Tuesday, June 17, 2014

የትግራይ ፖሊስ "ስራህን በአግባቡ እየሰራህ አይደለም" ተብሎ ሲነቀፍ "እነዚህ ዳኞች'ኮ ሊያሰሩን አልቻሉም፤ የታዘዙትን ትተው ያልተባሉትን ይፈርዳሉ" ብሎ መለሰ። የገዥው ፓርቲ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ተቋቁመው ፍትሓዊ ዳኝነት ለመስጠት ጥረት የሚያደርጉ ዳኞች እየመጡ ነው። የትግራይ ፖሊስ አንድ አይደለም፤ የትግራይ ፖሊስ ተወካይ ለህወሓት ባለስልጣናት የተናገረው ነው።

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
የትግራይ ፖሊስ "ስራህን በአግባቡ እየሰራህ አይደለም" ተብሎ ሲነቀፍ "እነዚህ ዳኞች'ኮ ሊያሰሩን አልቻሉም፤ የታዘዙትን ትተው ያልተባሉትን ይፈርዳሉ" ብሎ መለሰ። የገዥው ፓርቲ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ተቋቁመው ፍትሓዊ ዳኝነት ለመስጠት ጥረት የሚያደርጉ ዳኞች እየመጡ ነው። የትግራይ ፖሊስ አንድ አይደለም፤ የትግራይ ፖሊስ ተወካይ ለህወሓት ባለስልጣናት የተናገረው ነው።
አዎ! ፖሊስ ህዝብን ከመጠበቅ ይልቅ ገዥውን ፓርቲ እየጠበቀ ነው። በህዝብ ገንዘብ (ደሞዝ) እየኖረ ህዝብን ይበድላል፤ ገዥዎችን ያገለግላል። ምክንያቱም ፖሊስ መኖር ይፈልጋል። የሚያኖረው ደግሞ ህዝብ ሳይሆን ገዥው መደብ ህወሓት ነው። ምክንያቱም ስልጣን ያለው ህዝብ ሳይሆን ገዥው ፓርቲ ነው። በኢትዮጵያ ስልጣን የህዝብ ሳይሆን የፓርቲ ነው። ምክንያቱም ስልጣን የተገኘው ከህዝብ ድምፅ ሳይሆን ከጠመንጃ ነው። ስለዚህ ህዝብ የስልጣን ባለቤት በማድረግ ፖሊስ የህዝብ በዳይ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይ ማድረግ የሚቻልበት ዕድል አለ።
ካየኋቸው የትግራይ ፖሊሶች የዘቀጡ የዓዲግራት ፖሊሶች ናቸው። የዓረና አባላት ሲደበደቡ ቆመው ያዩ ነበር። ምናልባት ድብደባው ሲከብዳቸው መልሰው ደብዳቢዎችን ከመቱ "ህፃናት ደብድበዋል" ብለው የዓረና አባላትን ለማሳሰር ነበር ዓላማቸው። "ለምን እንደዛ ታደርጋላቹ?" ብለን (ከግዜ በኋላ) ሲንጠይቃቸው "ታዘን ነው። እኛ ደግሞ ወደን አይደለም፤ የታዘዝነው ነው የምንሰራው" አሉን። ይህን ሁሉ ያዘዘው የምስራዊ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ማሞ ገረዚሄር መሆኑ ስናውቅ ለምን ድርጊቱ እንደፈፀመ ስንጠይቅ "ላለመጠርጠር ብዬ ነው" አለ። "ምንድነው ደግሞ የሚጠረጠረው? የፖለቲካ አመለካከቱ ነው ወይስ የእንዳ አብርሃ ወ አፅብሃ የሙስና ጉዳይ?" ብለን ጠየቅን።
ከዛም የአፅቢና የሑመራ ፖሊሶች ናቸው። ማንም ካድሬ ያዛቸዋል። የፖሊስ ትእዛዝ አይደለም የሚጠባበቁ፤ የካድሬዎች ትእዛዝ ለመፈፀም ይተጋሉ። ምክንያቱም ካድሬዎች (ሰላዮች) የሚያውቁት ጥፋት (ወንጀል) አላቸው። ወንጀለኛ ነፃ ሊሆን አይችልም። ትናንት በሑመራ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተያዘው የፖሊስ አዛዥ ባለፈው የሑመራ ስብሰባችን አቶ ስልጣኑ ሕሸና አቶ ሀይለኪሮስ ታፈረ ያሰረ ነበር። ታዘዘ አሰረ።
ከነዚህ ሁሉ የባሱ በትግራይ ሙሉ ወደር የማይገኝላቸው ግፈኛ ፖሊሶች ግን የኲሓ ናቸው። የኲሓ ፖሊሶች የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ። ማንም ጠያቂ የላቸውም። በፈለጉት ግዜ ሰዎች ይደበድባሉ፣ ያስራሉ፣ ይገድላሉ። የኲሓ ፖሊሶች የሚፈፅሙት ወንጀል ለማመኑ ይከብዳል። ደርግ የኲሓ ፖሊሶች የሚፈፅሙትን ዓይነት ወንጀል ይሰራ ነበር ካላች ሁኝ አላምናችሁም።
በኲሓ ሦስት ፖሊሶች ተጠቃሽ ናቸው። ንግስት የተባለች ፖሊስ አለች። ህዝብ ታስፈራራለች፣ ትሰድባለች፣ ትደበድባለች፣ ታዋርዳለች። የብልግና ቃላት እየተጠቀመች እናቶችን ታሸማቅቃለች፣ ታስለቅሳለች። በህዝብ ላይ የምትፈፅመውን ተግባር ብትሰሙ ለማመን ይከዳችኋል። ገነት የምትባል መርማሪ ፖሊስ ደግሞ ሁለተኛ ነች። ንግስቲ ያሰረቻቸውን ሰዎች እየመረመርኩ ነኝ በሚል ሰበብ ታሰቃያለች። የበላይ አዛዥ ያላት አትመስልም። የፍትህ ቢሮ ሰዎችን ሳይቀሩ ይሰደባሉ፤ በእስረኞች ላይ ጥያቄ ካስነሱ። ሦስተኛው ለሰው ልጅ ክብር የሌለው፣ ዓፋኝ አምባገነን የኲሓ ፖሊስ አዛዡ ኮማንደር ለገሰ ነው። የሱ ስልጣን ገደብ የለውም። እስረኞች ለፍርድ ያለ ማቅረብና ጠበቃ የመከልከልም ስልጣን አለው። ይገርማል።
እነዚህ ፖሊሶች ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እዛው ናቸው። ኗሪዎች ያማርራሉ። ሰሚ ግን የለም። ጭራሽ አይቀየሩም። ጉዳዩ ሲገርመኝ "እነዚህ ፖሊሶች ቤተሰብ ምናምን የላቸውም እንዴ?" ብዬ ጠየቅኩ። በኲሓ ምንም የስጋ ቤተሰብ እንደሌላቸው ነገሩኝ። ከየት እንደመጡም አይታወቁም። ቤተሰብ ቢኖራቸው ኑሮ ይህን ያህን ህዝብ አይበድሉም ነበር ከሚል ነው።

No comments:

Post a Comment