Monday, June 30, 2014

እንደ ከሳሾቼ 100 ሺ የማከራየው ቤት የለኝም” ሲሉ አቶ ገብረውሃድ ተናገሩ June30/2014

እንደ ከሳሾቼ 100 ሺ የማከራየው ቤት የለኝም” ሲሉ አቶ ገብረውሃድ ተናገሩ
June30/2014
መንግስት በሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለፌዴራልከፍተኛፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ገብረውሃድ “በኢትዮጵያቴሌቪዥን 16 ቤትአለው ተብሎ በካሜራ ተቀርፆ መነገሩ የሚያሳዝን መሆኑን ፣ እርሳቸውበአዲስአበባውስጥአንዲትጐጆእንደሌላቸውና ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸው መጠለያ እንደማያጡ ተናግረዋል።
‹‹እንደከሳሾቼ 100,000 የማከራየውቤትየለኝም፤›› በማለት ንጽህናቸውን ለማስረዳት የሞከሩት አቶ አቶ ገብረውሃድ፣ ከሳሾቼ ያሉዋቸውን ሰዎች በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። ሪፖርተር እንደዘገበው አቶ ገብረውሃድ መሬት መቀበላቸውን ነገር ግን ቤት ለመሥራትአቅምስለሌላቸውምእንዳልሠሩበትዘግቧል።
ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ፋንታ በበኩላቸው ” ልንመሰገንበት በሚገባ ስራ ወንጀለኞች መባላችን ያሳዝናል ” ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ክደዋል።
“አቶመላኩ ከገቢያቸውጋርየ ማይመጣጠን ከ3.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ንብ ረትናገ ንዘብአፍርተዋል”በሚልለቀረበባቸውክስ፣እንደማንኛውምሰው 175 ካሬሜትር ቦታ ላይ ቤት መሥራታቸውን፣ይህ ደግሞ ለእሳቸው ብቻ ተነጥሎ ወንጀል ሊሆንእንደማይችል ገልጸው፣ ዓቃቤ ሕግ የቤቱን ግምት አሳስቶማቅረቡንም ተናግረዋል።
ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮቹን ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።

No comments:

Post a Comment