Friday, June 20, 2014

ሱዳን ሃገር የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ!!

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

ሱዳን ሃገር የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ!!
ከሦስት ሳምንታት በፊት ወደ ሊቢያ የሚጓዙ ቁጥራቸው 400 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በፖሊስ ክትትል ተይዘው ሁዳ ተብሎ በሚታወቀው እስር ቤት የታጎሩ ሲሆን ቀድም ብለው እዛው እስር ቤት ውስጥ ከነበሩት 300 ስደተኞች ጋር የቀላቀሏቸው ሲሆን እስር ቤት ሲገቡ ሰውነታቸው በውሃ ጥም እና በምግብ እጥረት በጣም የተዳከመ ሰለነበረ በቦታው የነበሩትም የሱዳን ፖሊሶች በቶሎ ውሃ እንዳይደርስላቸው ስለከለከሉ ብዙዎቹ ተዝለፍልፈው ሲወድቁ ነገሩን በቦታው ሆኖ ሲከታተል የነበረ አንድ የትግራይ ተወላጅ በሆነ እስረኛ በኩል ምናልባት በሚችሉት ቋንቋ ቢነገራቸው ሊሰማቸው ይችል ይሆናል ተብሎ ወደ ኤምባሲ በመደውል ነገሩን ቢያስታውቅም የተሰጠው ምልስ ግን ጭካኔ የተሞላበት እኛ እናንተን አናውቅም እንደገባችሁበት ተወጡት የሚል መልስ ነበር።
ባንጻሩ ግን የኤርትራ ተወላጅ የሆኑት ግን ወደ ኤምባሲያቸው ደውለው ነገሩን ሲያሳውቁ የኤንባሲው ባለስልጣኖች ሁኒታውን ለሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣኖች በማስረዳት ችግሩን እንዲፈቱ በማሳሰባቸው ሁኒታው የተነገራቸው የሱዳን ባለስልጣናት ጉዳዩ በትክክል መፈጸሙን ለማረጋገጥ ወደ ቦታው ሲሄዱ ያጋጠማቸው ነገር አስደንጋጭ ስለነበር 40 የሚሆኑት በሙቀቱ ምክኔያት እና በውሃ ጥም ራሳቸውን ስተው በመገኘታቻው ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ ተደርጓል ሦስቱ እዛው ሂወታቸው አልፏል የተወሰዱበት ሆስፖታል በትክክል ስላልታወቀ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለማንም ግልፅ አይደለም። ሱዳኖች እንኳን ለተራ ስደተኛ ኢትዮጵያውያኖች ቀርቶ ዲፕሎማት ነን ለሚሉትም ቅንጣት ታክል ክብር እንደሌላቸው ሰኔ ሁለት የተፈጸመው ክህስተት ምስክር ነው።
ይሄውም አቶ መሃመድ ቶፍ የሚባል የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በሱዳን ፖሊሶች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ እራሱን እስኪስት ተደብድቦ በቃሪዛአምቡላንስ ላይ ተጭኖ ወደ ሆስፒታል ተልኳል። ይህ የሆነው ማሃከማ ሱቅ አለ ማሃሊ በሚባል የገቢያ አካባቤ ባለ ፍርድቤት ውስጥ ነው። ነገሩም የተነሳው ህጋዊ ባልሆነ ርካሽ ሥራ ላይ ማለትም በካፍቴሪያ ስም በሴተኛ አዳሪነት ይተዳደሩ የነበሩ ሴት እህቶቻችን በጥቆማ ተይዘው ወድ እስርቤት ይላካሉ። ይህ ዲፕሎማት ደግሞ የጥቅም ሰውና ከታሰሩት መሃል በውሽምነት የያዛቸው ሴቶች በመኖራቸው መታሰራቸውን እና ዋስ እንዲፈልግላቸው ካልሆነ እሱ እራሱ ዋስ እንዲሆናቸው ደውልው ያስታውቁታል። ሴት የላከው እንዲሉ ይህ ዲፕሎማት እሴቶቹ ወደተያዙበት ፍርድ ቤት በመሄድ ለፖሊሶች መታወቂያውን በማሳየት ፖሎሶቹ የሰሩት ትክክል እንዳልነበር በቲቢት ተወጥሮ ይናገራል በዚህም አላቆመም ከአንድ ዲፕሎማት የማይጠበቅ ጽያፍ ቃላት በመናገር ጭራሽ ያዙኝ ልቀቁኝ አበዛ በወገኖቹ ላይ የለመደውን እብሪት የተሞላበት ዘለፋ አበዛ በሁኔታው ትግስታቸው ያለቀው የሱዳን ፖሊሶችም በሚያሳዝን ሁኔታ ቀጥቅጠው ሰባብረው ጣሉት በጣም አሳፋሪ ነበር።
ይህን ጉዳይ ለማስተባበል ኢንባሲው ውስጥ የተጠራው ስብሰባም በረብሻና በስድብ በድንጋይ ውርወራ ተጠናቋል።ድሮም በኢንባሲው ቂም የያዘው ስደተኛ በጉዳዩ ተበሳጭቶ ማፈሪያዎች እንደሆኑ ነግሯቸው ተበትኗል። በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በመታወቂያ ምክኔያት ተይዘው በእየስርቤቱ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ምንም መልስ ያልሰጠው ኤምባሲ ከሃገሪቱ ሸሪያ ህግ ጋር የሚጻረር የሰተኛ አዳሪነት ስራ ሲሰሩ ለተያዙት ሴቶች እህቶቻችንን ለማስፈታት ሲሞክሩ የደረሰበት ውርደት ከፍተኛ ነበር። ኤምባሲው ውስጥ የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ሲደበደቡ ይሄ የመጀመሪያ አይደለም ከዚህ በፊትም ተደብድበዋል።
ከመብት በፊት ጥቅምን የሚያስቀድመው ለወያኔ ግን ይሄ ምንም ማለት አይደለም። ለእኛ ኢትዮጵያውያኖች ግን አሳፍሪ ድርጌት ሆኖ ይቀራል።ወያኔ ሱዳን የጠየቀውን ማንኛውንም ነገር እሽ ከማለት ውጭ ሊላ አማራጭ የለውም። በሚያዘው ተይዟል! ይሄው ዲፕሎማት ሰዎችን ህጋዊ ባልሆነ መንግድ ከኢትዮጵያ እያመጣ ለሱዳኖች እንድሚሸጥም በሰፊው ይወራል ወያኔ ስለሆነ ነው እንጅ ጭራሽ ለዲፕሎማትነት ሊያበቃ የሚችል ስነመግባር የለለው የንዋይ ሰው እንደሆነ ነው የሚታወቀው። ለነገሩ ሱዳኖች ኢትዮጵያኖችን መናቅ የጀመሩት አሁን ሳይሆን ያኔ የአጼ ዩኋንስን አንገት ቆርጠው ሙዚየም ውስጥ ካስቀመጡበት ዘመን ጀምሮ ነው።
አባይ ድሮ አፈራችን ጨረስ አሁን ደግሞ ገንዘባችን ጨረሰ በቦንድ ግዥ የተሰቃየው የኢትዮጵያ ሕዝብ
አባባል ነው። በጣም የሚያስቆጣው ግፍ ሲፈፀምብን አይመለከተንም ያለው በጀት እየመደበ ይታፈሱልኝ የሚለው ወያኔ ለህዳሴ ግድብ ዕርዳታ ለመጠየቅ ከፍተኛ ዝግጅት ካርቱም በሚገኘው የኢምባሲው ክለብ ላይ አዘጋጅቶ ነበር። በልመና ተፀንሶ በልመና አድጎ በልመና እያረጀ ያለው ወያኔ ልመናን በሃሉ አድርጎት በልመና ባለመርካቱ እንደ ማፊያ ወደ ዝርፊያ የገባው ወያኔ በተለያዩ ሃገራት የተለያዩ የልመና ኮሚቴ አቋቁሞ ቢልክም እየተዋረደ እንደተመለሰ ሃገር ያወቀው ፅሃይ የሞቀው መሆኑ እየታወቀ አይኑን በጨው አጥቦ ወደ ካርቱም መጥቶ ቢሞክረም አልተሳካለትም !!

No comments:

Post a Comment