አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
Fasil Yenealem
ህወሃት አማራውን ከሌሎች ብሄሮች ጋር ለማጋጨት ከሚጠቀምባቸው ካርዶች መካከል አንዱ ታሪክ ነው- የተጣመመ ታሪክ፤ "ጆከሩ" ደግሞ አጼ ሚኒልክ ናቸው። አጼ ሚኒሊክ የግዛት መስፋፋት ሲያደርጉ በሌሎች ወገኖች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶችን እንደፈጸሙ በተለይ የህወሃት ካድሬዎች ደጋግመው ሲናገሩ እንሰማለን። የአጼ ሚኒልክን ሃጢያት የሚዘረዝሩ ብዙ መጽሃፎች በትግርኛም በአማርኛም ታትመው ተሰራጭተዋል። በጣም የሚገርመው ህወሃቶች የአጼ ሚኒሊክን ሃጢያት ሲዘረዝሩ ከእርሳቸው በፊት ስለነበሩት አጼ ዮሐንስ ትንፍሽ ለማለት አለመድፈራቸው ነው። ሁለቱም ንጉሶች ዘመኑ የሚጠይቀውን የአስተዳደር ጥበብ፣ በአብዛኛው በጉልበት ላይ የተመሰረተ፣ ተጠቅመው ገዝተዋል፤ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚገኘው ህወሃት ከሚፈጽመው ወንጀል በላይ ባይሆንም ጥፋቶችን ፈጽመዋል፤ ለአገራቸው በርካታ መልካም ነገሮችንም ሰርተዋል። ሁለቱም ንጉሶች ተመሳሳይ የአስተዳደር ዘይቤ የሚከተሉ ሆነው ሳለ አንዱን ሃጢያተኛ ሌላውን ጻድቅ እያደረጉ ማቅረብ ተገቢ አይደለም ብቻ ሳይሆን የማያሸንፉትን ክርክር መጀመር ነው።

ከላይ ያለውን መልእክት እንድጽፍ ያነሳሳኝ አለሙ ካሳ ረታና ሲሳይ መንግስቴ አዲሱ " የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ
እና የማእከላዊ መንግስታት ምላሽ፣ ከአጼ ዮሐንስ 4ኛ እስከ ኢህአዴግ" በሚል ርእስ በቅርቡ ያሳተሙት መጽሃፍ
ነው። በዚህ መጽሃፍ አጼ ዮሃንስ የሰሩዋቸው ብዙ ሃጢያቶች ተዘርዝረው ቀርበዋል፣ ለምሳሌ በገጽ 48 እና 49
የሚከተለው ሰፍሯል- " በአጼ ዮሓንስ የተመራው የመንግስት ጦር የራያዎችን ቤት አፍርሷል፣ ከብቶቻቸውን፣
ፍየሎቻቸውን ሳይቀር ዘርፎ ወስዶባቸዋል፣ ሰብሎቻቸውንም ጭምር ያለ ርህራሄ በእሳት አቃጥሎባቸዋል። የንጉሱ ወታደሮች
የሚበቃቸውንም ያክል ንበረት ሀርፈው ከወሰዱ በሁዋላ የአካባቢውን ነዋሪዎች ገድለውና አንገላተው በግፍ
ቀጥቅጠዋል... ከንግሱ ሰራዊት ራቅ ብሎ ይገኝ የነበረው ሌላኛው የራያ አካባቢ ህዝብ የአጼ ዮሐንስ ወታደሮች
መሆኒን፣ ወረባዩን፣ ደዩንና አካባቢውን እየደመሰሱና ከፍተኛ የሆነ ጉዳትም እያደረሱ ያካባቢውን ሰውም ሆነ እንስሳት
እየገደሉና ሰብሎቻቸውን ጭምር እያቃጠሉ መምጣታቸውን በአይናቸው ጭምር ሲመለከቱ በሰላም የለምንም ጦርነት
ሽንፈታቸውን ተቀብለው እጃቸውን በሰላም ለንጉሱ ወታደሮች በመስጠት ከአስከፊው የአጼ ዮሃንስ የበቀል ቅጣት ራሳቸውን
ማዳን እንዳለባቸው እያመኑ መጡ።"
በገጽ 50 ላይ ደግሞ " በኢትዮጵያ የተማከለ የአስተዳደር ታሪክም አንድን አካባቢ ህዝብ ለም ወደ ሆነ ሌላ አካባቢ በመውሰድ ማስፈር የተጀመረው በአጼ ዮሃንስ 4ኛ ያውም በራያ ውስጥ ዞብል አካባቢ መሆኑ ሲታይ በእርግጥ አጼ ዮሃንስ የራያን ህዝብ በጽናት የተዋጉዋቸው ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ለመግዛት ከነበራቸው ጉጉት ቫሻገር ለትግራይ ብሄር ህዝብ ማስፈሪያ ለማግኘት በማሰብ ጭምር መሆኑን እንገነዘባለን። ይላል።
መጽሃፉ በገጽ 54 ደግሞ የሚከተለውን አሰፍሯል " አጼ ዮሃንስ የራያን አካባቢ ሙሉ ለሙሉ በሃኢል እንደተቆጣጠሩ የተለያዩ መርሆዎችን አውጥተው ስራ ላይ ማዋል ጀመሩ። ከነዚህም መርሆዎች ውስት አንደናው መሪ ቃል ' ጋላ ይጥፋ ዱር ይገፋ' የሚል ሲሆን ትርጉሙም ብዙዎቹ የራያ አካባቢ ህዝቦች ኦሮሞዎች ስለነበሩ እንዲሁም ቦታው ከፍተኛ የሆነ ደን ሀባት ወይም ጫካ በስፋት የሚገኝበት ስለነበር የራያዎችን አሉታዊ ተጽእኖ ለመቀነስ ያስቀመጡት መሪ ቃል እንደሆነ ይታመናል። ይህን አላማ ለማሳካትም ከትግራይ፣ ከላስታና ከየጁ አካባቢ ሰዎችን በብዛት በማምጣት ራያ ውስጥ እንዲሰፍሩ ለማድረግ ሞከሩ።"
መጽሃፉ ብዙ በደሎችን ይዘረዝራል። ህወሃት የሰራውንም ሃጢያት ከመጥቀስ አይሰንፍም። "... አካባቢውን በበላይነት ይቆጣጠሩት የነበሩት የህዝባዊ ወያነ ሀረነት ትግራይ ( ህወሃት) አመራሮች የነበራቸውን የፖለቲካ ስልጣን የበላይነት ተጠቅመው በሰጡት ውሳኔ አማካኝነት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው የራያ ህዝብ ሳይቀር ወደ ትግራይ ክልል ተወስዶ በማያውቀውና የራሱ ባልሆነ የትግርኛ ቋንቋ እንዲዳኝ፣ እንዲተዳደር እና ልጆቹም የአፍ መፍቻ ባልሆነ ቋንቋ እንዲማሩ ተደረገ።" ይህንን ሁኔታ ተከትሎም የራያ ህዝብ የራሱ ያልሆነን ማንነት ( ትግራዋይነት) እንዲላበስ ለማደረግ ጥረት በመደረግ ላይ መገኘቱ የአደባባይ ሚስጢር እየሆነ መጣ ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ኢህዴን) በመባል ይታወቅ የነበረውና በዋነኛነትም የአማራ እና የአገው ህዝቦችን እወክላለሁ የሚለው አሁኑ ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ብአዴን)ም ቢሆን ሲያስተዳድራቸው የነበሩትን የወልቃይት፣ የጸገዴ፣ የቃፍታ ሁመራ፣ የአላማጣና የኦፍላ ወተዳዎችን ሳይቀር በምርቃት መልክ አሳልፎ በመስጠት የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ( ህወሃት)ን የመስፋፋት ፍለጎት ከመደገፍ አልፎ አማርኛና አገውኛ ተናጋሪ የሆኑት የራያ፣ የወልቃይትና አገው ህዝቦች ለምን ወደ ትግራይ ክልል ተወስደው ያለፍላጎታቸውና ያለቦታው ይካተታሉ የሚል ተገቢና ህዝባዊ የሆነውን ጥያቄ እንኳ አንስቶ እውነተኛ የህዝቦች ወኪል መሆኑን እንኳ ለማሳየት አልሞከረም።" ከገጽ 7-8።
ለማንኛውም ታሪክን በታሪክነቱ መተው ለሁሉም ወገን ይጠቅማል።

No comments:
Post a Comment