Monday, June 16, 2014

ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ



Golgul/ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ ሰላማዊ ወይስ የትጥቅ ትግል ወይስ ማንፈራጠጥ / መስፍን ወልደ-ማርያም የተማረ ወይም የእውቀት ባለቤት እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል ሰላማዊ ይሁን ወይስ በትጥቅ ትግል የሚለውን የጦፈ ክርክር ሲያደርግ ሃያ ሁለት ዓመታት ሆነው፤ ዳኛ የሌለበት ክርክር ስለሆነ የመደማመጥ ግዴታ ታይቶበት አይታወቅም፤ ስለዚህም በሁለቱ መሀከል ያለው ልዩነት ግልጽ ሆኖ አያውቅም፤ አንድ፣ ከሁሉ በፊት ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው፤ ሁለት፣ እንዲህ ከሆነ በሰላማዊ ትግል ለሚያምኑ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር በተለያዩ ዓላማዎችና ዘዴዎች ላይ መከራከርና ሀሳብን ማጥራት አስፈላጊ ነው፤ በሰላማዊ ትግል ተግባር አለ ቢባልም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የድጋፍ ወይም የተቃውሞ አቅዋሞችን ከማሳየት አያልፍም፤ አገዛዞች ጃዝ! ብለው ውሻና ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ሲለቁ የጉልበት ጥርስና ዱላ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያርፋል፤ ጉዳት ይደርሳል፤ ሰላም ይቃወሳል፤ በሕዝብና በአገዛዙ መሀከል ቂም ይጀመራል።
ሦስት፣ የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር፣ ብረት ከብረት ጋር ይጋጠማል፤ የሰው ልጅ ለእርድ ይቀርባል፤ በሕይወታቸው በልተው ያልጠገቡ ምስኪኖች ለጥቂት ሰዎች የሥልጣን ጉጉት ይታረዳሉ፤ ያለቀባሪ በጅብና በአሞራ ይበላሉ፤ ዕድለኞች የሚባሉት እጆቻቸው፣ ወይም እግሮቻቸው ተቆርጠው፣ ወይም ዓይኖቻቸው ጠፍተው፣ ወይም ከዚህ ሁሉ የባሰ ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት የሚቀሩት ናቸው፤ ከነዚህ በሕይወት በቀሩት የጦር ጉዳተኞችና በጦርነቱ ላይ በሞቱት መሀከል የትኛው የተሻለ አንደሆነ የሞቱት ባይናገሩም ጉዳተኞቹ ይናገራሉ፤የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› እያሉ። አራት፣ ሁለቱ የትግል ስልት ዓይነቶች በባሕርይ የተለዩ ናቸው፤ አንዱ ሌላውን የሚደግፍ አይደለም፤ ሰላማዊ ትግል የትጥቅ ትግልን ለመደገፍ ሰላማዊ የሚለውን ስያሜ መጣል አለበት፤ የትጥቅ ትግልም ሰላማዊ ትግልን ለመደገፍ ትጥቅ የሚለውን ስያሜ መተው አለበት፤ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል አራማጆች ድል ቢያደርጉ ማን ወንበሩ ላይ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ጠመንጃ የያዘው ሥልጣኑን ሲይዝ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል! ያውም ከተፈቀደለት! በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አርበኞች ሳይቀሩ በሩ ተዘግቶባቸው ለደጅ ጥናት እንደተዳረጉ አይተናል፤ መልኩን ለወጥ ቢያደርግም ደርግን ከተፋለሙት ውስጥ በአዲስ አበባና በአስመራ ወንበሮች ላይ ሲወጡ የተሸነፉት ወይ ለወያኔ ገብረው ሎሌነት ገቡ፤ ወይም በአሜሪካ መሽገው ያቅራራሉ፤ ዘመኑ እንዳለፈባቸውም ገና አልተረዱም። አምስት፣ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል ሁለቱም ብርቱ ቃል ኪዳንን ይጠይቃሉ፤የቃል ኪዳናቸው ልዩነት አንዱ እስከሞት ለመታገል፣ ሌላው ደግሞ እስከመግደልና እስከመሞት ለመታገል መሆኑ ነው፤ ለሰላማዊው ትግል ከፍተኛ መንፈሳዊ ወኔ የሚያጎናጽፈው ለመግደል ያለው ተቃውሞ ነው፤ ሕይወትን ለማልማት ሕይወትን መቅጠፍ የአስተሳሰብም የመንፈስም ጉድፍ ያለበት ሥራ ነው። የሰላማዊ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ ሕዝብን ለሥልጣን ባለቤትነት ማብቃት ነው፤ ሥልጣንን ለመያዝ አይደለም፤ ስለዚህም ኢላማው ሕዝብ ነው፤ በሥልጣን ወንበሩ ላይ ያሉት የሰላማዊ ትግሉን የሚቃወሙት በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ ነው፤ ሰላማዊ ትግሉ የሚያተኩረው በሕዝቡ ጆሮ፣ አእምሮና ልብ ላይ ነው፤ አገዛዙ በበኩሉ ጸጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛለት ሕዝብ እውቀቱ ዳብሮ፣ መብቶቹን ሁሉ ተገንዝቦ፣ በሕግ ለሕግ እንጂ ለሰው አልገዛም በማለት ልቡ እንዳይሸፍት አፈናውንና ማነቆውን በማጠናከር እያደነቆረ ለመግዛት ይፈልጋል፤ የሰብአዊ መብቶችን የሚያስተምሩና በአገዛዙ አካላት የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያጋልጡ ድርጅቶችን ማዳከም ወይም ማጥፋት ለአገዛዙ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፤ ኢሳት የሚባለው የቴሌቪዥንና የራድዮ ፐሮግራም ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት የሆነበት ለዚህ ነው፡፡ በሰውነት ደረጃ ሕዝቡ መብቶቹን ሁሉ እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣ በዜግነት ደረጃ ሕዝቡ ለሥልጣን የሚያበቃውን የዜግነትና የፖሊቲካ መብቶች እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ፣ ሕዝቡ የሰውነትና የዜግነት መብቶቹን ተገንዝቦ በአገዛዝ ስር አልተዳደርም የማለት መንፈሳዊ እምቢተኛነት እንዲያድርበት ማድረግ፣ በግልጽ ጭቆናን የሚጠላና ለመብቶቹና ለነጻነቱ በቆራጥነት የሚቆም ሕዝብ እንዲፈጠር ማበረታታት፣ መብቶቹንና የሥልጣን ባለቤትነቱን የተረዳና ከጭቆና ጋር የተጣላ ሕዝብ በፖሊቲካ መስመር ቡድኖችን እየፈጠረ እንዲደራጅ ማድረግ፣ ያወቀና የነቃ፣ በፖሊቲካ መስመር የተደራጀና ማናቸውንም ዓይነት ጭቆና የሚጠላ ሕዝብ ለማንም ጉልበተኛ የማይንበረከክ ሕዝባዊ ኃይል እንዲሆን መጣር፣ የትጥቅ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ በሥልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ አውርዶ ወንበሩን ለራሱ ለመውሰድ ነው፤ ይህንን ሲያደርግ ሕዝቡን ወደጎን ትቶ ወይም ዘልሎ ነው፤ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በጠመንጃ ሥልጣን የሚይዙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥልጣኑን ለሕዝብ እናስረክባለን፤ ትክክለኛ ምርጫ እናካሂዳለን በማለት ሕዝቡን በተስፋና በጠመንጃ ይዞ ነው፤ ነገር ግን ሥልጣንን ሕዝብ ለፈቀደው አስረክበው ከቤተ መንግሥት ሲወጡ አናይም፤ ሲሸሹ ወይም ሬሳቸው ሲወጣ እንጂ። ብዙውን ጊዜ የማይታሰብ ወይም ብዙዎች የሚዘነጉት የሁለቱ ትግሎች የገንዘብ ወጪ በጣም ከፍተኛ ልዩነት ያለው መሆኑን ነው፤ ሰላማዊ ትግል በሕይወትም፣ በንብረትም፣ በመሣሪያም በዝግጅትም የሚያስከፍለው ዋጋ ከትጥቅ ትግል ጋር ሲወዳደር በጣም አነስተኛ ነው። ስለዚህም በሁለቱ በተለያዩ ስልቶች አራማጆች መሀከል የሚደረግ ክርክር ምን ዓይነት ነው? የሰላማዊው የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ የትጥቅ ትግል የመጀመሪያ ደረጃ ኢላማው የወያኔ አገዛዝ ነው፤ በሌላ አነጋገር በሰላማዊ ትግል ሕዝቡ በሰላማዊ ትግል ትንሽም ቢሆን የነጻነትን አድማስ ለማስፋት እንዲችል ድፍረትን በማስተማር በኩል የማይናቅ አስተዋጽኦ ቢያደርግም አገዛዙን የመነቅነቅ ኃይል ገና አላዳበረም፤ አንድም ውጤት አላሳየም፤ የትጥቅ ትግሉ ከፉከራና ከሽለላ እስካሁንም አልወጣም፤ የሰላማዊ ትግል ዓላማ ሕዝቡ መብቶቹን እንዲያውቅ ለማንቃትና ለመብቶቹ እንዲታገል የሚያስችለውን ብቃት ለማስጨበጥ ነው፤ ስለዚህም ዘዴው በሕዝቡ ላይ ነው፤ የትጥቅ ትግሉ ዘዴ አገዛዙን በጉልበት ገልብጦ በዚያው ባልተለወጠ ሕዝብ ላይ ሌላ አገዛዝ ለመመሥረት ነው። በኢትዮጵያ ለውጥ እናመጣለን የሚሉ ሁሉ የቆሙበትንና የቆሙለትን ዓላማና ዘዴ በግልጽ ተገንዝበው ካልተሰለፉ በተንፈራጠጠ አስተሳሰብ የተባበረ ተግባር ሊገኝ አይችልም።


እስቲ አንድ ጉዳይ አንስተን ለመነጋገር እንሞክር ዘመዶቼ፡፡ ያለፈው ፅሁፌ ላይ ድንጋይ ሚሊዮን ወይም ቢሊዮን አመታትን ባህር ውስጥ መኖሩ አሳ እንደማያደርገው ፅፌ ነበር፡፡ ይህን የምል ወድጄ አደለም፡፡ በእርግጥ ልምድ ከትምህርታዊ እውቀት የተሸለ ሊያረጋግጥልንና አይናችን ባየውና ጀሯችን በሰማው መሰረት ያለምንም ጥርጥር ነገሮችን እንድንቀበል እንድንተዋቸው ወይም ደግሞ እንድንመሰክርላቸው እንድንፅላቸው አንዲሁም አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንድናደርግላቸው ያደርገናል ከዛ በተረፈ ግን በሁለቱ መካከል ያለው ሰማይና ምድር የሆነ ቋሚ ልዩነት ፈጥሮ አይታይም፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነታም ቢሆን ይሄው ነው፡፡ አንዳንዱ ፐሮፌሰር ሆኖ ምንም ቢባል ነባራዊ እውነታውን አልቀበል ብሎ ማለትም ሆን ብሎ ሳያውቅ ወይም አውቆ ሌላኛው ደግሞ ራሱ ፕሮፌሰሩ ከተፈጥሯዊ ተሰጥኦ እጅግ ሆድና ጀርባ ሆኖ ይወለድና ምንም ሳይገባው አንድ የአምስት አመት ህፃን የገባውን ያህል እንኳን ሳይገባው መመለስ ወዳለበት ይህን ዓለም እየበከለና እየመረዘ ቆይቶ ይመለሳል፡፡ ለዚህም ምስክር መቁጠር ሳያሻን እዚሁ በራችን ላይ የሁለት ዓመቷ ህፃን ኤሊሳ ሮበርትስ 156 አይኪው ተፈጥራ አለምን ያስደመመችውና ከአንስታይን በአራት አይኪው አንሳ ዓለምን መተንተን ትችላለች፡፡ ይህን ፐሮፌሰር ሆና አደለም ያገኘችው፡፡ ዓለም ላይ እጅግ ደደብ እና ምንም አርቆ የማሰብ ብቃት የሌላቸው ሚባሉ ፕሮፌሰርም ይሁኑ ምንም ያህል ዓመት ዓለምን የጠኙባት ሞልተዋል ለምሳሌ እንውሰድ እንደ ፕሮፌሰር ፕላይት ደደብ ካልተማረ ሰው በታች የሚያስብ ፍጡር የለም፡፡ ዘመዶቼ እንዲህ እንድትትል ምን አነሳሳህ ብላችሁ መጠየቃችሁ ስለማይቀር እስቲ ምክንያቴንና ደሜን ትክን ያደረገውን ጉዳይ ላንሳላችሁ፡፡ አንዱ የሃገራችን እጅግ የተከበሩና የሚደነቁ ፕሮፌሰራችን ናቸው እኔም ለእርሳቸው ያለኝ ክብርና አመለካከት እንዲሁም አድናቆት ወሰን አልነበረወውም ለነገሩ እነዚህ እንኳን ሚቀጥሉ ይመስለኛል፡፡ እና ምን መሰላችሁ እኚህ ፕሮፌሰር ስለ ሰላማዊ ትግልና ትጥቅ ትግል የፃፉት ትን አንገቴን አስቀረቀረኝና ለምን የራሴን አልሞነጭርም ተነሳሁ፡፡ ፕሮፌሰሩ ሰለማዊ ትግልን በራሳቸው አገላለፅ:: ሰላማዊ ትግል በሀሳብ ደረጃ መሆኑንና የትጥቅ ትግል ደግሞ በተግባር መሆኑን ለይቶ ለመረዳት ችግር ሆኖ ቆይቶኣል፤ በሌላ አነጋገር ሰላማዊ ትግል በሀሳብ፣ በንግግር፣ በተለያዩ ሀሳብን ለማስለወጥ መቀስቀሻ በሚሆኑ መንገዶች ተቃውሞን መግለጽ ነው፤ በአንጻሩ የትጥቅ ትግል በጠመንጃ ወይም በጉልበት ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ለመለወጥ የሚደረግ ሙከራ ነው ሲሉ ነው የገለፁት፡፡ እሽ እርሳቸው እንዳሉት ትጥቅ ትግል በጠመንጃ ሁለት ሟቾች የሚያደርጉት ግብግብ ነው እንበል በትንሹም ስለሚመስል፡፡ ሰላማዊ ትግልንም እንዲሁ እርሳቸው እንዳሉት በሁለት ሃይሎች መካከል የስሜት አካላትን ብቻ በመጠቀም አንዱ ቡድን ሟች በሆነ መልኩ ማሸነፍ ወይም መሸነፍ ሂደት ነው ሲጠቃለል፡፡ ታዲያ የኔ ቁጣ የጀመረው
 1. ሰለማዊ ትግል ማለት የሃሳብ ፍጭት ብቻና አንድ ቡድን ሟች ብቻ ያለበት የሚለው ላይና
 2. ትጥቅ ትግል ላይ ደግሞ ሁለት ሟቾችየሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› የሚሆንበት ነው ያሉት ላይ
3. ሰላማዊ ትግል ለምን የሚውል ለስልጣን፣ ለመሞት ብቻ ወይስ ለሰፊው ህዝብ ጥቅምና ለብሄራዊ አንድነት ወይስ መክሰስ ለመሆን
4ኛ. ትጥቅ ትግልስ ለም ለስልጣን የሰፊውን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ እና ለብሄራዊ አንድነት ወይስ ለመጠፋፋት ብቻ ለመተላላቅ
እነዚህን ጉዳዮች ለይተው ማየት ካልቻሉ ፕሮፌሰሩ እጅግ የተበላሸ መልዕክት ብቻ እያስተላለፉ እንደሆነ መገመት ለማንም የሚያቅት አይመስለኝም፡፡
እስቲ ከአንደኛው ጉዳይ እንነሳና የፀሃፊውን ፅሁፍ እንተች
1ኛ ሰላማዊ ትግል ለምን
ፕሮፌሰር እርስዎ እንደዛ ያሉለት ሰላማዊ ትግል ለምን እንዲውል ምን ኣላማና ግብ ይዞ የተነሳ ሰላማዊ ሰልፍ ነው እርስዎ ሚደግፉት ለዚህ ምላሽ በሚችሉት ሰዓትና በሚችሉት መልክ ቢሰጡ ደስታውን ልችለውም፡፡ ሰላማዊ ትል ማለት የስሜት ህዋሳት ለስሜት ህዋሳት የሚደረግ የማሸነፍና የመሸነፍ ድራማዊ እውነታ ነው፡፡ በዚህ መሃል ፀሃፊው እንዳሉት መሞት ሊኖር ይችላል፡፡ ምናልባትም በሰላማዊ መንገድ መታገያ መንገዶችን ሲጠቀም ታስሮ ተደብድቦና ተቀጥቅጦ በስቃይ ከሚሞተው እስከ ብስጭት ደርሶበት በተለያዩ በሽታዎችና አካል ጉዳቶች ተዳርጎ ያልጋ ቁራኛ ሆኖ እስከሚሞተውና የተከበረች ነፍሱን በዚህ ሰላማዊ ትል ሰበብ ከርቀት በተተኮሰች ጥይትም ይሁን ምግቡና መጠጠጡ ላይ በተጨመረች የአይጥ መርዝየሚሞተውን ያጠቃልላል፡፡
ዋናወ ጉዳይ ግን ሞት ባለበት ሁሉ የትኛው ነው ሰላማዊ ሊሆን የሚችለው ሰላማዊ ትግል ያለምንም ደምና ሞት ያለምን ኽፀፅ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ማናም ሳይጎዳ የስልፃን ሽግግር መደረግ ሲችል ነው፡፡ በመሰረቱ በርካታ ፀሃፍት እንደሚሉት በዚህ እውነተኛው ዓለም ላይ ምንም አይነት ሰላማዊ ትግል የለም፡፡
እርስዎ የሚሉት ሰላማዊ ትግል የትኛው ነው? በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉት ሁሉ ሰላማዊ ናቸው እንዴ? እርስዎ እንዳሉት ሰላማዊ ትግል አንደኛው ቡድን ማለትም ስልጣን ላይ ያልሆነው ወደ ስልጣን የሚሮጠው የህዝብን መብት አስከብራለው ለራሴ መብትም እታገላለው የሚለው አካል የሚሞትበት ቢሞትም እኳን ሰላማዊነቱን የማይነሽረው ስልጣን ላይ ያለው ደግሞ የእርሱ ማለትም ስልጣን ላይ ያለውና ወደ ስልጣን የሚሄደው ሁለቱም የማይጠፋፉበት ሲሆን ነው ሰላማዊ የሚባለው ካሉ ከዚህ የከፋ ስህተት የለም፡፡
ፕሮፌሰር እዚህ ላይ የኔ ማስተባበያየ ምንድን መሰልዎት?
1ኛ. ሰላማዊ ትግል ማለት እርስዎ እንዳሉት አንዱ ብቻ ከሞተ ማለትም "ተቃዋሚ ወይም ተቀናቃኝ" የሚባለው የሚሞትበት ስልጣን ላይ ያለው የማይሞትበት ግን ሊገድል ሊያስር እንዲሁም ሊያሰቃይ የሚችልበት የትግል ስልት አደለም፡፡ በእርግጥ ይህ ጠፍቶዎት ነው ማለት አደለም ነገር ግን ይህን እርስዎ በገባዎት መልክ ሌሎች ሊገባቸው ይችላል ብሎ ማስፈሩ ዋጋ የሚኖረው አይመስለኝም፡፡
ሰላማዊ ትግል ከሆነ ሰላማዊ ነው ምንም ክርክር የለውም ሰላማዊ ነው፡፡ ተጎጅና ጎጅ የሌለበት ነው፡፡ ፍፁም ነው ግን አላልኩም፡፡ በመሰረቱ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነው ብለው የሚያስቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሉ ተሳስተዋል፡፡ በእርግጥ እነርሱና ደጋፊና አባሎቻቸው ምንም አይነት ጉዳት አላደረሱም ማድረስም አይፈልጉም አድርሰውም አያውቁም እንበል ስለሆነም ነገር ግን "ሰላማዊ" የሚለው ቃል በሁለቱም አቅጣጫ ነው የሚሰራው፡፡ ከተቃዋሚውም ከገዥውም በኩል ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ሲቀር ነው ሰላማዊ የሚሆነው፡፡ ያለዚያ ግን ተቃዋሚዎች ብቻ ሰላማዊ ናቸው እንጅ የትግል ምህዳሩ ግን ሰላማዊ አደለም፡፡
እንዴት እንዴት ነው የምናስበው ኢህአዴግም እና ተቀጥያ ድርጅቶችም እኮ በዚህ ነው አሞታችን የቀመሱት ወንድነታችን ያበነኑት፡፡ ይህ አስተሳሰብ አንድ ነገር ያስታውሰኛል፡፡ አንድ መሪ ነበር አሉ ድሮ ነው፡፡ እና ሶስት ሚሊዮን የሚጠጋ ጦር አለው፡፡ እና ይህን ጦር ምን ብሎ አሰላው መሰልዎት፡፡ መጀመሪያ ምን ያህል አመት እርሱ መግዛት እንደፈለገ አሰላና 50 ዓመት በቃኝ አለ አሉ፡፡ ከዛም ጠላቶቹ በየስንት ጊዜው እየመጡ አደጋ እንደሚያደርሱበት አሰላና በየየስድስት ወሩ ስልጣኑን እንደሚገዳደሩት አወቀ አሰላ፡፡ ከዚያም በኋላ ሶስት ሚሊዮን ወታደሮቹን ለሃምሳ ዓመታት አካፈላቸው በዓመት ሁለት ጊዜ ጦርነት እንዳለ በማሰብ፡፡
ከዚያም በኋላ ሶስት ሚሊዮኑን ወታደር ለመቶ በማካፈል በሃምሳ ዓመታት የስልጣን እድሜያቸው ውስጥ መቶ ጊዜ ጠለላት እንደሚያጠቃቸው በማሰብ በአንድ ጦርነት 30 ሽህ ወታደሮችን ብቻ ለማሰማራት ለጦር መሪዎቻቸው ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ 30 30 ሽህ ወታደሮቹንም ከፊት ከሁዋላ ከፊት ከኋላ ከፊት ከኋላ አሰለፉ፡፡ አንዱ ካላለቀ በስተቀር ሌላኛው ሰልፍ አይንቀሳቀስም፡፡ ይህን አሰላልና አሰላለፍ ያወቀው ጠላት ለአንዱ የመሪው አሰላለፍ በሶስት እጥፍ ማለትም ለአንድ ወታደር ሶስት የራሱን ወታደር ሶስቱ ወታደሮች በመተጋገዝ አንዱን እንዲያጠፉ በሚል ስሌት ገጠሙ፡፡ ከዚያም የዛ መሪ ወታደሮች አንድ ባንድ የጠላታቸውን አንድ አስረኛ እንኳን ሳያጠፉ ሙሉ በሙሉ ወደሙ እናም የጠላቱ 90 ሽህ ብቻ ወታደር ሶስት ሚሊዮኑን የመሪውን ጦር ደመሰሰው፡፡
አያችሁ የመሪው ድክመት፡፡ ይህ መሪ ያሰላው በርካታ ሞር ስላለው ብቻ ያንን ከስልጣኑ ጋር ብቻ ያጣጣመ መስሎት ነው ጉድ የሆነው አንደኛው ሲያልቅ እቅድ እቅድ ነው ስለዚህ ሌላኛው ሰልፍ ሂደህ አግዝ ጠላትህን አጥፋ በሚል አደልም የሚታዘዘው፡፡ በዚህ ምክንያትም ጉድ ሆነ ተሸነፈ፡፡ ገና ለገና አንድ ሁለት አመራሮቻችን ታሰሩ ተገረፉ ተገደሉ ይህም የሰላማዊ ትግል አንዱ አካል ነው ብለን ካሰብን ሞኝነት ነው፡፡ ያንን መሪ መሆነ ነው፡፡
ሁሉም አባላትና ደጋፊዎች ሁሉም አመራሮች ታስረው ተገርፈው ተገድለው እስኪያልቁ ማየት ራሱ ከተጠያቂነት አያድንም ታዲያ ከዚያ በኋላ ማንን በሰላማዊ መልኩ አታግለን ልንል ነው፡፡ ይህ የድሮው ትውልድ ፍልስፍና ብቻ ነው፡፡ እንደእኔ እምነት ሰላማዊ ከተባለ ሰላማዊ ነው፡፡ ማንም መታሰር መገረፍ መሰቃየት መገደል የለበትም፡፡ ማንም በስነልቦና መጎዳት የለበትም፡፡ አማራጭ አቅራቢ ቅን ዜጋ ብቻ  ሆኖ  ብቻ ካልተቆጠረ ይህ ሰላማዊ ሳይሆን ነውጥ የሞላበት ለመሞት ብቻ ለመስዋዕትንት የተዘጋጁ ሰላማዊ አታጋዮች ያሉበት የሞኞች ስብስብ ነው የሚሆነው፡፡ በአጠቃላይ አንድ ሃገር ውስጥ አምባገነናዊ ስርዓት ገዥ መደብ በለበት ሁናቴ ሰላማዊ ትግል አለ ብሎ ማውራት ዘበት ነው፡፡ የለም!!!!! የለም፡፡ እነአንዷለም እነ እስክንድር ኤልባና ሌሊሳ በቀለ እንዲሁም ሌሎች ምርጥ ታጋዮቻችን እስር ቤት ታጉረው፡፡ በርሃብ በግርፋትና በሞት እየተቀጡ ይህ በምን ሂሳብ ነው በሰላማዊ የትግል ምህዳር የሚፈጠረው? እሽ አነርሱ በእጃቸው ምንም አይነት ጉዳት ማድረስ የማይችሉ በመሆናቸው ሰላማዊ ናቸው ምንም አያወላዳም ገዥው መደብ ካልሆነስ ሰላማዊ ትግል ነው እየተደረገ ያለው፡፡ ትግል በአንድ ወገን ብቻ አደልም የሚካሄደው ሁለት የሚላተሙ የሚፋጩ ሃይሎች ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም ሰላማዊ ካልሆኑ ትግሉ ሲጀመር ጀምሮ ሰላማዊ አደለም፡፡ ትግሉ ስልጣን ላይ ያልሆኑት ወይም ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ብቻ ለመሞት ይሰመርበት ለመሞት የተዘጋጁበት ዕቃ ዕቃ ነው፡፡ ስለዚህ እርስዎ ያሉት ሰላማዊ ትግል ሳይሆን ተቀናቃኞች ሰልጣን ላይ ያልወጡት ብቻ ለመሞት፤  ከተቻለም ሳንሞት ስልጣን ላይ ወጥተን የሰፊውን ህዝብ መብት እናስከብራለን እናከብራለን የሚሉበት ይህንን አውቀው ወደው የሚገቡበት ራስ መሃላ በመሆኑ ይህ ሰላማዊ የአንድ ቡድን ታጋይ ብቻ ያለበት የባዶ እጅ ጦርነት እጅ ሰላማዊ ትግል ነው ሊያስብለን አይችልም፡፡ ይህ የተቃዋሚ ሰላማዊነት እስኪሞት ይሰመርበት እስከሞት ሳይሆን እስኪሞት  ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ጫፉ ሞት እንደሚሆን አውቆ ሰላማዊ ትግል አካሂዳለው ይህ አካሄድ የሰላማዊ ትግል አንዱ አካል ነው ብሎ ለመሸንገል መሞከር ከገዳዮች ጋር መሰልፍ ነው የሚሆነው፡፡
ያ ምስኪን ያወቀም ያላወቀም ደጋፊና አባልማ ይህን ተቀብሎ አምኖ እንደሚሞት ሳያውቅ እስከ ፅዋው እለት ድረስ መታገሉ ጥፋት አይሆንበትም መንገድ የጠፋው እና መንገዱን ያላወቀ መሪ እንደሚከተለው መንገደኛ ብቻ ነው ሊፈረጅ የሚችለው፡፡ ይሕን ፕሮፌሰር እርስዎን የማከብረዎን እጅግ ለኢትዮጵያ ያሉ የሌሉ ብየ የምወድዎትን አንድም የቀለም አባቴን ሁለትም የትግል አስተማሪየን ለማሳነፍ ወይም ክብር ለመንሳት ብየ አደለም ግን ይህ እሳቤ ነው፡፡
በመሆኑም ፕሮፌሰር ሰላማዊ ትግል ጫፉ አስር፣ ግርፋት ስቃይ በየትኛውም ደረጃ እንዲሁም ሞትና ከሞት የሚብሱ ነገሮች መሆናቸው እየታወቀ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንችላለን ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ እናም ሰላማዊ ትል ብቸኛው መፍትሄ ብቻ ሊሆን እንደማይችል መገመት አለብን፡፡ ስዎች ሰው በመሰረቱ ናና እንዲህ አድርግ ከሚባል ራሱ በስሜት በብሽቀት በንዴት ወይም በወቅቱ በተፈጠረ ጉዳይ እንደምላሽ ብሎ የሚወስደው አፀፋ ትክክል ሆኖ የሚገኝበት ሰዓት እንዳለ መገመት ብልህነት ነው፡፡ ሰው ሊገድለው የመጣን እንካ ምታኝ ብሎ ይሄዳል ማለት ዘበት ነው ወይመ አጉል ውዳሴ ከንቱ ነው፡፡
ማንም ሊያጠፋው የመጣ ሳየቀደም ማጥፋት ይፈልጋል፡፡ ከቻለም ያጠፋል፡፡ ነገር ግን ይህ ይሁን ማለት አደልም፡፡ ግን ማመዛዘን፡፡ ሲመዛዘንም ይህ ሰላማዊ ታጋይ ከታንክ ጋር ከክላሽንኮቭ ጋር የገጠመ ሰው ከትክሻው ላይ ያለው የሰፊው ህዝብ ጥያቄና የመብትም ይሁን ሌላ መሰረታዊ መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ ከበድ ካለለት እርሱ አፀፋው መግደል ቢሆን ስዕተት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክን|ነቱም ሰውየው ማለትም በእርስዎ አገላለፅ ይህ ሰው የተሸከመው ሃላፊነት የህዝብ እስከሆነ ድረስ ወይም ትክክል እስከሆነ ድረስ ጠላት ሊነሳበት ተቃዋሚ ሊነሳበት የሚችል በስዕተት ብቻ በመሆኑ ቢያጠፋ በምንም መልኩ ምድራዊ ሃጢያት አደለም፡፡ ትክክል ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው ያለው አማራጭ ሁለተኛው ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰላማዊ ታጋዩ መጨረሻው እስራት ግርፋት ወይም ሞት እና መሰሎቹ መሆኑን ቀድሞ አውቆ ከሁለቱ አንዱን መምረጡ ትክክል ነው፡፡ መጨረሻው አስራት ግርፋትና መሰሎቹ ሞትና መሰሎቹ ካልሆነ ሰላማዊ ነው ትግሉ ማለት ስለሚቻል መታገል፡፡ ይሕ ካልሆነ ግን ሰላማዊ ትግል ስላልሆነ ትጥቅ ትግል ምንም አማራጭ የለውም፡፡ ይህ ሲባል ተጥቅ ትግል ጥፋት የለውም ማለት አደልም ግን ትርፍ ካለውሰ?
2ኛ. "የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ"
ፕሮፌሰር ይህ አባባል መች ለመጀመሪያ ጊዜ ለምን እንደተባለ ባውቀው ወዴትስ እንደተባለ መረጃ ባገኝ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር ግን አላውቀውም፡፡ ለማንኛውም እርስዎ ካሉት ተነስቼ ልሞንጭር፡፡ እስቲ እርስዎ በሶስተኛ ደረጃ ያሉትን እንይ ቃል በቃል
ሦስት፣ የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር፣ ብረት ከብረት ጋር ይጋጠማል፤ የሰው ልጅ ለእርድ ይቀርባል፤ በሕይወታቸው በልተው ያልጠገቡ ምስኪኖች ለጥቂት ሰዎች የሥልጣን ጉጉት ይታረዳሉ፤ ያለቀባሪ በጅብና በአሞራ ይበላሉ፤ ዕድለኞች የሚባሉት እጆቻቸው፣ ወይም እግሮቻቸው ተቆርጠው፣ ወይም ዓይኖቻቸው ጠፍተው፣ ወይም ከዚህ ሁሉ የባሰ ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት የሚቀሩት ናቸው፤ ከነዚህ በሕይወት በቀሩት የጦር ጉዳተኞችና በጦርነቱ ላይ በሞቱት መሀከል የትኛው የተሻለ አንደሆነ የሞቱት ባይናገሩም ጉዳተኞቹ ይናገራሉ፤የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!› እያሉ።
ፕሮፌሰር ምንድን ነበር ያሉት?
የትጥቅ ትግል ደግሞ በተዋረድ በሚተላለፍ ትእዛዝ የሚፈጸም ግዴታ ነው፤ በትጥቅ ትግል ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር እርስዎ እንዳሉት ጉልበተኛ ከጉልበተኛ ጋር ብረት ከብረት ጋር ብለው መግለፅዎት ትክክል አይመስለኝም፡፡ በመሰረቱ ጦርነት አማራጭ ከሌለ ሰላማዊ ትግል በላይ ውጠየታማ ነው፡፡ እነዚህ ስዎች ጉልበተኞች ሳይሆኑ አማራጭ ያጡ ርሃብና ጥም ሳይበግራቸው እንደስዎቹ ቦርጫቸውን አንገፍተው በየሴታዳሪና በየቡናቤቱ የሚዞሩ ምቾት ወቢ ያስተፋቸው ሳይሆኑ የሰላማዊ ትግል አማራጭ ያጡ የሰላማዊ ትግል መጨረሻውን ጠንቅቀው ያወቁ ድንቅ የብሄራዊ ኩራትና ሁለተኛ ህጋዊ ያልሆኑ /በገዥው መደብ ማለቴ ነው/ መከላከያ የብሄራዊ ክብር መመኪያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፡፡
እርስዎ እንዳሉት ጉልበት የደላቸው አደለሉም ፕሮፌሰር!!!
ጉልበታቸው ሃገራዊ ፍቅር ህዝባዊ ፍቅር ነው፡፡ ሞት የማያስፈራው ጉልበት ማንም የማይበግረው ጉልበት ይህ ነው የህዝብና የሃገር ፍቅር ያኔ ነው መስዋዕትነት ያለው፡፡ ከዚህ ውጭ ያለ ሞት ሞት ነው፡፡ የእነርሱ ግን መስዋዕትነት ነው፡፡ ለሚወዱት ህዝብና ሃገር፡፡ ለሚኖሩለት እውነት መሞትን ያህል ክብር የለም፡፡ የያዙት እውነት ነው ብረት ነው ግን ሰውን አደለም የሚገድሉበት አውሬን እንጅ፡፡ ወያኔ አቢዮተኛ ብሎ ራሱን ከጠራ በኋላ ትጥቅ ትግልን ማድረጉ ስህተት ነው የሚል ካል ትክክል አደለም፡፡ ትክክል ነው ወያኔ ያኔ መብቴን በሃይል አስከብራለው፡፡ ማለት ስህተት አደልም፡፡ ትክክል ነው አማራጭ ሲታጣ፡፡ ስለዚህ ወያኔ ይህን ማድረጉ ብርቅ ያደርገዋል በዚህም ጀግኖች ናቸው፡፡ ስእተቱ ምንድን ነው? ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ የመጣው ጭራቅነት የሞቱለት ዓላማ መና ሲቀር ነው፡፡ ያኔ ነው የሞቱለት ቀርተው የገደላት በላ ሊባል የሚችለው፡፡
ለዛም ነው ይህ አባባል አሁን ለወያኔ ኢህአዴግ የሚገጥመው፡፡ ያኔ አፈር በጥብጠው በልተው ጤዛ ልሰው ከፊታቸው ላይ ላይ እንደሸኮለለ እንኮይ ክብልል ደፋ ብለው የቀሩት ጀግኖችን አጥንት የሚያስወቅሱት ያኔ ነው፡፡ ለዚህም ነው ነባር ቅን ታጋዮች አሁን የሚንገበገቡት የሞቱለት ጓዶቻቸውንና ስንት ምሁራን ወንድም እህቶቻቸውን ያጡበትን ዓላማ ወና ሲበለው ሲያዩ ከንቱ ሲቀር እያዩ ይህኔ ያውም እነርሱና ሟቾች የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የሚሉት፡፡ እውነታው ይህ ስለሆነ እንጅ ትጥቅ ትግል በራሱ ያን አያስብልም፡፡ ጥያቄው እኮ ያለው በትጥቅ ትግል የመጣው ከአሁን በፊት በነበረው ታሪክ ተነስተን የምንተነብየው ጋር እንጅ ትጥቅ ትግል የህዝብ መብትን ማስከበሪያ ሃይልን በሃይል የሚለውን እውነታ አያጣምመውም፡፡ በርካታዎቹ የአፍሪካ ሃገራት በዚህና በመፈንቅለ መንግስት የሚታወቁ መሆናቸው ራሱ የተማረውም ያልተማረውም ከስልጣን በኋላ ያለውን ስርዓት በማየት ብቻ ትጥቅ ትግል አያዋጣም ወደሚል መደምደሚያ ይወስዳል ግን አሜሪካና አውሮፓዎችስ በዚህ ተለዋውጠው ቢሆን እንል ነበር ወይ ይህን ሳያደርጉ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ማድረጋቸው በራሱ አማራጩ ያ ብቻ እንደሆነና ትጥቅ ትግል ስኬታማ አደለም የሚለውን እውነታ ሊያፈርሰው አይችልም፡፡
መችም ይህን ስል የልጅ ነገር እነደማይሉኝ  አስባለው፡፡ ካሉም ምን አደርገዎታለው፡፡
እናም ትጥቅ ትግል በራሱ ስዕተት አደለም አማራጭ ግን ነው፡፡ ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሰላማዊ ለውጥ ቢኖር ጥሩ ነው፡፡ ግን ይህ ካልሆነ ትጥቅ ትግልን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ትጥቅ ትግል ካልሆነ ግን መፈላሰፍ ይጠይቃል፡፡ ለቀጣይ እንያዘው፡፡
3. ሰላማዊውም የትጥቅ ትግልም ለምን መዋል አለባቸው ለምን ከመዋላቸው በመነሳት ጠቃሚም ጥቅም አልባም ይሆናሉ
በመሰረቱ ጉዳት ማድረስ ጥቅምን ማሳጣት ወይም መጎዳት አደለም ባይ ዲፎልት፡፡ ዋናው ጉዳይ ሁለቱም የትግል ስልቶች ለምንድን ነው የሚውሉት? ይህ ጥያቄ በአግባቡ በተግባርም ሆነ በቲዎሪ ከተመለሰ አማራጩ የትኛውም ቢሆን ትክክል ነው፡፡ ቢያንስ በዛ ሰዓት የተሸለ አማራጭ የለም፡፡
መች ትክክል ይሆናሉ የሚሉትን እንይ አንድ ባንድ
ሰላማዊ ትግል ትክክል የሚሆነው
1.      ሰላማዊ ትግል አስፈላጊ ነው ወይ የሚለው ሲመለስ
2.     ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎች አሉ ወይ
3.     ምንም አይነት ሰላማዊ ትግል አድራጊ መታሰር የለበትም
4.     ምንም አይነት ሰላማዊ ታጋይ መታሰርና መሰሎቹ በደሎች ሊፈፀሙበት አይገባም
5.     ምንም አይነት ግድያ እና ተመሳሳይ በደሎች የማይደርሱበት ከሆነ
6.     ሰለማዊ ታጋዩ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት
7.     ምንም አይነት አድልኦና አስተዳደራዊ በደሎች ካልደረሱለትና ልክ ስልጣን ላይ እንዳልወጣ ግን እንደ ገዥ መደብ እንክብካቤና ባለቤትነት ስሜቱ ከተከበሩለት
8.     ዜጎች የሰላማዊ ታጋዮ ተመሪ ደጋፊና አባል መሆን መብታቸው እና በነሱ ፍላጎት ብቻ መሆን ሲችል
9.     የትናውም ዜጋ የፈለገው ፖለቲካል ፓርቲ ደጋፊ መሆን ሲችል
10.    ፖለቲካል ፓርቲው የራሱን አማራጭ የገቢ ምንጮች ማመቻቸት ሲችል
11.     ምርጫ አለመጭበርበር ሲችል ከብዙ በጥቂቱ ናቸው
እነዚህን ሌሎችም ያልተጠቀሱ ግን ለሰላማዊ ትግል አስፈላጌ የሆኑ መመዘኛዎች ካልተሟሉ ሰላማዊ ትግል አለ ሳይሆን ታጋዮቹ እስኪያልቁ እንደ ዳይኖዘር ከምድረገፅ እስኪያልቁ እየተላተሙ ነው ቢባል ይሻላል፡፡ ስለዚህ ቀጣዩ አማራጭ ትጥቅ ትግል ይሆናል፡፡
በመሰረቱ ሰው እጅግ ካልከፋው እንዴት ሞትና እሳት ከሚቀልቡበት ሜዳ ይገባል? እንዴ ሞኝማ አንሁን፡፡ አንድ ግልፅ የሆነ ለታጋዮቹ ለፕሮፌሰር ግን ምንም ግልፅ ያልሆነላቸው ወይም ደግሞ አውቀው የተውት ወይም ደግሞ መቸም ከአሁን በኋላ እዛ ሆኜ ልታገልና ላታግል አልችልም ከሚል ተስፋ መቁረጥ የተውት ጉዳይ አለ፡፡ እርሳቸው እንዳሉት እርሳቸው እርጅና ጉልበታቸውን ያሳጣቸው እለት እና ወደዛ ቦታ መሄድም መምራትም መመራትም እንደማይችሉ ሲሰማቸው መናገር ፈልገው ካልሆነ በስተቀር እንጅ መቸም የትጥቅ ትግልን ያህል ፈታኝ ያለጉልበተኛነት በደካማ አቅም ብቻ ደፋ ቀና የበዛበት የወንድ ልጅ ፈተና ቦታ የለም፡፡ ይህንን ግን እርሳቸው ከህዝብ ጉያ ጠፍተው የማያውቁት ከሚናገሩት አረመኔው ወያኔ ቢናገር ይሻላል፡፡ ትጥቅ ትግል ምን ያህል ፈታኝ ነው? ትጥቅ ትግል ምን ያህል ጉልበት የሚያሳጣ ሞትን እንደ ምግብና ውሃ ቀን በቀን እየጎበኙ የሚኖርበት ቦታ ነው? እንደምን በረሃብ በበረሃ በውሃ ጥም በእርዛትና በአሾህ እንደሚለበለቡ የማይገባው ይገኝ ይሆን፡፡ ግን ልብሳቸው ምግባቸው መጠጣቸው ሞራላቸውና ጉልበታቸው አንግበውት የወጡት ዓላማ እና አደራ እንደሆነ በታወቀ፡፡ ለነገሩማ እርሳቸው ይሆናሉ እንጅ ማንም የኣለም ዜጋ ያውቀዋል፡፡ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም፡፡ ይህን ስል አሁንም ሰላማዊ ትግል ግን የመጀመሪያው አማራጭና ተወዳዳሪ የማይገኝለት የመጀመሪያው አማራጭ ነው፡፡ ይ ካልሆነ ግን መቸስ ምን ይደረጋል፡፡ ፒኤችዲም ቢሆን ተይዞ ይገባል፡፡
አስቡት ፒኤችዲና ክላሽንኮቭ ፒኤችዲና መትረየስ አንድ ላይ በብዕር ጦርነት ቆመ ማለት ግን አይቻልም ሁለቱም ግን አንድ ላይ ይሄዳሉ፡፡ ሁለተኛ ከዛ በኋላ ግን አማራጭ ሌላ ሊገኝለት አይቻልም ማለት አይቻልም፡፡ ለማንኛውም ትጥቅ ትግል የሚከተሉት ሁሉ ከሆኑ አማራጭነቱ ትክክል ነው
1.      ሰላማዊ ትግል ሳይቻል ሲቀር
2.     የሰላማዊ ትግል ቁልፍ ቁልፍ መመዘኛዎች ብቻ ሳይሆነ ሰላማዊ ትግልን ሰላማዊ የሚያደርጉት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል ደረጃው ይነስ ይብዛ እንጅ ወደ ትጥቅ ትግል የሚወስዱት መስመሮች ይበቅላሉ ይህም ተፈጥሯዊ ነው፡፡
3.     ትጥቅ ትግል ለማድረግ ማሰልጠኛ ቦታዎችና ስትራቴጅካሊ ወሳኝ የሆነ ቦታ ሲያዝ ወይም ሲገኝ
4.     የገቢ ምንጮች ላይ እርግጠኛ መሆን ሲቻል
5.     የተለያዩ አቅርቦቶችን በምን መልክ እንዴት በየት በማን በኩል እንዲሁም መቅረብ ይችላሉ ወዘተ ሲመለሱ
6.     ራስን እየቀናነሱ እንደዛ መሪ ላለማስጨረስ የራስ ስትራቴጅ ሲዘጋጅና ሙሉ ስምምነት ላይ ሲደረስ
ወዘተ…
በአጠቃላይ ሰላማዊ ትግል አልሆን ሲልና የሰላማዊ ትግል መጨረሻው ወደ ድል እና ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሳይሆን ወደ ጥፋትና ኪሳራ የሚመራ ሲሆን ትጥቅ ትግል መሄዱ ምንም ጥያቄ አያስፈልገውም፡፡ ትክክለኛ አማራጭ ነው፡፡
ከዛ ቀጥለውም በአራትኛ ደረጃ አድርገው ያቀረቡት
ሁለቱ የትግል ስልት ዓይነቶች በባሕርይ የተለዩ ናቸው፤ አንዱ ሌላውን የሚደግፍ አይደለም፤ ሰላማዊ ትግል የትጥቅ ትግልን ለመደገፍ ሰላማዊ የሚለውን ስያሜ መጣል አለበት፤ የትጥቅ ትግልም ሰላማዊ ትግልን ለመደገፍ ትጥቅ የሚለውን ስያሜ መተው አለበት፤ ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል አራማጆች ድል ቢያደርጉ ማን ወንበሩ ላይ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ጠመንጃ የያዘው ሥልጣኑን ሲይዝ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል! ያውም ከተፈቀደለት! በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ አርበኞች ሳይቀሩ በሩ ተዘግቶባቸው ለደጅ ጥናት እንደተዳረጉ አይተናል፤ መልኩን ለወጥ ቢያደርግም ደርግን ከተፋለሙት ውስጥ በአዲስ አበባና በአስመራ ወንበሮች ላይ ሲወጡ የተሸነፉት ወይ ለወያኔ ገብረው ሎሌነት ገቡ፤ ወይም በአሜሪካ መሽገው ያቅራራሉ፤ ዘመኑ እንዳለፈባቸውም ገና አልተረዱም።
ብለዋል፡፡ እዚህ ላይም እኔ የተለየ አመለካከት አለኝ፡፡ ሁለቱም በባህሪ ቢለያዩም መድረሻቸው ግን አንድ ነው፡፡ ስለዚህ በዛም ሆነ በዚህ አንድ ዓላማ ይዘው ነው የሚሄዱት ይህ አላማቸውም የጋራ ጠላት እንዲኖራቸውና ይህ የጋራ ጠላታቸውን ለማጥፋት በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚሰሩት ሁሉ ለተመሳሳይ አላማቸው ስለሚውል ተመጋጋቢ የማይሆኑበት ምንም አይነት እውነት የለም የበለጠ እንዲያውም ሙሉ ያደርጋቸዋል እንጅ፡፡
እንዲያውም ፕሮፌሰር አንድ ጉዳይ ልንገርዎት ሰላማዊ ትግል ያለትጥቅ ትግል አነስ ባለ ድግሪ እና በተለይ ትጥቅ ትግል ግን ያለሰላማዊ ትግል እንደ እርስዎ አባባል አይሆኑም ቢሆኑም በርካታ ዓመታትን ከማራዘም አንግል ይወልዳል፡፡ በመሆኑም ትግል ትግል ነው የቅፅበት መዘናጋት ይጥላል፡፡ ትግል ትግል የሚሆነው በግራም በቀኝም ግጥም ተደርጎ ሲያዝ ነው፡፡
አንድ የኛ ፖለቲከኞች ረሱት ጉዳይ ቢኖር ዓላማን ማለትም ፖለቲካዊ እና ሃገራዊ ዓለማን ለማስፈፀም የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ አንድ አካል ስልጣን ያስፈልገዋል፡፡ ለምን መሸፋፈን እንደሚያስፈልግ አይገባኝም፡፡ እኛ ሃገር ላይ አንድ የፖለተካ ድርጅት
             እኔ ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ መብት መከበር ለብሄራዊ ልዕልና ምናምን…ነው የምንታገለው
ገለመሌ ይላሉ፡፡ ይህ ግን ስዕተት ነው ባትነግሩንም እኛ ስለምናውቀው አትሸውዱን ለስልጣን ነው፡፡ ቀድሞ ነገር ስለሚያስፈልግ ነው፡፡ ስልጣን ካልፈለጋችሁ ለቀቅ አድርጉን ተጣቂዎቹም ይሁን ሰላማዊዎች ለስልጣንላይ መውጣት ካልቻሉ ማን ሊወጣ ነው፡፡ ይህን በምን ማስተካከል ይቻላል መሰላችሁ….
ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን እንደ አማራጭ የሚያመጣን ብቁ ፖለቲካዊ ድርጅት ስልጣን ላይ እንዲወጣ እንታገላለን ቢሉ ይሻላል፡፡ ቆይ ኢህአዴግ ሰለማዊ ትግሉን ወይስ ትጥቅ ትግሉን የሚፈራ ይመስላችኋል፡፡ ያለምንም ጥርጥር ትጥቅ ትግሉን ይፈራል ይሀ ሲባል ሰላማዊ ያገር ውስጡን ትግልም አይፈራም ለማለት አደለም፡፡ ሁለቱ አማራጮች ግን በተመሳሳይ ሰዓት እንዲጠነክሩበትም ሆነ እንዲፈጠሩበት አይፈልግም፡፡ ለምን? ሰው ማንኛውም ሰላማዊ ታጋይም ይሁን በትጥቅ ትግል የሚያምን አማራጮች ተቀምጠውለታል ስለዚህ በምንም ሳያመካኝ ወደፈለገው ይሄዳል፡፡ ሰላማዊ ትግልን መንግስት በሃይል መደምሰስ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ይህ ኢላማን እንደመምታት ነው የሚቆጠረው ባዶ እጁን ያለን ህብረተሰብ በመትረየስ መግጠም ግዳይን በጥይት እንደመደብደብ ያህል ቀላል ነው፡፡ መንግስት እንደሆነ የትኛውንም ዓለማቀፋዊ ሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አይፈራም ከጥቅማቸው እንደማያስበልጡን ያውቃል፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ 100 ገድሎና አስሮ የትኛውንም ያህል ቢሊዮን ዶላር ጥቅም የሚያስገኝ ብሄራዊ ጥቅም ይለግሳል በጎን ይበደራል በጎን ተቃዋሚ የሚላቸውን ከምድረገፅ ለማጥፋት በቢሊዮን ያወጣል ለጥቃቅኑ ሁሉ ጥቅመኛ መንግስት ስለሆነ፡፡ ይህና ሌሎችም እንጅ ስህተተቶቹ ወያኔ ትጥቅ ትግሉ ከምንም በላይ ትክክል ነው፡፡
በመሰረቱ ፕሮፌሰር ከአሁን በኋላ ፖለቲካውን ሁሉ ፕሮ ነፃነት ፈላጊ ካልሆናችሁ በቃችሁ ራሳችሁን ጦሬታ አውጡ መንገዳችን ላይ ዞር በሉልን፡፡ ለህዝብ ከየትም ሆነው የሚጮሁ ወገኖቻችን አታስቀይሙብን፡፡ ተውን አቦ!!
አስቲ ወጣቱና የህዝብ ጥያቄን የሚያስተጋቡትን ሁሉ የሚደግፉትን አካላት ሁሉ ሳይጣንም ቢሆን ለጊዜው መደገፍ ሚችል ስራ ብቻ ስሩ፡፡ የወቅቱ ጥያቄያችን የፍላጎቶቻችን ማለትም የኢህአዴግ ስልጣን መውረድ ጥያቄ ነው፡፡ ያዋረደን ያደኸየን ያጣጣለንንን ሁሉ ተንከባክቦ የያዘ መንግስት ማፊያ ቡድን ወድቆ ማየት ይህንን ስልጣን መረከብ የሚችል አካል ጎን ለጎን መመስረት ነው፡፡ ስለዚህ እባካችሁን ውድ ከህዝብ ጎን የቆሙ ዲያስፖራዎቻችንን ተውልን እናንተ በቅናት አብዳችሁ ብታረክሷቸውም እኔና መሰሎቼ ግን እንፈልጋቸዋለን፡፡ ምንም ስንሆን የሚጮኹልን እና ድምፃቸውን የሚያስተጋቡልን እነርሱ ናቸው፡፡ ይህ ሲባል እንደ ሰማያዊ እና አንድነት አይነት ምርጥ ፖለቲካዊ ፓርቲዎቻችንም አትንኩብን፡፡ እዛው ቤት ውስጥ ማለቅ ያለበትን ሚስጥር ለህዝብ ጥሩ ታማኝ መስሎ ለመታየት በግላጭ ለጠላት አውጥታችሁ ተስፋችን አታጨልሙብን፡፡ ፕሮፌሰር እርስዎ እጅግ ትልቅ አስተዋፅኦ ለህዝብዎት አድርገዋል፡፡ ለዚህም እናመሰግናለን ያየንም ያላየንም፡፡ ነገር ግን ከአሁን በኋላ አስረክቡን እርስዎ ከሰሩት ሁሉ ብየ ማለት ባልፈልግም በውጭው ዓለም የሚኖሩት ሁሉ ግን ለኢትዮጵያ ያላቸውን ሞራልና ልዩ ፍቅር በእንባም  አጅበው ሳይ ነው ኢትዮጵያዊነቴን የማውቀው፡፡ ስለዚህ እነርሱ ለሃገራችን ህዝብ ዘብ ናቸው ታዲያ በተቃዋሚች ጥንካሬ ነው እንዴ እኛ ዓለማቀፋዊ አጀንዳ መሆን የጀመርነው፡፡ እዚህ ውስጥ የአንድነትና ሰማያዊ ፓርቲዎች አስተዋፅኦ እጅግ ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን ሳልገልፅ አላልፍም፡፡
በአምስተኛ ደረጃ እርስዎ ያነሱት ጉዳይ ም እንዲሁ ለኔ የተዋጠልኝ ጉዳይ አደለም፡፡
እንደ እርስዎ አባባል ከሆነ እስቲ ያሉትን ደግመው ይዩት፡፡
ሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል ሁለቱም ብርቱ ቃል ኪዳንን ይጠይቃሉ፡፡ የቃል ኪዳናቸው ልዩነት አንዱ እስከሞት ለመታገል፣ ሌላው ደግሞ እስከመግደልና እስከመሞት ለመታገል መሆኑ ነው፡፡ ለሰላማዊው ትግል ከፍተኛ መንፈሳዊ ወኔ የሚያጎናጽፈው ለመግደል ያለው ተቃውሞ ነው፡፡ ሕይወትን ለማልማት ሕይወትን መቅጠፍ የአስተሳሰብም የመንፈስም ጉድፍ ያለበት ሥራ ነው። የሰላማዊ ትግል ዋናውና ቀጥተኛው ተልእኮ ሕዝብን ለሥልጣን ባለቤትነት ማብቃት ነው፤ ሥልጣንን ለመያዝ አይደለም፤ ስለዚህም ኢላማው ሕዝብ ነው፤ በሥልጣን ወንበሩ ላይ ያሉት የሰላማዊ ትግሉን የሚቃወሙት በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት እንዳያገኝ ለማድረግ ነው፤ ሰላማዊ ትግሉ የሚያተኩረው በሕዝቡ ጆሮ፣ አእምሮና ልብ ላይ ነው፤ አገዛዙ በበኩሉ ጸጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛለት ሕዝብ እውቀቱ ዳብሮ፣ መብቶቹን ሁሉ ተገንዝቦ፣ በሕግ ለሕግ እንጂ ለሰው አልገዛም በማለት ልቡ እንዳይሸፍት አፈናውንና ማነቆውን በማጠናከር እያደነቆረ ለመግዛት ይፈልጋል፤ የሰብአዊ መብቶችን የሚያስተምሩና በአገዛዙ አካላት የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያጋልጡ ድርጅቶችን ማዳከም ወይም ማጥፋት ለአገዛዙ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፤ ኢሳት የሚባለው የቴሌቪዥንና የራድዮ ፐሮግራም ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት የሆነበት ለዚህ ነው፡፡
ቃል ኪዳናቸው እስከሞት አደልም እስከ ህዝባዊ ኣላማቸው ነው፡፡ ይዘውት ወደ ትግል እስከሚገቡለት ዓላማ ነው፡፡ በእርግጥ እርስዎ እንዳሉት ቃልኪዳኑ ብርቱ ነው፡፡  ምናልባትም ሚስጥራዊ አለትነቱን ይህ ቃል ላይገልፀው ይችላል፡፡ ሞት እዚህ መሃል መነሳት ያለበት ጉዳይ አደለም ሞት ሞት የሚሆነው የህዝብን ፍላጎት የህዝብን ዓላማ በከንቱ በነገ ነገ ሲያስረግጡ ነው፡፡ ሞት ሞት የሚሆነው በህዝብ ስም ሲነግዱበት እንጅ የህዝብን ጠላትማ ሲያጠፉና ለዛ ሲጠፉ ሞት ሳይሆን መስዋዕትነት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል ትልቅ ማንም ማይፈታውና የማያስማማው ልዩነት አለ፡፡
ነገር ግን ሁለቱም ትግሎች ህዝብን ስልጣን ላይ ለማውጣት መሆን ሲችሉ ነው ትክክክል ሚሆኑት፡፡ ያለዚያ ግን ዜሮ ድምር ጨዋታ ነው ሚሆነው ያውም ኪሳራ የሞት ሞት ያ ነው፡፡ በየትኛውም የትግል መስመር መጨረሻው ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ መሆን አለበት፡፡ ይህ ሲባል መቸም ግልፅ ጉዳይ ነው ህዝብን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲሳተፍ እንዲመርጥና እንዲመረጥ ማድረግ መቻል ነው ከዚያም በሰላም ስልጣንን መረከብና ማስረከብ መቻል ማለት ነው፡፡
እርስዎ ትጥቅ ትግልን የሚገልፁት ከታሪክ ብቻ አይን በማየት መሰለኝ ይህ አግባብ አይመስለኝም፡፡ ትጥቅ ትግል ሲታሰብ በዚያ ትግል ወቅት ሊያመጣ የሚችለው ትርፍና ኪሳራም ብቻ አደለም መታየት የሚገባው፡፡ ምክንያቱም ትጥቅ ትግሉ ማለትም ከሃይል ሚዛን ማስደፋት አስከ ስልጣን መብቃት ድረስ ያለው የፈጀውን ፈጅቶ ስልጣን ላይ ያለው አካል ትንሽ ቢቆይ ኖሮ ሃገሪቱን ድራሽዋን ሊያጠፋት ከነበረ ትጥቅ ትግሉ አስፈላጊነቱ ምንም አያወላውልም፡፡ ይህንንም ከሁሉም ሴክት አንግል ማስላት ያስፈልጋል፡፡
ኢሳት የዲያስፖራው እና የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑንም ባለመርሳት ለዲያስፖራዎች ያለዎትን አመለካከት ቢያስተካክሉ መልካም ይመስለኛል፡፡
ሌላውን ሌላ ጊዜ…
ኢትዮጵያ ለዘላልም ትኑር
አመሰግናለው!!
ይድረስ ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም የፃፍኩት ነው


#### ታሪክን የኃሊት ####
ክፉ ቀን 1881 - 83 .

ክፍል አንድ...

ዓፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ከተባለ ጀምሮ አንድ የተፈጥሮ አደጋ ተከስቶ ነበረ::ይኸውም በሕዝቡ ዘንድ 'ክፉ ቀን' በመባል ይታወቃል:: ዘመኑም 1881 - 83 . ነበር::ችግሩ የተከሰተው በከብት እልቂት ነበር::የከብቱ እልቂት እንዴት እንደ ጀመረና እንዴትስ እንደተዛመተ ኤኒሪኮ ቼሩሊ የተባለው የኢጣሊያ የፖለቲካ ሰውና ምሁር ጥቂት ፍንጭ ይሰጠናል::በእርሱ አባባል በሽታው የተነሣው ከኤርትራ ነበረ::ኢጣሊያኖች ከህንድ ገዝተው ያመጧቸው ከብቶች ሕመም ያላቸው ስለነበሩ የሀገሩን ከብት በከሉት::ከዚያ ቀስ በቀስ እየተዛመተ በደጋይቱ ኢትዮዺያ ያሉትን ከብቶች እየጨረሰ በያገሩ ተዛመተ::ዓፄ ዮሐንስም በደርቡሽ የተገደለው በዚያን ዘመን ነበረና እንዲህ ተባለ:

ይሻለዎ ነበር ሜዳው ለፈረሱ
ምነው ከላሙ ጋር አለፉ ንጉሡ::

በአጋጣሚ በዚያን ዓመት ራስ ጎበና ዐርፎ ደብረ ሊባኖ ስተቀበረ የእርሱ መሞትና የከብቱን እልቂት በማስተባበር እንዲህ ተብሎ ተገጠመ:

እውነትም ጎበና የኦሮሞ ልጅ ነው
ከብቱን ይዞት ሔደ ወተት እንዳያምረው::

በዚህ በቀውጢ ቀን በተጨማሪ የጎበና መሞት ሕዝቡን አሳዝኖት ነበረ::ይህንኑ የሚከተለው ስንኝ ይገልጠዋል::

ጎበና አባ ጥጉ ሞተወይ የምር
ወሬውም አያምር::

ምንም መከላከያ መድኃኒት ስላልነበር የከብት ሬሳ በያለበት ተረፍርፎ ይታይ ነበረና እንዲህ ተብሌ ተገጠመ:

ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ
በሬ ሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ

አንዱ ደግሞ የከብቶቹ ማለቅ ያሳዘነው ሰው እንዲህ በማለት ስሜቱን ገለፀ

የበሬዎቹ ስም ጠፍቶብኝ ነበረ
አሁንስ ባስታውስ ከብት ዓለም ነበረ::

የከብቱ ማለቅ የመዋለ ንዋይ ቀውስ ስላስከተለ የመንግስት ግብር ለመክፈል አልተቻለም::የከብት ዋጋ በጣም ጨመረ::አንድ በሬ ሁለት ብር የነበረው ከከብት እልቂት በኃላ 30 - 40 ብር ያወጣ ነበር::ገጣሚው ግን ሁኔታውን እንዲህ በማለት አቅርቦታል

በሬ በመቶ
ያውስ የት ተገኝቶ::

ገበሬው ቦዘኔ መሆኑንና የመንግስት ግብር ለመክፈል ያለመቻሉን ለመጠቆም እንዲህ ተብሎአል

ምድር በዶሮ
ዳሩ ማንገብሮ::

በዚያን ግዜ ምንም እንኯ ያልተለመደ ቢሆን አንዳርድ ሰዎች በጋማ ከብት እያረሱ ችግራቸውን ለመወጣት ሞክረዋል::ይህን የተመለከተ አንድ ሰው እንዲህ አለ

የበሬውን ውለታ ወሰደው ፈረስ
ያገጣጣ ጥርስ::


ልማትን አስቀድሜ ነፃነትን ከዛ በኋላ አከብራለሁ ተብሎ የልማታዊ ሰስርዓት አስተሳሰብ አይሰራም ሃገራችን ውስጥ እንዲሰራም አንፈቅድም!!
የስርዓቱ አቀንቃኝ ሚዲያው ተቀዳሚ ስራው ማኑፋክቸሪንግ ኮነሴንት መፍጠር አደል ምን የተለየ አለው፡፡ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ፖለቲካል ፓወር አገልጋይ ነው፡፡ ሁልጊዝ ህገመንግስት ይጠቀሳል ፍሪደም ኦቭ አሶሴሽን አሪፍ ቃል ነው፡፡ ግን መች አከበራችሁት የዶ/ር መራራን መፃፍ መገምገም እንኳን አልቻልንም፡፡ ታዲያ ይህ ነው ፍሪደም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ እቀባና አፈና አለ ህዝቡ የነፃነት ያለሽ እያለ ነው በየቦታው፡፡ ማን ነው አንድ ጉዳይ ሊሰራ ሲያስብ ገና ቀድሞ ነገር መንግስት ያስረኝ ይሆን ብሎ የማያስብ ማን አለ፡፡ ይህ ፍርሃት ከየት መጣ የሰው ልጅ እኮ ሲፈጠር ሲወለድ ፈሪ አደለም፡፡ የሰው ልጅ ህሊናው ንፁህ ነው እንዲያው የንፁህነት ጉዳይስ አይታሰብም ግን እስቲ በቅፁ በሂደት ይቆሽሽ በአንዴ በፍርሃት ሞልታችሁ የፍርሃት አቅማዳ ታደርጉን፡፡ ኧረ ተውውውው…በኋላ ይቆጫችኋል ኢህአዴጎች፡፡ ተውውውው…እንኑርበት፡፡
ድህነት ቀጥቅጦን እናንተ ቀጥቅጣችሁን ነፃነታችን አጥተን ምን እንሁን የት እንሂድላችሁ፡፡ ሰድባችሁን አዋርዳችሁን መሬታችን እኛ የምናርሰው እኛ የምናመርትበት መሬት ስናጣ ለባዕዳን እየሸጣችሁ፤ አባቶቻችን ያስከበሯትን ድንግል ሃገራችን እናንተ አቅቷችሁ እንኳን በሆነ ወዳችሁ ፈቅዳችሁ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን እየሸጣችሁ፡፡
ገና ለገና የታጠቁ ለሃገራችን ህዝቦች መብት መከበርና አንድነት ትጥቅ ትግልን በመምረጥ ዱር ቤቴ ጫካ ማደሪያየ ቅጠል እና ስሩን ምግባቸው አድርገው ሃገራችን እየጠበቁ ያሉት በዚያ በኩል ዝር እንዳይሉ ለማድረግ ሲባል ሃገርን ያህል ነገር አውሮፓዊቷን ሃገር ፈረንሳይን ሁለትና ሶስት የሚያህል መሬት መስጠትን በእውነት ጠየነኛነት ነው፡፡
አብዳችኋል እንጅ ሱዳን ከሚከላከለውማ የማይጠቅመንን አማፂም በሉት ታጋይ ኢትዮጵያዊው እንደማይጠቅመን ካወቅን ከገቡበት ገብተን ምንም ወንድሞቻችን እህቶቻችን ቢሆንም ቅሉ ምንም አይነት መሬታችን ሳትሰጡብን ታሪካችን ሳታበላሹ ሳታጠፉ እንመክታቸው አልነበር፡፡
ኧረ ተውውውውው…ይልቅስ ያንን መሬት ስለኢትዮጵያ ሃገራችን ስለክብሯ ስለእመብርሃን ብላችሁ አትስጡት ለእኛ ለስራ አጦች ስጡን እኛ እናልማው፡፡ እንጠብቀዋለን፡፡ መሸጥ ከፈለጋችሁም በረዥም ጊዜ ብድር እንከራያችሁ ለኢትዮጵያዊ ብቻ መሸጥ መለወጥ ስለማይቻል እንደ ህጉ፡፡
አይይይይይይይይ…ኢትዮጵያ የሞተልሽ ንጉስ ሚኒሊክ ንጉስ ዮሃንስ ንጉስ ቴወድሮስ ሞቱብሽ አደል…አሁን የገደሉሽ ይበላሉ፡፡ ኧረረረረ ምነው ባልተፈጠርኩ፡፡ ኧረ ምነው ባልተወለድኩ፡፡
ምነው ምን አደረገ የኢት|ዮጵያ ህዝብ ያለውን ግብረገብ ህዝብ ሳይፈራ ፈርቶ የሚኖር ፈሪ ሳይሆን ፈሪ የሆነ ህዝብ ነው ለመኖር ለሃገራችን ደህንነት ሲል ስለመፃኢ ዕጣ ፋንታዋ ሲል… ቆይ ግን ምን መጣብን ስዎች…
ዝም ያለ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃገራችን ላይ እንደግብፅ እንደ አረቡ ዓለም አቢዮት በአቢዮት ማተራመስና ምንግስትን ካለበት ተመቻችቶ ከተኛበት እንቅልፉ ማንቃት ብቻ አደለም ልቅምቅም አድርጎ ገደል መክተት ያቃተው መሰላችሁ አደል…እንደዛ ግን አደልም አያቅተውም ግን አንድም ጊዜ እንኳን ለሰላም ያለጦርነት መዋል ማደር ሳትችል የቀረችው እምየ ሃገራችን ትረፍ እስቲ ጉልበቷን እጥፍ ታድርገው ብለን ነው፡፡
አሁን ግን በቃን መሮናል በቃን…በቃንንንንን…
ስለዚህ ከሚከተሉት ከሁለቱ አንዱን እንደመጀመሪያ እርምጃ ማድረግ ግዴታችሁ ነው መብቶቻችን ተዋቸው አንዴ ትታችሁታል
1.      ድንግል ዳርድንበራችን ዜጋውን አፈናቅላችሁ ለማንም ቢሆን የሰጣችሁትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መልሱልን
2.     ከስልጣናችሁ ውረዱና ራሳችን እንደሚሆን እናድርገው…
ቻው!!

ወያኔ ኢህአዴግ ግን ለምንድን ነው አንድ ጉዳይ ሲመጣ ያለፉትን ስርዓቶች ዋቢ የሚያደርገው? ራሱን ከደርግና ከአፄው ጋር ያወዳድራል፡፡ ለምን ኧረ ተውን እኛ የማናውቃቸውን ስርዓቶች ሪፈር ከምታደርጉልን እባካችሁ የተሻለ ስርዓት የተሸለ ፖለቲካል ፓርቲ ከፊታችሁ እንዳለ ማሰብ ለምን አትችሉም ለዚህም…ነዋ ታዲያ ፖለቲካል ፓርቲዎች በምንም መልኩ የተሸለ ሃሳብ ይዘው እንዳይመጡ የምታደርጉት ይዘው የመጡትንም እዛውውውውውው ድምጥማጣቸውን ታጠፋላችሁ… ነንሰንስ!!

በመሰረቱ አባ መላን ወይም ደግሞ በትምህርት ስሙ ሳይሆን እናቱ ባወጣችለት ስሙ ብርሃኑ ዳምጤ ማለት 60ዎቹ ውስጥ ዕድሜው ያለና ከልጅነት እስከ እውቀት ድረስ ሃገሩንና ለትክክለኛ አላማ የቆሙ ጓዶቹን ሲክድና ለጥይት ደረታቸውን እንዲሰጡ ያደረገ የጭቃ እሾህ ነው፡፡ እስቲ ስሙን ካነሳነው አይቀር ትንሽ ስለ ተልዕኮዎቹና ተንኮሎቹ ግን ስለከሸፉት ሴራዎቹ ትንሽ እንበል፡፡
ብርሃኑ ዳምጤ በፖለቲካው ዓለም ከኖረ እጅግ በርካታ ዓመታት እነ3ደቆ በተለያዩ መድረኮች በተለይ ደግሞ በየፓልቶኮቹ ሲዘባጥር ይሰማል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ደግሞ በፖለቲካው ዓለም ያን ያህል ጊዜ ሲኖር በፖለቲካው ሳይንስ ምንም ሳያውቅ ደደብ ሆኖ እንደ እንሰሳ እንኳን ማሰብና ማገናዘብ ከልምድም መማር ያቃተው ሰው የለም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ሴረኛ ነው፡፡
 ሁልጊዜም ቢሆን ራሱን እንደ ሰላይና ደህንነት ራሱን ለሃገር ተቆርቋሪ በመቁጠር በራሱ ዓለም የራሱን ፖለቲካል ምህዳር ህሊናው ውስጥ ብቻ በማላወስ ሚባዝን ገፀ ባህሪ ነው፡፡ በመሰረቱ አባ መላ የተባለበት እውነተኛ ታሪክም ቢሆን በርካታ ነገር ቢባልምና እራሱ ሚለው ቢኖርም ምንጮች ግን የሚሉት አንድ ስራ ሲሰጠው ሰውን በየትኛውም መንገድ በራስ በእግር ሲፈልግም ከጉልበት ተደፍቶ በማንባትም ቢሆን ከቻለ አጭበርብሮ ካልቻለ ደግሞ አለቃቅሶ /…ጠብቶ/ እንደሚባለው ተልሞስሙሶ ይቀርብና ሁልጊዜም መቃብርን ሲቆፍር የሚያዝ ጭራሽ እንኳን አንድም ቀን ቢሆን ከእርሱ ጋር የተቀራረቡ ስዎች ሳይደሰቱበትና ጋራ አላማና አቋም የያዙም ቢሆኑ ሳይተማመኑበት እዚህ ነው ሲሉት እዛ እዛ ነው ሲሉት እዚህ እያለ ቂቤ እንዳጨማለቀው አሎሎ እና እንደአሳ መያዣው ሲጠፋቸው ይለዩታል፡፡
በእርሱ ምክንያት የጀመሩትንም ዓላማ በእንጭጩ እንዲቀጭ የሚያደርግ እንስሰሳ ነው በአጠቃላይ እርሱ ማለት በሃር ውስጥ ያለ ዓለት ነው፡፡ ምንም የማይታመን አሁን ይጣልህ መች የማይታወቀው ዓለት መቸው ትንሹን እንሰሳ ያህል እንኳን ያህል ማሰብ የማይችል ከብት ነው፡፡ ለማንኛውም ግን ሲጀመርም ከቤተምንግስት /ጠፍቶ የማያውቀውና ኢህዴግ ሲጠቀምበትና ሲጠባው የኖረው ብርሃኑ ዳምጤ አባ በላ ዳምጤ ብዋለው ወደ ውጭው ዓለም የተቀላቀለው እርሱ እንዳለው የውጭውን ሃይል ለመቀላቀልና የኢትዮጵያን ህዝብ ነፃነት ትግል ለማጠንከር ዋልታና ምሶሶ እንኳን ባይሆን ሌሎች እንዲሆኑ ለማገዝ ሳይሆን ሆን ተብሎ ይህንን ባህሪውን የተረዳው ወያኔ በውጭው ዓለም እያስጨነቁት ያሉትን እንደ ግንቦት ሰባት ለእኩልነትና ለፍትህ ፖለቲካል ፓርቲዎችን እንዲሁም ሌሎች ጠንካራ መሰረት ያላቸውን በተለይም ደግሞ የተቀጣጠለውን የአማመራና ኦሮሞ ህዝቦቹን አንድነት በዲያስፖራው ወደ ሃገር ቤት ይመጣኛል ብሎ በመፍራት ይህንን ፍቱን ህሊና የሚጠይቁ ክህደቶች ላይ አይኑን በጨው አሽቶ መካድ የሚችል ስው የላከው አባ በላ ዳምጠው፡፡

በእርግጥ አባ በላ ዳምጠው ሲሄድ ሙሉ መብት ተሰጥቶት ነው የሄደው በቻለው አቅምና በቻለው ቦታ እንዲሁም የአማርኛና እንግሊዝኛ ቋንቋ ቃላቶች ካላተሩት በስተቀር ያለምንም መሰቀቅና መደንገጥ ኢህዴግ ወያኔን እንዲያጥላላ መረጃ ሚመስሉ ነገር ግን መንግስትን አደጋ ላይ የማይጥሉ ክህደት የሚመስሉና ጭቃ አርከበር ውስጥ የማይከቱ ንግግሮችን በማድረግ እስከ ግለሰብ ባለስልጣናትና ፍትህን አበላሽተዋል በሚባሉ አካላት ላይ ሁሉ ሁለት ስራ እንዲሰራ ነው አንድም ስማቸውን በማጥፋት እነዚህ መንግስታዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሃይሉ የማይፈልጋቸውን ባለስልጣናት ማንም ይሁን ማን ከተፅዕኖ ፈጣሪው ውጭ ያሉትን ማጋለጥ ይህን ለማለትም እንዲመቸውም የገንዘብና መረጃ ፈሰሱን መንግስት ሊሞላለት ሲስማማ በሌላ መልኩ ደግሞ ማንኛውንም እርሱ ሚፈልጋቸውን ባለስልጣናት ውሸት ሆነ ምንም ዓይነት መሰረት የሌለው ወሬ እንበለው በመንዛት ለዛም ፎርጅድ ወይም ፌክ መረጃና ማስረጃ በማቅረብ ዲያስፖራው ክፍል አንድም እርሱ ላይ ያላቸውን አመኔታ እንዲጨምር ለማድረግና እርሱን ወደ ተሻለ ስልጣን ከፍ እንዲል እንዲያደርጉት የተወጠነ ሲሆን ሁለትም የተናገረው መረጃ ውሸት እንደሆነ ያላወቁት የዲያስፖራው አባላት በተለይ ተቃዋሚዎች የሚያገኙት መረጃ ትልቅ ሚስጥር መስሏቸው ጓጉተው እንዲከታተሉትና ይህ የነገራቸውን  ኢንፎርሜሽን ወዲያዉኑ በመከተል መንግስት ዲያስፖራውን እንዲወናበድ ለማድረግ ሌላ እውነተኛ መረጃ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡
በዋናነት ግን ይህ ተልዕኮው እንደከሸፈበት ለላኩት አካላት እንደተናገረ መረጃዎች አሉ፡፡ ምን ሲሰራ እንደነበር በምሳሌ እናስደግፍ፡፡
ለምሳሌ፡- የተሰጠው ስራ አቶ መላኩ ፀሃይ ሙስና ሰርተዋል ብሎ መረጃ እንዲሰጥ ተነገረው በመንግስት ይህን በመናገሩ ብቻ አቶ መላኩ ፀሃይ ስልጣን ላይ ስለነበረ ከየት አመጣው መረጃውን ይህ ሰው በእውነትም ጠቃሚ ነው እንዲባል እርሱ ይህን መረጃ እንዳወጣው ወዲያውኑ ትንሽ እንደቆዩ መንግስት ራሱ ያወጣውን መረጃ ተመሳሳይ ኮፒ ይናገራሉ በውሸት ሚዲያቸው…ከዛም
1.      ዲያስፖራው ዋው አባ በላ አያችሁት ይዞልን በጭራሽ ምንም ልዩነት የለውም እኮ ያመጣው መረጃ ይሉና በደስታ ተፍነክንከው ማመን ይጀምራሉ፡፡
2.     ሌሎች መረጃዎችን ከእርሱ እንዲናፍቁ ያደርጋል ዲያስፖራውን እንዲያውም ድልቅቅ ማለት ጀምሮ ነበር አሉ ተጨማሪ መረጃ እንደሚጠብቁ ስለሚያውቅ፤ የመረጃ ምንጩ መንግስት ጋር በየጊዜው ስለሚገናኝ የመረጃ ምንጩም አይደርቅም ቀጣዩን ታርጌት በእንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይነገረዋል መከረኛ ባለስልጣን ከተፅዕኖ ፈጣሪው ቡድን ውጭ የሆነ ሁሉ ይጋለጣል ወይም በውሸት ይነዛበታል ተቃዋሚ ሚዲያወችም ይጨመራሉ ምንግስትና አባ በላ ስኬታማ ሆኑ ለጊዜውም ቢሆን
3.     ዲያስፖራው በአባ በላ ላይ አመኔታው እየጨመረ እውነትም ሙሉ በሙሉ ምንግስትን ክዶ ነው መጣ አታዩትም ከመንግስት ጋር እኮ በመረጃ ሳይቀድመኝ ልቅደም ነው የያዙት እየተባለለት ነው በምሳሌያችን መሰረት እርሳቸውም አባ በላም በኩራት መንደላቀቅ ጀምረዋል እንዲያውም እኔ ያልኩት ካልሆነ ደሞ እኔ ያልጋገርኩት ማለትም አብዝተው ነበር…ምንግስትም እየተከተለ አንዳንዴ ተቃራኒውን ሌላጊዜ ራሱ አባ በላ ያቀረበውን መረጃ እያቀረበ ነው…
4.     በየእለቱም የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ደረጃ በደረጃ ያወቀውን ያህል ለመንግስት ይሸጣል ገንዘብም ይላክለታል ወዳጀቼ ገንዘብ የሚላክለት በእጅ ነው፡፡ ምንግስት ሞኝ አደለም በባንክ መላክ ምናምን አያውቅም ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ አደል፡፡ ይህን በማድረጉ ብቻ በርካታ ስራ ለምንግስት ይሰራል፡፡ አንዱና ዋናው ግን ይህን የወጣውን መረጃ ተከትሎ ትንሽም ብትሆን ማነው ይህንን መረጃ ብሎ ለመንግስት የሰጠ ይህንን የሰጠማ እኛን በቁማችን ያርደናል በማለት በተቃዋሚዎች መካከል አለመተማመን በመፍጠር እርስ በራሳቸው እንዲረካከሱና እንዲፈረካከሱ ያደርጋል፡፡ ቢችል አስቡት ሲያጋድልም ጠቅላላ ተቃዋሚውን ሁሉ ለማባላት ነበር አላማው አባ በላ፡፡ ሁለተኛው ተግባሩም ይህን መረጃ በመስጠቱ ቀጣይ የተቃዋሚዎች ስራ ምን ሊሆን እንደሚችል ተቋሚ መስመሮችን መዘርጋትና አዳዲስ የመረጃ ባቡሮችን መተለም መግዛት ነው፡፡ ለዚህማ ወያኔ ሌላ ስራ አይበሉት እንጅ፡፡
5.     የተዛቡ መረጃዎችን እምነት ላሳደሩበት ዲያስፖራው ተቆርቋሪዎች መስጠትና አሁንም ራስ በራሳቸው እንዲጠላሉ ብሎም እስከመጨረሻው እንዳይተማመኑ ማድረግ ነው፡፡
6.     ስማቸውን የሚያጠፋቸው ባለስልጣናት አንዳችም እንኳን ከስልጣን መውረዳቸውም ሆነ መቆየታቸው የሃገሪቱ ፖለቲካ ላይ ጥቅም የሌለው እንዲያው ለጊዜው ብቻ የህዝብ አቅጣጫ ማስቀየሻ የሚሆን ብቻ ነው፡፡ የሳይጣን ድሎትና ስጦታ መሆኑ ነው፡፡ ይህን ሲያደርግ የተቃዋሚ ሚዲያዎች ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያለ የሌለ አቅማቸውን ተጠቅመው እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ በተራ ወሬ ብቻ ሰውን እንዲነፉት ያደርጋል፡፡ በዚህ መንግስት የሚጠቀመው ጥቅም ተቃዋሚዎችን በሚሳየል ከመምታት በላይ እንደተሳካለት አድርጎ ይወስደዋል፡፡ ተቃዋሚዎችም ይህ በማድረጋቸው ኪሳራ ላይ እንዳሉ አወቁትም አላወቁት ይከስራሉ፡፡
7.     ይህ ሰው ከዚያ በኋላ እምነት እስከተጣለበት ድረስ በመንግስትም በተለይ በተቃዋሚው ጎራ ስራው ቀሎለታል ውሳኔዎች ላይ ጣልቃ መግባት ይጀምራል፡፡ ያኔ ድምፅ አገኘ ማለት አደለ ስራውን በይፋ ሽና ያበጅለታል፡፡ በቀደደው ሽናም መስመርም ስራዎቹ የተልዕኮው ስኬቶቹም ይንቦለቦላሉ ወደ ማን ወደ መንግስት መረጃ ካዝና፡፡ ይህን ባመድረጉ በፕሮግራሙ መሰረት ይሸለማል በገሃድ አደለም እናንተ ስዎች በእጅ ነው፡፡ በተዘዋዋሪ፡፡ ሆዳሙ አባ በላም ይበላል ይባላል!!
8.     የዲያሥፖራው ስራ ሁሉ መና መና መና እየሆነ ትግሉ እየመነመነ እየመነመነ ይሄዳላ፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሰውየ በኢህዴግ ወያኔ ሴራና ምክር እንዲሁም ልምድ ነገ ብረት የማይሆን ደረቅ እንጨት የተቃዋሚው ምድጃ ውስጥ ቆስቁሶ እሳቱ እነንዲነነድ ያደርጋል አመኔታውን ለመጨመር፡፡ እንጨቷም ነዳ ታልቃለች፡፡ ተቃዋሚዎችም ሌላ የሚቀጥልና የሚቀጣጠል ሲጠብ ቁልጭ ምንም የለም፡፡ አባ በላ በልቶታል ቶሎ የምታልቅ እንጨት ቆስቁሶ ሌላ እንጨት መፍትሄማ የለኝም ይላል፡፡ ይሕን እንዲልም እንዲያደርግም የሚያዝዘው ወያኔ ከአዲስ አበባ ነዋ፡፡ ያኔ የሚቃጠል እንጨት የትግሉን ምድጃ የሚያንቦገቡግ እንጨትና ሰው ሳይሆን የሚገኘው እንደ እምድጃው የሚቃጠልና የሚንቦገቦግ መተማመን ያቃተው አመድ የሆነ ታጋይ ተቃዋሚ ነው፡፡ ይህን በማድረግ ረገድ በትንሹም ቢሆን የሆነ ጊዜ እንደተሳካ ማረጋገጥ ይቻላል በተለያየ አጋጣሚ ይሐን ለመስራትም የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ አንዱ ረዳቱ እንደነበር ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ ይህ አባ በላ ዳምጠው ዓላማው የተቃዋሚውን ጎራ በተቃውሞ ሰዓት ተቃዋሚ በተረጋጋ ሰዓት እሳት የላሰ የተቃዋሚ አነሳሽ ሆኖ ሲሰራ ነበረ ዱዋል ኤጀንት ነበር፡፡ አንደኛው ኤጀንትሽፕ ግን ፌክ ወይም ማጭበርበር እንጅ እውነተኛ አልነበርም ግን እውነት ሳይሆን እውነት እንደሆነ ተደርጎ ተወሰደ ሽወዳ ብለው ይሻላል፡፡ ለዚህም አደል ቁጥራችን ቀላል ማንባል ስዎች ይህንን ሰው ተቃዋሚ ስለመሆኑ መንግስትን ስለመካዱ አሁን ለነፃነት የሚታገለውን ዲያስፖራ እንደተቀላቀለ ያለምንም ተጨማሪ መረጃም ሆነ ማስረጃ ያመንነው፡፡ እንዲሁም የማመናችን ጥንካሬ ምንግስት እንኳን ይህንን ሰው እኔ ነኝ የላኩት ይህንን መረጃ የሚሰጠኝ እርሱ ነው ቢለን እንኳን አንገታችን እንሰጣለን እንጅ ይህንን ሰውማ አሳልፈን አንሰጠውም ማለታችን አይቀርም ነበር፡፡
ለነገሩ አሁንማ መንግስትም ፈርቶታል እና አንድም እስር ቤት ያለያም እንዳይነቃበትና ብዙ ከፈለገ የቁም እስረኛ እንደሚያደርገው አለያም እንደሚገድለው እሙን ነው፡፡ የሚያበሳጨው ይህ ሰው ሲሞት አይዞህ ደርሸልሃለው አየሚለው እንኳን ማጣቱ ነው፡፡ ያለውን ለእርሱ ያለውን ሁሉ ጨርሷል፡፡ ወያኔ ነበር የቀረው እርሱ ከተፋው ተፋው ነው፡፡ እንዲያውም አንድ ጉዳይ አስቧል መንግስት ራሱ ከገደለው በኋላ አወጋን የሚባል አማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ ገደለው ሊል አስቧል፡፡
ይህ እውነት ነው፡፡ ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ነው፡፡ ለማንኛውም ለተቃዋሚማ ይህንን ሰው ተገላገልን ማለታቸው እንደማይቀር ኧረ ይህ ሰው የእኛ ስዎች ናቸው መንግስትን ለመሰለል የላኩት ብለውም ሳይተባበሩ ሚቀሩ አይመስለኝም፡፡
ያም ሆነ ይሕ ግን ኦቦ አባ በላ ዳምጤ በሁሉም አቅጣጫ የተሳካለት አይመስልም ምክንያቱም
1.      አባ በላ የተላከው ለስድስት ዓመታትና ኢህአዴግ በቃህ ሲለው ብቻ ሲሆን እርሱ ግን ቀድሞ አቆመ
2.     አሁን የወሰደውን እርምጃ የወሰደ እርሱ እንዳለው በረዳት ፓይለቱ ምክንያት በተፈጠረ አለመስማማት ሳይሆን ቀድመው የነቁት ተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ከምንም ዓይነት ድርጅታዊ መረጃ እርሱን ያላቀረቡት መሆኑን ጠንቅቆ ሲያውቅ እንዳልተሳካለት በመወሰን መንግስት ባላወቀው መልኩ ሲሾልክ ሲሆን ለዚህም ማስተባበያ እንዲሆነው እንደተለመደው ማለትም በርካታ ለተቃዋሚ ሚዲያዎች እና አባላት ግልፅ የሚያደርጋቸው ካለውም ከላይ በተጠቀሰው መልክ የተፈጋጁ ውሸት መረጃዎችን ሊያቀርብ በብዛትም ሳይኖረው እንዳለው እየዋሸ ለመኖር እንደጣረው ሁሉ መንግስትን በርካታ መረጃዎችን እንዳመጣ በመንገር ነው በዚህም መንግስት የተበሳጨበት ይመስላል መቸረሻውን አብረን እንይ፡፡
3.     እስካሁን ለምንግስት ከዳዊት ከበደ ጋር ያቀረቡት መረጃ ውሸት መሆኑና አንዳንድ የሾለኩትንም ተቃዋሚ ዲያስፖራዎች የእርምት እርምጃ በመውሰዳቸው ስለተቀደመ
4.     ለምንግስት ወሳኝ ሰዓት ላይ እንደደረሰ ለምንገር በመሞከር ሚያደርገውን ጥረት ውድቅ የተደረገበት መሆኑ፤ ማለትም ኢህአዴግን ግንቦት ሰባት እንዲሁም ሌሎች ለትጥቅ ትግል ወጡ ሃይሎች እየተደራጁ እና ሃይላቸውና አቅማቸው አንዲሁም ቁጥራቸው በበርካታ ክፍለጦሮች አንድነት እየፈጠሩ ስለሆነና ይህንንም ለመስራት ግንቦት ሰባት የአንበሳውን ድርሻ በማደራጀቱ በኩል እንደያዘና አንድነት በመፍጠር ያሉት ደምሂት፣ አርበኞች ግንባር፣ አማራ ፎርስ፣ ለፍትህና እኩልነት፣ ጋምቤላ ታጋይ እንዲሁም ሌሎች አንድ ላይ እንዲሆኑ በተለይም ደግሞ አርበኞች ግንባርና ደምሂት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የታጠቀ ሃይል እንዳላቸውና ግንቦት ሰባትና ሌሎች ጠንካራ ድርጅቶችም ከውጭና ከሃገር ውስጥ በሚገኝ የገቢ ምንጭ በመታገዝ አንድነታቸውን አተናክረው ምንግስትን ከመገዳደርም አልፈው መመጨፍለቅ ከሚችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ ስላወቀ ይህንን ቀድሞ ማሳወቅ ሚችለው እናም በአጋጠጣሚ ይህንን እውነት ሚያውቅ እርሱ በመሆኑ ከዳዊት ከበደ በላይም ለዚህ መንግስት ፍቱን የሚለውን መፍትሄ እንዲያቀርብ ለመምከር የመጣ ለመምሰል ነው፡፡
ይህ ጉዳይና መረጃም ከተሰጣቸው በኋላ ነው መንግስት እነዚህ ሃይሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የከፈተው፡፡ ለዚህም ነው በቅርቡ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኤርትራ በኩል ሙሉ አሰሳ ልናደርግ ነው ታጋዮችን ልንፈጃቸው ነው ምናምን ሚሉት፡፡
ይህ አሰሳ ለምን ይህንን ጦርነት መንግስት ማወጅ ፈለገ ስለፈራ ነው ስለሰጋ ነው እንዳይባል ይህን ተግባር ሁልጊዜም በየዓመቱ እንደሚከውኑ ተናገሩ፡፡ አይ ውሸት ለነገሩ እነ አባ በላ ና መሰሎቹ ያመጡባቸው ኮተት ነው፡፡ አንዲያው እስቲ አስቡት ታጋዮች እጃቸው ጭድ ነው አመድ የያዘ የሰፈር ጎረምሳ ያውም ባዶ እጁን ያለ እንደሚፈልጉ ሁሉ እንዴት ቀለል እንዳደረጉት፡፡
እኔ ግን አንድ እውነት ልንገራችሁ ምንግስት ይህንን ተግባር ቢሞት አይሞክረውም ቢሞትም ቢሞክረው እንኳን ጉዳቱ ለእርሱ ነው የሚብሰው፡፡ ለሰኮንድ ተቀምጦ የሚረፈርፍ ታጋይ ነው ያለው፡፡ ለዚህም አደል እንዴ ወደ ሁመራ በኩል ብትሄዱ እኮ ቤቀኑ ማለት ይቻላል ቢያንስ ለሶስት ሰዓታት ያህል ጦርነት አለ ወንድማማቾች ጦርነት፡፡ እስቲ ጦር ሃይሎች እና ባህርዳር መኮድ የወታደሮች ህክምና ቦታዎች ሂዱና አንዱን ገብታችሁ አውሩት፡፡ ከነዚህና መሰል ሆስፒታሎች ብትገቡ እጁ የተቆረጠ እግሩ የተቆረተ ቢያንስ ቢያንስ በሳምንት ከ150 በላይ ስለኛ ታገኛላችሁ፡፡
እናም እንዴ የምን ጦርነት ደግሞ አሁን አለ ስትሏቸው… መልሳቸው
"እህህህ"
ብለው ፈገግ ካሉ በኋላ በቁስል ህመም በሞት ጣር በተሸኘ ፈገግታ
"እህህህ እናንተ በእኛ ሞት በወንድሞቻችን ገዳዮች ቀን በቀን እናልቃለን ላንመሰገን እናንተ በሰላማችሁ አላችሁ…ይህ መንግስት እንደሆነ ለወታደር አይሆንም፡፡ ሞታችን ሞት አይመስለውም፡፡ ወታደር ለመሞት የተፈጠረ ይመስለዋል፡፡ በእርግጥ ውትድርና ሞት ባይሆንም ትሞታለህ ወይም ትገድላልህ፡፡ ግን ለትክክለኛ ዓላማ ካልሆነ ሞት አደለም የሞት ሞት ነው፡፡ ለነገሩ ለህዝብ ነፃነት ሲል ለራሱም ነፃነት ሲል ትግል ጫካ የገባውን ወንድሜን ከምገድለው እኔ አውቄም ሳላውቅ እሱ ላይ አፈሙዝ ያዞርኩት መሞት ሲያነሰኝ ነው፡፡"
የሚሉ ድምፆቸን ቤቱን ሞልተው ታገኛላችሁ፡፡ በቢጫ ኦራሎችና ሌሎችም ሽፍን ተሳቢ መኪኖች ተጭኖ ተጭኖ በከፍተኛ ሚስጥር ወደአልኳችሁ ቦታዎች የሚጋዙ አስከሬኖችን በየጊዜው ቤቱ ይቁጠረው፡፡
እነዚህን ምንም እንኳን ወንድሞቻቸው እንደሆኑ ቢያውቁም የህዝብ ነፃነት ናፍቋቸው ጠምቷቸው ወንድምና እህቶቻቸው ምናልባትም የስጋ ወንድምና እህቶቻቸው ላይ ቃታ ስበው ውድ ህይወታቸውን መቅተፉንማ በታጋዮች ይብሳል እናም ዝም ብለው እንደመሬት በለን ናና አስሰን የሚሉት አይምሰላችሁ ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው ካልሆነም ሚጎዳው መንግስት ነው ወገኖቼ፡፡
እናም የዚህ ሁሉ ሴራ የመጋረጃ ጀርባው ተዋናኞች ዳዊት ከበደ አባ በላና መሰሎቹ ከመንግስት አሳሳችና ተሳሳች ሃይሎች ናቸው፡፡
በነእርሱ መረጃ በመነሳትም ነው መንግስተ አውሮፓዊቷነ ፈረንሳይን ሶስት ጊዜ ማከል የሚችል መሬት ለሱዳን መሰጠቱ እና የጋራ ጦር ሃይል በዓለም እና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመስማማት ማቀዳቸው የዚህ ሁሉ ማሳያ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ የዚህን የጋራ ጦር ክፍያ የምትከፍለው ኢትዮጵያ መሆኗ ነው፡፡ በነገራችን ላይ መንግስት ይህንን ያደረገበት ምክንያት ከዚህ እና ከግብፅ ጋር ተያይዞ ያለውን ሞኝነትም ይሁን ብልጠት ትተን እንዲሁ አማፂያንን ለመከላከል ከሆን እንኳን የሱዳን ወታደሮች ምን ያህል ከኢትዮጵያ ወታደሮች ተሸለው አማፂያንን የመመከት አቅም አላቸው እና ነው፡፡ ወይስ ሱዳን አማፂያንን እንደምታሰለጥን አያውቅም ማለት ነው ሃሃ ቀልድ ናት አቦ¡
ለማንኛውም ይህ ሁሉ እርምጃ ነዚህ አባ በላና የዳዊት ከበደእና መሰሎቻቸው ዱዋል ኤጀንትሽፕ ስራና ውጤቱ ነው፡፡
5.     ኢሳቶች ቃለመጠየቅ ሲያደርጉ ለአቦ በላ ዳምጤ ብልጥ ነበሩ ይህንን ጉዳይ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በብቃት ቃለመጠየቃቸውን ያተናቅቃሉ ምንም ዓይነት መረጃ ሳይሰጡት እሱ ሚስጥር ሰጭ እንጅ ሆኖ የሚያበቃው መረጃ ያገኘበት ቃለመተየቅ ሆኖ አያውቁም በድጋሚ መመልከት ትችላላችሁ ሁሉንም ቃለመጠይቆች፡፡ ይህንን ማድረጋቸው ደግሞ በምንም መልኩ ስህተት ሳይሆን ብልጠት ነበር፡፡
6.     ሲጠየቅ መለሰ እንጅ ጠይቆ አደልም የሚወጣው ቀድሞ ነገር ይህንን ጠንቅቀው የሚያውቁ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው በእውነተኛነታቸው መንገስት ሲውጥ ሲተፋቸው ሲያስር ሲፈታቸው ለመግደልም የሚፈልጋቸው ሲሰቃዩ የኖሩ ሲመራቸው አገራቸውን እየወደዷት የተለዩዋት ትልልቅ ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ እናም የሚሸወዱ አደሉም፡፡
7.     ግንቦት ሰባት ላይ የሚናገረው ነገርም አንድም መንግስትን በማስፈራራት የእሱን ተጨማሪ መረጃ በመፈለግ ወደ እነርሱ እንዲያስጠጉት የዘየደው እና ጥንካሬያቸውን መጥፎ ነገሮችን በማውራት የሚያጣጥል ስለመሰለው ነው እንጅ እውነታውን ያውቃል ከእነርሱ አጠገብም ምንም ዝር እንዳላደረጉት እርግጠኛ ነኝ፡፡ በመሰረቱ ይህን ሰው መጨረሻ ላይም ቢሆን ማጋለጥ ይፈልጉ እነደነበረ ማለትም መረጃዎችን ከሰበሰቡ በኋላ ማንነቱን ለህዝቡ ሊያሳዩ እንደነበረ አልጠራጠርም፡፡ ኢሳት የመንግስት ሰላዮችንና ውስጥ አርበኞቹን በመላክ ከተቃዋሚዎች ከሚያገኘው መረጃ በላይ መንግስት በየሰኮንዷ የሚሰራትን ትርኪምርኪ ነገር ሳይቀር ለኢሳትና ለሌሎች የማህበረሰብ ድረገፆች የሚያደርሱ የውስጥ አርበኞችና ነፃነት ናፋቂዎች ቁጥር ቀላል አደለም ከመንግስት በላይ ነው እንጅ፡፡
በአጠቃላይ ኦቦ በላ ዳምጤ ወይም አባ መላ ዳምጤ ዱዋል ኤጀንትነታቸው ሳይሳካላቸው ቅሌታቸውን አትርፈው ተመልሰዋል ከፊልድ እናም ኢህአዴጎችና ቡችሎቻቸው አጨብጭባችሁ እልል ብላችሁ ተቀበሏቸው፡፡እርቃናቸውን ስለመጡም ልብስ ጣል አድርጉባቸው፡፡ ያሰቡትም ምንም ስላለትሳካላቸው አሳኩላቸው ግን በናታችሁ እንዳትገድሏቸው፡፡
ቻው ቸር ይግጠመን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

No comments:

Post a Comment