Wednesday, June 18, 2014

SECRETARY-GENERAL APPOINTS LIEUTENANT GENERAL YOHANNES FORCE COMMANDER OF UNITED NATIONS MISSION IN SOUTH SUDAN

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን ኢትዮጵያዊው ሊውተናንት ጀነራል ዩሃንስ ገ/መስቀልን የተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልእኮ (UNMISS ) የጦር ሃይል ኮማንደር አድርገው ሾሙ፡፡
ሊውተናንት ጀነራል ዩሃንስ ገ/መአስቀል ለቦታው የተሾሙት ጋናዊው ሜጀር ጄነራል ደላሊ ጆንሰን በተያዘው ወር ተልእኳቸውን መፈጸማቸውን ተከትሎ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
ሊውተናንት ጀነራል ዩሃንስ ገ/መአስቀል ለቦታው የተመረጡት በኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ውስጥ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ እና በግጭት በተጋለጡ አካባቢዎች በሰጡት የ35 ዓመታት አገልግሎት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ደቡብ ሱዳንን እና ሰሜን ሱዳንን እያከራከረ ባለው የአብዬ ግዛት የተባበ ሩት መንግስታት የደህንነት ጉዳዮች ኮማንድር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
ሊውተናንት ጀነራል ዩሃንስ ገ/መአስቀል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ peace and security የማስተርስ ዲግሪ እንዳላቸውም የተባበሩት መንግስታት ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

No comments:

Post a Comment