫው መርገጥ፣ ፍትህንም መደፍጠጥ ገና በጠዋቱ በስልጣን መሟሸት ጀመረ፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ገሸሽ በማድረግ ማህበሩን በዘር ፖለቲካው ትታዩ ‹‹የአማራ››፣ ‹‹የኦሮሞ››፣ ‹‹የትግራይ››፣ ‹‹የሶማሊ››፣ ‹‹የደቡብ››... ወዘተ መምህራን ማህበር እያለ
ለማዋቀር የቀየሰውን እቅድ አዲሱ የኢመማ አመራር በግልፅና በአደባባይ ስለተቃወመ አገዛዙ በማህበሩና በአባላቱ ላይ እመቃ፣ ወከባ፣ እስራት፣ ማፈናቀል፣ መሰወር ስራዬ ብሎ ተያያዘው፡፡ ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት
ተለጣፊ ማህበር አቋቁሞ ህጋዊ ማህበሩንና አመራሩን እየከሰሰ 4 ጊዜ ለኢመማ ፍ/ቤት ቢፈርድም እስከዛሬ ድረስ ተፈፃሚ አልሆነም፡፡ የባሰውና የከፋው አደጋ የትምህርቱ ጥራት መዝቀጡ በመምህራን፣ በተተኪው ትውልድና በሀገሪቱ ላይ ከደረሱት አደጋዎች የሚደመር ነው፡፡ ስለሆነም ኢመማና መምህራን ካለፉት ስርዓቶች በከፋ መልኩ አደጋ ላይ የወደቁበት ጊዜ ላይ የምንገኝ ይመስለኛል፡፡
ማጠቃለያ
ዛሬ የሀገራችን ህልውና በጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባበት ሁኔታ ላይ ነው የምንገኘው፡፡ ምን እስኪሆን ነው ዝም ብለን የምንመለከተው? ዝምታ ለበግም አልበጃት፡፡ ቤታችን የውጪ ጠላቶቻችንና የጥቂቶች መፈንጫ ሆኖ
የለ!! ክብር፣ ነፃነት፣... ሁሉም ነገር የሚገኘው በሀገር ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ለእኛ መምህራንና ለምሁራን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ነው፡፡ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ጋር በመሆን ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የህይወት መስዕዋትነት የከፈሉት እነ ዘርዓይ ድረስ፣ ሞገስ አሰገዶም፣ አብርሃ
ደቦጭ፣ እኮ መምህራን ነበሩ፡፡ ለሀገር መሞት አኩሪ ግዳጅ መሆኑን ያስተማሩ ብርቅዬ ጀግኖች፡፡ አርዓያነታቸውን ልንከተላቸው ይገባል፡፡ ኢመማ ከተመሰረት 65 አመት አልፏል፡፡ ሆኖም ግን ኢመማ ስሙ ብቻ የቀረ ይመስለኛል፡፡
የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያት፣ አቶ አወቀ፣ አቶ አባተ አንጎሬ፣ አባት መምህር ከበደ ደስታ፣ አሰፋ ማሩ፣ አያሌው ይመር፣ አቶ ካሳሁን፣ አያሌው አስረስ፣ ወ/ሮ ብርሃነ ወርቅ ወዘተ... የታሰሩለት፣ የሞቱለት፣ የተሰደዱለት አንጋፋው ኢመማ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ አባላት ቢኖሩትም ድምጹ አይሰማም፤ ለምን? የእነዚህ ቁልፍ ጥያቄ መልስ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መምህር እጅ ውስጥ የሚገኝ ይመስለኛል፡፡
የአገሩ ህልውና የሚያሳስበው መምህር በሙሉ ነፃ የሙያ ማህበር ለመመስረት መታገል ይገባዋል፡፡ ዘወትር በጓዳ ውስጥ ማንጎራጎር የሚጠቅመን አይመስለኝም፡፡ የቀለም ቀንዲሉ መምህር እንደ ጧፍ ነዶ ለሀገር ብርሃን መስጠት አለበት፡፡ የኢትዮጵያን መምህራን በሙሉ ለአንድ ቀን እንኳን ቢተባበሩ ስርዓቱ ሊያዳምጥ ይችል ነበር፡፡ ይሄ ግን እውንሊሆን አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት የእንጀራ ገመዴ ይበጠሳል በማለት በፍርኃት ቆፈን ውስጥ ገብተናል፡፡ የኢመማ ታሪክ በአንፀባራቂ ኮከብ የተፃፈ መሆኑን የእዚህ ዘመን መምህር ይገንዘብ፡፡
የትምህርት ጥራት መዝቀጥ፣ የተማሪዎቻችን የትምህርት ፍላጎት መሞትና የንባብ ባህል በከፍተኛ ደረጃ መውረድ እንዲሁም ኩረጃ እንደ ወረርሽኝ መዛመት እንቅልፍ ሊነሱን ይገባል፡፡ ሁሉንም ሀጢያቶች በህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ ላይ መጫኑ (ማላከኩ) ከታሪክ ተጠያቂነት አያድንም፡፡ ቁጭ ብለን የሰቀልናቸውን ቆመን ለማውረድ እየተቸገረን ነው፡፡ በየትምህርት ቤቱ የተሰገሰጉ የስርዓቱ ባለሟሎች መምህሩ የሚመገበውን ሳይቀር ለመቆጣጠር ይዳዳቸዋል፡፡ ሆኖም ጉዳዩ የኢትዮጵያ ጉዳይ በመሆኑ ከተቻለ ማስተማር ይገባል፡፡ ዘይትና ውኃ እን
ደማይደባለቁ ሁሉ ፖለቲካና ትምህርት ሊደባለቁ አይገባቸውም፡፡ ትምህርት በፖለቲካዊ ፍልፍስና ተቦክቶና ተጋግሮ ከቀረበ ትውልዱን ያጠፋል፡፡
ለመሆኑ ት/ቤቶች ውስጥ በፖለቲካ ስብሰባዎች ምክንያት የክፍል ጊዜዎች
ብክነት ሲያጋጥም ለምን ብለን ጠይቀን እናቃለን? የገናዋ በግ በፋሲካዋ በግ... እንዲሉ የኢትዮጵያውያን መምህራን መብት ሳይጠበቅ ለጥቂቶች ብቻ ማርና ወተት ቢዘንብላቸው የትም መድረስ አይቻልም፡፡
ውድ መምህራን ነፃ እና ገለልተኛ ማህበር መስርተን በመጀመሪያ የሰውነታችንን መብት እናስከብር፤ ለጥቆም ለዚች ሀገር የሚበጀውን የአስተዳደር ስርዓት ለማምጣት እናስተምር፤ እንመራመር፤ የኢትዮጵያ መምህራን ታሪክ የሚነግረን ይሄንኑ ነው፡፡ የትግራይ፣ የአማራ፣ ኦሮሞ፣...
ወዘተ መምህራን ማህበር እያሉ ለመደራጀት መሞከር በእውነቱ አንገትን ያስደፋል፡፡ የመምህር ነጭ፣ ጥቁር፣ ቀይ የለውም፡፡
መምህር የትም ቦታ መምህር ነው፡፡ ስንቁ ጠመኔ፣ እስኪቢርቶ ደብተርና መፅሐፍ ነው፡
ደረጃ መላኩ
Tilahungesses@gmail.com
ታምራት ታረቀኝ
ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ

No comments:
Post a Comment