Friday, June 20, 2014

ከምዕራብ ወለጋ የተፈናቀሉ እና አሁንም በአካባቢው ያሉ ዜጎች ፍትህ ማጣታቸውን ተናገሩ ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ከቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ ተከትሎ ኢሳት ከጊምቢ በታች በሚገኘው አሹ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን እንዲሁም ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል አንዳንዶቹን አነጋግሮ እንደተረዳው ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖች በብዙ መቶዎች ይቆጠራል።

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

ከምዕራብ ወለጋ የተፈናቀሉ እና አሁንም በአካባቢው ያሉ ዜጎች ፍትህ ማጣታቸውን ተናገሩ
ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ከምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢና ከቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ያቀረበውን ዘገባ ተከትሎ ኢሳት ከጊምቢ በታች በሚገኘው አሹ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን እንዲሁም ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል አንዳንዶቹን አነጋግሮ እንደተረዳው ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖች በብዙ መቶዎች ይቆጠራል።
አሹ ቀበሌ ውስጥ የሚኖረው በንግድ ስራ የሚተዳደረው ወጣት እንደተናገረው ወንድሙ አካባቢውን ለቆ ባህርዳር ቢገባም፣ እርሱና ቤተሰቡ ግን ለመውጣት አልቻሉም። ” መውጣት መግባት አልቻንልም፣ ንብረት ተቃጥሎአል፣ ሰዎችም ተገድለዋል” የሚለው ወጣቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት እጅ አለበት ብሎ እንደሚያምን ገልጿል። ድርጊቱን የሚፈጽሙትን ወጣቶች የሚያደራጁት ልዩ ሃይሎች፣ ፖሊሶችና ባለስልጣኖች መሆናቸውን ከድርጊታቸው መረዳት ይችላል ብሎአል
ተፈናቅለው ባህርዳር ከሚገኙት መካከል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ፖሊሶች ልበሳቸውን ቀይረው እየመጡ ድርጊቱን የሚፈጽሙትን እንደሚያበረታቱዋቸው ገልጿል
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተፈናቃዮችን ቢያነጋገሩዋቸውም፣ ምንም አይነት መፍትሄ ሊሰጡዋቸው አለመቻላቸውን ተፈናቃዮች ተናግረዋል ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የመኢአድ የሰሜን ቀጠና ሃለፊ ኢንጂነር ሽፈራው ዋሌ የክልሉ መንግስት ሰዎቹን በአድማ በታኝ ፖሊስ ከመስተዳድሩ አካባቢ እንዲርቁ ማድረጉን ገልጸዋል
ተፈናቅለው ወደ ባህርዳር ከመጡት መካከል አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውንም ኢ/ር ሽፈራው ገልጸዋል
በጉዳዩ ዙሪያ የአማራ ክልል እና የኦሮምያ ክልል ባለስልጣኖችን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ የኦሮምያ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ራብያ ኢሳ ተፈናቃዮቹ መቶ የማይሞሉ መሆናቸውን ገልጸው ፣ አንድ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ እና 2 የሌሎች ብሄር ተወላጆች መሞታቸውን ገልጸው መንግስት ሌሎችም እንዳይፈናቀሉ፣ የተፈናቀሉትም እንደሚለሱ የአማራ ክልልና የኦሮምያ ክልሎች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል

No comments:

Post a Comment