Tuesday, June 17, 2014

ከፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ጀርባ ያሉ ባለስልጣናት ከየኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የተሰጠ መግለጫ

አዎ እኔም የእብድ የቃውስ የሸርሙጣ ትርጉም ለነፃነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ግፈኞችን የሚታገል…ለኢትዮጵያዊነት የሚኖር ከሆነ አዎ እብድ ነኝ አዎ ቀውስ ነኝ አዎ ሸርሙጣ ነኝ እላቸዋለው፡፡

ከፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ጀርባ ያሉ ባለስልጣናት ከየኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የተሰጠ መግለጫ

የሠሞኑ ዶ/ር ኢ/ር ሳሙዔል ዘሚካኤል ጉዳይ የበርካታ ኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ ከመሆንም አልፎ በርካቶችን ሐገሪቱ ወዴት እያራመራች ነው እንዲሉ አስገድዷል፡፡ በሐገራችን በተለይም ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ የትምህርት ጉዳይ አሳሳቢ ከመሆንም በላይ ህገወጥ የትምህርት ማስረጃዎች ይዘው ትላልቅ ቦታዎች ላይ መቀመጥ ህጋዊ መምሠል ጀምሯል የሳሙኤል ዘሚካኤልም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም የሚገርመው በህወሀት ከፍተኛ ቁጥጥር ውስጥ ሆኖ የሳሙኤልን ጉዳይ የዘገበው ተለጣፊው ሬዴዮ ፋና ጉዳይ ነው፡፡ ይሉሽን ባልሠማሽ ገበያ ባልወጣሽ እንዲሉ አበው ሬዴዮ ፋና በሐገራችን ያለውን ብልሹ የትምህርት ስርዓት ከመዘገብ እና በህገወጥ መልኩ ዛሬ ላይ የማስተርስ እና የዲግሪ ባለቤት የተባሉትን ባለስልጣኖች ሳያጋልጥ አንድ ተራ ሰው ላይ ጣቱን ቀስሮ ለሐገራችን የትምህርት ጥራት እንቅፋት የሆነ ሠው ያዝኩኝ የሚል አይነት ሽለላ እየሸለለ ነው፡፡
ለማንኛውም ይህ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ የተሰኘ ገፅ ቢሻቸው የሬዴዮ ፋና ጋዜጠኞች ካላወቁ እንዲያውቁበት የኢትዮጵያ ህዝብም ከፎረጂድ ዲግሪዎች ጀርባ ያሉ ባለስልጣኖቻችን ማንነት እንዲያውቁ በሚል ተስፋዬ ገብረአብ የተባለ የቀድሞ የህወሀት ጋሻ ጃግሬ ድርጅቱን ለቆ ከኮበለለ በኋላ ካሳተመው የደራሲው ማስታወሻ መፅሐፍ ላይ የተገኘ አንድ ስለባለስልጣናቶቻችን የተፃፈ አጭር ፅሁፍ እነሆ ብለናል
……………————–……………-.———……………….————–…………
“ህገወጥነቱ በችሎታ ያገኙት አለመሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላገኘ ሠው ሁለተኛ ዲግሪ ቢያቀርብ ተቀባይነት አይኖረውም የሚል ለዘመናት ሲሠራበት የቆየ የትምህርት ሚኒስቴር ህግ አለ፡፡ ከዚህ ህግ አነፃር በረከት ስምኦን እና ተፈራ ዋልዋ ብቻ ሳይሆኑ መለስ ዜናዊ ጭምር የማስትሬት ዲግሪ ለመያዝ ህጉ አይፈቅድላቸውም፡፡ በረከት ጎንደር ሳለ ትምህርቱን 10ኛ ክፍል ነበር ያቋረጠው፡፡ ተፈራ አዲስ አበባ ላይ ተግባረእድ ሲማር ከ9ኛ ክፍል በላይ አልዘለቀም፡፡ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ሳይዙ የሃርቫርድ እና የኦክስፎርድ ዲግሪ ለማግኘት የበቁ የወያኔ አባላት ከጥቂት በላይ ናቸው፡፡
የማስትሬት ዲግሪ ይዘዋል ተብለው የመምሪያ ሀላፊነት ቦታዎችን የወረሩት አብዛኞቹ የወያኔ ባለስልጣናት የግንቦት 20 ፍሬዎች ናቸው፡፡ ግንቦት 20 ት/ቤት ከመነሻው አስቂኝ ህጎች ነበሩት፡፡ ተማሪዎች 75% የሚያዝላቸው በትምህርታቸው ሳይሆን በመስሪያ ቤታቸው የስራ አፈፃፀማቸው ነበር፡፡ 25% ደግሞ ከወረቀት ፈተና ይያዝላቸዋል፡፡ በመሆኑም አንድ የግንቦት 20 ተማሪ 0 ከ25 ቢያገኝ እንኳን ከ50 በላይ ማግኘቱ ስለማይቀር መውደቅ አይኖርም፡፡
ይሄ እንደቀልድ ሊታለፍ በቻለ ነበር
ግንቦት 20 ት/ቤት ገብተው ያልተማሩ ወይም ትምህርቱን ያቋረጡም ነበሩ፡፡ እነዚህ 12ኛ ክፍል ሳይደርሱ በድብቅ ለማትሪክ ፈተና እንዲቀመጡ ተደርገዋል፡፡ ለፈተናው የተቀመጡት ምስጢር እንዲጠበቅ ተብሎ በቀድሞው ሙሉጌታ ቡሊ የጦር ማሠልጠኛ ካምፕ ውስጥ ነበር፡፡
እዚያ ካምፕ ውስጥ እንዲቀመጡ ከተደረጉት የጦር ሠራዊትና የሲቪል ባለስልጣነት መካከል ከመለስ ሚስት አዜብ መስፍን ባሻገር፣ ሰአረ መኮንን፣ ባጫ ደበሌ፣ ወዲ መድህን፣ አብርሐ መጅሙአ፣ አበባው ታደሰ፣ የተባሉት ጀነራሎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ባለስልጣኛቱ እንደየችሎታቸው ሳይሆን እንደ ስልጣን ደረጃቸው ውጤት እንዲያገኙ ተደርገዋል፡፡ ፈተና አቀማመጣቸው በፕላኔታችን ላይ ተፈፅሞ የማያውቅ ተዐምራዊ የሚባል ነበር፡፡ በተዘጋጀላቸው ወንበር ላይ ተቀመጡ፡፡ የፈተና ወረቀቱና መልስ ማቅለሚያው ተሠጣቸው፡፡ መልሱም በሌላ ወረቀት ታደላቸው፡፡ ያንን ገለበጡት፡፡ ከዚያም መኪኖቻቸውን እያስነሱ ወደ አዲስ አበባ ተፈተለኩ፡፡
ይህ መልስ የመስጠት ሒደት ላይ ልዩ መመሪያ ተዘጋጅቶለት ነበር፡፡ ለጄኔራል መኮንኖች ከ7 የትምህርት አይነት የ4ቱ ሙሉ መልስ ተሰጣቸው፡፡ ለኮሎኔሎቹ 3A፣ ለበታቾቹ 2A፣ ለተራ ወታደሮች 1A መልስ ተሰጣቸው
በዚህ መንገድ እንደ ስልጣንና ደረጃቸው ደረጃውን የጠበቀ ውጤት እንዲያመጡ ተደረገ፡፡ በመሆኑም መልሱን በትክክል መገልበጥ የቻሉ ጀነራሎች 3.8 ሲያመጡ ኮሎኔሎች 3.6 አገኙ”
……………————–……………-.———……………….————–…………
ምነዋ ሬዴዮ ፋና ይህንንስ አታውቁ ኖሯል ወይንስ ጉልበታቹህ እንደእነ ሳሙኤል ባሉ ከፖለቲካው ራቅ ባሉ ሠዎች ላይ ነው፡፡ ምንም እንኳን የሰውዬው ማለትም የሳሙኤል ዘሚካኤል ጉዳይ ትልቅ ወንጀል ቢሆንም ከዚህም በላይ በርካታ ህገወጥ የትምህርት ማስረጃዎች አራት ኪሎ ቤተመንግስት ውስጥ ይገኛል፡፡
ክብር ለኢትዮጵያውያን መምህራን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ሠኔ 09/2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment