Monday, June 30, 2014

በአዲስ አበባ በባህር ዳር እና በደሴ የተቃዋሚዎች መዋቅር ላይ በአዲስ መልክ ጥቃት ሊከፈት ነው።

በአዲስ አበባ በባህር ዳር እና በደሴ የተቃዋሚዎች መዋቅር ላይ በአዲስ መልክ ጥቃት ሊከፈት ነው።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎UDJ‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎AEPO‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)via

አብቢን

የወያኔው መንግስት በመጪው ምርጫ ከተቃዋሚዎች ይገጥመኛል የሚለውን ከባድ ፈተና ለመደምሰስ የመጀመሪያ ዙር የተቃዋሚዎችን መዋቅር የሚበጣጥስበትን አዲስ ጥቃት በአዲስ አበባ በባህር ዳር እና በደሴ እንደሚጀምር የጥቃቱን ዘመቻ በበላይነት የሚከታተለው በረከት ስምኦን መሆኑን ከብአዴን ጽ/ቤት የተገኙ ምንጮች ጠቁመዋል።
ምንጮቹ እንዳሉት አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ በተለይ መኢአድ በስፋት መዋቅራቸውን እንደዘረጉበት የሚታውቁት እና በቅርቡ በተደረጉ ውይይቶች እና ጥናቶች መሰረት ከፍተና የህዝብ ተቀባይነት እናትብቸዋለን ተብለው በታሰቡ ዋና ዋና ከተሞች ላይ ወያኔ በመዝመት የተቃዋሚ አባላት ላይ ከረቀቀ ግድያ ጀምሮ ከስራ ማፈናቀል ሰበብ ፈልጎ ማሰር እንድሁም ከሃገር እንዲሰደዱ ማድረግ ንብረታቸውን መንጠቅ በገንዘብ መደለል እና የመሳሰሉት ጥቃቶችን በአዲስ መልክ አጠናክሮ ሊጀምር መሆኑ ታውቋል። በዚሁ ዘመቻ ላይ እንዲሳተፉ የተመለመሉ የተቃዋሚ አመራሮች እና ሰርጎ ገብ አባላት ያሉ ሲሆን አስፈላጊውን ዳጎስ ያለ ክፍያ እንደተፈጸመላቸው

No comments:

Post a Comment