Wednesday, June 18, 2014

በአንዋር መስጂድ ኢመም እና በህገ ወጡ ምጀሊስ ፕሬዝደነት ዶ/ር አህመድ መካከል የቃላት ፀብ ተነስቶ እንደነበር ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

በአንዋር መስጂድ ኢመም እና በህገ ወጡ
ምጀሊስ ፕሬዝደነት ዶ/ር አህመድ መካከል
የቃላት ፀብ ተነስቶ እንደነበር ምንጮቻችን
ዘግበዋል፡፡
FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ]
ዶ/ር አህመድ በድርጊቱ በጣም ተበሳጭቶ
በአዲስ አበባ ህገ ወጥ መጅሊስ ውስጥ
በፀሃፊነት የምትሰራውን ሃናን የምትባለውን
የሃጂ ጠሃን ልጅ ለአክራሪዎች መረጃ
ትሰጫለሽ በሚል ሰበብ ከስራ እንዳፈናቀላት
ለማወቅ ተችሏል፡፡
እንደምንጮቻችን ዘገባ መሰረት በአንዋር
መስጂድ ኢማም በሃጂ በጠሃ መሪነት
የተጀመረው የኡለሞች መውሊድ በሚል
በየአመቱ የሚያክብሩት ዝግጅት ላይ
የፌደራል ህገ ወጡ መጅሊስ እና የአዲስ አበባ
ህገ ወጥ መጅሊስ አመራች በክብር እንግድነት
ይጋበዛሉ፡፡በዚህ እለት የአዲስ አበባ አህባሽ
መጅሊስ በዶ/ር አህመድ መሪነት በግዜ
በዝግጅቱ ቦታ ይቢገኙም የአዲስ አበባ ህገ
ወጡ መጅሊስ በቦታው ላይ ሲደርስ ብዙም
የሞቀ አቀባበል እንዳልተደረገለት ተገልፆል፡፡
ከተወሰነ ቆይታ ቡሃላ የፌደራል አህባሽ
መጅሊስ በሼህ ኪያር መሪነት በዝግጅቱ ስፍራ
ሲደረሱ ሼህ ጠሃ ተነስቶ እንዲህ አለ፡-
የተከበሩት የፌደራል መጅሊስ ፕሬዝደንት
ሼህ ኪያር መጥተዋል በማለት ከፍተኛ የሆነ
አቀባበል አደረጉላቸው በዚህን ግዜ የአዲስ
አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዝደንት ዶ/ር
አህምድ ፊቱ የተቀያየረ ሲሆን የአንዋር
መስጂድ ኢማም ሼሃ ጠሃ ሌሎችም ሰዎች
ለሼህ ኪያር አቀባበል እንዲያደርጉላቸው
ጥያቄ በማቅረብ ታዳሚው በሙሉ ሞቅ ባለ
ሁኔታ ሼህ ኪያርን ተቀብሏቸዋል፡፡፡
የፌደራል ህገ ወጥ መጅሊስ ፕሬዝደንት ሼህ
ኪያር በፐሮግራሙ ላይ በህዝብ ገንዘብ በ300
ሪያል የገዙትን ተስቢህ ለደሴው ሼህ ለተባሉት
ግለሰብ የሸለሙ ሲሆን በመቀጠልም ሼህ
ኪያር የተወሰነ ንግግር ካደረጉ ቡሃላ ሰውን
ተሰናብተው ሲወጡ በፐሮግራሙ የታደሙ
ሰዎች ባጠቃላይ ተከትለው መወጣታቸው
ተሰምቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በ ስፍራው
የቀሩት ሼህ ጠሃ ፤ዶ/ር አህምድና በሱ ዙርያ
ያሉ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ ይሄኔ ዶ/ር አህምድ
በጣም በመበሳጨት በጠሃ ላይ እየዛተ ይህንን
ሁሉ ያደረከኝ አንተ ነህ ጠብቅ በዚህ ሁለት
ሳምንት ውስጥ ዋጋህን እሰጥሃለው በማለት
ሲናገረ ሼህ ጠሃም ቀበል አድርገው
በማሽሟጠጥ በ3 ቀን አይሻልም በማለት
እንዳሽሟጠጡበት እና ሼህ ጠሃም አስከትሎ
እናንተ የህዝበ ሙስሊሙን ገንዘብ የበላችሁ
ሌቦች በማለት በዶ/ር አህመድ ላይ የስድብ ናዳ
እንዳወረደበት የፍትህ ራዲዬ ውስጥ
ምንጮች አጋልጠዋል፡፡
ከዚህ ዝግጅት መጠናቀቅ ቡሃላ በነበረው
ጁምአ 29/09/2006 ላይም በአንዋር
መስጂድ ሃጂ ጠሃ -አንዳንድ ሰዎች የህዝበ
ሙስሊሙን ገንዘብ የሚበሉ አሉ በማለት
መናገር ሲጀምር ሸምሱ አባስ የሚባለው የዶ/
ር አህመድ ሎሌ የአንዋር መስጂድ አስተዳዳሪ
አላህን ፍራ፤ አላህን ፍራ በማለት በጠሃ ላይ
ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን ሃጂ ጠሃም
በመገረም እንዴ ትላንት የኔ ተላላኪ የነበረ
ዛሬ እኔን አላህን ፍራ ይለኛል በማለት በህዝብ
ፊት በመናገር ንግገግሩን ማቆሙ ተዘግቧል፡፡
በጁምአ ቀን በህዝብ ፊት ሃጂ ጠሃ ተናገረው
ንግግር የደረሰው ዶ/ር አህመድ በድርጊቱ
በጣም ተበሳጭቶ በአዲስ አበባ ህገ ወጥ
መጅሊስ ውስጥ በፀሃፊነት የምትሰራውን
ሃናን የምትባለውን የሃጂ ጠሃን ልጅ
ለአክራሪዎች መረጃ ትሰጫለሽ በሚል ሰበብ
ከስራ እንዳፈናቀላት ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment