አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡
በሃረር ከፍተኛ የውሃ እና የምግብ ዘይት ችግር ተከሰተ
June16/2014
ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በከተማዋ በተለይም ቀበሌ 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18 እና 19 እንዲሁም በሸንኮራ፣ ጀጎልና ቀለዳምባ አካባቢዎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመከሰቱ ህዝቡ የጀኔሪካን ውሃ በውድ ዋጋ ለመግዛት ተገዷል።
የክልሉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት ከሃረር በ75 ኪሜ ርቀት ላይ አሰሊሶ በሚባለው ቦታ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ካስቆፈራቸው 17 የውሃ ጉድጓዶች መካከል 6 ቱ በመደፈናቸው ችግር መፈጠሩ ታውቋል። በስራ ላይ ከሚገኙት 11 ጉድጓዶች መካከል 2ቱ ተመሳሳይ የመደፈን እጣ እየገጠማቸው ነው።
ጉድጓዶቹ ከመቆፈራቸው በፊት ባለሙያዎች አስቀድመው አስጠንቅቀው የነበረ ቢሆንም፣ በከተማው ውስጥ አጋጥሞ የነበረውን አሳሳቢ የውሃ ችግር ለመቅረፍ በሚል በፖለቲካ ውሳኔ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው እንዲገነቡ ተደርጓል።
በሌላ ዜና ደግሞ መንግስት የሚያከፋፍለው ዘይት በከተማው ውስጥ በመጥፋቱ ፣ ቀድሞ 115 ብር ይሸጥ የነበረው ዘይት ነጋዴዎች 175 ብር እየሸጡ ሲሆን በአገር ውስጥ የሚመረተው ዘይት ደግሞ በሊትር 40 ብር እየተሸጠ ነው።
በከተማዋ የተከሰተውን የውሃ እና የዘይት እጥረት በተመለከ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

No comments:
Post a Comment