Sunday, June 29, 2014

ፍትህ የምጎልበት እና ሕግ የማይከበርበት ሀገር ..ሀገር ሊሆን አይችልም ::

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

ፍትህ የምጎልበት እና ሕግ የማይከበርበት ሀገር ..ሀገር ሊሆን አይችልም ::
ሃገርን ሀገር ተብላ እንድትጠራ የሚያደርጋት የህዝቦቹዋ በሕግ ስር ተስማምተው ሕግን አክብረው ሲኖሩ እና ፍትህ ለሁሉም ሕዝብ እኩል ሲደርስ ነው:: አለበለዚያ አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ከሆነ .. አንዱ አዋቂ ሌላው አላዋቂ ከሆነ ...አንዱ ተሰሚ ሌላው መናገር የማይፈቀድለት ከሆነ እኩልነት የለም ፍትህም የለም ስርአትም የለም ሀገሪቷ ለአንዱ ሀገር ለአንዱ እስር ቤት ነች ማለት ነው በዚህ ሁኔታ ሀገር ሕልውናዋ አደጋ ላይ ይወድቃል ::
በኢትዮጵያችንም እየታየ ያለው ይህ ነው ኢህአዴግ እና ደጋፊዎቹ ከሕግ በላይ ሌላው ሕዝብ ከሕግ በታች የሆነበትን ስርአት እየኖርን ነው:: የሀገር እና የህዝብ ሀብት ለፓርቲ አገልግሎት የሚውልበት ስርአት ኢ-ህገመንግስታዊ እና በግልፅ ህገመንግስትን መጣስ ነው:: ኢህአዴግ ህገመንግስትን በየቀኑ እየጣሰ ስለሚኖር ህገ መንግስቱን ሙት ደብዳቤ አድርጎታል ሌላው ሕዝብ ግን እንኩዋን ህገ መንግስትን መጣስ ቀርቶ ህገመንግስታዊ መብት የሆነውን መቃወም ያሰድበዋል ሌላሌላም ብዙ መዘዞችን ያስከትላል::
ኢህአዴግ ትልልቅ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን እንደፖለቲካ ክንፉ እየተጠቀመባቸው የህዝብ ሃብት መሆናቸውን ህዝብም ኢህአዴግም እረስተውታል :: እነዚህ ትልልቅ መስሪያ ቤቶች በሙሉ ኃይላቸው የሚያገለግሉት መጀመሪያ ኢህአዴግን ነው ለምሳሌ እያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ በት ሰራተኞቹ የኢህአዴግ ደጋፊ ያደርጋል ያልሆኑትን በሰበብ አስባብ ያባርራል (ኢ-ህገመንግስታዊ ) በመስሪያ ቤት ውስጥ ቅስቀሳ ማድረግ / የመንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ግንባታዎችን ለኢሕአዴግ ደጋፊ ለሆኑ ተቅዋራጮች መስጠት (ሙስና) መሬት ለመንግስት ደጋፊዎች እና ሹማምንት መስጠት (ሙስና) ትልልቅ መስሪያ ቤቶች ዕቃ ግዥ ሲፈፅሙ ከኢህአዴግ ደጋፊዎች ወይም አባል ነጋዴዎች መፈፀም (ሙስና).......እንደዚህ እያለ ስር የሰደደ ሙስና እና ህገመንግስትን መጣስ ሊከናውን የቻለው የሕግ የበላይነት በኢህአዴግ እና በደጋፊዎቹ ላይ ስለሌለ ነው::
ዛሬ የኮንዶምንየም ቤቶች ግንባታ ኢህአዴግ ድሃውን ሕዝብ የቤት ባለቤት ለማድረግ እና ኑሮን ለማሻሻል እንዳደረገው ደጋግሞ ይናገራል እውነታው ግን ይህንን ፕሮጀክት የጀመረው የጀርመን ተራዶ ድርጅት የሆነው GTZ ከ መንግስት ጋር በመተባበር ነበር ሆኖም በውስጡ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ ሲካሄድበት እንደነበር ይታወቃል ከገበያ ዋጋ በላይ ዕቃ እንደተገዛ በማድረግ ብዙ የኢህአዴግ ወጣት ካድሬዎች ሀብት አግበስብሰውበታል የህንፃውን ግንባት ከባለሙያዎች ገንዘብ በመቀበል ያለትክክለኛ ጫረታ ውል በመፈፀም በአነስተኛ ወጪ ሊገነባ የሚችለውን ግንባታ ከፍተኛ ገንዘብ በኢህአዴግ ደጋፊ ካድሬዎች በመባከኑ ህዝቡ ከኑሮ ውድነቱ ተጨማሪ ሌላ ወጪ እንዲከፍል ተደርጉዋል::
ልማት ቀጣይነት ያለው ነገር ነው መንግስት ቢቀየር ልማት አይቆምም ስለዚህ ልማት ማታለያ ሊሆን አይገባም ኢህአዴግን እና ሃገርን ነጣጥለን ማየት መቻል አለብን ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅት ባለቤቱም ጥቂት ሰዎች ናቸው ኢትዮጵያ ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት ነች ኢህአዴግ ኖረም አልኖረም ኢትዮጵያ ትኖራለች ኢህአዴግ ከመኖሩም በፊት ኢትዮጵያ ኖራለች ከኢህአዴግ በሁዋላም ኢትዮጵያ ትኖራለች :: ለነፃነታችን ባገኘነው ቀዳዳ እንውጣ በምርጫ 2007 ኢህአዴግን በፍፁም ባለመምረጥ ለሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ዕድል እንስጥ:: ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘላለም ትኑር ::
ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያውያን ::

No comments:

Post a Comment