አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
ሰበር#
"ይሄ
ለጅማዎች ሞት ነዉ"
በጅማ ቆጪ በሚገኘዉ እስር ቤት ከመሸ በሀላ የከተማዉ ደህንነቶችና የፖሊስ አካላት ሰክረዉ በመግባት ወንድሞቻችን
ላይ በደል ፈፀሙ.
"ሴት ታሳሪዎችም ጭቆናዉ በዛብን እያሉ ነዉ"
ከአስር ወር በላይ ከፍተኛ ችግር ሳይበግራቸዉ በእስር ላይ የሚገኙት አሸናፊ ግዛዉና ካሊድ ካሚል ዛሬም ኢሰብአዊ
በደል እየተፈፀመባቸዉ መሆኑ የዉስጥ ምንጮቻችን አጋለጡ.
በቅርቡ ከመሸ በሀላ የከተማዉ ደህንነቶችና የፖሊስ አካላት በከፍተኛ ስካር ዉስጥ ሆነዉ ወደ እስር ቤቱ በመግባት
በምሽት ወንድሞቻችንን ወደ አዲስ አበባ በመዉሰድ ከፍተኛ ማስፈሪያና ዛቻ ከፈፀሙባቸዉ በሀላ ወደ ጅማ
እንደመለሱዋቸዉ ተጋልጦዋል ስሙ እንዳይጠቀስ የነገረን የዉስጥ ምንጫችን እንዳለዉ በስካር መንፈስ ተገፋፍተዉ ሌላ
እርምጃ ከመዉሰዳቸዉ በፊት ጉዳዩን ለበላይ አካል ብታመለክቱ ይሻላል ብሎናል::
ከአራት ወር በላይ በእስር ቤት ያለ ምንም ጥፋቱ እየተንገላታ የሚገኘዉ ወንድም ቶፊቅ አብደላ ፖሊሶች ባደረሱበት
ድብደባ የግራ ጆሮዉ የህመም ስሜት እየተሰማዉ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል::
በተመሳሳይ ከአራት ወር በላይ በእስር እየማቀቀች የምትገኘዉ ተወዳጇ ሙስሊም እህታችን ፋጡማ ያሲን የሚደረግብኝ
ተፅእኖ እየበዛብኝ ነዉ ትለናለች በመርማሪዎች የደረሰብኝ ሰምቼ የማላዉቃቸዉ አስፀያፊ ስድቦች ከዱላም በላይ ያማሉ
ትለናለች ያለ ምንም ጥፋቴ ከቤተሰቤ ተለይቼ በጠባቧ ክፍል መደረጌን በፅኑ አወግዘዋለሁ ትለናለች.
አይሻ ከድር የምትባል ፖሊስ ሴት ታሳሪዎችን ጭቃ ላይ በማንበርከክና የተለያዩ ቅጣቶችን እንደምትፈፅምባቸዉ የዉስጥ
ምንጫችን መረጃዎች ይጠቁማሉ.
የጅማ ሙስሊም ማህበረሰብ በንፁሀን ላይ የሚደረገዉን በደል አዉግዞ ከታሳሪዎች ጎን እንዲቆም እንጠይቃለን.
ሰኔ 17 ወንድሞቻችን እና እህታችን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ከጎናቸዉ በመሆን አጋርነታችንን እናሳያቸዉ ፍትህ ለመላዉ
ሙስሊም ታሳሪዎች በሙሉ!!
#EthioMuslimPrisoners
#EthioMuslimCommitteeTrial
በሀቅ መመስከር ዲናዊም፣ ታሪካዊም ገድል ነው!
(ክፍል 1)
ማክሰኞ ግንቦት 26/2006
መንግስት ኮሚቴዎቻችንን፣ ጋዜጠኞቻችንን እና ዑለሞቻችንን በሀሰት ክስ መስርቶ በግፍ እስር ማንገላታቱን
እንደቀጠለበት ይገኛል፡፡ እነዚህ ወንድሞቻችንን ጨምሮ አሁንም ድረስ በመላው ሀገሪቱ ባሉ እስር ቤቶች እየተንገላቱ
ያሉት እህቶችና ወንድሞች ሁሉ ወንጀል ፈፅመው እንዳልሆነ ደግሞ መንግስትም ሆነ ሌላው አካል አብጠርጥሮ ያውቀዋል፡፡
ምናልባት ወንጀል ሰሩ ከተባለ ሙስሊም መሆናቸው ብቻ ነው፡፡ በኢህአዴግ መንግስት ሙስሊም ሆኖ መብት መጠየቅ
ከትምህርት ያፈናቅላል፤ ከስራ ያስባርራል፤ ያስገድላል፤ ያስደበድባል፤ እንዲሁም ያሳስራል፡፡
ሰሞኑን የመከላከያ ምስክሮቻቸውን እያቀረቡ የሚገኙት ጀግኖቹ ኮሚቴዎቻችን ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ህዝበ
ሙስሊሙ በህጋዊ ሰነድ ላይ ፊርማውን አኑሮ ከመንግስት ጋር እንዲነጋገሩለት የወከላቸው የምርጦች ሁሉ ምርጥ ናቸው፡፡
የጀግኖች ሁሉ ጀግና ናቸው፡፡ በሰው ላይ ቀርቶ በነፍሳት ላይ እንኳ እጃቸውን የማያነሱ ንፁሃን ናቸው፡፡ የተማሩና
የተከበሩ ሀገር ወዳድ ዜጎች ናቸው፡፡ ‹‹እነዚህን የህሊና እስረኞች መንግስት ምን አድርገው ነው ያሰራቸው?››
ከተባለ መልሱ እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ሙስሊም ሆነው መብት በመጠየቃቸው ብቻ! ለህዝባቸው መብት ሰላማዊ በተባለው
የትግል መድረክ ፊት ለፊት በመጋፈጣቸው ብቻ! ‹‹ህገ መንግስታዊና ሀይማኖታዊ መብቴ ይከበርልኝ!›› እያለ
በሰላማዊ መንገድ እየጠየቀ ያለው ህዝበ ሙስሊም ተወካዮች በመሆናቸው ብቻ!
እነሱ ከሽብር ጋር በተያያዘ ስማቸው ሊነሳ የሚገባቸው አልነበሩም፤ ትውልድ የሚዘምርላቸው የመብት ተሟጋቾች እንጂ!
እነሱ በመንግስት ተሸባሪ ሆነው ሳለ ‹‹ለሽብር በማነሳሳት›› ወንጀል እንዲከሰሱ መደረጋቸው ተቀባይነት የሌለው ክስ
ነው፤ ምክንያት ቢባል በተጨባጭ ህዝብን እያሸበረ ያለው ማን እንደሆነ ተሸባሪው ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡
ሩቅ ሳንሄድ ግን ከማንም በፊት ለእነዚህ ንፁሃን ወንድሞች እውነተኛ ምስክርነት የሰጠው ራሱ መንግስት መሆኑን
አንርሳ፡፡ ሰላማዊ ትግሉ በተጀመረ ሰሞን መንግስት ‹‹እናንተ አሸባሪ ሳትሆኑ የህዝበ ሙስሊሙ ህጋዊ ወኪል ናችሁ፤
እናንተን አሸባሪ ብሎ መጥራት ከእናንተ ጋር ቁጭ ብሎ የሚነጋገረውንም መንግስት አሸባሪ ማለት ነው›› ብሎ በራሱ
ቢሮ አነጋግሯቸዋል፡፡ በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ኮሚቴዎቻችን ጋር
የመጀመሪያውን ዙር ንግግር ካደረጉ በኋላ ምሽት ላይ በኢቲቪ መስኮት ቀርበው ‹‹ለውይይት የተመቹ፣ ሰላም ወዳዶች››
በሚሉ ውብ ቃላት ኮሚቴዎቻችንን መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ዛሬ ቃላቸውን አጥፈው ምን እያሏቸው እንደሆነ ደግሞ
ህዝብ እያደመጠና እየተመለከተ ነው፡፡ (ይቀጥላል)
በሀቅ መመስከር ዲናዊም፣ ታሪካዊም ገድል ነው!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
ህገ
-ወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ ሲጋለጥ
ቢቢኤን ሰኔ 2/2006
ህዝበ ሙስሊሙ ዛሬም ነገም እኛ ወደንና ፈቅደን እንዲሁም መርጠን ስልጣን እስካልሰጠናቹህ ድረስ በኢትዮጰያ አስልምና
ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምትገኑ አመራሮች አትወክሉንም በማለት ተቃውመውን ማሰማት ከጀመረ እንሆ ሁለት
አመታትን አስቆጠረ፡፡
ህገ-ወጡ መጅሊስ ግን በህገ ወጥ መንገድ ህዝብ ሳይመርጣቸው በመንግስት ድጋፍ ስልጣንነ ይዘው እነሆ ዛሬም የህዝበ
ሙስሊሙን ንብረት እና ሃብት እየበዘበዙ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ወንጀልን የማጋለጥ ፁሁፍ ተኩረቱን ያደረገው በህገ-ወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ ነው፡፡በመጅሊሱ ውስጥ ያሉ
ህገወጥ አመራሮች እነማን ናቸው? ስራቸው ምንድን ነው? አውን ህዝቡን የማስተዳደር ብቃት አላቸውን? ተከታዩን
ከታማኝ የውስጥ ምንጮች የገኝነውን በአርጋታ እንመልከት፡፡
የአዲሰ አበባ ሙስሊሞች እንደ ሁሉም ኢትዮጰያ ክልሎች ምርጫችን በመስጅዳችን እያለ ታላቅ ህዝባው ተቃውሞ በመሳጅዶች
ላይ አሰምታል፡፡ሆኖም ግን መንግሰት በእስልምና ለይ እጁን አርዝሞ በማስገባት የህዝብን ፍላጎት እና መብት ወደጎን
በመተው የመጅሊስ አመራሮችን በቀበሌ ካልመረጣቹህ ቢልም ሀዝበሙስሊሙ የኛ ተቃም መስጅድ ነው ስለዚህ ምርጫው
በመስጅድ ነው መካሄድ ያለበት እንጂ በቀበሌ አይድለም ስለዚህ በዚህ ምርጫ አንሳተፍም የሚል ምላሽ ሰጥቶል፡፡ዳሩ
ግን አባገነኑ የኢ.ሓ.ዲ.ግ መንግሰት የህዝብን መብት ከማክበር ይልቅ ጭቆናን በመምረጥ የራሱን ጋሽ አጅግሬዎቸ
በመሰብስብ መስከረም 27/2005 ህገ ወጥ ምርጫ አከያሂዳል፡፡ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚበጅህን እኛ ነን የምናውቅልህ
በማለት ለአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዶ/ር አህመድ አበዱረህማንን ፕለዝዳንት፣መሃመድ ኑር አህመድን ምክትል ፣ አቡበከር
ካሚልን ፀሃፊ በማድረግ መርጣቸዋል፡፡
ከላይ ህዝበ ሙስሊሙን እንዲያስተዳድሩ ከተመረጡት ውስጥ ለአብነት ያህል እንደ መነሻ ከፕረዝዳንቱ የግል ጉዳዮች
እንነሳ፡፡
ይህ ግለሰብ እንካን የአዲስ አበባን ሙስሊሞች ሊያስተዳድር እና ሊመራ ቀርቶ ቤተሰቦቹን እንካን ወደ እስልምና
ሊመልስ ያልቻለ ባለቤቱ የአዋሽ ውይነ ጠጅ ስራ አስኪያጅ የሆነች፤ሁለቱ ልጆቹ የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ፤ከባለቤቱ
ጋር የማይስማማ ፤አባቱን ዋሀቢያ ናቹህ እያለ የሚያሰቃይ ግለሰብ ነው፡፡ታዲያ ይህ እራሱን እና ቤተሰቡን
ማስተዳደር የልቸለ ግለሰብ በምን መልኩ ነው ሕዝብን የሚመራው፡፡ በፍፁም ሊሆን እንደማይችል ሳይታለም የተፈታ
ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ጉዳይ ግለዊ ነው ብንል እንካን በመጅሊ አመራርነት ስልጣን በመንገስት ከተሰጠው እንካን የህዝብን
ንብረት እና ሃብት እያባከነ መገኝቱ ፍፁም ከአንድ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሚጠበቅ አይድለም፡፡
በአዲስ አበባ መጅሊስ ከዚህ ቀደም በጋሮ በር እንካን ገብተው የነበሩ አመራሮች በከፍተኛ ሁኔታ በሙስና የተጨማለቁ
እንደነበር የአደባባይመስጥር ነበር፡፡አሁን ግን ሙስናን የሚሰሩት የህዝብን ሃብት የሚያባክኑት በጥበብ እነደሆነ
የተወሰኑ ማሳያወችን አንደሚከተለው እናስቀምጣለን፡፡
አንድ/ ቀድሞ በነበሩት የመጅሊስ አመራሮች ወርሃዊ ደሞዛቸው ከ7-14ሺ ብር ነበር ፡፡አሁን በስልጣን ላይ መንግስት
የሾማቸው ግን እስከ 30ሺ ብር እንደየ ስልጣናቸው የህዝብን ሃብት እየመዘበሩ ይገኛሉ፡፡ይህንን የክል ደሞዝ
ለመወሰድ እንደ ምክንያት የሚቀርቡት ለካርድ፣የስልጠን አበል(የቦታ)፣የቤት ኪራይ፣የምግብ እና የአልጋ በሚል ሰበብ
የህዝብ ሃብት እየተሞጨለፈ ይገኛል፡፡የሚያስገርመው እና የሚያሳዝነው ለአዲስ አበባ መጅሊስ አመራርነት የተመረጡት
ከዚሁ ከአዲስ አበባ ሆነው የአልጋ የአበል የምግብ እያሉ እያሉ የሙስሊሙን ሃብት መበዝበራቸው ነው፡፡
ለአመራሮች በየእለቱ ምግብ ከሆቴል እየመጣ እዛው ቢሮ ውስት መበላቱ፣ጫት እየተገዛ ከሳአት ቦሃላ እዛው መቃሙ እና
ይህ ሁሉ ወጪ በየእለቱ ከቢሮ ወጪ መደረጉ ነው፡፡
ሁለት/ በየወሩ አንዴ ወይም ሁለቴ ከ60-80ሺ ብር ገደማ በመመደብ በመውሊድ ስም የትራንስፖረት፣የአበል እና
የተለያዩ ወጪዎች እየተባሉ የህዝብ ገንዘብ እያባከኑ ነው፡፡
ይህንን ያህል ገንዘብ በወሩ እየመዘበሩ ከመሆናቸውም ባሻገር እጅግ በጣመ የሚያሳዝነው ሞሊድ ቦታው ላይ እንካነ
አለመገኝታቸው ነው፡፡ከቢሮ ፍቃድ ይወሰዳ ሞሊድ ሊሄዱ ነው በማለት ከዘያ እዚሁ አዲሰ አበባሲዝናኑ ከርመው
ይመለሳሉ፡፡ለአብነት የክል ለመጥቀስ በጉራጌ አካባቢ በተከበረው ሞሊድ እንካን የአንዋር መስጅድ ኢማም ሸኅ ጣሃ ብቻ
መገኘታቸው የመጅሊሱ ህገወጥ አመራሮቹ የት ነበሩ ብሩ የት ገባ ያስብላል፡፡በቅርቡም መሰል ሂደቶች ይጠበቃል
ብለዋል የውስጥ ምንጮቻችን፡፡
ሶስት/ የመጅሊሱ ፕረዝዳነትዶ/ር አህመድ የራሱን የግል መኪና በመግዛት የድርጅቱ መኪና ስለትበላሸ በሚል ምክንያት
የመኪና ኪራይ እና የነዳጅ ከ10ሺ ብር በላይ በየወሩ እየተመዘበረ ይገኛል፡፡መኪናውን ለማይት የምትሹ በአዲስ አበባ
መጅሊስ ግቢ ውስጥ ነጭ ማርቸሃድስ ታገኛላቹህ፡፡
የአዲስ አበባ መጅሊስ የስልጣን ሹክቻ
ከአዲሰ አበባ መጅሊስ የስራ አስፈፃሚ አባላት መካከል ኢንጂነር ተማም ሰኢድ እና አብዱልሃሚድ አበዱላሂ አውነትን
በመናገራቸው እና ለእውነት በመትጋታቸው የተለያዩ ጫናዎች በበላይ አመረሮች ሲደርሰባቸው ድርጅቱን ለመልቀቅ
ተገደዋል፡፡
ኢንጂነር ተማም የልማት ዘርፍ ሀላፊ የነበሩ ሲሆን ከአምስት ወራት በፊት ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ዶ/ር
አህመድ በግላቸው የስልጠኔ ተቀናቃኝ ሊሆኑብኝ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት እንደነበራቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ
የቀቅርብ ምንጮች አስረድተዋል፡፡አቶ አብዱልሃሚድ አበዱላሂ በተደጋጋሚ ዋሃቢያ ነው በማለት ግምገማ የበዙበት
እንደነበር ለማውቅ ተችላል፡፡
አቶ አህመድ ይማኑ የተባለው የስራ አስፈፃሚ አባል ግን ከአመራረች ጋር አብረ እያገበደደ ተሰሚነቱን ሊያተርፍ
ችላል፡፡በቅርበ ጊዜ እንካን እነ ሸህ ጣሃ እና የፌደራል ጉዳዮች የበላይ አመራረችን ለሙስሊሙ ማህበርስብ ጥሩ
ሰርታቹሃል በማለት ሽልማት ስሰጥ የነበረ ግለስብ እንደሀን በቪዲዮ የተመለከትነው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ይህ
ግለስብ ግን ልጁን እንካን ከአለማዊ ፊልም ሰሪነት ወይም ተገላልጣ ፎቶዋን በየአደባባዩ ከማሳየት መገሰፅ ያልቻለ
ግለሰብ ነው የሙስሊሙን ዋና ድርጅት እየመራ የሚገኝው፡፡
የአዲስ አበባ መጅሊስ ቅርንጫፎች ማለትም የክፍለ ከተማ መጅሊስ አመራረች በስልጣን ሹክቻ እና በደመዝ ምክንያት
ከፍተኛ የሆነ የእርስ በእርስ ሹክቻ ውስጥ ናቸው፡፡የክፍለ ከተማ የመጅሊስ አመራሮች አሁን እየጣሩ የሚገኝት
መንግሰት አሁን የሉትን አውርዶ እኛን ይተካናል የሚል አስተሳሰብ እንዳላቸው የቅርብ ምንጮች ይገልፀሉ፡፡ አታላዩ
እና ህገወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ የክፍለ ከተማ አመራሮችን አፋቸውን ለማዘጋት ከአባሳደር ልብስ ስፌት ለ70
አባላት ሙሉ ልብስ ማሰፋቱ ታውቃል፡፡
ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች በተደጋጋሚ የስልጣን ሹክቻውን ተከትለው ወደ ፍትህ ቢሮ በያመሩም ቢሮው የሰጣቸው ምላሽ
አርፋቹህ ተቀመጡ አለበለዚያ ሁላችሁንም እናሰናብታቹሃለን የሚል ምላሽ ተሰጥታቸዋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ አመራሮቹ
ከአቶ ሽፈራውም ጋር አለመግባበት ላይ እንዳሉ ታውቃል፡፡
የታላቁ አንዋር መስጅድ የወቅፍ መስጅዶችን ጉዳይ በተመለከተ አመራሮቹ ለሁለት ተከፍለዋል፡፡አንደኛው ግሩፕ በዶ/ር
አህመድ የሚመራ ሲሆን ሶስት የስራ አስፈፃሚ አባላት ይገኙበታል ፡፡አቋማቸውም ሱቆቹ ለዋና አከራዮች ይገባል የሚል
ሲሆን በዚህም ምክንያት ገንዘብ እና ጥቅማ ጥቅሞቹን አጊንተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግመ ስምንት የስራ አስፈፃሚ አባላት ሱቆቹ ን ሊይዙት የሚገባው ተሸንሽኖ የተሰጣቸው ናቸው የሚል
አመለካከተ በማራመድ የተለየ ሃሳብ በመያዛቸው የእርስ በእርስ ሹክቻውን ሊያባብሰው እንደቻለ ከታማኝ ምንጮች
ያገኝነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አላሁ አክበር
No comments:
Post a Comment