Tuesday, June 17, 2014

ጠበቃው በፖሊሰ እየታደነ ነው!

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
ጠበቃው በፖሊሰ እየታደነ ነው!
የሰማያዊ ፓርቲ መስራች የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በፖሊስ እየታደነ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡ ጠበቃ ሳሙኤል ከአሁን ቀደም በሌላ ሰው ስም ‹‹ህዝብ እየተበደለ ነው ብለህ የአስተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ አስተያየት ሰጥተሃል›› ተብሎ ከመከሰሱም ባሻገር በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት ‹‹አገር ለቀህ ካልተሰደድክ እንገድልሃለን›› ተብሎ እንደነበር በወቅቱ ለነገረ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሰል፡፡
በአሁኑ ወቅት ትዕዛዝ ያወጣበት የባሶ ሊበን ወረዳ ሲሆን ፖሊሶቹ ወረዳው ውስጥ የጁቤ የተባለ ቦታ እንዲወስዱት ትዕዛዝ መሰጠቱን ምንጮች እንዳረጋገጡለት አቶ ሳሙኤል ገልጾአል፡፡ ደብረ ማርቆስ ውስጥ እየሰራ የሚገኘው ጠበቃ ሳሙኤል ለምን ወደ ባሶ ሊበን እንዲወሰድ ማዘዣ እንደወጣበት ስንጠይቀው ‹‹ወደዛ እንድወሰድ የተፈለገው ለእኔ ድምጹን የሚያሰማ ሰው አይኖርም በሚልና ለአፈናው እንዲመቻቸው ነው›› ሲል ገልጾልናል፡፡

No comments:

Post a Comment