Monday, June 16, 2014

ይሄም ደግሞ ፖለቲካ ነው በሉ!!! እነ እንትና!!



ውድ ኢትዮጵያዊያን ሱዳን ላይ የሞት ፍርድ ለተፈረደባት እህታችን ሂወቷን ለመታደግና ክርስትያንነቴን አልለውጥም በማለቷ ብቻ ይህ ስረዓት አልባ የኢህአዴግ አቀብቃቢ የአልበሽር አገዛዝ በማን አለብኝነት ሊፈፅምባት ይችላል፡፡ ይህን ዘገባ ቢቢሲና ሌሎችም ዜና አውታሮች ሞት ፍርዷ ሊለወጥና ነፃ ልትወጣ እንደምትችል ዘግበው ነበር ነገር ግን የሱዳን መንግስት ይህን ለማስተባበል እየሞከረ ነው…
በመሆኑን ለዚህች ኢትዮጵያዊ እህታችን ውሳኔው ይቀለበስላትና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቷ ተጠብቆ ነፃ ትለቀቅ ዘንድ ሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ልዩነት እምነት ሃይማኖት ቋንቋ ዘር ገለመሌ ኢቭን ፖለቲካዊ እና መደባዊ ልዩነቶቻችን ወደ ጎን ትተን ድጋፋችን በሰላማዊ ሰልፍ ብናሳያትና ለሱዳን መንግስት ተደጋጋሚ ግፍ ለማውገዝ መዘጋጀት አለብን፡፡ ይህንንም የተቃዋሚው ጎራ ወገኖቻችን አስተባብራችሁ እውን እንደምታደርጉት ተስፋ አለን፡፡

ይሄም ደግሞ ፖለቲካ ነው በሉ!!! እነ እንትና!!

እኔ የሚገርምና የሚደንቀኝ ነገር ለምንድን ነው የሚዋሹት…ይህች ሃገር በቃ…እንዴ እድሜ ልኬን ስኖር ፖለቲካ ቁማር ገለመሌ እያሉ ስላስፈራሩኝና ለመብቴ እንዳልታገል እንዳልጠይቅ ስላደረጉኝ እጅ እግሬን አጣጥፌ ኖርኩኝ…ነገር ግን ሰው ስለተናገረና ስለፃፈ ስላዳመጠም ጭምር መታሰር መሞት መንገላታቱ አሸባሪ መባሉ ለምንድን ነው? በዚህ ምክንያት እንዲሁም ሳንበላ በሉ ሳንለብስ ለበሱ ሳንጠጣ ጠጡ እያሉ በስማችን የሚመጣውን ሁሉ እብስብስ አድርገው ሲበሉ…እዚህ በየጎዳናና ደሳሳ ጎጆው ርሃብ እንቅልፍ ሆኖ እየደፋቸው እስከወዲያኛው እያዩ አይቀፋቸውም…
ለምንድን ነው ኢትዮጵያዊነታችን የሚነፍጉን…
ለምንድን ነው ኢትዮጵያንና ህዝቧን አንድ እንዳይሆኑና እንዳይኖሩ የማይፈልጉት
ለምንድን ነው ህዝቡ የመብት ጥያቄ ሲያነሳ እነርሱ ጠመንጃና ዱላ የሚያነሱበት
ለምንድን ነው ይህ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን እንዳያጠናክር የሚያደርጉት
ለምንድን ነው በልዩነቶቻችን እየገቡ ፍዳችን ካሳዩ በኋላ በሽንቁሮቻችን ሁሉ በመግባት ሊለያዩን የሚሹት
ለምንድን ነው በዘር በቋንቋ በቀለም በመሬት በዝምድና በፖለቲካዊ አመለካካት በቤተሰብ በጎጥ በሃይማኖትና እምነት ገለመሌ የሚከፋፍሉን ምንድን ነው የሚያገኙት ይህን በማድረጋቸው፡፡ ምናልባት እንደሚባለው እንደ ኦነግ… ሞኞች ናቸው…እንዴት ነው ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን ነብርዥንጉርጉርኑነቱን የሚለውጡት…
ለምንድን ነው አንዱ ኢትዮጵያዊ ያለምንም ገደብ የትም ተንቀሳቅሶና ሰርቶ መብላት የማይፈቀድለት ኢትዮጵያ ውስጥ…ኧረ አሳፋሪ ነው!!!
ኧረ ስንቱ ለማንኛውም በነዚህና ነገና ከነገ ወዲያ በምገልፀቸው ምክንያቶች ውድ ጓደኞቼ ወደ ፖለቲካው ዓለም በመቀላቀሌ እንዳይከፋችሁ…
ሁላችሁንም አከብራችኋለው



ነፃ ናችሁ እስቲ አስቡት ነፃ ናችሁ ወይ የምትፈልጉትን ሁሉ ያለማንም ጫና እየሰራችሁ ነው ወይ? ነፃነታችሁን አግኝታችኋል ወይ…እሽ ነፃ ካልሆናችሁ ግን ነፃ መሆንን ትሻላችሁ ማለት ነው፡፡ ነፃነት ካልተሰጣችሁም ነፃነታችሁን ትፈልጋላችሁ፡፡ ነፃ ነን ነፃነታችን እኮ በግንቦት 20 ምናምን አገኘን ካላችሁ ደግሞ እሱ ደስ ይላል ነፃ ካልሆነና ነፃነት የለኝም ከሚል ህዝብ መሃል መገኘታችሁ ቢያስደነግጥም፡፡ የናንተ ነፃ መሆንና ነፃነት ማግኘት ቢያስደሳተንም ቅሉ… ጎረቤትህ ወንድምህ ዘመድ አዝማድህ የምታውቀው የማታውቀው ኢትዮጵያዊነት ከአንተ ጋር ያስተሳሰረህ ኢትዮጵያዊ በምንም ሳታዳላና ቅድሚያ ሳትሰጥ በእኩል አይን ነፃ ነው ወይ? አንተስ የሌሎችን ነፃነት አልነፈግህም ወይ…?
እነዚህም ጥያቄዎች ፀጥ ብለህ ከቻልክም አይንንህን ጨፍነህ አስባቸው…ሚናልባት ማሳጅ እያደረክም ብታስባቸው መልካም ነው…ያኔ እውነትና አንተ ትፋጠጣላችሁ…
እኔን ብትክደኝም እውነትን ግን ለመካድ አትሞክር…

አንድ ጓደኛየ
 "…ፖለቲካሽ ያስፈራል…"
የሚል መልዕክት ታይም ላይኔ ላይ ላከልኝ እኔም…እንዲህ ብየ መለስኩ…
"…ለምን ትፈራለህ እኔም አሁን ነቃሁ ለካስ ያለሃገሬ የለሁም ለካስ ያለ ህዝቤ የህዝብ አካል አደለሁም… እኔ እኮ የምታገለው እና ነፃ ለመሆን የምጥረው ከመንጋየ ከህዝቤ ጋር ለመቀላቀል ነው፡፡ ያለህዝቤ የህዝብ አካል ያለሃገሬ ባለሃገር አደለሁም፡፡ ሁላችንም ጫፋችን ይህ መሆን አለበት… ጫፋችን ኢትዮጵያዊነታችን እና ኢትዮጵያችን መሆን አለበት፡፡ እና ሁላችንም ከታሸግንበት እስር ቤት ሰብረን እንውጣ… ካልተፈለፈልንበት እንቁላላችን ቅርፊቱን ሰባብረን እንውጣ እናቲቱ ዶሮ ከሌለች አማራጭ የለንም እርሷማ እንኳን እኛን ልትፈለፍልና ከእንቁላሏ ልትደርስ ከወደቀችበትም የያዛት ሸለምጥማጥ አላንቀሳቀሳትም…ታዲያ መፈልፈያችን ጊዜ አልፎ እያለ ምነው ውስጥ ሆነን እንንሴጠሴጣለን? ከታሸግንበት እስር ቤትና ካልተፈለፈልንበት እንቁላላችን ራሳችን እናውጣ… ያኔ ለእንቁላል ሲነኩት ለሚፈረከሰው በፍርሃትና ሽበር ታስረን ልንፈረካክሰው ስለሰጋን ባለማድረጋችን ከመቆጨት አልፎ ለዚህ የማይረባ ቅርፊት ሲንሴጠሴጥ መቆየታችን ፈሪዎች እንደነበርን ተሳስተን እንደቆየን እናውቃለን…እኔ ከአሁን በኋላ ይሔው ከሁለችሁም ፊት ከኢትዮጵያ እናቴ ፊት ቃል ገባሁ መቼም ቢሆን ትግሌን ላላቆም ይህ ምስኪን ህዝብና ይህች ምስኪን ሃገር ነፃ ሆነው ነፃነታቸውን እስኪያውጁ…ከማን ለምትሉ…ቁርጥ ያለው መልስ ከወያኔ/ኢህአዴግ ነው መልሱ!!!"
ብየ ጨረስኩ…
ሳትሳደቡ የራሳችሁን ኮሜንት አድርጉ

No comments:

Post a Comment