ኢትዮጵያዊነት
ከምንም በላይ መሆኑን ለማረጋገጥ እኮ ሃገራችን ማን እንደሆነች ማወቅ በቂ ነው…ሃገራችን ኢትዮጵያ ናት ኢትዮጵያ ሃገራችን ናት…ታድያ
ከሃገር በላይ ማን አለ…ይህን ቅድሚያ ከሰጠን ደግሞ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊነት በላይ ምን አለ!!! ታድያ ኢትዮጵያዊነትን እና
ኢትዮጵያን እንደመጠበቅና እንደመንከባከብና ምን አለ!!!
እናንተ ለካስ
አማራጭ ያጣ ህዝብ ሰይጣንንም ውድድር ውስጥ ያስገበዋል… ጦርነት ሳይወድ ጦርነት እንዲፈልግ የተደረገ ህዝብ…!!!!
እኔ ከኦሮሞኛ
ውጭ ምናልባት አማርኛ ተናጋሪ ቤተሰብ እንጅ ሌላ ኢትዮጵያዊ ቋንቋ የሚናገር ቤተሰብ የለኝም… ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ግን ወደ መቶ
የሚጠጉ ቋንቋዎችን እንደሚናገሩ አውቃለው፡፡ በጣምም ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ማማረጥ ያለምንም ማዳላት እወዳለው አከብራለው፡፡
ፀብ ሊኖር ይችላል ፍቅርም ሊኖር ይችላል፡፡ አንድም ቀን ግን ይህ የተፈጠረ ፀብ ወይም ፍቅር ከየትኛውም ቀለምን፣ ቋንቋን፣ ዘርን፣
እመነትና ሃይማኖት፣ አካባቢ፣ ሰፈር፣ ምናምን ልዩነት መሰረት በማድረግ ሆኖ አያውቅም እንዲሆንም ፈልጌ አላውቅም ከዚህ መሰረት
ያደረገ ጥላቻና ፍቅርንም አወግዛለው፡፡ እኔ አዳማ እና አዲስ አበባ /ፊንፊኔም ይባል ከተፈለገ ቀልባቸው እስኪሰበሰብ የቋንቋ ችግር
ስለሌለብኝ/ ሄጄ ሰውን ልወድ ልጠላ እችላለው ይህ መውደድና መጥላቴ ግን ይህ/ች ሰው ከየት ስለመጣ፣ ምን ቋንቋ ስለተናገረ፣ ምን
እምነት ስለተከተለ፣ ምን ቀለም እንዳለው፣ ምን ደጋፊ ስለሆነ፣ ወዴት እንደሚሄድ፣ የት ሰፈር እንደተወለደ፣ እነማን ዘመዶቹና ጓደኞቹ
ስለሆኑ፣ የሃብታም ልጅ የድሃ ልጅ ወዘተ… ስለሆነ/ች ሳይሆን ሰው በመሆኑ ሲቀጥልም ኢትዮጵያዊ መሆኑ ብቻ ነው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊ
ሲሰፋም ለሁሉም የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ክብርም አለኝ፡፡ ብችል ቋንቋዎችን ሁሉ ችየ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር በቀላሉ ብግባባ
ደስ ይለኝ ነበር /ልዩነቶች መኖር እንዳለ ሆኖ/ ምክንያቱም ልዩነቶቻችን /በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ/ ፍፁም ተፈጥሯዊና ብንታክት
ብንላላጥ ብንጋጋጥ ለጊዜው ይመስለናል አንጅ የማንፍቃቸው የማናጠፋቸው አብረውን የሚኖሩ አብረውን የሚሞቱ አብረውን የሚቀበሩ ናቸው
ልዩነቶች አሉን እነዚህን ልዩነቶቻችንን ምንም ያህል ብነዘምን ምንም ያህል ብንማር ብንመራመር በምንም ዲሲፕሊን ማሰተር ብናደርግ
ልናስወግዳቸው አንድ አይነት ልናደርጋቸው አንችልም፡፡ ልዩነቶቻችንን ተቀብለን ብቻ አንዲት አንድ የምታደርገንን ሰው ከመሆናችን
ውጭ አንድነታችንን የምታስተምረንን ኢትዮጵያዊነታችንን ማስቀጠል አማራጭ የለውም፡፡ /ቀለል አድርጋችሁ አንብቡት አታካብዱት/
እኔ እንደኦሮምኛ
ቋንቋ ተናጋሪነቴ በእኔና በሌሎች መካከል በርካታ ልዩነቶች በመኖራቸው አልከፋኝም በምንም መልኩ ሊከፋኝና ላዝንም አልችልም ማንም
መርጦ ወይም ተመርጦለት አይወለድም፤ ምክንያቱም ከዚህ በላይ የሚያግባባኝ የሚያስተሳስረኝ አንድ የሚያደርገኝ የማንነቴ መገለጫ ከወዴትነቴ
መልስ የሚሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ቋንቋ የሚናገሩ የአሁኑ ትውልድ ኢትዮጵያዊ አባት እናቶች በምንም ሳይለያዩ የሞቱላት የወደቁላት
በሞትና በህይወት መካከል ሆነው አደራ ቃል ያስተላለፉላት…ቆስለው ወድቀው በአጥንታቸውም ሊጠብቋት እዚህችው ከሞትኩባት ከወደቅሁባት
ላይ ሳይሆን ወስዳችሁ የብሄራው ክርክሟ የሉዓላዊነቷ መቋጫ ከሆነው ዳር ድንበሯ ላይ ወስዳችሁ ቅበሩኝ ብለው አጥንትና ደማቸው እንኳን
እንዲጠብቃት የተናዘዙላት ኢትዮጵያ የምትባል እናት ሃገር አለችኝ፡፡
በቃ በየትኛውም
አገዛዝ ውስጥ አንድ መጥፎ ታሪክ እንዳለ ሁሉ መልክም ታሪክ ይኖራል፡፡ ሁሉም አገዛዞች እነዚህ ሁለት ገፅታዎች አሏቸው፡፡ ከነዚህ
አገዛዞች ሁሉ የሚከፋውና እንደገዛን በምንም መንገድ የማንፈቅድለት ግን ወደፊት ሃገራችን የማንነታችን መገለጫ የጫፋችን ጫፍ የሆነችው
ኢትዮጵያችንን ሊያጠፋ ወይም እንድትጠፋ አድርጎ የሚያስረክበንን አገዛዝ ነው፡፡ ይህንን አጥፊ ቀመር ቀምሮ ሊያስረክበን የሚሻውን
አካል ግን ተከታትለን አፈር ድሜ ማስገባት "አይኑ እስኪፈስ" እና ወደ አፈርነት ተቀይሮ ከመሬት ጋር እስክንረገጠው
ድረስ "ለሰባት ቀናት" ያህል መጠበቅ የሚገባን ይህንን በኢትዮጵያዊነታችን የሚመጣን ጠላት ነው፡፡ ይህን ጠላትም
ከውጭ ወራሪ ማንነታችን ሉዓላዊነታችን እንደደፈረ የውጭ ወራሪ ታሪካዊ ጠላታችን ብቻ ሳይሆን ከእኛነታችን ጋር ተላክኮ ተላምዶ አፈር
ጋር አፈር ሆኖ ከብረት ጋር በረት ሆኖ ከስለት ጋር ስለት ሆኖ መሬትን እስክንቀምስ ድረስ ለቅፅበትም እኛና ሞትን ለማገናኘት ከማይተኛው
ኤች አይ ቪ ጋርም ብቻ ሳይሆን የምናወዳድረው ነፍሳችን ወደ ሲኦል እንድትወድቅ ከሚደክመው ሰይጣን ጋርም ሳይሆን የምናወዳድረው…
በአጠቃላይ ክምንም ጋር ሳይሆን የምናወዳድረው ልጁን በለው በለው ብሎ እስዳስገደለው ናታኒም ሳይሆን የምንቆጥረው እስከነፍሳችን
እሳት ጉድጓድ ውስጥ እንዳስገባን ስጋዊ ጠላታችን ብቻም ሳይሆን የምንቆጥረው… እጅ እግራችን አስሮ ሳንሞት እያየነው አካላችን እየቆራረጠ
እየከታተፈ ዕድሜ ልካችን ሳንፈታ ትንሽ ትንሽ ሽርፍ ቁርጥ እያደረገ ከፊታችን ከሚነደው እሳት ስጋችን እየጠበሰ በራሳችን ስጋ ራሳችንን
እያቀረና እንደሚበላው ተረታዊ ጭራቅ… እየጮህን ያለማንም ረዳት ያለማንም አዳኝ የነፍስ ብለን እየለመንነው ትንሽ ትንሽ ቁርጥ አሁንም
ቁርጥ እያደረገ በአዋዜ እያየነው ስጋችን ሰዋዊ ጮማችን እንደሚበላው እንደሚጎርሰው ሰው ነው፡፡ ይህንን ያህል እየቆራረጨ ነፍሳችን
ሳይወጣ ስጋችንን ጮማ ጮማችንን ሲበላ ያየነውን ሰው ምናልባት አንዳች ተዓምር ቢያስጥለንና የተረፈችውን ስጋችንን ይዘን ቁስላችንን
ይዘን ከቁስላችን ብናገግምና ድነን ይህንን ሰው እጅ እግሩ ታስሮ ይቅርና አንድ ቦታ ብናገኘው ምን ልናደርገው እንደምንችል አስቡት፡፡
ሃገራችን ላይ አሁን ተመሳሳይ ግፍ የሚሰሩ ሃገራችን ኢትዮጵያን እጅና እግሯን አስረው ስጋዋን ቡጭቅ ሙትርፍ መንተፍ እያደረጉ እርሷ
እስከነፍሷ የድረሱልኝ ጩኸት እያሰማች አይኗ እያየ ጥለው እየበሏት ነው፡፡ እፉኝት እየሆኑባት ነው፡፡ አለም ላይ በቁጥር አናሳው
ፍጡር እፉኝት ነው፡፡ በዓለም አንድ አለያም ሁለት ፍሬ ብቻ እፉኝት ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም እፉኝት ሁለቴ ብቻ ነው የሚሞተው፡፡
አንድም ወንዱ እፉኝት ፆታዊ ግንኙነት ሲያደርግ እንደጨረሰ ይሞታል ሴቷም ያረገዘችው ፅንስ ሁለቱም ቀደዋት ይወጣሉ…ያኔ ትሞታለች፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱም እንደዛው ይቀጥላሉ ግን እፉኝት ዓለም እስካለ ድረስ እንዲህ ይኖራሉ፡፡ እና ኢትዮጵያም ሴቷ እፉኝትን
ትመስላለች አሟሟቷ ነገር ግን ኢትዮጵያ እንደ እፉኝቷ ሞታ አትቀርም፡፡ ትነሳለች፡፡
ኦሮምኛ ተናጋሪነቴን
አሁን ደግሞ እንግሊዝኛ ትግርኛና አማርኛን እንደሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተናጋሪዎች አቀላጥፌ ማውራት የምችል መሆኔን እጅግ መልካም
ቢሆንም የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ መሆኔ ኢትዮጵያዊነቴን ሊያወርደው ኢትዮጵያዊነቴ ከምንም ከማንም በላይ የማንነቴና ለምንነቴ መሰረት
መሰረት ሆኖ እያለ ሊያኮስሰው አይችልም፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነቴ የእኔነቴ ሁሉ ቁልፍ ነው፡፡ ቁልፉ ካለተከፈተ ማንነቴን ማንም
አያውቅም ማንነቴን ምንም እኔን አይገልፀኝም፡፡
ኢትዮጵያዊነት
የማንነቴ ራስ ነውና፡፡
አብቢን ነኝ!!!
No comments:
Post a Comment